Walaloof jechoota barnoota dabarsan.

Call Website Contact the university

Walaloof jechoota barnoota dabarsan. walaloof jechoota ergaa dabarsan page kana irratti maxxansuun wal barsiisuuf walirraa barachuun kaayyoo fuula kanaati.

Kanaaf namni kamuu fuula/page kanarratti maxxansuun ni danda'a.

29/10/2021

🌀🌀 ይሄን ፅሁፍ ማንበብ 100 መፅሐፍት እንደማንበብ ነው!

✅ በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ ፤ ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል ። ሰምቶ ማመን ፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ ። የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም ። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል ።

✅ ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው ። በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው ። ብልህ ከሆንህ በሰው ከደረሰው ትማራለህ ፣ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ ።

✅ የታየህን አሳይ ፣ ያልታየህን አጥራው ። በደንብ ያልተረዳኸውን አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ ። የሰማኸውን ሁሉ አትመን ። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ ፣ የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል ። የሰጠኽውን እርሳ እንጂ አታውራ። ፍፃሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ ። ቀኑ ሳይመሽ ቀኑ ጥሩ ነው አትበል ።

✅ ዓይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ ። ነገ ላይ እንድትደርስ የትናንቱን አትርሳ ። የምትሄድበት እናዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ ።

✅ የአባቶችህን መልካም ሥራ አብነት አድርግ ። ካሳለፉት ሕይወት ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን ። ሌሎች መሆን ያለባቸውን ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ እንዳይጠፋህ ተጠንቀቅ ። ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው ።

✴ ክፋት አይሙቅህ ፣ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ ። ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት ።

✴ ገንዘብ የሚመልሰው የገንዘብን ጥያቄ ብቻ ነውና ሁሉንም ነገር ገንዘብ ያስገኝልኛል ብለህ አታስብ ። ላለው አትሩጥ ፣ ምጽዋትህና ተግባርህ በአቅምህ መጠን ይሁን እንጂ ከአቅምህ አትነስ ። ድሃም ሆነህ ተበድረህ ስጦታ አትስጥ ። በጣም ካልቸገረህ ለቅንጦት አትበደር ። ያንተን ድርሻ ከጨረስህ ያልተጨረሰ የሌሎችን ድርሻ ፈፅምላቸው ።

✴ ለሀብታም አትሳቅ ፣ የደሀ ጉልበት አይለፍብህ ፣ ያለ ሰው ሰው አልሆንክምና ሰው አትጥላ ፣ የወጣህበትን መሰላል አትገፍትር ፣ ለመውረድም ያስፈልግሃልና ፣ ያየኽውን ሴት ሁሉ የመውደድ ጠባይህ ካለቀቀህ ትዳር አትያዝ ፣ ካልጋበዙህ በቀር አማካሪ አትሁን ፣ ባልጠሩህ ሥፍራ አቤት አትበል ፣ ካልሾሙህ መሪ አትሁን ፣ ጉድለት በሌለበት ቦታ ጊዜህን አታባክን ፣ የሰው ፊት ጥገኛ ሁነህ ሲስቁልህ የምትስቅ ሲቆጡህ የምታለቅስ አትሁን ፣ ነገርህን በልክ ፣ ቃልህን በጣዕም ፣ ድምፅህን በዝግታ ፈፅመው ።

✴ እውር እንዳይሉህ ያልታየኽን አያለሁ አትበል ። ጨካኝ እንዳይሉህ ያልተሰማህን ጩኸት እሰማለሁ አትበል ። ንፉግ እንዳይሉህ ያለ አቅምህ እረዳለሁ አትበል ። ነገር አይገባውም እንዳይሉህ ያልገባህን እንደገባህ አድርገህ አትለፍ ። አንድ በጎ ዕውቀት ሳትጨብጥ የዋልክበትን ቀን እንደ ኖርክበት አትቁጠረው ፣ ስለዚህ መፅሐፍትን አንብብ ፣ አዋቂዎችን ጠይቅ ፣ ሁሉን ሳትንቅ ስማ ።

✴ ሥልጣን ሲሰጥህ መሪ እንጂ አለቃ አትሁን ፤ ከፊት እየቀደምህ አስከትል እንጂ ከኋላ ሆነህ አትቅደም ።

✴ በዓላማ ኑር ፤ እንቅፋቶች የሚያጸኑህ እንጂ ተግባርህን የሚያስተውህ አይሁኑ ። ሕይወት ትምህርት ቤት መሆኑና ባለማወቅ ብዙ ትህምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ ።

✴ የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን ፤ የትላንቱንም አስብ ፤ አንገት የተፈጠረው ዞሮ ለማየት ነውና ።

🌀 ዓለም ዋዣቂ ናት ። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ ፤ ፀሐይ ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች ። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆናል ። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም ። ከሀዘን በኋላ ደስታ ይሆናልና በርታ!

🌀 መነቀፍን አትፍራ ፤ ነቀፋህን ግን አጥራው ፤ ስለ ሀሰት ሳይሆን ስለ እውነት ተገፋ ፤ ሌሎችን ውደድ ፍቅር ስጦታ እንጂ ብድር አይደለምና አልወደዱኝም ብለህ በአበዳሪዎች አንቀጽ አትካሰስ ፤ የገባህን አድርግ የዚህ ዓለም ሰው ሲወድህም ሲጠላህም ባለማወቅ ነው ። ብዙዎች ስለወደዱህ ይወድሃል ፤ ብዙዎች ስለጠሉህ ይጠላሃል ።

🌀 ሁልጊዜ የበላዮችህን አትመልከት ፤ የበታቾችህንም ተመልከት ። ለድምፅ አልባዎች ጩህላቸው ፣ ለተጠቁት ተሟገትላቸው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታጣው ሀሰተኛ ወዳጅህን ብቻ ነው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታተርፈው ግን እውነተኛ ወዳጅን ነው ።

🌀 ደጋፊዎች ተከታዮች አይደሉም ። ሰዎች ስለደገፉህም የያዝኩት እውነት ነው ብለህ መንቻካ አትሁን ፤ ምናልባት ዛሬ የሚጮሁልህ ዛሬን ሊረሱብህ ሊሆን ይችላልና ። ሲያለቅሱልህም ቃልህ ማርኳቸው ሳይሆን የሞተ ዘመዳቸው ትዝ ብሏቸው ሊሆን ይችላልና አለቀሱ ብለህ ንግግርህን ድንበር አታሳጣው ። እውነትንም በደጋፊ ብዛት እንዳትመዝናት ተጠንቀቅ ።

🌀 ለእውነታ እንጂ ለይሉኝታ አትኑር ፤ ያን ስልህ የምትኖርበት ሕዝብና ባሕል ከእውነት ጋር እስካልተጋጨ መጋፋት የለብህም። ሠዎች የሚቀበሉህ ባሕላቸውን ስታውቅና ስታከብርላቸው ነው ።

🌀 ልጅነት የለሰለሰ መሬት ፣ ወጣትነት የአዝመራ ዘመን ፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል ። በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ ።

🌀 የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው !!

🌀 ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ።

✅ ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከዕውቀትና ከትሕትና ይርቃሉ ። ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ ። አንተ ግን ቆንጆ ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ ፤ ቆንጆ ትዳርን እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ ፤ የላይ ነገር ከንቱና ኀላፊ ነውና በሚፈርስ አካል ፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል።

✅ እወድሃለሁ ብለህ የምትናገረውን ቃል ውለታ አታድርገው ፣ መውደድህን የምትናገረው እንወድሃለን እንዲሉህ አይሁን ፣ ሠላም ያለው አፍቃሪ የራሱን ፍቅር ያለ ምክንያት መፈፀም የሚችል ብቻ እንደሆነ እወቅ ። መወደድህን ለመስማት አትጠብቅ ።

✅ የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው ።

✅ ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ ሁን ፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት ፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ ።

✅ ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ። ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ።

✅ ቂም አፍን የሚያመር ፣ ልብን የሚያነቅዝ ፣ ተግባርን የሚያልፈሰፍስ ነውና ለበደለህ ሰው ቅያሜህን ግለጥለት ፤ ቂመኝነት በክፉ መሸነፍ እንጂ ጀግንነት አይምሰልህ ።

✅ ከህሊናህና ከመንፈሳዊ አማካሪህ ሳትመክር ምንም ነገር አትወስን ፤ አጥርተህ ሳትሰማ ቃል አትግባ ። መከራ ካልደረሰ በቀር ባል በሌለበት ቤት ውስጥ ከሚስቲቱ ጋር ብቻህን አትቀመጥ ።

✅ የሚበልጥህ ልኩራብህ እንዳይልህ ፣ ያነሰህ ልድረስብህ ብሎ እንዳያጠፋህ የሀብትህን ልክ እንዳታወራ ፤ በገዛ አፍህ ባንዱ ትከብራለህ ባንዱ ትቀላለህና።

❇ በጣም በማክበርህ እንዳታመልከው ፤ በጣም በመናቅህ እንዳታዋርደው ሠው እንዳንተ መሆኑን እወቀው ።

❇ የእኔ መናገር ምን ይለውጣል? ብለህም ስህተትን አትለፍ ፤ የእኔ አስተዋፅኦ ምን ይጠቅማል ? ብለህም ስጦታህን አትጠፍ ።

❇ መልካም ቃል ከስጦታ ይበልጣልና መልካም ቃል ተናገር ፤ ማንኛውም ስጦታ ከልመና ወንበር አያስነሣም ። የተስፋ ቃል ግን እንደሚያስነሣ አውቀህ ለሰዎች የተስፋ ቃል ስጣቸው ።

❇ ትምህርት ለዕውቀት ያዘጋጃል እንጂ ዕውቀትን አይጨርስም ። ዕውቀትህን የምትይዝበትን ሥነ-ሥርዓት ግን ያሳይሃል ። አእምሮህን ለማረቅ ትምህርት ፣ ሰውነትህን ለመግዛት ትዕግስት ፣ ከማንም ጋር ለመኖር ሥነ-ሥርዓት ያስፈልግሃል ። ለህሊናህ እረፍት ግን እምነት ያሻሃል ። ተከታይ ለማበጀት ደግሞ ግልጽ መሆንና ታማኝነት ግድ ይልሃል ።

❇ አንተው እውነትን ጠልተሃት ዘመኑ እውነትን ጠልቷል አትበል ። ዘመን እኔና አንተ ነን ፤ በራሱ ክፉና ደግ የሆነ ዘመን የለም።

❇ መልካም ምክር ብትሰማ ሕይወት ቀላል ይሆንልሃል ። ትክክለኛም ውሳኔ ከመልካም ምክር ነውና..!!
አንብበው ለወዳጅዎ ካላካፈሉት እንዲሁም የተሰማዎትን ካልፃፉ ሲበዛ እራሥ ወዳድ ነዎት ማለት ነው!!!!

ሌላ ምርጥ መጣጥፎች እንዲደርስዎ ከፈለጉ ላይክ ያድርጉ።
ሼርርርር
ምርጥ መጣጥፎች

28/10/2021
24/10/2021

✴❇ ❇✴

🌀 🌀
✅ ጤንነት ያለው ተስፋ አለው ተስፋ ያለው ሁሉ እድገት አለው፡፡
/አረቦች/

✅ ትንሽ ኮከብ እንኳ በጨለማ ውስጥ ያበራል፡፡/ፊላንዶች/

✅ አርባ የወጣትነት ደረጃ እድሜ ነው ፡፡ ሀምሳ ደግሞ የእርጅና ወጣት እድሜ ነው፡፡/ ፈረንሳዮች/

✅ ከአንድ ሽህ ዓመት የሠላም ኑሮ የአንድ ቀን የእስር ኑሮ ይረዝማል
/ሩሲያውያን /

✅ ሳታይ አትጠጣ ፤ስታነብ አትፈራም /ስፔያውያን/

✅ ለዳቦ ሲል የሚሠረቅ ንጹህ ነው ፤ለወርቅ ሲል የሚሠረቅ ግን ጥፍተኛ ነው /ዓራዳውያን /

✅ ጆሮ ምንም ቢያድግ ከራስ አይበልጥም /ሱዳኖች /

✅ የአንድ አመት ጎዳና ከአንድ እርምጃ ይጀመራል /ቻይናዎች /

🌀 🌀

✴ ፈረስ የሚተኛው ቁሞ ነው፡፡
✴ በከብት ልብ ውስጥ ኦስኮርዶስ የሚባል አጥንት ይገኛል፡፡
✴ በውሻ ልብ ውስጥ አስፒነስ የሚባል አጥንት ይገኛል፡፡
✴ ፈረስ የሃሞት ከረጢት የለውም፡፡
✴ ምላስህ ሊናገር የማይፈልገውን ፊትህ እንዳይናገር ተጠንቀቅ፡፡
✴ አትቸኩል በዚህ አለም ላይ የሚያስቸኩል ነገር የለም፡፡
✴ ባትቸኩልም ህይዎት ራሷ አጭር ናት፡፡
✴ መልካም ስራና እውነት ውሎ አድሮ ከትቢያ መነሳታቸውንና የክብር ስፍራቸውን መያዛቸው አይቀርም፡፡
✴ እለት ከእለት የሚያጋጥሙህን ችግሮች ለማሸነፍ ከፈለግህ
ትግዕስትህን መከታ አድርግ፡፡
✴ ከእውነት ጋር የተጣላች ነፍስ ምንጊዜም የፍርሃት ባሪያ ናት፡፡

🌀 🌀

🚺 የቤቱ ውበት ………………..ስርዓት
🚺 የቤቱ ጠባቂ………………… ታማኝነት
🚺 የቤቱ ደስታ………………… ፍቀር
🚺 የቤቱ በረከት ……………… ልጆች
🚺 የቤቱ ህግ…………………... ልግስና
🚺 የቤቱ ጽናት………………... ባለው መርካት
🚺 የቤቱ ራስ…………………… አምላክ ነው

🌀 #አይታሰብም 🌀

🚹 አምላክ………………….ያለመስዋት
🚹 ፖለቲካ………………… ያለመመሪያ
🚹 ሃብት…………………… ያለስራ
🚹 ደስታ…………………... ያለ ህሊና
🚹 እውቀት……………… ያለጸባይ
🚹 ገንዘብ ………………. ያለ ስነ ምግባር
🚹 ሳይንስ………………... ያለሰባዊነት
🚹 ስኬት…………………. ያለፈተናና መከራ አይታሰብም

🌀 🌀

🟢 ጤንነትዎን መንከባከብና መጠበቅ ይወቁ፡፡
🟢 ታማኝ መሆኑን አይርሱ፡፡
🟢 እንቅስቃሴዎችን ለመገንዘብ ይሞክሩ፡፡
🟢 በሙሉ ልብ ለሌሎች ፍቅር ይኑርዎት፡፡
🟢 ሁሉም ሰው ክብርና ውድ መሆኑን ይገንዘቡ፡፡
🟢 ለራስዎ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ያስቡላቸው፡፡
🟢 ጊዜን በጥበብ ይጠቀሙበት፡፡
🔵 እነዚህን ማከናወን ከቻሉ ከአካባቢው ጋር እኩል መራመድ ይችላሉ ስራዎም በቀና ይከናወናል፡፡

🌀 🌀

✴ የሰው ልጅ ጊዜን መጠቀም ከጀመረ ወዲህ እያንዳንዱ ሰው ቅሬታን ማሰማት ጀመረ፡፡ ጊዜ አላገኘሁም እያለ፡፡

✴ ስኬት በ30 ቀን ህይወት የተቃርኖና የተቃራኒ ነገሮች ውህደት ናት
በጉያዋ መኖርና አለመኖር ፤መሆንና አለመሆን ፤ ደስታና ሃዘን ፤ ማሸነፍና መሸነፍ፤ ወዘተ አቅፋ የምትኳትን ባተሌ መንገደኛ ናት።

🌀 🌀

✴ ሽፍቶች ህይዎትህን ወይም ገንዘብህን ይጠይቁሃል፡፡ ፍቅረኛህ ግን ሁለቱንም ትጠይቅሃለች፡፡ / ከህሊና ሲታወር/

እያንዳንዱ ሰው በአንድ ወቅት የሚመልሳቸው የእንባ ብድሮች አሉበት፡፡ / ከጥበብ መንገድ/

✴ አንድ ሐገር ለትውልድ የሚያቆየውን የተዋጋበትን አይደለም ፤ ያሸነፈበትን ታሪክ ነው፡፡/ ከእንቅልፍና እድሜ/

✴ ሁላችንም ብንሆን ክፋትን ፤ደግነትን፤ ጠማማነትን፤ ቅንነትን፤
ብልግናን፤ ጨዋነትን ፤ ትዕቢትን፤ ትህትናን፤ ጥላቻንና ፍቅርን፤ ጦርነትንና ሰላምን፤ እውቀትን፤ ጭካኔን፤ ርህራሄን፤ ተልዕኮንና ግልጸኝነትን ፤ብልጠትንና ልግስናን አሸንፋዋቸው ካየን
ስለበጎነትም ሆነ ስለ ክፋት ብዙ እንድንናገር የሚገፋፋን ምክንያት አይኖርም። / ከአልወለድም/

✴ በአወንታዊ አስተሳሰብ ውስጥ ስኬት ፤ጤና ፤ፍቅር፤ እርካታ ፤
ሃሴት፤ ደስታ፤ ሰላምና ነጻነት ይኖራሉ፡፡ / ከ-ዙ-ማይድ/

🌀 #ያውቁታልን?🌀

✅ አንድ ሰው በ 85 አመት እድሜው ቢያንስ 1,000,000 ማይል ርቀት ይጓዛል።

✅ የወንዶች የሰውነት አጥንቶች በ21 አመት አካባቢ እድገታቸውን ያቆማሉ።

✅ የቴሌፎን የፈጠራ ባለቤት የሆነው የአሌክሳንደር ግራሃምቤል ቀብር በተፈጸመበት ዕለት ሃዘኑን ለማሰብ ሲባል የአሜሪካን የቴሌፎን መስመሮች በሙሉ ለአንድ ደቂቃ ተቋርጠው ነበር።

🚹🚺 / Traints and citizens good characters/

✳ ተግባቢነት /civility/
✳ እራስን በስነ ምግባር ማነጽ / self disciple/
✳ የዜግነት ስሜት/ civic mindedness/
✳ የአምዕሮ ክፍተት / open mindedness/
✳ መቀራረብና መደራደር / compromise/
✳ ልዩነትን መቻል / tolerance of diversitiy/
✳ ትግዕስትና ጽናት / presence and parses tense/
✳ ለሌሎች ማሰብ / compassion/
✳ ተቆርቋሪነት/ generosity/
✳ ጀግንነት / courageous/
✳ ሰዓት አክባሪነት / punctuality/
✳ ቁርጠኝነት / civic commitment/
✳ ግላዊ ነጻነት /Individual liability/
✳ ወንጀልን መዋጋት / Fighting/
✳ ሃገር ወዳድነት / patriotism/
✳ ለህገመንግስቱ ታማኝ መሆን / loyality/

✅🚺 ✅🚹

🔶 ️አለቃዬ አየኝ አላየኝ ሳትል በፍላጎትህ ጠንክረህ ስራ ሐገር
የምትገነባው በስራ ነውና።

🔶 ከሰዎች ጋር ተግባብቶ የመኖር ችሎታ ይኑርህ ፤ የግል ጥረት ብቻውን ውጤቱ አያምርምና።

🔶️ በየትኛውም ስዓት ቀጠሮ አክባሪ ሁን ፤ጊዜ ወርቅ ናትና።

🔶️ የቤተሰብ ሃላፊነትን የምታመጣ ሁን ቅድሚያ መፈተሻ ነውና።

🔶️ መጀመሪያ ካልተሳካልህ ደጋግመህ ሞክር።

🔶️ እራሱን ያወቀ ሰው ሁልጊዜ ደስተኛ ነው፡፡

🔶️ በአካልና በአምዕሮ የተዋቡ ሰዎች ወርቅ አያስፈልጋቸውም።

🔶️ ማንኛውም ነገር መጀመሪያ እንዳለው ሁሉ መጨረሻ አለው።

🔶️ በአለም ላይ ትልቅ/ታላቅ/ የሚባለው ነገር የትነው የቆምነው የሚለው ሳይሆን በየት አቅጣጫ እንሂድ የሚለው ነው።

🌀 #ችግር 🌀

✅ ፈተና ነውና………………………. ድፈነው
✅ በሽታ ነውና………………………. ታከመው
✅ ጸበል ነውና……………………….. ቅመሰው
✅ ሰንሰለት ነውና…………………….. በጥሰው
✅ ያለነውና …………………………… አድንቀው
✅ ግልጽ ነውና………………………… ደብቀው
✅ ደራሽ ነውና…………………………. አምልጠው

ምርጥ መጣጥፍ ሆኖ ካገኙት ሼርርርር
ምርጥ መጣጥፎች

24/10/2021

🚺🚹 🚺🚹

🌀✅ የ13 ዓመት ልጅ ከመደብር ዳቦ ሰረቀ ዘበኛው ይዞት ነበርና ሊያመልጥ ሲል የመደብሩ መደርደሪያ ወድቆ ተሰበረ።

❇✴ ዳኛው የወንጀሉን ክስ ሰማና ልጁን እንዲህ ሲል ጠየቀው!
"የሆነ ነገር፥ ማለትም ዳቦ ሰርቀህ ነበር?"
❇✴ ልጁ - እያፈረ "አዎን ሰርቀአለሁ"
❇✴ ዳኛው - "ለምን?"
❇✴ ልጁ - "አስፈልጎኝ"
❇✴ ዳኛው - "መግዛት አትችልም ነበር?"
❇✴ ልጁ - "ገንዘብ አልነበረኝም" 🙄
❇✴ ዳኛው - "ከቤተሰብህ ለምን አትወስድም?"
❇✴ ልጁ - "እናት ብቻ ናት ያለችኝ፥ እሷም በጠና ታምማ እቤት ተኝታለች"
❇✴ ዳኛው - "ምንም ስራ የለህም?"
❇✴ ልጁ - "መኪና እጥበት እሰራ ነበር፥ ነገር ግን እናቴን ለማስታመም አንድ ቀን ከስራ ስቀር አባረሩኝ"
❇✴ ዳኛው - "ሌሎች እንዲረዱ አልጠየቅኽም?"
❇✴ ልጁ - "በጧት ነው ከቤት የወጣሁ፥ እንዲረዱኝ 50 የሚሆኑ ሰዎች ጋ ሄጄ ነበር፤ አንድም የሚረዳኝ ሰው ግን አላገኘሁም፤ በቃ መጨረሻ ላይ ይህንን መጥፎ ውሳኔ ወሰንኩ"

🌀✅ ጥያቄው ሲጠናቀቅ #ዳኛው ውሳኔ ማስተላለፍ ጀመረ።
እንዲህም አለ "ዳቦ መስረቅ፥ በተለይ የተራበ ልጅ ዳቦ መስረቅ እጅግ በጣም አሳፋሪ ወንጀል ነው፤ እናም እኛ ሁላችንም የዚህ ወንጀል ተጠያቂ ነን። እኔን ጨምሮ

🌀✅ በዚህ ቤት ውስጥ ያላችሁ በሙሉ ወንጀለኛና ተጠያቂ ነን።
ስለዚህ እያንዳንዱ በዚህ ችሎት ላይ የታደመና እዚህ ቤት ውስጥ ያለ አስር (10) አስር ዶላር እንዲከፍል ፍርድ ቤቱ ወስኗል። ማንም ሰው ሳይከፍል መውጣት አይችልም በማለት አስር ዶለር ከኪሱ አውጥቶ ወረቀት ላይ መመዝገብ ጀመረ።

🌀✅ በተጨማሪ ዳቦ ቤቱ የተራበ ልጅ ለፖሊስ አሳልፎ በመስጠቱ 1000 ዶላር እንዲከፍል ውሳኔ አስተላለፈ። ይህ በ24 ሰአት ውስጥ ካልተፈጸመ ፍርድ ቤቱ ዳቦ መደብሩን ያሳሽጋል።

🌀✅ ፖሊስም የተራበ ልጅ ፍርድ ቤት በማቅረቡ 1000 ዶላር እንዲቀጣበት ወሰነ። የተወሰነለትን ገንዘብ ለልጁ ካስረከበ በኋላ ፍርድ ቤቱ ልጁን ህዝብ ፊት ይቅርታ ጠየቀው!

🌀✅ የዳኛውን ውሳኔ ከሰሙ በኋላ በችሎቱ ላይ የነበሩ ታዳሚዎች ሁሉ በእንባ ተራጩ።

🌀✅ የልጁ እጅ ላይ የነበረው ሰንሰለት ተፈታለት። ዳኛው እንባ እየተናነቀው ሲያወራ ልጁ ያይ ነበር።

🔵🔵🔵🔵🙏🙏🙏🔵🔵🔵🔵

🚺🚹 በኛ ማህበረሰብ ውስጥ ያለው የፍትህ ስርዓት ግን ምን ይመስላል? የተራበ ልጅ ዳቦ ሰርቆ ቢያዝ ወንጀሉም እፍረቱም ለህዝቡ ነው 😢

🚺🚹 ይህ መልዕክት ልብህን ከነካ እባክህን ለአንድ ሰው ዳቦ ግዛ።
አንተ እያለ ሌላው ጾም ማደር የለበትም።

✅ በዙሪያህ ካሉ ከብዙዎች አንድ ሰው መርጠህ አስደስተው!
✅ !
✅ ከብዙዎች ትሻላለህና ካለህ ጥቂት ነገር ላጡት አካፍል!
✅ ይህንን ከባድ ጊዜ ተጋግዘን እንለፈው 🙏
✅ ይህንን በማረጋችሁ ፈጣሪ ያስብላቹኋልና 🙏

#ሼርርርር በማድረግ ለሁሉም አድርሱ
©ዋልተንጉስ ዘሸገር
ምርጥ መጣጥፎች

18/10/2021
16/10/2021

As koottuu asin jira
Qallayyoo mudhiin
Fo'aa migiraa......... xumuraa

14/10/2021

Cabni Oromoo Booranaa
Kan wallaggaafi jimmaa
Kallattii afraniinuu..........
Oromoo maraaf dhimma!
~
https://t.me/joinchat/9SSJ4VtUn04wNzZk
Gaaf-tokko woraanamu
Yoo hin qoorsineef madaa
Fayyinaan nuti tokkoon
Amansiiftiiree badaa?
~
Aanaasaa rakkoo baasuuf
Tasa-n bubbutu ceekuu
Gaafa rakkoo gaachana
Firri Kan ani beeku..........
~
Beela qomoo arginaan
Ofii dhiisee hiixata
Muddama isaa gaggaba
Ulfa sabaa miixata!
~
Yoo tokko utubaa ta'u
Kaanis taanee dagalee
Iyya sabaa dhageenyaan
Waliif taana sagalee.....
~
Booranaafi baarentuu
Warra humbannaaf ituu
Wallo mataa keenyadha
Abadan nurraan citu!
~
Warri maccaaf tuulamaa
Warri sabboofi goonaa
Gaafa Tokkummaan kaane
Diina adamsinee m***a!
~
Gaafa nu wal jaalanne
Kallattii afraniinuu......
Woraabessa dhiisaatii
Mixiinuu nun ciniinu!
~
Tokkummaan hirbuudha
Kan gootota kumaatii
Caba wolii okkolaan
Dhaamsa kiyya dhumaati!

✍️....

https://t.me/joinchat/9SSJ4VtUn04wNzZk

Address

Oromiyaa/Naqamte
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Walaloof jechoota barnoota dabarsan. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Walaloof jechoota barnoota dabarsan.:

Shortcuts

Share