ኮልፌ ወረዳ 10 ፅዳትና ውበት ፅ/ቤት - Kolfe Woreda 10 cleansing manegment office

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • ኮልፌ ወረዳ 10 ፅዳትና ውበት ፅ/ቤት - Kolfe Woreda 10 cleansing manegment office

ኮልፌ ወረዳ 10 ፅዳትና ውበት ፅ/ቤት - Kolfe Woreda 10 cleansing manegment office በኮልፌ ወረዳ 10 አስተዳደር የታቀዱና የሚከወኑ የፅዳትና ውበት ተግባራቶችን ከማህበረሰብ ጋር የምናሰናሰንበት የተግባቦት ገፃችን ነው!!

23/08/2026

የፅዳት ዘመቻ🔥

ሳምንታዊ የወረዳ 10 ቅጥር ግቢን የማፅዳት  መርሃ ግብር ተከናወነ።ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 ጽዳትና ውበት አስተዳደር ጽ/ቤት15/12/2018የወረዳ 10 ቅጥር ግቢን የማጽዳት መርሃ ግብር ...
21/08/2026

ሳምንታዊ የወረዳ 10 ቅጥር ግቢን የማፅዳት መርሃ ግብር ተከናወነ።
ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 ጽዳትና ውበት አስተዳደር ጽ/ቤት
15/12/2018
የወረዳ 10 ቅጥር ግቢን የማጽዳት መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት የተከናወነ ሲሆን ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ ሳምንታዊ የአንድ ማዕከል የተቋማት ጽዳት ዘመቻ ንቅናቄ ሲካሄድ የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚን ጨምሮ ፣ የተለያዩ የፅ/ቤት ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል።

ምቹ የስራ ከባቢ መፍጠር ብቻ ሳይሆን የተፈጠረውንም ምቹ የስራ ከባቢ ፅዳቱንና ውበቱ የተጠበቀ እንዲሆን ለማስቻል ሁሉም በባለቤትነትና በእኔነት ስሜት የተሳተፈ ሲሆን ይህንንም አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሚሰራ ተገልጿል።

"ተቋማዊ ግንባታ ለተቋማዊ ዕድገት "

የሃምሌ ወር ስራዎችና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስመልክቶ ውይይት ተካሄደ።ቀን:- 23/11/2018 ዓ/ምየ ደረቅ ቆሻሻ  አገ/አሰ እና ግብዓት  አስተዳደር ቡድን  አጠቃላይ ደጋፊ ባለሙያ...
30/07/2026

የሃምሌ ወር ስራዎችና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስመልክቶ ውይይት ተካሄደ።
ቀን:- 23/11/2018 ዓ/ም
የ ደረቅ ቆሻሻ አገ/አሰ እና ግብዓት አስተዳደር ቡድን አጠቃላይ ደጋፊ ባለሙያዎች ፣ የማህበራት አመራሮች ፣ የመንገድ ፎርማኖች በተገኙበት ውይይት ማድረግ ተችሏል።
የውይይቱ አጀንዳዎች የሀምሌ ወር እቅድ አፈፃፀም የመንገድ ጽዳት እና የማህበራት የማታ ሽፍት ስምሪት አስመልክቶ የማህበራት የውስጥ እና የውጪ ኦዲት ፣ የድጋፍ እና ክትትል ተግባራት ላይ ውይይት ተካሂዷል።

ውይይቱን የመሩት ከደ/ቆ/አገ/አሰ/ግብዓት አስተዳደር ቡድን መሪ:- አቶ ተክለብርሀን ወሉ እና የጽ/ቤቱ አስተባባሪ ወ/ሮ እመቤት ፋንታሁን ሲሆኑ በአጠቃላይ ከውይይቱ ጋር ተያይዞ ሁሉም የተገኙት ተሳታፊ አባላት ሀሳብ እና አስተያየት መስጠት ችለዋል።
በመጨረሻም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ላይ በመነጋገር የስራ ስምሪት በመስጠት ተጠናቋል።

"አዲስ አበባን እንደ ስሟ ጽዱ፤ ውብ እና ሳቢ ማድረግ ተቀዳሚ ተግባራችን ነው"

በመንገድ ዳር የሚገኙ ያደጉ ሳሮችና አረሞችን የመጨፍጨፍና መንገዱን ንፁህ የማድረግ  ስራ ተሰራ።ኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ 10 ፅዳትና ውበት አስ/ፅ/ቤትበክረምት ምክንያት የበቀሉ መንገድ ዳርቻ ላ...
29/07/2026

በመንገድ ዳር የሚገኙ ያደጉ ሳሮችና አረሞችን የመጨፍጨፍና መንገዱን ንፁህ የማድረግ ስራ ተሰራ።
ኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ 10 ፅዳትና ውበት አስ/ፅ/ቤት
በክረምት ምክንያት የበቀሉ መንገድ ዳርቻ ላይ የሚገኙ አረሞችና በአላሶፈላጊ ደረጃ ያደጉ ሳሮችን የመከርከምና የማስወገድ ስራ መሰራቱ ተገለፀ። ይህም መንገዶች በስታንዳርዳቸው መሰረት ፅዱ ለዕይታ ሳቢና ማራኪ እንዲሆኑ ያስቾላቸዋል።

22/07/2026

ሳምንታዊ የብሎክ ፅዳት ዘመቻ

🧹🧹🧹  !! 🧹🧹🧹         ሀምሌ 12/2018 ዓ.ም             **************የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  በ2018 በጀት ዓመት ከማዕከል እስከ ክፍለ ከተማ ድረስ የ...
22/07/2026

🧹🧹🧹 !! 🧹🧹🧹
ሀምሌ 12/2018 ዓ.ም
**************
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2018 በጀት ዓመት ከማዕከል እስከ ክፍለ ከተማ ድረስ የስራ አፈጻጸም ምዘና አካሄዷል።

በምዘናውም የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ የላቀ አፈጻጸም በማስመዝገቡ ከክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የዘመናዊ ተሽከርካሪ መኪና ተሸላሚ ሆኗል።

ለዚህ ውጤት መብቃት ከከተማ እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮችና ፈጻሚዎች : ባለድርሻ አካላት : የፅዳት አምባሳደሮቻችን እና አጠቃላይ የከተማዋ ነዋሪ ህብረተሰብ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ።

በዚሁ መሠረት ከተማ አስተዳደራችን ባስመዘገብነው ውጤት ለተገኘው ሽልማት ከላይ እስከ ታችኛው መዋቅራችን ከፍተኛ ቅንጅት እና ቁርጠኝነት የተሞላበት ተሳትፎ በመሆኑ ሽልማቱ የጋራችን ነው።

ሽልማቱም ለቀጣይ ስራዎቻችን ስንቅና ትጥቅ ሞራል መሆኑን የገለፁት የኤጀንሲያችን ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ ተባብረን በላቀ አንድነት ለመስራት የተሰጠ አደራም ጭምር ስለሆነ መላው የተቋማች አመራሮችና ሰራተኞች፣ የፅዳት አምባሳደሮች፣ ባለድርሻ አካላት እና መላው የከተማችን ነዋሪዎች ከዚህ የበለጠ ውጤት እንድናመጣ አደራ እላለሁ ብለዋል።

🙏 በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ🙏
አቶ ገዛኸኝ ደሲሳ
የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር

የሽርክና ማህበራት ለመልሶ መጠቀም የሚውሉ ፕላስቲኮችን በመሰብሰብ የሚወጡት ሚና የጎላ መሆኑ ተገለፀ።በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ጽዳትና ውበት አስተዳደር ጽ/ቤት በመልሶ መጠቀምና...
17/07/2026

የሽርክና ማህበራት ለመልሶ መጠቀም የሚውሉ ፕላስቲኮችን በመሰብሰብ የሚወጡት ሚና የጎላ መሆኑ ተገለፀ።

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ጽዳትና ውበት አስተዳደር ጽ/ቤት በመልሶ መጠቀምና ዑደት ማድረግ ቡድን የብርሀኑ ፣ መኮንን እና ጓደኞቻቸው ደረቅ ቆሻሻ መሰብሰብና ማጓጓዝ ህ/ሽ/ማህበር ለመልሶ መጠቀምና ዑደት ማድረግ የሚውል ፕላስቲክ ሃይላንድ የማጓጓዝ ስራ ተሰርቷተል።

ቀን - 10/11/2018 ዓ.ም

13/07/2026

አዲስ ለተተከሉት የደስትቢኖች ኮድ የመስጠት ስራ ሲሰራ🔥🔥🔥🔥

12/07/2026

የውበት ቡድን ስራዎቻችን 🔥🔥🔥

12/07/2026

የደረቅ ቆሻሻ ለይቶ ማስቀመጪያ ማዳበሪያ ቤት ለቤት ሲሰጥ 🔥🔥

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኮልፌ ወረዳ 10 ፅዳትና ውበት ፅ/ቤት - Kolfe Woreda 10 cleansing manegment office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share