AAU Portal

AAU Portal University Updates, News, Schedules and Opportunities � Unofficial

የፈተና የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ሆነ‼️የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ።የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሠርተፊኬት (12ኛ ክፍል ፈተና) ከሰኔ 24 እስከ ሃምሌ 17 ቀን 2018 ዓ...
24/04/2026

የፈተና የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ሆነ‼️
የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ።
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሠርተፊኬት (12ኛ ክፍል ፈተና) ከሰኔ 24 እስከ ሃምሌ 17 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቆናል።

በሌላ በኩል ፦

- የሬሜዲያል ፕሮግራም ሀገር አቀፍ ፈተና ከግንቦት 17 እስከ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ/ም ➡️ ግንቦት 19 ኢድ አልአድሃ

- የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ/ም

- የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና (NGAT) ከሃምሌ 29 እስከ ሃምሌ 30 ቀን 2018 ዓ/ም

- የመሰረታዊ የንባብና የስሌት ክህሎት ምዘና ጥናትና ምርምር መረጃ መሰብሰብ ከሚያዚያ 26 እስከ ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ/ም ይሰጣል።
=====================

✅ኢንተርኔት የማይፈልገው አዲሱ Gemma 4 AI በስልካችሁና በላፕቶፓችሁ! 🚀💻📱https://t.me/AAUPortalየዓለማችን ትልቁ የቴክኖሎጂ ኩባንያ Google በቅርቡ Gemma 4 የተባለ...
16/04/2026

✅ኢንተርኔት የማይፈልገው አዲሱ Gemma 4 AI በስልካችሁና በላፕቶፓችሁ! 🚀💻📱
https://t.me/AAUPortal
የዓለማችን ትልቁ የቴክኖሎጂ ኩባንያ Google በቅርቡ Gemma 4 የተባለውን እጅግ የረቀቀ የ-AI ሞዴል ይፋ አድርጓል። ይህ ሞዴል ከሌሎቹ (እንደ ChatGPT ወይም Gemini) የሚለየው ትልቁ ነገር ያለ ምንም ኢንተርኔት (Fully Offline) በራሳችሁ መሳሪያ ላይ መስራቱ ነው!

Gemma 4 ምንድን ነው?
Gemma 4 የ-Gemini ቴክኖሎጂ ውጤት ሆኖ፣ ማንኛውም ሰው ዳውንሎድ አድርጎ በራሱ ኮምፒውተር ወይም ስልክ ላይ እንዲጠቀምበት ተደርጎ የተሰራ "Open Model" ነው።

ለምን ይጠቅመናል?
1. ፍጹም ሚስጥራዊነት (Privacy)፦ የምትጠይቁት ጥያቄም ሆነ የምታገኙት መልስ ስልካችሁ ወይም ላፕቶፓችሁ ውስጥ ብቻ ይቆያል። ወደ Google ሰርቨር አይላክም!
2. ኢንተርኔት በማይኖርበት ቦታ፦ በበረሃ፣ በባህር ላይ ወይም አይሮፕላን ውስጥ ሆናችሁ ያለ ዳታ መጠቀም ትችላላችሁ።
3. ሁለገብ (Multimodal)፦ ጽሁፍ መጻፍ ብቻ ሳይሆን፣ ምስሎችን ማየትና ድምፅን መረዳት ይችላል።

እንዴት በላፕቶፕ (Laptop) ላይ መጠቀም ይቻላል?
ኮምፒውተራችሁ ቢያንስ 6GB RAM ቢኖረው ይመረጣል።
1. Ollama መጫን፦ [ollama.com](https://ollama.com) ላይ በመሄድ ሶፍትዌሩን ጭኑ።
2. ሞዴሉን መጥራት፦ ኮምፒውተራችሁ ላይ Terminal ወይም Command Prompt ከፍታችሁ ollama run gemma4 ብላችሁ ጻፉ።
3. ጨርሳችሁ! አንዴ ዳውንሎድ ካደረገ በኋላ ኢንተርኔቱን አጥፍታችሁ እንደፈለጋችሁ ማውራት፣ ኮዲንግ መስራት ወይም ሰነዶችን ማጠቃለል ትችላላችሁ።

እንዴት በስልክ (Mobile) ላይ መጠቀም ይቻላል?
ለዚህ ተግባር ቢያንስ Android 12 ወይም iOS 17 ያስፈልጋችኋል።
1. አፑን ዳውንሎድ አድርጉ፦ Play Store ወይም App Store ላይ በመሄድ "Google AI Edge Gallery" የሚለውን ኦፊሴላዊ አፕሊኬሽን ጭኑ።
2. ሞዴሉን ምረጡ፦ አፑን ከፍታችሁ Gemma 4 E2B (ለፈጣን ስራ) ወይም Gemma 4 E4B (ለበለጠ ብልህነት) የሚሉትን ሞዴሎች አንዴ ዳውንሎድ አድርጉ።
3. አይሮፕላን ሞድ (Airplane Mode)፦ ዳውንሎድ ካለቀ በኋላ ኢንተርኔቱን አጥፍታችሁ የ-AI ቻት፣ የፎቶ ትንተና እና የድምፅ ትርጉም አገልግሎቶችን በነፃ መጠቀም ትችላላችሁ።
https://t.me/AAUPortal
https://t.me/AAUPortal/1121

🎓 Everything about Addis Ababa University in one place 📢 Announcements & academic alerts 📅 Schedules & important dates 🎓 Scholarships & opportunities 🏫 Campus news & student resources ⚠️ Unofficial 📚✨

🚨 ሰበር ዜና፦ የኡጋንዳው ጄኔራል በቱርክ ላይ የ1 ቢሊዮን ዶላር እና "የቆንጆ ሚስት" ጥያቄ በማቅረብ ዓለምን አስገረሙ!ሚያዚያ 04 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኡጋንዳ መከላከያ ሰራዊት...
13/04/2026

🚨 ሰበር ዜና፦ የኡጋንዳው ጄኔራል በቱርክ ላይ የ1 ቢሊዮን ዶላር እና "የቆንጆ ሚስት" ጥያቄ በማቅረብ ዓለምን አስገረሙ!

ሚያዚያ 04 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኡጋንዳ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ አዛዥ እና የፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ የሆኑት ጄኔራል ሙሁዚ ኬይነሩጋባ በቱርክ ላይ ባቀረቡት ያልተለመደ ጥያቄ እና ማስጠንቀቂያ ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ አስነስተዋል።

ጄኔራሉ በኤክስ (X) ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ቱርክ ለኡጋንዳ 1 ቢሊዮን ዶላር ካሳ እንድትከፍል የጠየቁ ሲሆን ለዚህም እንደ ምክንያት ያቀረቡት የኡጋንዳ ጦር በሶማሊያ ሰላም ለማስከበር በከፈለው መስዋዕትነት ቱርክ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ሆናለች የሚል መከራከሪያን ነው።

ከገንዘቡ በተጨማሪ "ከሀገሪቱ እጅግ ቆንጆ የሆነችውን ሴት ሚስት ማድረግ እፈልጋለሁ" የሚል አነጋጋሪ የግል ጥያቄ ማቅረባቸው ለጉዳዩ የበለጠ ትኩረት ሰጥቶታል።

ቱርክ እነዚህን ጥያቄዎች በ30 ቀናት ውስጥ ካልፈጸመች በካምፓላ የሚገኘው የቱርክ ኤምባሲ እንዲዘጋ፣ የቱርክ አየር መንገድ ወደ ኡጋንዳ እንዳይበር እንዲታገድ እና ሁሉም ዓይነት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች እንዲቋረጡ እንደሚያደርጉ ጄኔራሉ ዝተዋል።

ይህ ድርጊት በሁለቱ ሀገራት መካከል የቆየውን መሻከር የሚያሳይ ሲሆን በተለይም ቱርክ በሀገሯ የሚገኘውን የመንግስት ተቺ ፍሬድ ሉምቡዬን አሳልፋ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኗ እና ኡጋንዳ ከቱርክ ኩባንያ ጋር የነበራትን የቢሊዮን ዶላር የባቡር መስመር ስምምነት ሰርዛ ወደ ቻይና ማዞሯ ለውዝግቡ ዋነኛ መንስኤዎች እንደሆኑ ይታመናል።

ጄኔራል ሙሁዚ ከዚህ ቀደምም በጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ላይ መሰል የጋብቻ ጥያቄ አቅርበው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን የኡጋንዳ መንግስት ግን እስካሁን በጉዳዩ ላይ የሰጠው ይፋዊ መግለጫ የለም።

🌙✨ Eid Mubarak! ✨🌙Wishing all students and the community of Addis Ababa University a joyful and peaceful Eid al-Fitr!May...
19/03/2026

🌙✨ Eid Mubarak! ✨🌙
Wishing all students and the community of Addis Ababa University a joyful and peaceful Eid al-Fitr!
May this special day bring you happiness, success, and new beginnings. May your hard work be rewarded and your dreams come closer to reality.
🤍 Enjoy this beautiful moment with your family and loved ones.
📚 AAU Portal wishes you continued success in your academic journey!
🌟 Eid Mubarak! 🌟

Address

Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AAU Portal posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share