General Wingate Poly Technic college / ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • General Wingate Poly Technic college / ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

General Wingate Poly Technic college / ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የ ISO 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት። for any support inbox us

welcome to General wingate poly technique college page.

ቅዳሜ:- ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ∙ምየ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ!!የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።በትምህርት ዘመኑ...
22/08/2026

ቅዳሜ:- ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ∙ም

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ!!

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በትምህርት ዘመኑ ፈተናውን ለመውሰድ ከተመዘገቡ 563 ሺህ 960 ተማሪዎች መካከል 550 ሺህ 210 ተማሪዎች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 12.8 በመቶ (70 ሺህ 544 ተማሪዎች) 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ በማምጣት ማለፍ ችለዋል።

50ከመቶ እና ከዚያ በላይ ካመጡ ተማሪዎች መካከል በተፈጥሮ ሳይንስ 16.5 በመቶ እንዲሁም በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 8.33 በመቶ ናቸው።

የተመዘገቡ ከፍተኛ ውጤቶችን በተመለከተ ተፈጥሮ ሳይንስ በወንድ 591.6 ከ 600 እና በሴት 583 ከ 600 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ በወንድ 576.2 እና በሴት 569.1 ነው።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንደገለጹት የዘንድሮው ውጤት ከባለፉት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ በመሆኑ የሚቀበሉት የሬሚዲያል ተማሪዎች ቁጥር የሚቀንስ ሲሆን የመቁረጫ ነጥቡ ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል።

ተማሪዎች ውጤታቸውን ከሰኞ ጠዋት ወይም ማክሰኞ ከሰዓት ጀምሮ መመልከት የሚችሉ ሲሆን ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎችም ለ5 እና 6 ቀናት ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉም ተብሏል።

የብሔራዊ ፈተና ውጤት መለቀቁን ተከትሎ ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅም የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በሚቆርጠው የመግቢያ ነጥብ መሠረት የ2019 ዓ.ም አዲስ ሰልጣኞችን ለመቀበል ሙሉ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቋል።

ኮሌጁ በ11 ዲፓርትመንቶች እና 30 በሚደርሱ የሙያ መስኮች በቀን፣ በማታ እና በቅዳሜና እሁድ መርሃ ግብሮች ለማሰልጠን ሰብዓዊና ቁሳዊ ግብዓቶችን በማሟላት አዲስ ሰልጣኞችን ለመቀበል ዝግጁ ነው።

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

ሐሙስ:- ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ∙ም የጀነራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅን ድህረ-EASTRIP ፕሮጀክት ዘላቂነት የሚያረጋግጥ የምክክር መድረክ ተካሄደ!! የEASTRIP ፕሮጀክት መጠናቀቅን ...
06/08/2026

ሐሙስ:- ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ∙ም

የጀነራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅን ድህረ-EASTRIP ፕሮጀክት ዘላቂነት የሚያረጋግጥ የምክክር መድረክ ተካሄደ!!

የEASTRIP ፕሮጀክት መጠናቀቅን ተከትሎ የጀነራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅን ሁለንተናዊ የለውጥ ጉዞ ለማስቀጠል የሚያስችል የዘላቂነት ማስተር ፕላን ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ ተካሄደ።

በዚህ መድረክ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ በከተማ አስተዳደሩ ስር የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ዲኖች፣ የኢንዱስትሪ ተወካዮች ተሳትፈዋል።

የምክክር መድረኩ ዋና ዓላማ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ተቋማት ከፕሮጀክት ጥገኝነት በመውጣት ራሳቸውን ችለው መቀጠል እንዲችሉና ከፕሮጀክት ድጋፍ ወደ መንግሥትና የግል ዘርፍ አጋርነት (PPP) የሚሸጋገርበትን ስልታዊ አቅጣጫ ማስቀመጥ እንደሆነ ተገልጿል።

በግምገማው ወቅት ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ኮሌጁ ራሱን ችሎ መቀጠል እንዲችል የውስጥ የገቢ አቅሙን የሚያሳድግበት ስልታዊ አቅጣጫዎች የተቀመጡ ሲሆን ሌሎች ኮሌጆችም የጀነራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅን መልካም ተሞክሮ በመውሰድ ለውጥ ለማምጣት ትልቅ መነቃቃት ሊፈጥሩ እንደሚገባ ተመላክቷል።

በአሁኑ ወቅት በአጋርነት ከጀነራል ዊንጌት ጋር አብሮ ለመሥራት ፍላጎት አሳይተው ወደ ሥራ የገቡ በርካታ አካላት መኖራቸውንና በቀጣይም አብረው ለመሥራት አቅደው በዝግጅት ላይ ያሉ በርካቶች መሆናቸው ተገልጿል።

ከጋራ ውይይቱ በተጨማሪ በተካሄዱ ተናጠል ስብሰባዎች የቢሮው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና የኮሌጅ ዲኖች በግልና መንግሥት አጋርነት (PPP) አተገባበር ዙሪያ ትኩረት አድርገው የመከሩ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ የአድቫይዘሪ ቦርድ አባላት በበኩላቸው የነበራቸውን የሥራ እንቅስቃሴና አፈፃፀም ገምግመው በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አድርገዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች ፕሮጀክቱ ለሀገሪቱ ብቁና የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት ያለውን ከፍተኛ ፋይዳ በማድነቅ በቀሪው የፕሮጀክት የሥራ ጊዜ የሚከናወኑ ተግባራት በግልጽ ዕቅድና መሪ አቅጣጫ እንዲመሩ በጋራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። በተለይም በኮሌጆችና በኢንዱስትሪዎች መካከል ያለው ቅንጅትና ትስስር ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ የቀረበ ሲሆን ውይይቱ የኮሌጆችን ዘላቂ እድገት ለማረጋገጥ ትልቅ መሠረት የጣለ እንደነበር ተጠቁሟል።

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

06/08/2026
ማክሰኞ:- ሐምሌ  28 ቀን 2018 ዓ.ም የኮንስትራክሽን ዲፓርትመንት በድምቀት የተጠናቀቀው የጀነራል ዊንጌት የክረምት እግር ኳስ ውድድር ሻምፒዮን ሆነ! በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ...
04/08/2026

ማክሰኞ:- ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም

የኮንስትራክሽን ዲፓርትመንት በድምቀት የተጠናቀቀው የጀነራል ዊንጌት የክረምት እግር ኳስ ውድድር ሻምፒዮን ሆነ!

በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሲካሄድ የቆየው የአሰልጣኞች የክረምት ስፖርታዊ የእግር ኳስ ውድድር እጅግ ማራኪ እና ፉክክር በታከለበት የፍፃሜ ጨዋታ በዛሬው ዕለት በድምቀት ተጠናቋል። በጉጉት ሲጠበቅ በነበረው የዋንጫ ጨዋታ የኮንስትራክሽን ዲፓርትመንትን ድንቅ ብቃት በማሳየት የዘንድሮው የዋንጫ አሸናፊ መሆን ችሏል።

ለፍፃሜው ደርሰው ዋንጫውን ለማንሳት የተፋለሙት አይሲቲ ዲፓርትመንት (Wingate Best) እና ኮንስትራክሽን ዲፓርትመንት ያደረጉት ጨዋታ በእግር ኳስ አፍቃሪዎች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን ያተረፈ ነበር። ከጨዋታው በፊት ለዋንጫው ሰፊ ቅድመ ግምት ተሰጥቷቸው የነበሩት የአይሲቲ ዲፓርትመንት ተጫዋቾች የጨዋታ የበላይነት በመውሰድ የመጀመሪያውን ግብ ከመረብ ጋር ማዋሃድ ቢችሉም ኮንስትራክሽኖች በአጭር ጊዜ ውስጥ አቻ የሚያደርጋቸውን ግብ አግኝተዋል።

ከእረፍት መልስም ሁለቱም ቡድኖች በማጥቃት ላይ የተመሰረተ ጨዋታ በማሳየት ተጨማሪ ሁለት ሁለት ግቦችን አስቆጥረው መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 3 ለ 3 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል። አይሲቲዎች በኳስ ቁጥጥሩ ብልጫ ወስደው ወደ ግብ ክልል በተደጋጋሚ በመድረስ ሙከራዎችን ቢያደርጉም የኮንስትራክሽኑን ግብ ጠባቂ ማለፍ እና ኳስ ከመረብ ማገናኘት አልተቻላቸውም።

አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው የፍፁም ቅጣት ምት የኮንስትራክሽን ዲፓርትመንት ግብ ጠባቂ የሆነው ዘካሪያስ ገብሬ የዕለቱ ኮከብ በመሆን አድምቋል! ዘካሪያስ ሁለት የአይሲቲ ቅጣት ምቶችን ድንቅ በሆነ ብቃት አምክኖ ቡድኑን ታድጓል። አይሲቲዎች በበኩላቸው የተሰጣቸውን ኳሶች መከላከል ባለመቻላቸው ኮንስትራክሽን ዲፓርትመንት በ2 የግብ ልዩነት በማሸነፍ የዋንጫው ባለቤት ሆኗል።

ከዋንጫው ጨዋታ አስቀድሞ የደረጃ ፍልሚያ የተካሄደ ሲሆን ጀነራል መካኒክስ /GM/ (Iron Man) ከአግሮ ቢዝነስ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ጀነራል መካኒክስ ተጋጣሚውን 6 ለ 2 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ የ3ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

በውድድሩ መዝጊያ ስነ-ስርዓት ላይ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ይዘው ላጠናቀቁት ዲፓርትመንቶች ደማቅ የሽልማት አሰጣጥ ስነ-ስርዓት ተካሂዶ የዘንድሮው የክረምት እግር ኳስ ውድድር በስኬት ተጠናቋል።

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

24/07/2026
ሰኞ:- ሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ⚽️  የኮሌጁ አሰልጣኞች የክረምት እግር ኳስ ውድድር በድምቀት ተከፈተ! የአይሲቲ ዲፓርትመንት ደግሞ የጎል ናዳ አዘነበ! በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ...
20/07/2026

ሰኞ:- ሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም

⚽️ የኮሌጁ አሰልጣኞች የክረምት እግር ኳስ ውድድር በድምቀት ተከፈተ! የአይሲቲ ዲፓርትመንት ደግሞ የጎል ናዳ አዘነበ!

በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተዘጋጀው የአሰልጣኞች የክረምት ስፖርታዊ የእግር ኳስ ውድድር በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀመረ። የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ባገኘበት ማግስት የተጀመረው ይህ የአሰልጣኞች ውድድር ስድስት የተለያዩ ዲፓርትመንቶችን የሚወክሉ ቡድኖች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በዚህ ውድድር አውቶሞቲቭ ዲፓርትመንት (Turbo Striker)፣ ጀነራል መካኒክስ /GM/ ( Iron Man)፣ አይሲቲ ዲፓርትመንት (Wingate Best)፣ አግሮ ቢዝነስ (ከተማ ግብርና እና የቢዝነስ)፣ ኤሌክትሪክና ሰርቬይንግ እና ኮንስትራክሽን (ኮንስትራክሽንና ውድ ወርክ) ባከተተ ምድብ ተከፍሎ የሚካሄድ ሲሆን የደረጃና የፍጻሜውን የዋንጫ ጨዋታ ጨምሮ በአጠቃላይ 10 የእግር ኳስ ግጥሚያዎች ይስተናገዳሉ።

የምድብ ጨዋታው ሲጠናቀቅ ሶስተኛ የሚወጡት ቡድኖች የሚሰናበቱ ሲሆን፤ ከየምድቡ አንደኛ እና ሁለተኛ የሚወጡት አራት ቡድኖች ወደ ቀጣይ ዙር ጨዋታ ያልፋሉ። አሸናፊውን ለመለየትም የአንደኛው ምድብ አሸናፊ ከሌላኛው ምድብ ሁለተኛ ጋር ይፋለማል።

በዛረው የመክፈቻው ጨዋታ ላይ ሁለት ምድቦች ግጥሚ ያደረጉ ሲሆን መጀመሪያ ላይ አውቶሞቲቭ (Turbo Striker) ከ ጀነራል መካኒክስ (Iron Man) ጋር ተፋልመዋል፡፡

በዚህ ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች እጅግ ማራኪ የሆነ የማጥቃት እና የመከላከል ብቃት ያሳዩ ሲሆን እስከ እረፍት ሰዓት ድረስ ባደረጉት ጠንካራ ፉክክር ጨዋታው ያለ ምንም ግብ ተጠናቆ ከእረፍት መልስ ሁለቱም ቡድኖች አቻ የሚያደርጋቸው አንድ አንድ ግብ በማስቆጠር 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ነጥብ ተካፍለዋል።

በሁለተኛው ጨዋታ ደግሞ አይሲቲ ዲፓርትመንት (Wingate Best) ከ ኮንስትራክሽን ጋር የተደረገ ሲሆን አይሲቲ ዲፓርትመንት ኮንስትራክሽንን 11 ለ 5 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት በማሸነፍ አስገራሚ የበላይነቱን አሳይቷል።

አይሲቲ ዲፓርትመንት ወደ ተቃራኒ የግብ ክልል በተደጋጋሚ በማምራት በርካታ ግቦችን አከታትሎ በማስቆጠር ድንቅ አጨዋወት ሲያሳይ ኮንስትራክሽን ዲፓርትመንቶች ደግሞ በአቅም የተፈተኑበትና አንድ ደርዘን የሚጠጉ ግቦችን ያስተናገዱበት ፈታኝ ጨዋታ ሆኖ አልፏል።

የኮሌጁ የክረምት ስፖርታዊ ውድድር በእግር ኳስ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን የሰራተኞችን የእርስ በእርስ ግንኙነት እና ጤንነት ለማጎልበት ታስቦ የመረብ ኳስ እና የጠረጴዛ ቴኒስ ጨዋታዎችም ጭምር ይካሄዳሉ።

ውድድሩን በአሸናፊነት ለሚያጠናቅቁ ቡድኖች የዋንጫ ሽልማት እንደሚበረከት አዘጋጅ ኮሚቴው የገለጸ ሲሆን የዛሬው የመክፈቻ ቀን እጅግ የተሳካና የተመልካችን ቀልብ የሳበ በመሆኑ በቀጣይም ይህ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

🚀 የስራ እድልዎን የሚቀይር አዲስ የስልጠና ጥሪ! 🚀ለአጫጭር ጊዜ ስልጠና ፈላጊዎች በሙሉ፤ አንጋፋው ጀኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከዩኒቨርሳል የስልጠና እና ስራ አመራር ማማከር አገልግ...
09/07/2026

🚀 የስራ እድልዎን የሚቀይር አዲስ የስልጠና ጥሪ! 🚀

ለአጫጭር ጊዜ ስልጠና ፈላጊዎች በሙሉ፤

አንጋፋው ጀኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከዩኒቨርሳል የስልጠና እና ስራ አመራር ማማከር አገልግሎት ጋር በመተባበር የሚሰጠው የ3ኛው ዙር ስልጠና በደመቀ ሁኔታ ቀጥሏል! 🔥

እርስዎም የገበያ ፍላጎትን መሰረት ያደረጉ ስልጠናዎቻችንን በመውሰድ ብቁና ተወዳዳሪ ይሁኑ።

📚 የምንሰጣቸው ስልጠናዎች፦

🎨 ለፈጠራ ባለሙያዎች (Creative Arts)
• Advanced Video Editing 🎬
• Advanced Photoshop 📸
• Advanced Graphic Design 🎨

📊 ለሂሳብና ቢዝነስ ባለሙያዎች (Business & Finance)
• Modern Peachtree Accounting 📉
• Leadership & Management Skills 👔

🔍 ጥናትና ምርምር (Research)
• Research Methodology & Advanced SPSS 📊

🗣️ ቋንቋና ቴክኖሎጂ (Language & Tech)
• English Language Skills 💬
• Basic Computer Skills 💻

💼 የማማከር አገልግሎት (Consultancy)
• የፕሮጀክት አዋጭነት ጥናት (Feasibility Study) 📝
• የፕሮጀክት ፕሮፖዛል (Project Proposal) 📑

🌟 አሁኑኑ ይደውሉ፤ ይመዝገቡ!

📞 ስልክ ቁጥር፦
👉 0933884400
👉 0911972393

📱 የቴሌግራም አድራሻችን፦
👉 https://t.me/WWETC1

ከልብ እናመሰግናለን!❤

ለእውቀትና ለክህሎት ማደግ በትጋት እንሰራለን! 👍❤

At Universal, we are dedicated to equipping individuals and organizations with the essential skills and knowledge needed 0933884400

ረቡዕ:- ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ምኮሌጁ ከ1,800 በላይ ለሚሆኑ ተመራቂ ሰልጣኞች ለሀገር አቀፍ የብቃት ምዘና የሚያበቃ ሞዴል ፈተና መስጠት ጀመረ!! ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ...
08/07/2026

ረቡዕ:- ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም

ኮሌጁ ከ1,800 በላይ ለሚሆኑ ተመራቂ ሰልጣኞች ለሀገር አቀፍ የብቃት ምዘና የሚያበቃ ሞዴል ፈተና መስጠት ጀመረ!!

ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2018 ዓ.ም ተመራቂ ሰልጣኞችን ለሀገር አቀፍ የሙያ ብቃት ምዘና (CoC) ብቁ የሚያደርገውን ተቋማዊ የሞዴል ምዘና በዛሬው ዕለት በይፋ መስጠት ጀመረ።

ፈተናው ሰልጣኞች ወደ ስራ ዓለም ከመቀላቀላቸው በፊት ክህሎታቸውን የሚፈትሹበት ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑ ተገልጿል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ የተዘጋጀው ይህ ምዘና በ11 ዲፓርትመንቶች እና በ25 የሙያ ዘርፎች ስልጠናቸውን ላጠናቀቁ 1,876 ዕጩ ምሩቃን እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን በዚህ ምዘና 691 ወንድ እና 1,185 ሴት ተመራቂ ሰልጣኞች ይሳተፋሉ።

ተመራቂዎቹ ከሚመዘኑበት አጠቃላይ ውጤት ውስጥ 30% የፅንሰ ሀሳብ (Theory) ምዘና በበይነ-መረብ (Online) እየተሰጠ ሲሆን 70%ቱ ደግሞ የተግባር (Practical) ምዘና በስልጠና ወርክሾፓቸው እየተመዘኑ ነው።

"የዚህ ተቋማዊ ሞዴል ዋነኛ ግብ ተመራቂዎቻችን ለሀገር አቀፉ የብቃት ምዘና ማዕከል ከመቅረባቸው በፊት ያላቸውን እውቀትና ክህሎት ለመፈተሽ እና ክፍተቶቻቸውን ለይቶ ለማረም ነው" ያሉት በኮሌጁ የስልጠና እና አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ዲን የሆኑት አቶ ጄበሳ ሙላቱ ናቸው።

ምክትል ዲኑ አክለውም ሰልጣኞች በስራ ገበያው ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ብቃታቸውን ከፍ ለማድረግ በሚረዱ አምስት የተለያዩ ዘርፎች የልል ክህሎት (Soft Skills) ስልጠናዎች ከምዘናው ጎን ለጎን እየተሰጣቸው መሆኑን አብራርተዋል።

በዛሬው ዕለት የኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ፣ የሆቴልና ሆስፒታሊቲ፣ የሰርቬይንግና ድራፍቲንግ፣ የውድ ወርክ እንዲሁም የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) ሞዴል ምዘናዎች የተሰጡ ሲሆን ቀሪዎቹ በ5 ቀናት ውስጥ ተጠናቀው ሁሉም ተመራቂዎች ለዋናው ፈተና ዝግጁ እንደሚሆኑ ታውቋል።

በተያያዘ ዜና ሁሉም የበጀት ዓመቱ ተመራቂዎች የኮሌጁን የውስጥ ብቃት ምዘና ማለፋቸውም ተጠቁሟል።

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

📣 2ኛው ዙር ምዝገባ ተጀምሯል፤ ስልጠናውም ሐምሌ 6 ቀን 2018 ይጀምራል! ስለሆነምአዋጭና በገበያው ላይ እጅግ ተፈላጊ የሆኑ የአጫጭር ጊዜ ስልጠናዎች ጥሪ እንሆ! የወቅቱን የገበያ ፍላጎት...
07/07/2026

📣 2ኛው ዙር ምዝገባ ተጀምሯል፤ ስልጠናውም ሐምሌ 6 ቀን 2018 ይጀምራል!

ስለሆነም

አዋጭና በገበያው ላይ እጅግ ተፈላጊ የሆኑ የአጫጭር ጊዜ ስልጠናዎች ጥሪ እንሆ!

የወቅቱን የገበያ ፍላጎት ያገናዘበ፣ በተግባር የተደገፈ እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ የሚያስገባ አስተማማኝ ክህሎት ማግኘት ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ እኛ ጋር መፍትሄው አለ!

ኮሌጃችን በኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ ራስዎን እና ተቋምዎን የሚቀይሩባቸውን እጅግ አዋጭ የስልጠና መስኮች ይዞላችሁ ቀርቧል።

1. ለዘመናዊ የመሰረተ-ልማት እና የሀይል አማራጮች
የሕንፃ ላይ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታና ሶላር ሲስተም (Building Electrical Installation & Solar System)

2. ለኢንደስትሪና ለከፍተኛ ማሽነሪዎች
የኢንደስትሪያል ሞተር ኮንትሮል እና ጀነሬተር ዝርጋታና ጥገና
ኢንደስትሪያል አውቶሜሽን (Industrial Automation)

ኒውማቲክስ ሲስተምን ጨምሮ
የሞተር ዋይንዲንግ (Motor Winding)

3. ለቴክኖሎጂ፣ ለደህንነት እና ለቤት ውስጥ እቃዎች
CCTV ካሜራ ዝርጋታና ኮንፊግሬሽን (CCTV Installation & Configuration)

ሳተላይት ዲሽ ዝርጋታ፣ LED TV እና ሬሲቨር ጥገና
የቤት ውስጥ እቃዎች ጥገና (Home Appliances Maintenance)

📌 እኛን ሲመርጡ?
በተግባር (Practical) ላይ ያተኮረ ስልጠና
ምቹ የስልጠና ክፍለ-ጊዜዎች
ብቁ እና ልምድ ያላቸው አሰልጣኞች
ስልጠናውን በጥራት ላጠናቀቁ የምስክር ወረቀት

🎯 ማሳሰቢያ: የስልጠናው ቦታ ውስን ስለሆነ ፈጥነው በመመዝገብ የዕድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ!

📞 ለበለጠ መረጃና ምዝገባ
አድራሻ: - ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ስልክ ቁጥር: 0913143307 ወይም 0923609969

"ክህሎት ያነገበ ትውልድ — ለቀጣይ ብሩህ ተስፋ!"

ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ በመክፈት ይጠቀሙ
https://forms.gle/5wCXaR6bs81Jmqob9

04/05/2026

Address

Addis Ababa, Wingate Street
Addis Ababa
100

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when General Wingate Poly Technic college / ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to General Wingate Poly Technic college / ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ:

Shortcuts

Share