22/06/2026
“ያለ ጥናትና ምርምር መሪነት የሚከናወን ሥራ፤ በጨለማ በድፍረት እንደ መጓዝ ነው” አቶ ይታሰብ ስዩም
ቱ ማ ኢ
ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ተቋማዊ እድገቱን ይበልጥ ለማጠናከር ያለመና በበጀት ዓመቱ በአሰልጣኞቹና ተመራማሪዎቹ የተሰሩ አጠቃላይ የጥናትና ምርምር ሥራዎች ይፋ የተደረጉበት የምርምር መድረክ እየተካሄደ ነው።
ይህ መድረክ የተቋሙ አንጋፋ አሰልጣኞችና ተመራማሪዎች በቱሪዝም እና ሆስፒታሊቲ ዘርፍን ላይ ያሉ አሰራሮችን ለማዘመንና ውጤታማነታቸውን ለማሳደግ ታስበው የተሰሩ 6 (ስድስት) መሠረታዊና ከተግባራዊ ሥራ ጋር የተገናኙ የምርምር ሥራዎቻቸውን የሚቀርብበት ነው።
የምርምር መድረኩን በንግግር የከፈቱት የጥናትና ምርምር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም፤ በማንኛውም ተቋማዊ ዕድገት ውስጥ በማስረጃና በምክንያት ላይ የተመሰረቱ ጥናቶች ያላቸውን ምትክ የሌለው ሚና አጽንኦት ሰጥተው አብራርተዋል።
“ማንኛውንም የአሠራር ማዕቀፍ ሁለንተናዊ ከሆነ የጥናትና ምርምር መሪነት ውጭ ለመተግበር መሞከር በጨለማ ውስጥ በድፍረት እንደመጓዝ ይቆጠራል” ያሉት አቶ ይታሰብ፤ “በአሁኑ ዘመናዊ ማኅበረ-ኢኮኖሚያዊ እውነታ ውስጥ፣ ተቋማዊ ተልእኮዎችን ያለ ጥልቅና ሳይንሳዊ ምርምር ለማሳካት መሞከር በፍጹም አማራጭ ሊሆን አይችልም” ሲሉ ገልጸዋል።
ይፋ የተደረጉት ስድስቱም የምርምር ሥራዎች ሙሉ በሙሉ በተቋሙ የውስጥ አሰልጣኝ ተመራማሪዎች የተሰሩ በመሆናቸው፤ ግኝቶቹ በቀጥታ እውነታውን መሠረት ያደረጉና ተግዳሮቶችን የሚፈቱ ናቸው ተብሎ ይጠበቃል።
መርሃ ግብሩ ኢንስቲትዩቱ ጥራት ያለው ስልጠና ከመስጠት ባለፈ፤ ለዘርፉ የዕውቀት ምንጭና የምርምር ማዕከል የመሆን አቅሙ እያደገ መምጣቱን የሚያሳይ ነው ተብሏል።
በዚህ የጥናትና ምርምር መድረክ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/