16/12/2025
ከትላንት ወዲያ አወስትራሊያ ሲድኒ ውስጥ ሁለት ታጣቂወች ቦንዲ የሚባል የባህር ዳርቻ ተኩስ ከፍተው በአል የሚያከብሩ አይሁዶችን መጨፍጨፍ ጀመሩ። (ሰምታችኋል ሌላ ምን ስራ አላችሁ እዚሁ አፍጥጣችሁ ነው የምትውሉት) እና አገሬው እግሬ አውጭኝ ሲልና እግሩ ያላወጣው በጥይት እየተመታ ሲወድቅ አንድ የ43 ዓመት ጎልማሳ፣ ያውም የሁለት ሴት ልጆች አባት፣ የሶሪያ ስደተኛ፣ ሙስሊም... ዘሎ አንዱን ተኳሽ አነቀው። ማነቅ ብቻ አይደለም መሳሪያውን ነጠቀው።
አህመድ አል አህመድ ይባላል። ራሱ ቆሰለ ግን ካርታ ሙሉ ጥይት ሊጨፈጭፈው የሚችለውን ህዝብ ታደገ። ይታያችሁ ይሄ ሰው ሙስሊም ነው፣ ሶሪያዊ ነው፣ አይሁዶች ሲባል መጀመሪያ አገሩ ላይ የተደረገውን ሙስሊሞች ላይ የሆነውን ሁሉ ማሰቡ አይቀርም፤ ግን የግፍ ጭፍጨፋ የትም በማንም ላይ ልክ አይደለም አለ ፣ ከእኔነት ወጥቶ ነፍሱን ሰጥቶ ህዝብ ታደገ! አወስትራሊያ በጠቅላይ ሚንስትሯ በኩል ብሔራዊ ጀግና አለችው። በሚሊየን የሚቆጠር ዶላር ከመላው አለም በዶኔሽን ጎረፈለት(ሆስፒታል ነው)
የገረረረረረረረመኝ ነገር ...ኔትንያሆ የሚባል እንጉልፋቶ ሰውየ ምን ቢል ጥሩ ነው?
"አንዱን ተኳሽ ተናንቆ ብዙሃን እንዳይገደሉ የታደገው ((( የኛው አይሁድ ነው)) ቪዲዮ ባይኖርና ልብሳቸውን ጥለው ሲሮጡ ባናይ እሽ። ይሄን ሰውየ እንዲህ ዓለም ያየውን ከካደ ጋዜጠኛም ምስክርም በሌለበት የፍልስጤምና ሶሪያ ንፁሐን ላይ በቲቪ እየቀረበ የሚቀባጥረውን ማን ያምናል?