Alu tub21

Alu tub21 First i would like thanks to God ....�
Next One of the things that make me happy is seeing people's happiness���

16/06/2023
 #የቱን ትመርጣለህ !ኢላማህን በሁለት መንገድ መምታት ትችላለህ ለረጅም ሰዓት የቱ ጋር መምታት እንዳለብህ በማሰብ ወይስ ዝም ብለህ ለኢላማህ ቅርብ የመሰለህ ቦታ ተኩሰህ እያስተካከልክ ኢላማ...
29/01/2023

#የቱን ትመርጣለህ !

ኢላማህን በሁለት መንገድ መምታት ትችላለህ ለረጅም ሰዓት የቱ ጋር መምታት እንዳለብህ በማሰብ ወይስ ዝም ብለህ ለኢላማህ ቅርብ የመሰለህ ቦታ ተኩሰህ እያስተካከልክ ኢላማህን መምታት።

መልስህን ለህይወትም ተጠቀምበት !

መልካም እለተ ሰንበት ተመኘን 🙏

ደስተኛ መሆን አለብህ!አንዳንዴ በጣም ከባድ ችግር የመሰለህ ነገር አስቂኝ ሆኖ ቁጭ ይላል፤ በዚህ ምድር ለመኖር የቀረህ 1 ሳምንት ነው ቢባል የትኛው ሰው ነው የኑሮ ውድነት የሚያሳስበው? የ...
26/09/2022

ደስተኛ መሆን አለብህ!

አንዳንዴ በጣም ከባድ ችግር የመሰለህ ነገር አስቂኝ ሆኖ ቁጭ ይላል፤ በዚህ ምድር ለመኖር የቀረህ 1 ሳምንት ነው ቢባል የትኛው ሰው ነው የኑሮ ውድነት የሚያሳስበው? የትኛው ሰው ነው የፍቅረኛው ስልክ አለማንሳት የሚያበሳጨው? ያለህን አጭር ጊዜ እንዴት አጣጥመህ እንደምታልፈው ታስባለህ እንጂ በፍፁም አተክዝም።

አየህ ወዳጄ አሁንም የቀረህ እድሜ ስንት እንደሆነ አታውቀውም፤ ተኝተህ ማደርህን እንኳን እርግጠኛ አይደለህም! ስለዚህ ለማን ብለህ ነው የምታዝነው? በፈጣሪህ እመን ከዛ የምትችለውን ሞክር የቀረውን ለነገ ተወው!

ገራሚ ምሽት ተመኘሁ

እምነት!ልፋትህ መና የሚቀር ከመሰለህ ተሸውደሀል፤ ፀሎትህ ደመና ላይ የሚንሳፈፍ ከመሰለህ የፈጣሪ አሰራር አልገባህም ማለት ነው። ከጠየክ የማይሰጥህ ነገር የለም፤ ወዳጄ ተስፋ ቆርጠህ ልታቆም...
21/09/2022

እምነት!

ልፋትህ መና የሚቀር ከመሰለህ ተሸውደሀል፤ ፀሎትህ ደመና ላይ የሚንሳፈፍ ከመሰለህ የፈጣሪ አሰራር አልገባህም ማለት ነው።

ከጠየክ የማይሰጥህ ነገር የለም፤ ወዳጄ ተስፋ ቆርጠህ ልታቆም ስትል ይሄንን ሀሳብ አስታውስ 'አንተ ስትጨርስ እሱ ይጀምራል!' ከልፋት በኋላ ደስታ....ከመጨነቅ በኋላ እርካታ እንዳለ አማኞች ምስክር ናቸው!

ተስፋ የሞላበት ሌሊት ተመኘሁ🙏

ሀሳብና ስሜትማንኛውም ሀሳብ ወዳንተ ሲመጣ ስሜት ሰጥተህ ከተቀበልከው አንተ ውስጥ ይቀራል ህይወትህንም ይቆጣጠረዋል ለምሳሌ የሰው ጉዳት አይተህ ልብህ እስኪሰበር ካዘንክ አንተ ጋር ተመዘገበ ...
15/09/2022

ሀሳብና ስሜት

ማንኛውም ሀሳብ ወዳንተ ሲመጣ ስሜት ሰጥተህ ከተቀበልከው አንተ ውስጥ ይቀራል ህይወትህንም ይቆጣጠረዋል ለምሳሌ የሰው ጉዳት አይተህ ልብህ እስኪሰበር ካዘንክ አንተ ጋር ተመዘገበ ማለት ነው ፤ ስለዚህ የምትፈልገውን ህልምህንም ልብህ እስኪደነግጥ በስሜት አንተ ውስጥ አስቀረው ።

ምርጥ ምሽት ተመኘን 🙏

ጠንካራ ሁን !ብዙ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እየመጡ ነው የኛን ህይወት ለማቅለል እኛም ያለገደብ ህይወታችንን ካቀለልን ምን አገባን ብለን መጠቀማችንን ቀጥለናል። አንዳንዴ ግን ቆም ብለን እንጠይቅ...
11/09/2022

ጠንካራ ሁን !

ብዙ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እየመጡ ነው የኛን ህይወት ለማቅለል እኛም ያለገደብ ህይወታችንን ካቀለልን ምን አገባን ብለን መጠቀማችንን ቀጥለናል። አንዳንዴ ግን ቆም ብለን እንጠይቅ የምር ህይወታችንን እያቀለልን ነው ወይስ ከጥንካሬያችን አየቀነሰ ስንፍናን እየሸለመን ነው?

የፍቅር ምሽት ተመኘሁ 🙏

ጥሩ ነገሮች ላይ ትኩረት ስናደርግ ህይወታችን ውስጥ ሁሌም ጥሩ ነገር ይኖራል
07/09/2022

ጥሩ ነገሮች ላይ ትኩረት ስናደርግ ህይወታችን ውስጥ ሁሌም ጥሩ ነገር ይኖራል

ግድ የለሽ አትሁን!ጎርፍ ሲወስድህ እያሳሳቀ ነው፤ ስንፍና በአንድ ቀን ከሰው በታች አያደርግህም፤ በየቀኑ የምታደርጋቸው ትናንሽ የስንፍና ውሳኔዎች ግን ተጠራቅመው ነገ ዋጋ ያስከፍሉሀል። ከዛ...
04/09/2022

ግድ የለሽ አትሁን!

ጎርፍ ሲወስድህ እያሳሳቀ ነው፤ ስንፍና በአንድ ቀን ከሰው በታች አያደርግህም፤ በየቀኑ የምታደርጋቸው ትናንሽ የስንፍና ውሳኔዎች ግን ተጠራቅመው ነገ ዋጋ ያስከፍሉሀል።

ከዛ ገቢህን ስታየው ያንስብሀል ይሄ አይገባኝም ትላለህ፣ ስራህን ስታየው ውጤት አልባ ልፋት ነው፣ በምድር ለመደሰት አልታደልኩም ማለት ነው እስክትል ድረስ ህይወት አድካሚ ትሆናለች።

ህይወትህን እንዲህ አርጎ የሚያበላሸው ለነገ የምታሳድረው ስራ፣ ምንም ችግር የለውም ብለህ የተውከው የቀን ግዴታህና የማይረቡ ትንንሽ ውሳኔዎችህ ናቸው። ግድየለሽ አትሁን ትንሹ ጥረትህ ነው ትልቁን ውጤት የሚያመጣው!

ድንቅ ምሽት መኘሁላችሁ🙏

ህልመኛ መሆን አለብህ!ህልመኛ ማለት መጀመሪያ ምን እንደሚፈልግ ጠንቅቆ የሚያውቅ ነው፤ ከዛ ለምን እንደሚፈልገው ማወቅ የሚችል ነው፤ ቀጥሎ ግን እንዴት አርጎ የሚፈልገውን ማግኘት እንዳለበት ...
03/09/2022

ህልመኛ መሆን አለብህ!

ህልመኛ ማለት መጀመሪያ ምን እንደሚፈልግ ጠንቅቆ የሚያውቅ ነው፤ ከዛ ለምን እንደሚፈልገው ማወቅ የሚችል ነው፤ ቀጥሎ ግን እንዴት አርጎ የሚፈልገውን ማግኘት እንዳለበት ለማወቅ ጊዜ እና ትዕግስት ያለው ሰው ነው።

"እንዴት አድርጌ የምፈልገውን ላግኝ?" የሚለውን ጥያቄ ወይ ፈጣሪ ይገልጠዋል፣ ወይ የራስህ እውቀትና ልምድ በጊዜ ሂደት ይመልሰዋል ወይ አንተ ባልገመትከው መንገድ ጥያቄህ መልስ ያገኛል። ወዳጄ አሁን የደረስክበትን በአንድ ወቅት ደጋግመህ ታስበው ነበር እንጂ እንዴት እዚህ ጋር እንደምትደርስ አታውቅም ነበር እኮ!

ውብ ቀን ተመኘሁላችሁ🙏

👉👉 ሰባተኛ ፎቅ             𝕒𝕝𝕦  ✍ሰውየው ሰባተኛ ፎቅ በረንዳ ላይ ሆኖ ንፋስ ይቀበላል። አካባቢውን እየቃኘ እያለ አንድ ሰውምድር ላይ ሆኖ እጁን ሲያውለበልብለት ይመለከታል።በድም...
02/09/2022

👉👉 ሰባተኛ ፎቅ
𝕒𝕝𝕦 ✍

ሰውየው ሰባተኛ ፎቅ በረንዳ ላይ ሆኖ ንፋስ ይቀበላል። አካባቢውን እየቃኘ እያለ አንድ ሰው
ምድር ላይ ሆኖ እጁን ሲያውለበልብለት ይመለከታል።
በድምፅ መደማመጥ ስላልቻሉ ምድር ያለው ሰውዬ ሰባተኛ ፎቅ ላይ ያለውን ሰውዬ በምልክት 'ና' ይለዋል።
ሰባተኛ ፎቅ ላይ የነበረው ሰውዬ ስለሰውዬው ማንነትና ስለፈለገው ነገር እያሰበ ከፎቁ ይወርዳል። የምድሩ ሰውዬ ጋር እንደደረሰም: ፎቅ ላይ የነበረው: "አቤት ወንድሜ ምን ፈልገህ ነው?" ምድር ላይ ያለው: ፊቱን አሳዛኝ ካደረገ በኋላ "ይቅርታ ጌታዬ አለፋሁዎት አይደል? ለማኝ ነኝ። እስኪ ስለ እግዚአብሔር ብለው ያለዎትን ይመፅውቱኝ" ሲለው ሰውየው ከሰባት ፎቅ ድረስ በቁም ነገር ወርዶ በሰማው ነገር እጅግ ስለተበሳጨ
ለማኙን ካልገደልኩ ብሎ አስቸገረ።
ትርምሱ በአገላጋዮች ከረገበ በኋላ ለማኙ ላይ እየዛተ ወደነበረበት ፎቅ ይመለሳል።
እየተመለሰ እያለ ግን ለማኙ የምሩን ተቸግሮስ ቢሆን እያለ እያሰበ ነበር።
መጀመሪያ የነበረበት ሰባተኛ ፎቅ ላይ ደርሶ ወደታች ሲመለከት ለማኙ አሁንም አንጋጦ
ሲመለከተው ያያል።
ተስፋ ቆርጦ በረጅሙ ከተነፈሰ በኋላ ያፏጭና ለማኙን ይጠራዋል።
ለማኙ በደስታ እየተፍነከነከና የሰውዬውን ልብ ያራራለትን አምላክ እያመሰገነ ሰባተኛ ፎቅ ከወጣ በኋላ:
ምድር የነበረው (ለማኙ): እየተቅለሰለሰ "አቤት የኔ ጌታ?" ቢለው
ፎቅ ላይ ያለው (ተለማኝ): "እግዚአብሔር ይስጥልኝ!!!" ብሎት እርፍ 😁😁

Address

Bahir Dar
HTTPS://WWW.INSTAGRAM.COM/P/CH-SCR5MVTL/?IGSHID=YMMYMTA2M2Y%3D

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Alu tub21 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Alu tub21:

Share