04/12/2025
እንደሚታወቀው፣ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ነፃ የህግ ድጋፍ ማዕከል ከ19 በላይ ለሚሆኑ ዓመታት፣ ጠበቃ መቅጠር የማይችሉና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ግለሰቦች፣ ማለትም ለሴቶች፣ ሕጻናት፣ ለአረጋውያንና የኢኮኖሚ አቅም ለሌላቸው ወገኖች ነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱ ይታወቃል።
አሁንም የተለያየ የሕግ ድጋፍ የሚያሻቸው ሁሉ፣ ድጋፍ ለማግኘት በየትኛውም ቢሮአችን መምጣት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
በባህር ዳር የሚገኙ የቢሮዎቻችን አድራሻዎች የሚከተሉት ናቸው።
1. በባህር ዳርና አከባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ
2. ባህርዳር ዙሪያ ወረዳ ፍርድ ቤት፣ 《ዲፖ፣ በአማራ መምህራን ማኅበር ቅጥር ግቢ ውስጥ》
3. በባህር ዳር ማረሚያ ቤት ናቸው።
As is known, for more than 19 years, the Bahir Dar University Free Legal Aid Service Center has been providing free legal aid services to vulnerable and indigent groups, including women, children, the elderly, and individuals of low economic status who cannot afford attorneys. Those in need of legal assistance may visit any of our offices to receive support. Our offices in Bahir Dar are located at:
1. Bahir Dar and its surrounding High Court (within the compound)
2. Bahir Dar Zuria Woreda Court (around Dipo, within the Amhara Teachers Association compound)
3. Bahir Dar Prison Administration Center