Asrat Woldeyes Health Science Campus , Debre Berhan University, Ethiopia.

Asrat Woldeyes Health Science Campus , Debre Berhan University, Ethiopia. Hakim Gizaw Hospital

የሀኪም ግዛው ሆስፒታል በአጣዬ ከተማ ነፃ የቀዶ ሕክምና ዘመቻ ማካሄድ ጀመረ============================የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ሀኪም...
20/08/2026

የሀኪም ግዛው ሆስፒታል በአጣዬ ከተማ ነፃ የቀዶ ሕክምና ዘመቻ ማካሄድ ጀመረ
============================
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ሀኪም ግዛው ሆስፒታል፣ ከአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጋር በመተባበር በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር በአጣዬ ከተማ ነፃ ምርመራና የቀዶ ሕክምና ዘመቻ ማካሄድ ጀምሯል።

በዘመቻው ላይ የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ የሕክምና ትምህርት ቤት ዲን ዶ/ር አሰፋ ፋንታሁንን ጨምሮ የተለያዩ የሕክምና ባለሙያዎችን ያካተተ የቀዶ ሕክምና ቡድን በስፍራው ተገኝቷል።

ቡድኑ በዘመቻው ወቅት የእንቅርትና የአንገት አካባቢ እጢዎች፣ የሐሞት ጠጠር፣ የአንጀትና የፊንጢጣ አካባቢ ችግሮች እንደ ፊስቱላና ኪንታሮት፣ በተለያዩ የሰውነት አካባቢዎች የሚከሰቱ እብጠቶች፣ የጡት ካንሰር፣ የትርፍ አንጀት ችግሮች፣ የድንገተኛ ሕክምና፣ በእግር ላይ የሚታዩ የደም ሥር ችግሮች እንዲሁም የሽንት ቱቦ እጢዎችና የተለያዩ ችግሮች ላይ ነፃ ምርመራና የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ይሰጣል።

የሕክምና ቡድኑ ከነሐሴ 13 እስከ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለሰባት ተከታታይ ቀናት በአጣዬ ከተማ በመቆየት፣ ከአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች ጋር በመሆን ለከተማው ማኅበረሰብ አገልግሎቶችን በነፃ እንደሚሰጡ ታውቋል።

በተያያዘ ዜና በዚሁ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር የሀኪም ግዛው ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች ቡድን ወደ ሀገረ ማሪያም ከሰም ወረዳ ቱለፋ ከተማ አስተዳደር በመሄድ ለከተማው ማህበረሰብ የተለያዩ የጤና ምርመራና የሕክምና አገልግሎቶችን በነፃ እየሰጠ ይገኛል። በተጨማሪም ቡድኑ ለማህበረሰቡ የጤና ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን ያከናውናል፡፡
*************************
ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም
የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ቡድን

ታዓማኝ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት:-
በፊስቡክ ፡- https://www.facebook.com/profile.php?id=100087595710493
በቴሌግራም፡- https://t.me/asratcampus
በዩቲዩብ ገጻችን፡- www.youtube.com/
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/
ዌብሳይት፡ https://www.dbu.edu.et/campus/awhsc/awhsc_latest በመወዳጀት ይከታተሉን፡

19/08/2026
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጠናክሮ ቀጥሏል========================ነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም፡፡ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ሀኪም ግዛው ሆ...
19/08/2026

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጠናክሮ ቀጥሏል
========================
ነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም፡፡ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ሀኪም ግዛው ሆስፒታል በተለያዩ የጤና አገልግሎት ዘርፎች እያከናወነ ያለው የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ከሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት አራት ሳምንታት በተካሄደው የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር ለበርካታ ዜጎች ነፃ የጤና ምርመራ፣ የሕክምና እና የጤና ግንዛቤ ማስጨበጫ አገልግሎቶች ተሰጥተዋል።

በዚሁ መርሃ ግብር የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያዎች ቡድን በደብረ ብርሃን ከተማ በሚገኘው ኢታል አልሙኒየም ፋብሪካ በመገኘት ነፃ የደም ግፊትና የስኳር ምርመራ፣ የጡት ካንሰርና የማህጸን በር ካንሰር ምርመራ፣ እንዲሁም ተያያዥ የሕክምና አገልግሎቶችን ሰጥተዋል።

በተጨማሪም ወደ ጫጫ ከተማ በመሄድ ለከተማው ማህበረሰብ የተለያዩ የጤና ምርመራና የሕክምና አገልግሎቶችን የተሰጡ ሲሆን ከሕክምና አገልግሎቱ በተጨማሪም በተለያዩ የጤና ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ የጤና ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን ተከናውኗል።

በሌላ በኩል ከጫጫ ጤና ጣቢያ ጋር በመተባበር በከተማው የሚገኘውን የአረጋውያን መኖሪያ መንደር እና የሰርቲ ጤና ኬላን በመጎብኘት ያሉበትን ሁኔታ በመመልከትና በመገምገም ተጨማሪ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች ለመለየት ጥረት ተደርጓል።

የሀኪም ግዛው ሆስፒታል የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱን በማጠናከር ለማህበረሰቡ ተደራሽ፣ ተገቢና ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለማቅረብ እየሰራ ይገኛል። ይህም ለማህበረሰቡ ያለውን ማህበራዊ ኃላፊነትና ቁርጠኝነት የሚያሳይ ተግባር ነው።
*********************************
ታዓማኝ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት:-
በፊስቡክ ፡- https://www.facebook.com/profile.php?id=100087595710493
በቴሌግራም፡- https://t.me/asratcampus
በዩቲዩብ ገጻችን፡- www.youtube.com/
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/
ዌብሳይት፡ https://www.dbu.edu.et/campus/awhsc/awhsc_latest በመወዳጀት ይከታተሉን፡
********************
የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ቡድን

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አመራሮች በአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ጉብኝት አካሄዱ============================================ነሐሴ 12 ቀን 2018...
18/08/2026

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አመራሮች በአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ጉብኝት አካሄዱ
============================================
ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም (አ/ወ/ጤ/ሳ/ካ) ። የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አመራሮች በዩኒቨርሲቲው የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ጉብኝት አካሄዱ።

በጉብኝቱ የኢፌዴሪ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር እና የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ፣ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሰማረ መለስ፣ የቦርድ አባልና የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት፣ ሌሎች የቦርድ አባላት፣ የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዝዳንቶች እና የካምፓሱ ሥራ አስፈጻሚዎች ተገኝተዋል።

የቦርድ አመራሮቹ በጉብኝታቸው ወቅት የካምፓሱን ዘመናዊ የመማሪያ ክፍሎችና ላቦራቶሪዎች፣ የተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ፣ የተማሪዎች መኝታ ቤቶች እንዲሁም የግቢውን መሠረተ ልማትና የውበት ሥራዎች በመዘዋወር ተመልክተዋል።

በጉብኝቱም የካምፓሱ የመማርና ማስተማር ሁኔታ፣ የላቦራቶሪዎች አቅም፣ የተማሪዎች መኖሪያና መመገቢያ አገልግሎቶች እንዲሁም የግቢው መሠረተ ልማት አፈጻጸም በተመለከተ ምልከታ ተደርጓል።

ጉብኝቱ የካምፓሱን የሥራ አፈጻጸም በተጨባጭ ለማየት፣ ያሉትን ጥንካሬዎች ለማጠናከርና በቀጣይ የሚሻሻሉ ጉዳዮችን ለይቶ በመሥራት የተሻለ የትምህርትና የጤና ሳይንስ ሥልጠና አካባቢ ለመፍጠር ያለውን ትኩረት ያሳያል ።
*********************
ታዓማኝ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት:-
በፊስቡክ ፡- https://www.facebook.com/profile.php?id=100087595710493
በቴሌግራም፡- https://t.me/asratcampus
በዩቲዩብ ገጻችን፡- www.youtube.com/
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/
ዌብሳይት፡ https://www.dbu.edu.et/campus/awhsc/awhsc_latest በመወዳጀት ይከታተሉን፡

NGAT ተፈታኞች በሙሉ ==============
18/08/2026

NGAT ተፈታኞች በሙሉ
==============

A Historic Achievement for the School of Pharmacy, Asrat Woldeyes Health Sciences Campus, DBU===========================...
17/08/2026

A Historic Achievement for the School of Pharmacy, Asrat Woldeyes Health Sciences Campus, DBU
===========================
On August 17, 2026, the School proudly witnessed the successful thesis defenses of the first-ever cohort of six MSc students in Pharmacology. This historic achievement marks a significant step forward in the development of postgraduate education, research, and academic excellence within the School of Pharmacy.

After two years of dedicated study, rigorous research, perseverance, and commitment, these students have successfully reached this important milestone. Their achievement reflects not only their hard work and determination, but also the invaluable guidance of their supervisors and the unwavering support of the School, the University, academic and technical staff, families, and all those who contributed to their journey.

Heartfelt congratulations to all six MSc graduates, their supervisors, academic and technical staff, families, and everyone who contributed to this success!

May this remarkable beginning inspire many more generations of postgraduate students and pave the way for greater achievements in pharmaceutical education, research, and professional service.

Congratulations on making history!

DBU Asrat Woldeyes Health Sciences Campus School of Pharmacy
****************************
For reliable and up-to-date information:
Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100087595710493
Telegram: https://t.me/asratcampus
YouTube: www.youtube.com/
TikTok፡- https://www.tiktok.com/
Website: https://www.dbu.edu.et/campus/awhsc/awhsc_latest
Follow us by liking

14/08/2026
የሀኪም ግዛው ሆስፒታል በደብረ ብርሃን ማረሚያ ቤት ነፃ የቲቢ ምርመራ በማካሄድ የምርመራ መዘግየትን አስቀረ==================================የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አ...
14/08/2026

የሀኪም ግዛው ሆስፒታል በደብረ ብርሃን ማረሚያ ቤት ነፃ የቲቢ ምርመራ በማካሄድ የምርመራ መዘግየትን አስቀረ
==================================
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ሀኪም ግዛው ሆስፒታል በክረምት ወቅት አጠናክሮ በቀጠለው የክረምት በጎ ፍቃድ የጤና አገልግሎት መርሃ ግብር በደብረ ብርሃን ማረሚያ ቤት ለሚገኙ ታራሚዎች ነፃ የቲቢ (የሳንባ ነቀርሳ) ምርመራ እያካሄደ ነው።

ሆስፒታሉ ዘመናዊና ፈጣን የምርመራ ቴክኖሎጂ የሆነውን GeneXpert የላቦራቶሪ መሳሪያ በመጠቀም ከታራሚዎች የሚሰበሰቡ የአክታ ናሙናዎችን በመመርመር ፈጣንና አስተማማኝ የቲቢ ምርመራ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተገልጿል።

በመሆኑም የሀኪም ግዛው ሆስፒታል የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎቱን በማረሚያ ቤቱ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች በነፃ በመስጠት በርካታ ጥቅሞችን ማስገኘት አስችሏል። ከነዚህ መካከል ናሙናዎችን ወደ ሌሎች ላቦራቶሪ በመላክ የሚመጣውን ጊዜና እንግልት ቀንሷል፤ የቲቢ ምልክት ያላቸው ታራሚዎች በወቅቱ ተመርምረው ውጤቱ በማወቅ በፍጥነት ወደ ህክምና እንዲገቡ ዕድል ፈጥሯል በተጨማሪም ቲቢን በቅድመ ምርመራ መለየት፣ የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠርና የማረሚያ ቤቱን የጤና ደህንነት ለማጠናከር ያግዛል ነወ የተባለው።

ይህ ተግባር የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሀኪም ግዛው ሆስፒታል ከመደበኛው የህክምና አገልግሎት ባሻገር ለማህበረሰቡና ለልዩ ትኩረት ለሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚያደርገውን የጤና ድጋፍና የበጎ አድራጎት ቁርጠኝነት በተግባር ያሳየ አርአያነት ያለው ሥራ ነው።
***************
ነሐሴ 08/2018 ዓ.ም
አ/ወ/ጤ/ሳ/ካ

ታዓማኝ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት:-
በፊስቡክ ፡- https://www.facebook.com/profile.php?id=100087595710493
በቴሌግራም፡- https://t.me/asratcampus
በዩቲዩብ ገጻችን፡- www.youtube.com/
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/
ዌብሳይት፡ https://www.dbu.edu.et/campus/awhsc/awhsc_latest በመወዳጀት ይከታተሉን፡

Address

Debre Birhan
0000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Asrat Woldeyes Health Science Campus , Debre Berhan University, Ethiopia. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Asrat Woldeyes Health Science Campus , Debre Berhan University, Ethiopia.:

Shortcuts

Share