GIS , Autocad , Surveying and Engineering information

GIS , Autocad , Surveying and Engineering information Give conditonal information conducted with surveying, architectureal , constructional and other tec

these page is created to give educational information conducted with SURVEYING , CIVIL ENGINEERING, ARCHITECTURAL department. to address this information for other please SHARE, LIKE,COMMENT

https://www.facebook.com/share/14Lrs3HYJZE/
14/08/2025

https://www.facebook.com/share/14Lrs3HYJZE/

ካዳስተር ማለት ምን ማለት ነው?
*********
ካዳስተር ማለት የመሬት ይዞታን መሰረት ያደረገ የመሬት መረጃ ሥርዓት ሲሆን የሚደራጁት መረጃዎችም በዋናነት ሁለት ዓይነት ናቸው፡፡

ይኸውም የካርታ መረጃ (spatial data) የይዞታውን መገኛ ቦታ፣ ወሰኑን፣ ስፋቱንና ቅርፁን፣ አጎራባች ይዞታዎችን እና አዋሳኝ መንገዶችን የሚያሳይ ሲሆን ሌላኛው ገላጭ መረጃ (non-spatial data) በመባል የሚታወቀው የባለይዞታውን ማንነት (ስም፣ አድራሻ፣ ጾታ፣ የጋብቻ ሁኔታ፣ ወዘተ.)፣ በይዞታው ላይ ያለው መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት፣ የቦታው አገልግሎትና ደረጃ፣ ወዘተ… እንደ ካዳስተር ዓይነቱ ተዘርዝረው የሚያዙ መረጃዎችን ያካትታል፡፡ እነዚህ ሁለት የመረጃ ዓይነቶችም በልዩ የይዞታ መለያ ኮድ እንዲገናኙ ይደረጋል፡፡

ካዳስተር በሦስት ዓይነት ይከፈላል፡-
>አንደኛው ህጋዊ ካዳስተር ሲሆን ለእያንዳንዱ ህጋዊ ወሰን ለተለየለት ይዞታ፣ የይዞታ መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት የሚያመለክት መረጃ ከይዞታው ካርታ ጋር አጣምሮ የያዘ ወቅታዊ የመሬት ይዞታ መረጃ ሥርዓት ሲሆን አስፈላጊነቱም የትኛው ይዞታ በማንና በምን አግባብ ተይዟል የሚለውን በማጣራት የባለይዞታውን የይዞታ ዋስትና ለማረጋገጥ ነው፡፡

>ሁለተኛው ዓይነት ፊስካል ካዳስተር ሲሆን በይዞታው ላይ ስላረፈው ቋሚ ንብረት ዝርዝር መረጃ እና የመሬቱን ወቅታዊ ግምት ከይዞታው ካርታ ጋር የሚይዝ ሆኖ ለቦታና ለንብረት ግብር ክፍያ የሚያገለግል ሥርዓት ነው፡፡

> ሦስተኛው ዓይነት ካዳስተር ሁለገብ/ሁሉን አቀፍ ካዳስተር/ የሚባለው በሁለቱ የካዳስተር ዓይነቶች የተገለፁትን መረጃዎች የሚይዝ ሆኖ በተጨማሪም የመሰረተ ልማት፣ የአካባቢ ጥበቃ እና ሌሎች መረጃዎችን እና ካርታን አካቶ የሚይዝ የመረጃ ሥርዓት ነው፡፡

የካዳስተር ሥርዓት በመገንባት ሂደት በርካታ ልምድ ያላቸውና ብዙ ርቀት የሄዱ አገሮች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በዚህ የግንባታ ሂደት እያንዳንዱ አገር ከራሱ ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር አጀማመሩና አካሄዱ የተለያየ ነው፡፡

አንዳንድ ሀገሮች ከፊስካል ካዳስተር ጀምረው ወደ ሁለገብ የሄዱ አሉ ለምሳሌ ፈረንሳይ፤ ሌሎች ደግሞ ከህጋዊ ካዳስተር ጀምረው ወደ ሁለገብ የካዳስተር ሥርዓት የተሸጋገሩበት ሁኔታም አለ ለምሳሌ ኔዘርላንድ፡፡

በእኛ አገር ደረጃም ከዚህ ቀደም በከተማ ደረጃ ሥርዓቱን ለመዘርጋት በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ የተሞከሩትም ሁለገብ ካዳስተርን በመዘርጋት ነበር ሆኖም ግን የሚፈለገውን ውጤት ሊያመጣና የሥርዓቱን ዘለቄታዊነት የሚያረጋግጥ ሊሆን አልቻለም፡፡

በመሆኑም በቅድሚያ ባለይዞታውን ተጠቃሚ የሚያደርገው ከተማ አስተዳደሮችም መሬታቸውን ቆጥረው ሊያውቁ የሚችሉበትን የህጋዊ ካዳስተር በመዘርጋት በመቀጠልም የፊስካል ካዳስተር ብሎም ወደ ሁለገብ ካዳስተር የሚያድግ ሥርዓት መዘርጋቱ ሥርዓቱን ቀጣይ ለማድረግ የሚያስችል በመሆኑ ተመርጧል፡፡ በዚህ ሂደት የካርታው መረጃ አንድ ጊዜ የሚዘጋጅ ሲሆን ለውጥን ተከትሎ ወቅታዊ ማድረግ የሚያስፈልግ ሆኖ ሁሉም የካዳስተር ዓይነት መሰረት የሚያደርገው በህጋዊ ካዳስተር የተዘጋጀውን የካዳስተር ካርታ ነው። ሌሎች መረጃዎች ተደማሪ እየተደረጉ ወደ ሁለገብ ካዳስተር ሥርዓት የሚያድግ ይሆናል፡፡

የህጋዊ ካዳስተር ዝርጋታ ተግባራዊ መሆን የሚያስገኛቸው ፋይዳዎች

*******
✍️በአገር ደረጃ በአገልግሎት አሰጣጥ የሚስተዋለውን የተወሳሰበ ችግር ይህ የአሰራር ስርአት ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ በሚሆንበት ወቅት ይሄን ችግር በመሰረታዊነት እንደሚፈታ ይታመናል፤

✍️በዘርፉ የግብይት ስርአቱን ቀላል፣ ግልፅ፣ ተደራሽ በማድረግ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ከማድረጉ ባሻገር በአገር ኢኮኖሚ እድገቱ ላይ የራሱን አውንታዊ ሚና መጫወት ይችላል፤

✍️በዘርፉ በመረጃ አያያዝ ጉድለት የነበረውን ችግር ተጠቅመው ጥቂቶች አላግባብ የሚበለፅጉበትንና ህጋዊ ባለይዞታዎችን ለተለያዩ ጉዳቶች ይዳርግ የነበረውን የአሰራር ችግር ሊፈታ ይችላል ተብሎ ይታመናል፣

✍️ በክልልም ሆነ በፌደራል ደረጃ በዘመናዊ መንገድ የሚደራጀው የከተማ መሬት ይዞታ መረጃ አዳዲስ ፖሊሲዎችን፣ አሰራሮችንና ህጎችን ለማመንጨት የተሻለ ግብአት ሆኖ ያገለግላል፤

✍️ የከተማ አስተዳደሮች የሚያስተዳድሩትን መሬት ቆጥረው እንዲያውቁ፣ የትኛውን መሬት ለየትኛው አገልግሎት ማዋል እንዳለባቸው አቅደው እንዲሰሩና በተገቢው መንገድ እንዲያስተዳድሩ ከፍተኛ እገዛ ያደርግላቸዋል፤

✍️ከተሞች ከመሬት ሃብታቸው መሰብሰብ የሚገባቸውን ግብር እና ኪራይ በተገቢው መንገድ በመሰብሰብ ለለከተማው የመሰረተ-ልማት ግንባታ በማዋል ከተሞች በስርአቱ ያድጋሉ፣ የከተማው ነዋሪም የልማቱ ተጠቃሚ ይሆናል፤

✍️የካዳስተር ስርአቱ በሚፈጥረው የመረጃ ምልዑነት በከተማ መሬት ይዞታ የሚስተዋለውን በዜጎች መካከል የሚፈጠረውን ክርክር ይቀንሳል፣ በዚህ ምክንያት የሚያጠፋውን ገንዝብ፣ ጊዜ እና የፍትህ መጓደል ይቀንሳል፤

✍️ማንኛውም ዜጋ በከተማ መሬት ይዞታ ዘርፍ ማግኘት የሚፈልገውን መረጃ ብዙ ውጣውረድ ሳይገጥመው በቀላሉ እንዲያገኝ ያደርጋል፤

✍️በከተሞች ህጋዊ ካዳስተርን መገንባት ከተቻለ የውጭም ሆነ የአገር ውስጥ ባለሃብቶች እምነት ስለሚያሳድሩ ሃብታቸውን ልማት ላይ ያውላሉ በዚህም ነዋሪው ተጠቃሚ ይሆናል፣ ከተሞች ያድጋሉ፣ ሳቢም ይሆናሉ፤

✍️በዘርፉ ሙያ ለተሰማራው አመራርም ሆነ ባለሙያ የእውቀት ሽግግር እንዲፈጠር ያደርጋል፣ አቅምም ይገነባል፣ በዚህም በየደረጃው ተጠቃሚ እንዲሆን ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡

09/03/2025

🚨🌹 Explore Dream Houses 🌹🚨
Floor plans👉https://bit.ly/4eWYzgx

Owning your own home offers numerous benefits, whether during youth or after retirement. It is a significant milestone that provides both financial and personal advantages.

One of the primary benefits of homeownership is financial stability and growth. Building equity in a home provides a stable financial foundation and the opportunity for wealth accumulation over time. Real estate often appreciates, making it a solid investment compared to renting.

Personalization and freedom are also key advantages. When you own your home, you have the freedom to personalize and renovate to your taste. From choosing paint colors to landscaping, it is all up to you without needing a landlord's approval. This level of control allows you to create a living space that truly reflects your personality and preferences.

Homeownership fosters a sense of community and belonging. Settling down in a neighborhood encourages stronger ties and a greater sense of belonging. You become part of a community, building relationships with neighbors and contributing to the local area.

There are also significant tax benefits to owning a home. Homeowners can take advantage of various tax deductions, including mortgage interest and property taxes. These deductions can significantly reduce your taxable income, making homeownership even more financially advantageous.

For retirees, owning a home means no monthly rent payments, which can significantly reduce living expenses. Additionally, owning your home provides a sense of security and stability during retirement, allowing you to enjoy your golden years without the stress of housing costs.

Finally, making consistent mortgage payments can positively impact your credit score, helping you secure better interest rates for future loans and financial endeavors. This can open up additional financial opportunities and provide further stability.

Types of houses that are low cost and capable of

09/03/2025
09/03/2025

Perfect design for personal house

09/01/2023

UTM coordinates

Address

Debre Birhan

Telephone

+251961113111

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when GIS , Autocad , Surveying and Engineering information posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to GIS , Autocad , Surveying and Engineering information:

Shortcuts

Share