DTU College of Health sciences.

Website

DTU College of Health sciences. Debre Tabor University College of Health Sciences has introduced “Innovative Curriculum” since its foundation.

An innovat curriculum is for problem-solving, creativity and imagination. Its approach is student-centered making the learner the major player

18/08/2026
DEBRE TABOR UNIVERSITY COLLEGE OF HEALTH SCIENCES CONDUCTS OBE CURRICULUM REVIEW & INTERNAL VALIDATION WORKSHOP​Debre Ta...
27/07/2026

DEBRE TABOR UNIVERSITY COLLEGE OF HEALTH SCIENCES CONDUCTS OBE CURRICULUM REVIEW & INTERNAL VALIDATION WORKSHOP

​Debre Tabor, Ethiopia — In its continuous effort to advance educational quality and academic excellence, the College of Health Sciences at Debre Tabor University successfully conducted an Outcome-Based Education (OBE) Curriculum Review and Internal Validation Workshop today.

​The workshop convened academic staff, curriculum review committee members, and educational experts to evaluate and align the college's academic programs with both national accreditation standards and international higher education benchmarks.

​​During the event, University Leadership highlighted that regular curriculum review is essential for nurturing innovative health professionals capable of making meaningful contributions to Ethiopia's healthcare system and the global medical field.

​The successful completion of this workshop underscores Debre Tabor University’s steadfast commitment to continuous improvement, societal responsiveness, and excellence in higher education.

Connect with DTU:

✈️ Telegram: https://t.me/DTUniversity

🔵 Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=61561529794471&mibextid

​Debre Tabor University has a Historical Duty to Answer Tewodros’s Quest for Knowledge!

​

10/07/2026
የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የህክምና ተማሪዎች በብቃት ፈተና 98 በመቶ ከፍተኛ ስኬት አስመዘገቡ! 🩺​የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህክምና ትምህርት ቤት አምስተኛ ዓመት ተማሪ...
19/06/2026

የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የህክምና ተማሪዎች በብቃት ፈተና 98 በመቶ ከፍተኛ ስኬት አስመዘገቡ! 🩺

​የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህክምና ትምህርት ቤት አምስተኛ ዓመት ተማሪዎች ወደ ተግባራዊ ልምምድ (Internship) ከመሰማራታቸው በፊት የተሰጣቸውን የብቃት ፈተና (Qualification Exam) 98 በመቶው በከፍተኛ ውጤት ማለፋቸውን የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር ዶ/ር ሙሉጌታ አሻግሬ ገልጸዋል።

​
​ፈተናው በዋናነት ተማሪዎች ወደ ቀጥታ ክሊኒካዊ ልምምድ ከመግባታቸው በፊት ለታካሚዎች ደህንነቱና ደረጃውን የጠበቀ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ብቃትና ክህሎት ማዳበራቸውን ለማረጋገጥ ያለመ እንደሆነ እና በዝግጅት ​ሂደቱም ተማሪዎቹ በንድፈ-ሀሳብ፣ በታካሚ አጠገብ ትምህርት (patient-side learning)፣ በችግር ፈቺ መማር ማስተማር (problem-based learning) እና በሴሚናሮች እና በሌሎች ሲሰለጥኑ የቆዩ ሲሆን ​የአፈታተን ሥርዓቱ ግልጽነትና ጥራትን ባረጋገጠ መልኩ 70 በመቶው በውስጥ መምህራን፣ ቀሪው 30 በመቶ ደግሞ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በመጡ የህክምና ዶክተሮች አማካኝነት በተግባር እንዲፈተኑ ተደርጓል።

ሶስት የትምህርት ክፍሎች ማለትም በህጻናት ህክምና ፣ በቀዶ ጥገና ህክምና እና በማህጸንና ጽንሥ ህክምና ፈተናውን የወሰዱ 42 ተማሪዎች ሁሉም 100% ፈተናውን በላቀ ስኬት ያለፉ ሲሆን​ በውስጥ ደዌ ህክምና ት/ት ክፍል ደግሞ ከ42ቱ ተማሪዎች 41ዱያለፉ ሲሆን ይኸም 98% አልፈዋል።የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አምሳሉ በለጠ በበኩላቸው እንደገለፁት፤ የህክምና ተማሪዎች ያስመዘገቡት ውጤት የዩኒቨርስቲውን እና የመምህራንን ጠንካራ የሥራ ቁርጠኝነት ያስመሰከረ ነው ብለዋል።

ረዳት ፕሮፌሰር አምሳሉ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ከተለያዩ የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች መጥተው፣ ሙያው በሚፈልገው ልክ ተማሪዎችን በመመዘን ውጤት ላሳወቁ እና ለኮሌጁ ገንቢ ሀሳብ ለሰጡ ፈታኝ መምህራን በሙሉ በራሳቸውና በዩኒቨርሲቲው ስም የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

​ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የመጡት ፈታኝ መምህራን በበኩላቸው ተማሪዎቹ በፅሁፍና በተግባር ፈተናው ያሳዩት ከፍተኛ ብቃት የኮሌጁ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት በጥሩ መሠረት ላይ የተጣለ መሆኑን በተግባር ያሳየ ነው ብለዋል።

​ለተፈታኝ ተማሪዎቻችን፣ ለደከሙ መምህራንና ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን!

​

የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የስነ-ልቦና ዝግጅት ስልጠና ሰጠ​ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ፤ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም.​የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለዳግማዊ ...
28/05/2026

የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የስነ-ልቦና ዝግጅት ስልጠና ሰጠ

​ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ፤ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም.

​የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለዳግማዊ ቴዎድሮስ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2018 ትምህርት ዘመን የሀገር አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎች የስነ-ልቦና ዝግጅትና ማጠናከሪያ ስልጠና ሰጠ።

​ስልጠናው በዋናነት ተማሪዎች በፈተና ወቅት የሚገጥማቸውን ፍርሃትና ጭንቀት በማስወገድ፣ በራስ መተማመናቸውን እንዲጨምሩና ያላቸውን እውቀት በሙሉ አቅማቸው ተጠቅመው ለላቀ ውጤት እንዲበቁ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

​የጤና ሳይንስ ኮሌጅ እያደረገ ስላለው ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ስልጠናውን በይፋ ያስጀመሩት የኮሌጁ ችፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ረ/ፕሮፌሰር አምሳሉ በለጠ እንደገለጹት፤ ተማሪዎች በተለይም በፈተና ወቅት የሚከሰትባቸውን ከፍተኛ የስነ-ልቦና ጫና መቋቋም የሚያስችላቸውን አቅም ማጎልበት ይኖርባቸዋል። አያይዘውም «ጭንቀትና መረበሽ የተሞላበት አዕምሮ እምቅ አቅምን ስለሚገታ፣ ተማሪዎች ራሳቸውን በማረጋጋት ለጥሩ ውጤት መዘጋጀት አለባቸው» ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

​በመስኩ ምሁራን እየተሰጠ በሚገኘው በዚህ ስልጠና ላይ የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑት ተማሪዎቻችን ከቀሰሙት እውቀትና ክህሎት ባሻገር፣ የፈተና ስነ-ልቦና ዝግጅታቸውን ሊያዳብሩ የሚችሉባቸው በርካታ ጠቃሚ ነጥቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

​የጤና ሳይንስ ኮሌጁ መሰል ማህበረሰብ አቀፍ የስነ-ልቦና ድጋፍ ስልጠናዎችን ለአካባቢው ተማሪዎች በዓመቱ ውስጥ በተያያዥነት ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል።

📖​Debre Tabor University has a Historical Duty to Answer Tewodros’s Quest for Knowledge!

👉 Telegram=https://t.me/DTUniversity

​

28/04/2026

⏰ Upcoming Event:

⏰ 1 Day left !!

5th Annual National Research Conference

​Debre Tabor University is honored to host its 5th Annual National Research Conference, a platform dedicated to bridging the gap between academic research and sustainable societal growth. Under the inspiring motto, "Debre Tabor University Has a Historical Duty to Answer Tewodros’s Quest for Knowledge!", DTU invites you to join this prestigious gathering.

​📜 Grand Theme

​"Research, Technology Transfer, Community Engagement, and Culture for Sustainable Development"

​📍 Event Information
​Date: April 30 – May 05, 2026 (Miazia 22 – 27, 2018 E.C.)
​Venue: Aleqa Tekile Gebrehana Hall
​Host: Debre Tabor University

​💡 Why Attend?

​This conference serves as a vital hub for:

📖​Innovation: Exploring the latest in technology transfer and scientific advancements.

📖​Culture: Integrating traditional values and cultural heritage into modern development.
​Impact: Strengthening the bond between the university and the community through actionable research.

📖​DTU looks forward to welcoming researchers, students, and community leaders as It fulfills its' historical duty to advance knowledge and development.

​Debre Tabor University

Dear Researchers,We are honored to invite you to submit your scholarly work to the Journal of Interdisciplinary Science ...
22/04/2026

Dear Researchers,
We are honored to invite you to submit your scholarly work to the Journal of Interdisciplinary Science and Technology (JIST).
We welcome submissions of original articles, review papers/meta-analyses, and case reports across a wide range of disciplines, including:
• Medicine and Health Sciences
• Agriculture
• Engineering and Technology
• Social Sciences
• Humanities
• Business & Economics (FBE)
• Law
• Natural Sciences
• 📌 Submission Link: https://www.dtujist.com/index.php/jist/about/submissions

Sincerely,

The Journal of Interdisciplinary Sciences and Technology (JIST) publish original contributions in both basic and applied research across medicine and health sciences, social sciences, natural sciences, engineering, and agriculture.

🌿 የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች የትንሣኤ በዓልን ከመምህራኖቻቸው ጋር በድምቀት አከበሩ ።
13/04/2026

🌿 የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች የትንሣኤ በዓልን ከመምህራኖቻቸው ጋር በድምቀት አከበሩ ።

የትንሳኤ በዓል በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የሱስ ማገገሚያ ማዕከል በድምቀት ተከበረ​የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የሱስ ማገገሚያ ማዕከል የሚገኙ የሥነ-አእምሮና...
12/04/2026

የትንሳኤ በዓል በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የሱስ ማገገሚያ ማዕከል በድምቀት ተከበረ

​የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የሱስ ማገገሚያ ማዕከል የሚገኙ የሥነ-አእምሮና የሱስ ታካሚዎችን ለማበረታታት የታለመ የጋራ የምሳ መርሃ-ግብር ተካሄደ።

በዝግጅቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የደብረ ታቦር አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አመራሮችና ሠራተኞች ተገኝተዋል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የደብረ ታቦር አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅና የቀዶ ጥገና ሐኪም ዶ/ር ገብሬ ድንቃየሁ፤ መሰል የሱስ ማገገሚያ ተቋማት በሀገራችን ቁጥራቸው አነስተኛ መሆኑን ጠቅሰው ለወደፊቱም ተቋማቱ እንዲስፋፉና በማዕከሉ የሚገኙ ታካሚዎች በፍጥነት አገግመው ለቤተሰባቸውና ለሀገራቸው የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

​በተጨማሪም የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ችፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር አቶ አምሳሉ በለጠ በበኩላቸው፤ ተቋሙን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

​ምስጋና ለባለቅን ልቦች

የተሃድሶ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ጌታሰው ለጋስ በመርሃ-ግብሩ ላይ ለተገኙ አካላትና ተቋሙን በውጭ ሀገር ሆነው ለሚደግፉ ኢትዮጵያውያን ምስጋና አቅርበዋል። በተለይም ለበዓሉ መርሃ-ግብር መሳካት በምዕራብ አውስትራሊያ ፐርዝ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ፋሲካ አዳነ
አቶ እንዳልክ ታደሰ እና አቶ አማኑኤል ጋሻው ላደረጉት የላቀ ድጋፍ ልዩ ምስጋና አቅርበዋል።

ባለቤታቸውን ለማሳከም በማዕከሉ የሚገኙ አንድ አባወራ በሰጡት አስተያየት፤ በዓልን ከቤተሰብ ርቆ ማክበር የሚፈጥረውን የብቸኝነት ስሜት የዩኒቨርሲቲው አመራሮች አብረዋቸው በመሆኑ እንደረሱት ገልጸዋል። "ከገዛ ቤተሰቦቻችሁ ይልቅ እኛን አስቀድማችሁ አብራችሁን ስላከበራችሁ እናመሰግናለን" ሲሉ ልባዊ ምስጋናቸውን አጋርተዋል።

Address

Technique Road
Debre Tabor
272

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when DTU College of Health sciences. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share