GS BS Family of Wollo University,Tita Campus

  • Home
  • GS BS Family of Wollo University,Tita Campus

GS BS Family of Wollo University,Tita Campus MEDIA INFLUENCERS!

ሉቃስ 18¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯⁹ ጻድቃን እንደ ሆኑ በራሳቸው ለሚታመኑና ሌሎቹን ሁሉ በጣም ለሚንቁ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፥¹⁰ እንዲህ ሲል፦ ሁለት ሰዎች ሊጸልዩ ወደ መቅደስ ወጡ፥ አንዱ ፈሪሳዊ ...
28/02/2025

ሉቃስ 18
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ ጻድቃን እንደ ሆኑ በራሳቸው ለሚታመኑና ሌሎቹን ሁሉ በጣም ለሚንቁ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፥
¹⁰ እንዲህ ሲል፦ ሁለት ሰዎች ሊጸልዩ ወደ መቅደስ ወጡ፥ አንዱ ፈሪሳዊ ሁለተኛውም ቀራጭ።
¹¹ ፈሪሳዊም ቆሞ በልቡ ይህን ሲጸልይ፦ እግዚአብሔር ሆይ፥ እንደ ሌላ ሰው ሁሉ፥ ቀማኞችና ዓመፀኞች አመንዝሮችም፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ስላልሆንሁ አመሰግንሃለሁ፤
¹² በየሳምንቱ ሁለት ጊዜ እጦማለሁ፥ ከማገኘውም ሁሉ አሥራት አወጣለሁ አለ።
¹³ ቀራጩ ግን በሩቅ ቆሞ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ሊያነሣ እንኳ አልወደደም፥ ነገር ግን፦ አምላክ ሆይ፥ እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ እያለ ደረቱን ይደቃ ነበር።
¹⁴ እላችኋለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱን ግን የሚያዋርድ ከፍ ይላል።

እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፤ °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°1) ትዕቢተኛ ዓይን፥ 2) ሐሰተኛ ምላስ፥ 3)...
27/01/2025

እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፤
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
1) ትዕቢተኛ ዓይን፥
2) ሐሰተኛ ምላስ፥
3) ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥
4) ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥
5) ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥
6) በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር
7) በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።
(መጽሐፈ ምሳሌ ምዕ. 6፥16_19)

20/01/2025

🚨 ስለወንጌል!!

"ሌሎች መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ፤ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ ተፈተኑ፥ በመጋዝ ተሰነጠቁ፥ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ፥ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤"

ዕብ - 11፥36-37

🚨 በዘመናችን ለወንጌል ምን አይነት ዋጋ እየከፈልን ነው?

የተቀበልነው እውነት በስጋ እስከ ሞት የሚያደርስ ቢሆን ምን ያክል ዝግጁዎች ነን?

ስሙ የተቀበልነው ወንጌል ብንኖርበት ብቻ ሳይሆን ብንሞትለን የማያስቆጭ ነው። ወንጌል የገባው ሰው ለራሱ ክብር፤ ለራሱ ዝና አይኖርም።

🚨 በዚህ በወደቀ ዓለም በልጦ ለመታየት አይኖርም፡፡ በሚበሰብስ አካሉ አይመካም።

በሰዎች ዘንድ ለመታወቅ አይሰራም አይኖርምም። ምክንያቱም ዓለም ሳይፈጠር በፊት በእግዚአብሔር የታወቀ ስለሆነ።

በዚህ በእኛ ዘመን ለወንጌል የቆረጠ ትውልድ ይነሳል። የእግዚአብሔር ደስታ ይሄ ነው። ብዙዎችም ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን በቃሉ መገለጥ እየመጡ ይገኛሉ!!

🟠 ጌታ ሆይ ከእንቅልፌ ስነቃ አስብሃለሁ፥ በእያንዳንዱ የቀን ጊዜዬ ከአንተ ጋር እቆራኛለሁ። ጌታ ሆይ አንተ የነፍሴ እስትንፋሰ ነህ። በእርግጥ ይሄን የምለው ለማለት ብዬ አይደለም። ያለአንተ...
19/01/2025

🟠 ጌታ ሆይ ከእንቅልፌ ስነቃ አስብሃለሁ፥ በእያንዳንዱ የቀን ጊዜዬ ከአንተ ጋር እቆራኛለሁ። ጌታ ሆይ አንተ የነፍሴ እስትንፋሰ ነህ። በእርግጥ ይሄን የምለው ለማለት ብዬ አይደለም። ያለአንተ ምንም ላደርግ እንደማልችል የነገርከኝ ቃል እውነት መሆኑን ስላረጋገጥኩኝ ነው። “ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና…” (ዮሐ 15፡5)።ኦ ሃሌሉያ! ጌታ ሆይ አንድን ነገር ለማድረግ ሳስብ የማስብህ ያለአንተ ምንም አደርግ ዘንድ ስለማይቻለኝ ነው። አንድ ጊዜ ሙሴ የተናገረው ትዝ ይለኛል “አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህስ፥ ከዚህ አታውጣን።” ጌታ ሆይ አንተን ሳልይዝ ወዴት ነው የምወጣው? አንተን ሳልይዝ ምንድነው የምናገረው? ሲጀመር እኮ የምሄድበት ቦታ ለመሄዴ ምክንያቱ አንተ ነህ። የምናገረውንም ለመናገሬ ምክንያቴ አንተ ነህ። ታዲያ አንተ ከሌለህበት ምን እሰራለሁ? ለምን እናገራለሁ? አቤቱ የተቤዥከኝ ጌታ ሆይ አንተ ሕይወቴን በዋጋ አልገዛሃትምን? “ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ አንተ የእኔ ነህ” (ኢሳ 43፡1)። እኔ የአንተ ነኝ። የትኛው የራሴ ፍላጎትና የትኛው የራሴ መሻት ሲኖረኝ? ጌታዬ እኮ ነህ። ሕይወቴ ነህ አባት ሆይ! ሕይወቴ ነህ፤ የምኖርህ ነህ።

🟠 “በመኝታዬም አስብሃለሁ፥ በማለዳም እናገርልሃለሁ፤ ረዳቴ ሆነኸኛልና፥ በክንፎችህም ጥላ ደስ ይለኛልና። ነፍሴ በኋላህ ተከታተለች፥ እኔንም ቀኝህ ተቀበለችኝ” (መዝ 63፡6-7)። እግዚአብሔር እኔን የተቀበለ ወዳጄ ነው። የእርሱ ፍቅር ያስተማምነኛል። በአብሮነቱ ምክንያት ደህንነት ይሰማኛል። እጅግ በጣም የሚወደኝ አምላክ ነው ያለኝ። በክንፎቹ ጋርዶ ሚስጥራዊ በሆነ ስፍራ ያነጋግረኛል። ነፍሴ ታውቀዋለች። በእርሱ ትደገፋለኝ። በፍቅሩ ትጓደዳለች። እግዚአብሔር ይወደኛል። እግዚአብሔር ያናግረኛል። እግዚአብሔር ወዳጄ ነው። ሃሌሉያ! “ጠማማ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ርኩስ ነው፤ ወዳጅነቱ ግን ከቅኖች ጋር ነው” (ምሳ 3፡32)። አቤት! እንዴት ድንቅ ነው። እግዚአብሔር ወዳጁ የሆነለት ሰው ምን አይነት ሰው ነው? ጓደኛህ ማን ነው ተብሎ ሲጠየቅ እግዚአብሔር ነው ብሎ መመለስ የሚችል ማነው? ኧረ እግዚአብሔር የእኔ ወዳጅ ነው! ጌታ ኢየሱስ የቅርብ ወዳጄ ነው። “ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባርያ ጌታው የሚደርገውን አያውቅምና፤ ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ፥ ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ለእናንተ አስታውቄአችኋለሁና” (ዮሐ 15፡15)። ኧረ ሃሌሉያ! ሃሌሉያ! ሃሌሉያ! ሃሌሉያ!

🟠 ኢየሱስ ክርስቶስ የሚለበስ እንደሆነ ታውቃላችሁ? መፅሀፍ ቅዱስ በገላትያ 3፡27 ላይ "ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና" ይላል። ኦ! ይህ ምን ...
11/01/2025

🟠 ኢየሱስ ክርስቶስ የሚለበስ እንደሆነ ታውቃላችሁ? መፅሀፍ ቅዱስ በገላትያ 3፡27 ላይ "ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና" ይላል። ኦ! ይህ ምን ማለት ሊሆን ይችላል? ክርስቶስስ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ? እርሱን መልበስ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ታውቃላችሁ? በመጀመሪያ አንድ ነገር ልምከራችሁ። የእግዚአብሔር ቃል እውነት መሆኑን አረጋግጡ። አንድ ሰው በግሉ ያለው አስተሳሰብ የእግዚአብሔር ቃል በሕይወቱ ላይ እንዳይሰራ ወይም እንዲሰራ ማድረግ ስለሚችል ማለት ነው። የእግዚአብሔር ቃል ምንም ያህል ሃይል ቢኖረው እንኳን አንድ ሰው ግን በሕይወቱ ላይ እንዳይሰራ ማድረግ ይችላል። ይሄን የሚያስረዳ ቃል ላሳያችሁ። "ባስተላለፋችሁትም ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ Making the word of God of none effect through your tradition" (ማር 7፡13)። መሻር ወይ none effect እንዲሆን ማድረግ ማለት እንዳይሰራ፥ ህያው ሆኖ እንዳይገለጥ ማድረግ ማለት ነው። ነገር ግን ለሚቀበለው ሰው "የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና የሚሰራም" (ዕብ 4፡12)። ኦ ሃሌሉያ!! እኔ የእግዚአብሔርን ቃል ከሚቀበሉት ነኝ። እናንተስ?

🟠 ክርስቶስ ማን ነው? ከላይ ለብሳችሁታል የተባለው ክርስቶስ ማን ነው? መልበስስ ምን ማለት ነው? ከመጨረሻው ብጀምር ልብስ የተገለጠውና የሚታየው ክፍል ማለት ነው። ለምሳሌ መፅሀፍ ቅዱስ ትህትናን እንደ ልብስ ልበሱ ሲል መገለጣችሁ እና መታወቂያችሁ ትህትና ይሁን ማለቱ ነው። እግዚአብሔር ክርስቶስን ለብሳችሁታል ሲል አሁን የምንታየው እኛ ሳንሆን ክርስቶስ ነው ማለቱ ነው። ኦ! ጳውሎስ የተናገረው ክርስቲያኖች የሆንን ብዙ ጊዜ በውስጣችን የምናሰላስለው "እኔ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ በሕይወት ይኖራል" የሚል በገላትያ 2፡20 ላይ የተፃፈ ቃል አለ። አሁን ስትመላለሱ እናንተ አይደለም እየታያችሁ ያላችሁት፥ ክርስቶስ ነው እየታየ ያለው። ምክንያቱም ለብሳችሁታል። የክርስቶስን ባሕሪ ለብሳችሁታል፥ የክርስቶስን ሃይል ለብሳችሁታል። ጌታ ሃይሉ ምን ያህል ነው? የእርሱን ሃይል ለብሳችሁ እየተመላለሳችሁ ነው። ይሄ አስተሳሰብ (Consciousness) ይኑራችሁ። ለዚህ ነው ክርስቶስን በጥልቀት ማጥናት ያለብን። ማንነቱን፥ ባሕሪውንና ክብሩን እያወቅን ለመግለጥ። ጳውሎስ "እርሱንና የትንሳኤውን ሃይል እንዳውቅ" ብሎ የተናገረው ለዚህ ነው። ስለክርስቶስ "ስልጣን በሰማይና በምድር ተሰጠኝ" ስላለ በስፍራ ሁሉ ስትሄዱ ያንን ስልጣን የተሰጠውን ክርስቶስ ለብሳችሁት ነው የምትሄዱት። ስለዚህ በስሙ አጋንንትን ለማውጣት ስልጣን አለን፥ በሽተኞችን ለመፈወስ ስልጣን አለን። ይሄ እውነት ነው። ሃሌሉያ!

🟠 ጌታ የዋህና በልቡ ትሁት ነው። በባሕሪው ፍፁም የእግዚአብሔር ምሳሌ ነው። ክርስቶስን ለብሳችሁ ስትመላለሱ ትሁትና የዋህ ነው ምትሆኑት። ማንነታችሁ ክፋትን የሚፀየፍ ስለሆነ ያ ማንነታችሁ ክርስቶስን በማወቅ ይገለጣል። በመጨረሻ ሮሜ 13፤14 ላይ ያለውን ቃል ላሳያችሁ... "ጌታን ክርስቶስን ልበሱት ምኞቱንም እንዲፈፅም ለስጋ አታስቡ"። ሃሳባችሁ በክርስቶስ የተያዘ ሲሆን ስለእርሱ ስታሰላስሉ እርሱ ይገለጣል፥ ምኞትና ሃጢያት እድል ወይም በር አያገኝም። ክርስቶስ ማን እንደሆነ ትኩረት አድርጋችሁ አጥኑ። እርሱ ሕያው ሆኖ በሕይወታችሁ ላይ ሲገለጥ ትመለከታላችሁ።

ፍጹም ክብር ካለበት ዓለም ፍጹም ውርደት ወዳለበት ምድር ለእኛ ሲል ተወለደ ፤ ባለ ወግ ሊያደርገን ባለ በረት ሆነልን ። ባለ ሰማይ ሊያደርገን ባለ መስቀል ተባለልን ። የኪዳን ቀለበት ሊያደ...
07/01/2025

ፍጹም ክብር ካለበት ዓለም ፍጹም ውርደት ወዳለበት ምድር ለእኛ ሲል ተወለደ ፤ ባለ ወግ ሊያደርገን ባለ በረት ሆነልን ። ባለ ሰማይ ሊያደርገን ባለ መስቀል ተባለልን ። የኪዳን ቀለበት ሊያደርግልን በችንካር ቆሰለልን ። ነገሥታት ሊያደርገን የእሾህ አክሊል ደፋልን ፣ ካህናተ ጽድቅ ሊያደርገን ሐሰተኛ ተባለልን ። ሰማይና ምድር የማይችሉት በድንግል ማኅጸን አደረ ፤ በኪሩቤል ጀርባ የነገሠው በንጽሕት ድንግል እቅፍ ውስጥ አረፈ ። በዙፋኑ የሚጠብቀን እንደ ትንሽ ሕጻን ተሯሯጠ ። ሁሉ እንዲሆንልን ሁሉ የሌለው ሆነ ። የጌታችን እግሮች በረገጧት ምድር ላይ ስላላችሁ ደስ ይበላችሁ ። እርሱ ባለፈበት ሕይወት ስለምታልፉ እልል በሉ ። ኑሮ እንዳያሰጋችሁ ሕይወት ሆኖ ተወለደላችሁ ። በጊዜያዊው ነገር እጅ እንዳትሰጡ የዘላለሙን ፍስሐ አወረሳችሁ ።

በእውነት እንኳን አደረሳችሁ!

" ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።"
(ኢሳ 9: 6)

❄️❄️Happy christmass❄️❄️!!!!!

❗️❗️❕በተለያየ አጋጣሚ በአካል የተገናኘን ጓደኞቼ ሁሉ! ከአንደኛ ደረጃ ት/ቤት ጀምሮ ኮሌጅ እስከነበርኩባቸው ጊዜዎች እንዲሁም በስራና በተለያየ አጋጣሚ በአካል ተገናኝተን የነበርን ሁላችሁ...
05/01/2025

❗️❗️❕በተለያየ አጋጣሚ በአካል የተገናኘን ጓደኞቼ ሁሉ! ከአንደኛ ደረጃ ት/ቤት ጀምሮ ኮሌጅ እስከነበርኩባቸው ጊዜዎች እንዲሁም በስራና በተለያየ አጋጣሚ በአካል ተገናኝተን የነበርን ሁላችሁ። ከእናንተ ጋር መገናኘቴ ለእኔ ደስታና ክብር ነው። እንደ አጋጣሚ ሳይሆን እግዚአብሔር ለእናንተ ወንጌልን አደርስ ዘንድ እድልን ሰጥቶኝ አግኝቻችኋለሁ። ለአብዛኞቻችሁ የክርስቶስ ኢየሱስን አዳኝነት በተለያየ መንገድ ነግሬያችኋለሁ። አሁን ለእናንተ በክብርና በፍቅር የምነግራችሁ ነገር አለኝ። የክርስቶስ ኢየሱስን ብቸኛ አዳኝነትና አማላጅነት እንዲሁም አምላክና ጌታ መሆኑን የማይቀበል ሃይማኖት ውስጥ ካላችሁ በእርግጥ ያ ሃይማኖት ወደ ሲኦል ይዟችሁ እየሄደ ነውና እባካችሁ አምልጡ! ከሀጢያትና ከዘላለም ሞት የሚያድነው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። ይሄን የምነግራችሁ እውነት ስለሆነና ለዘብ አድርጌ ልገልፀው የማልፈልገው ነገር ስለሆነ ነው። መፅሐፍ ቅዱስ ይህን እውነት አስረግጦ ያስረዳል። “መዳን በሌላ በማንም የለም፣ እንድንበት ዘንድ ለሰው ልጆች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና” ይላል (ሐዋርያት ስራ 4፡12)። እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ሲናገር “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም” ብሏል (ዮሐንስ ወንጌል 14፡6)። ይህንን ግልፅ እውነት ያልተቀበለ የትኛውም ሃይማኖት የእግዚአብሔርን ስም ሊጠራ ይችላል፣ የአምላክን ስም በየዕለቱ ሊጠራ ይችላል፤ ነገር ግን በፍፁም ከእግዚአብሔር ጋር ሊታረቅም ሆነ የዘላለምን ህይወት ሊያገኝ አይችልም። አስታውሱ አይሁዳውያን እግዚአብሔርን ሲያመልኩ የኖሩ ህዝቦች ነበሩ የእግዚአብሔርን ስም ከማናችንም በላይ ይጠራሉ። ነገር ግን አልዳኑም። ይልቁን አዳኙን ኢየሱስን ሰቀሉት። አሁንም ከጥቂቶቹ በስተቀር ብዙዎቹ አልዳኑም። ነገር ግን የእግዚአብሔርን ስም ይጠራሉ። ያልዳኑበት ምክንያት የመዳን ቁልፉ ያለው ኢየሱስ ጋር እና ኢየሱስ ጋር ብቻ በመሆኑ ነው። ይሄ ጌታ ይወዳችኋል! ከሀጢያታችሁ ያነፃችኋል። አዲስ ሰው ያደርጋችኋል። በኦርቶዶክስ፣ በካቶሊክ፣ በይሓዋ ምስክር፣ በኢሬቻ አጋንንታዊ አምልኮ፣ በዋቄ ፈታ ውስጥ ያላችሁ እንዲሁም በግዴለሽነት አስተሳሰብ የምትኖሩ ሁላችሁ፤ የኢየሱስን ጥሪና ልመና ዛሬም እኔ ለእናንተ አቀርባለሁ። እባካችሁ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኑ! እርሱ የግድ ያስፈልጋችኋል! አባካችሁ ነፍሳችሁን አድኑ!

❤ ❤=============================✍️ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በስሙ ያመኑትን አማኞች በዚህ ምድረበዳ አለም ብቻቸውን አልተዋቸውም ከአባቱ ዘንድ አጽናኝ የሆነውን መንፈስ ቅዱስን...
02/01/2025

❤ ❤
=============================
✍️ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በስሙ ያመኑትን አማኞች በዚህ ምድረበዳ አለም ብቻቸውን አልተዋቸውም ከአባቱ ዘንድ አጽናኝ የሆነውን መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸዋል።ከዚህም የተነሳ ቅዱሳን ይህንን ምድረበዳ አለም አቋርጠው የተባረከውን ተስፋቸውን ኢየሱስ ክርስቶስን እስኪገናኙ ድረስ መንፈስ ቅዱስ በተለያየ አይነት መንገድ ይረዳቸዋል።

✍️ በአዲስ ኪዳን ስለመንፈስ ቅዱስ የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ስናጠና በኢየሱስ ክርስቶስ የቤዛነት ስራ አምነው የጸደቁትን ቅዱሳን በተለያየ አይነት አገልግሎት እንደሚያገለግላቸው ተጽፏል።

✍️ አማኞች ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለን ህብረት ለመንፈሳዊ ህይወታችንና ለእድገታች አማራች የሌለው እውነት ስለሆን ከእርሱ ጋር ያለንን ህብረት ልናሳድግ ይገባናል።

📌 መንፈስ ቅዱስ ከአማኞች
ጋር በተያያዘ የሚሰራው ስራ፦
=====================================

👉1) ዳግም ልደትን ይሰጣል
------------------
ቲቶ 3 (Titus)
5፤ እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤

👉2) ይመራናል።
-------------
“ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።”ዮሐንስ 16፥13

👉3) ያስተምረናል።
-------------
“አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።”ዮሐንስ 14፥26

👉4) ያጽናናልና (ይመሰክርናል።
---------------------
“ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል፤”ዮሐንስ 15፥26

👉5) የጸሎት አቅም ይሰጠናል።
--------------------
ሮሜ 8 (Romans)
26፤ እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤

👉6). የጸጋ ስጦታን ይሰጣል።
-------------------
1ኛ ቆሮንቶስ 12 (አዲሱ መ.ት)
⁷ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ሰው የሚሰጠው ለጋራ ጥቅም ነው።

¹¹ እነዚህ ሁሉ የዚያው የአንዱ መንፈስ ስጦታዎች ሲሆኑ፣ ለእያንዳንዱ ሰው እርሱ ራሱ እንደ ፈቀደ ይሰጠዋል።

👉7) የእግዚአብሔርን ነገር እንድንረዳ ያደርገናል።
-----------------------------------
1 ቆሮንቶስ 2 (1 Corinthians)
12፤ እኛ ግን ከእግዚአብሔር እንዲያው የተሰጠንን እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም።

👉8) የእግዚአብሔር ልጆች እንደሆንን ይመሰክርልናል።
---------------------------------
ሮሜ 8 (Romans)
16፤ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል።

👉9) የእድሜ ዘመን የሀጥያት ስርየት እንዳገኘን ይመሰክርልናል።
---------------------------------
ዕብራውያን 10 (Hebrews)
17፤ ብሎ ከተናገረ በኋላ፥ ኃጢአታቸውንና ዓመጻቸውንም ደግሜ አላስብም ይላል።

👉10) ክርስቶስን እንድንናፍቅ ያደርገናል
----------------------------
ራእይ 22 (

🎄Merry Christmass all of you 🎄RHAPSODY OF REALITIES(Amharic)Wednesday December 25th, 2024(ረቡዕ — ታሕሳስ 16 — 2017)የክርስቶስ ልደ...
25/12/2024

🎄Merry Christmass all of you 🎄

RHAPSODY OF REALITIES
(Amharic)

Wednesday December 25th, 2024
(ረቡዕ — ታሕሳስ 16 — 2017)

የክርስቶስ ልደት ቀን: በውስጣችሁ የለው ክርስቶስ በዓል

📖 ════════
“ለእነርሱም እግዚአብሔር የዚህ ምስጢር ክብር ባለጠግነት በአሕዛብ መካከል ምን ያህል እንደ ሆነ ለማሳወቅ መረጠ፤ እርሱም የክብር ተስፋ የሆነው በእናንተ ውስጥ ያለው ክርስቶስ ነው።” (ወደ ቈላስይስ ሰዎች 1:27)

ፓስተር ክሪስ
━━━━━━━━━
ለአንዳንድ ሰዎች፣ የክርስቶስ ልደት በዓል (ገና) ስለ ምግብ እና ቤተሰብ ብቻ ነው:: ስለዚህ፣ በክርስቶስ ልደት ቀን በቤተሰብ መሃል በመሆን መብላታቸውን: መደገሳቸውን እና መደሰታቸውን እርግጠኛ ይሆናሉ:: ሆኖም ከመደሰት ባለፈ የክርስቶስ ልደት ስለ ክርስቶስ ነው፤ ማን እንደሆነ፣ ምን ሊሰራ እንደመጣ በተጨማሪም ዓላማውን በትክክል ስለመፈፀሙ እውነታ ነው:: ዓላማውን ባይፈፅም ኖሮ ህይወት ባዶ ይሆን ነበር::

እናንተ ትኖሩ ዘንድ፣ መጣ፣ ኖረ፣ ሞተ ከዛም ወደ ህይወት ተመለስ:: በዮሐንስ ወንጌል 10:10 ላይ እንዲህ ብሏል “ሌባው ሊሰርቅ፣ ሊገድልና ሊያጠፋ ብቻ ይመጣል፤ እኔ ግን ሕይወት እንዲኖራቸውና እንዲትረፈረፍላቸው መጥቻለሁ።” 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3:8 እንዲህ ይላል “... የእግዚአብሔር ልጅ የተገለጠውም የዲያብሎስን ሥራ ያፈርስ ዘንድ ነው።” ይኸው ኢየሱስ እራሱ ዳግም ይመጣል እናም አሁን እርሱን በእውነት የምታገለግሉበት ጊዜ ነው፤ እርሱን በእርግጠኛነት የምታውቁበት ጊዜ ነው::

ወደ ቲቶ 2:13 ኢየሱስ ማን እንደሆነ ቆንጆ አድርጎ ይነግረናል– እርሱ ታላቁ እግዚአብሔር እና አዳኛችን ነው: “ይህም የተባረከ ተስፋችን የሆነውን የታላቁን የአምላካችንንና የአዳኛችንን የኢየሱስ ክርስቶስን…”(ወደ ቲቶ 2:13-14):: ይህን አያችሁ? ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው:: በመካከላችን በተወለደ ጊዜ “አማኑኤል” ተብሎ ተጠርቷል: እግዚአብሔር ከኛ ጋር ማለት ነው::

ወደ ቆላስያስ ሰዎች 1:19 ላይ መፅሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል የመለኮት ሙላት በእርሱ ይኖራል:: አጠቃላይ መለኮትነት በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ አድሯል:: “በእርሱ የአምላክነት ሙላት በስጋ አድሯል::” ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር አካል ነው፤ እግዚአብሔር የሆነው ሁሉ፣ በኢየሱስ ውስጥ አለ::

ነገር ግን በጣም የሚያነቃቅው ነገር ይህ ነው፤ ይህ ኢየሱስ፣ ታላቁ እግዚአብሔር እና አዳኛችን፣ ዛሬ ከእናንተ ጋር ብቻ አይደለም በውስጣችሁም ነው እንጂ:: ይህንን ነው በመግቢያ ጥቅሳችን ላይ ያነበብነው፣ የክብር ተስፋ የሆነው ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ነው:: ይህ ነው ትክክለኛው የክርስቶስ ልደት (ገና) ትርጉም። የክርስቶስ ልደት በውስጣችን የሚኖረው ክርስቶስ በዓል ነው:: ክርስቶስ በልባችሁ ክፍል ውስጥ እንደሚኖር እስካልተረዳችሁ ድረስ የክርስቶስ ልደት ምን ማለት እንደሆነ እና እንዴት እንደምታከብሩትም አታውቁም ማለት ነው::

እውነተኛው በዓል የሚጀምረው ስለ ክርስቶስ የልደት በዓል የእግዚአብሔር መገለጥ ላይ ስትደርሱ ነው: ያም የክብር ተስፋ የሆነው ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ መኖሩ ነው። ይህ ነው ከመጀመሪያም የእግዚአብሔር እቅድ፤ ይህንን ነበር እርሱ ሁሌም የሚፈልገው– ልክ ክርስቶስ እንደነበረው እኛም በእግዚአብሔር ሙላት እንድንሞላ ነው::

የእምነት አዋጅ
━━━━━━━━
የሰውን ልጅች ሁሉ ከሞት፣ ከሲኦል እና ከሃፍረት ያላቀቀው እንዲሁም ህይወትን እና ያለመሞትን ወደ ብርሃን ያመጣው ኢየሱስ እርሱ ታላቁ እግዚአብሄር እና አዳኛችን እንደሆነ በሚያሳየው መለኮታዊ እውነት እደሰታለሁ:: ከክርስቶስ ጋር ያለኝን አንድነት እና በውስጤ ያለውን የእርሱን መለኮትዊ ህይወት አከብራለሁ፤ ይህም ማለት ድል፣ ጥንካሬ፣ አሸናፊነት፣ ክብር በሃጢያትና በጨለማው ሃይል ላይ ያለኝ የበላይነት ነው:: አሜን::

ለተጨማሪ ጥናት:
ቆላስያስ 1:26-27;
ቲቶ 2:13-14;
ቆላስያስ 1:19;
ቆላስያስ 2:9;
ኤፌሶን 3:19
━━━━━//━━━━━

19/12/2024

🙏 እረኛ አላችሁ?

🟠 ሕይወት ከእኛ በላይ የሆነ አቅምና ጥበብን የምትጠይቅ አይመስላችሁም? እውነት ነው የሚመራን፥ የሚረዳን፥ የሚያስተምረን፥ በሕይወት መንገድ የሚጠብቀን ያስፈልገናል አይደል? በገዛ ራሱ ብቻ የሚመላለስ ሰው እንዴት ምስኪን ነው! በራሱ ይጥራል፥ በራሱ ይሞክራል፥ በራሱ ውጤት ላይ ለመድረስ ይለፋል። ነገር ግን በፍፃሜው ይወድቃል እንደገና ደግሞ ለመነሳት ይሞክራል። ወዳጆቼ እኔና እናንተ እንደዚህ አይደለንም። እንደዚህ ነበርን... እንዲህ ተብሎ እንደ ተፃፈ "እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ" (ኢሳ 53፡7)። በገዛ መንገዳችን ሄደን ነበርን። ክርስቲያን በመሆናችን ግን ይሄ ታሪክ ተቀይሯል። ጴጥሮስ ከላይ ያስቀመጥኩትን በትንቢተ ኢሳይያስ መፅሀፍ ላይ የተፃፈውን ጠቅሶ ምን እንዳለ ታውቃላችሁ... (1ጴጥ 2፡25) "እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል"። ኦ ሃሌሉያ! ጌታ እራሱ ነው ወደ እረኛችሁ ተመልሳችኋል ያለን። ወዳጆቼ እኛ ጌታ ኢየሱስን የተቀበልን ሰዎች እረኛ አለን። እናንተ እረኛ አላችሁ! እረኛ ምንድነው? ጌታ እግዚአብሔር ራሱ የተናገረውን ቃል ላካፍላችሁ።

🟠 (ሕዝ 34፡11፥15-16) "ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ እኔ ራሴ በጎቼን እሻለሁ፤ እፈልግማለሁ... እኔ ራሴ ቦጎቼን እሰማራለሁ አስመስጋቸውማለሁ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። የጠፋውንም እፈልጋለሁ፤ የባዘነውንም እመልሳለሁ፤ የተሰበረውንም እጠግናለሁ፤ የደከመውንም አፀናለሁ፥ የወፈረውናና የበረታውንም አጠፋለሁ፤ በፍርድም እጠብቃቸዋለሁ።" ኦ ጌታ እግዚአብሔር ይመስገን። ጠፍታችኋል? ጌታ እኮ የጠፋውን የሚፈልግ እረኛ ነው። እየባዘናችሁ ነው? ኧረ እረኛችን የባዘነውን የሚመልስ ነው። ወይስ ደክማችኋል? ጌታ የደከመውን አይጥልም ይልቁን ሀይልን ሞልቶ ያፀናል። በትዳር ተከድታችሁ፥ ወይም አንዳች ውድቀት ደርሶባችሁ ልባችሁ ተሰብሯል? "እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፥ መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል" (መዝ 34፡18)።

🟠 በአዲስ ኪዳን ወልድ (ጌታ ኢየሱስ) ራሱን ካስተዋወቀባቸው ስሞች አንዱ "እረኛ" የሚል ነው። እንዲያውም "መልካም እረኛ እኔ ነኝ" ብሏል ጌታ (ዮሐ 10፡11)። ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎችም መዝሙር 23 ላይ የተጠቀሱትን የእረኛ ባህሪዎች ጨምሮ ለምን እንደሚተገብር ታውቃላችሁ? ኢየሱስ ከአባቱ የተሰጠው አደራ አለ። እኔ ያንን አደራ አስቤ እረፍት ተሰምቶኛል። ለእናንተም ልንገራችሁ። "አብ የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፥ ወደ እኔም የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም። ፈቃዴን ለማድረግ አይደለም እንጂ የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ ወርጃለሁና። ከሰጠኝም ሁሉ አንድን ስንኳ እንዳላጠፋ በመጨረሻውም ቀን እንዳስነሳው እንጂ የላከኝ የአብ ፈቃድ ይህ ነው" (ዮሐ 6፡36-39)። ኧረ እግዚአብሔር ፍቅር ነው። ቃሉን አያችሁት? የሰው አይምሮ ልጠፋ እችላለሁ የሚል ስጋት ስላለበት፤ የምጠፋው እኔ እሆንን የሚል አስተሳሰብ ስላለው ጌታ እርግጠኛ ለማድረግ፥ አንዳችን እንኳን ሳንቀር ሁላችንንም ለማሳረፍ ብሎ "እንድን ስንኳ እንዳላጠፋ" የሚል ቃል ተጠቀመ፤ "ከቶ" የሚል ቃል ተጠቀመ። ሃሌሉያ! ሃሌሉያ! አቤቱ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ አከብርሃለሁ።

🟠 ታዲያ እረኛችን ኢየሱስ አባቱ የሰጠውን አደራ የሚወጣው ይመስላችኋል? አደራውን በመፈፀምስ የሚሳካለት ይመስላችኋል? እኔ በኢየሱስ ለማመን ወስኛለሁ። እረኛ አለኝ ብያለሁ። እናንተስ? አዎ እንዳመናች

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when GS BS Family of Wollo University,Tita Campus posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Want your university to be the top-listed University?

Share