Dilla Polytechnic College Official

Dilla Polytechnic College Official Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dilla Polytechnic College Official, College & University, Dilla.

Dilla Polytechnic College is one of Ethiopia’s leading TVT institutions, committed to empowering youth with practical skills, innovative mindsets, and industry-relevant training.

22/07/2026
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ዘርፍ የ2018  በጀት ዓመት ክልላዊ የዕቅድ አፈጻጸም ገመገመ።ሰኔ 23/2018  ዓ/ም  አርባምንጭበመድረኩ የቢሮ...
30/06/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት ክልላዊ የዕቅድ አፈጻጸም ገመገመ።

ሰኔ 23/2018 ዓ/ም አርባምንጭ

በመድረኩ የቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ዘርፍ ኃላፊ ኢንጅነር በዛብህ ገበየሁ የዘርፉን ክልላዊ አፈጻጸም ሪፖርት ገለጻ አድርገዋል።

አብዘኛዎቹ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጆች በቴክኖሎጂ ፈጠራና በማሰልጠን ሥራ ላይ አበረታች ዉጤት እንዳስመዘገቡ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

ዜጎች በመረጡት ስራ መስክ ኢንዳስትሪ ሆኖ እንዲወጡ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማትም ሆነ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባም ተገልጿል።

ኮሌጆች የመንግስትን ድጋፍ ከመጠበቅ ይልቅ በራስ አገዝ ሀብትን ፈጥሮ የሥልጠና ቅበላን በማስፋት አጫጭርና መደበኛ ሥልጠና በበቂ ሁኔታ ሊሰጥ እንደሚገባ አጽንኦት ተሰጥቷል ።

ከሪፎርም ተግባራት አንጻር ከ11ዱ ዘር-መል ወይም ዲኤንኤ ትግበራ አንጻር ዘርፉ በእያንዳንዱ ዘረ-መሎች የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገቡ ተገልጿል።

በሪፖርቱ ከተመላከቱት ዉስንነቶች የISO/ አለም አቀፍ ስታንዳርድ / በጠበቀ መልኩ የሥልጠናና ምዘና ሥርዓት ዘርግቶ ከመስራት አንጻር፣ RPL/ በልምድ የተገኙ ሙያዎችን ሴርትፋይድ ከማድረግ አንጻር፣ ከአቅርቦት-መር ወደ ፍላጎት-መር በመሻገር አዳዲስ ሰልጣኞችን ከመቀበል አንጻር ዉስንነቶች መኖራቸዉ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

በሪፖርቱ መነሻ ሰፊ ዉይይት ተደርጎ ከተሳታፊዎች አስተያየትና ጥያቄ ተነስቶ ከዘርፉ የማኔጅሜንት አካላትና ከቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የዘርፉ ኃላፊ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥተዉባቸዋል።

በመድረኩ የዞኖችና ሪጂኦ ፖሊስ ከተሞች የሥራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊዎች እና የፖሊ ቴክኒክግንኙነትኮሚኒኬሽንዋናና ምክትል ዲኖች የተሳተፉ ሲሆን በመጨረሻም በቢሮ ምክትል ኃላፊ የቀጣይ ስራ አቅጣጫ ተቀምጦ መድረኩ ተጠናቋል።

ዘገባዉ የሥራና ክህሎት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነዉ።

ክልላዊ የቴክኖሎጂና የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድርና ኤግዚቢሽን በአርባ ምንጭ ከተማ ተጀመረ ሰኔ 23/2018 ዓ.ም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ "በቴክኖሎጂ እንቀድማለን፤ ...
30/06/2026

ክልላዊ የቴክኖሎጂና የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድርና ኤግዚቢሽን በአርባ ምንጭ ከተማ ተጀመረ

ሰኔ 23/2018 ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ "በቴክኖሎጂ እንቀድማለን፤ ወደ ስኬት እንደርሳለን" በሚል መሪ ቃል በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ያዘጋጀው ክልላዊ የቴክኖሎጂና የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድርና ኤግዚቢሽን በአርባ ምንጭ ከተማ ተጀምሯል።

የኤግዚቢሽኑንና የውድድሩን መርሃ ግብር የቢሮው ምክትል ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ኃላፊ አቶ በዛብህ በላይነህ በይፋ ከፍተዋል።

በውድድሩና ኤግዚቢሽኑ በክልሉ በሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የተሠሩ ለቴክኖሎጂ ሽግግር የሚያገለግሉ ማሽነሪዎች፣ የማቀነባበሪያ መሣሪያዎች፣ የተግባራዊ ምርምር ውጤቶች እንዲሁም የዕደ ጥበብ ውጤቶች ለዕይታ ቀርበዋል።

በመክፈቻ ፕሮግራሙ የቢሮው ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የዞን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ኃላፊዐዎች፣ የኮሌጅ ዲኖች፣ ሰልጣኞች፣ ተማሪዎች፣ አሰልጣኞች፣ የውድድሩ አስፈጻሚዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በዛሬው ዕለት በዲላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ12ኛ ክፍል ፈተና ለሚፈተኑ 871 ተማሪዎች ኦረንቴሽን/የፈተና ገለፃ ተሰጥቷል። በገለፃው ወቅት ተማሪዎች የሚፈቀዱና የማይፈቀዱ ተግባራቶች በአግባቡ ...
29/06/2026

በዛሬው ዕለት በዲላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ12ኛ ክፍል ፈተና ለሚፈተኑ 871 ተማሪዎች ኦረንቴሽን/የፈተና ገለፃ ተሰጥቷል። በገለፃው ወቅት ተማሪዎች የሚፈቀዱና የማይፈቀዱ ተግባራቶች በአግባቡ እንዲያውቁና በስነ-ልቦና ዝግጁ እንዲሆኑ ተደርጓል።

የዲላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከአሁን ቀደም ተቋርጦ የነበረውን የአግሮ ፕሮሰሲንግ ህንፃን ጨምሮ የዋና መግቢያ በር እና የተቋሙን አጥር ግንባታ አስጀምሯል። ግንባታው ተቋሙ በ5 አመት ውስጥ ወጥኖ...
28/06/2026

የዲላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከአሁን ቀደም ተቋርጦ የነበረውን የአግሮ ፕሮሰሲንግ ህንፃን ጨምሮ የዋና መግቢያ በር እና የተቋሙን አጥር ግንባታ አስጀምሯል። ግንባታው ተቋሙ በ5 አመት ውስጥ ወጥኖ ከያዛችው የተለያዩ ተግባራቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን ተቋሙ በመማር ማስተማርና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ላይም ከፍተኛ እንቅስቃሴዎች በማድረግ ላይ ይገኛል።

የዲላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከሰኔ 23-ሐምሌ 16 ለሚካሄደው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዝግጅቱን አጠናቋል። ፈተናው በሀገር አቀፍ ደረጃ በበይነ መረብና በወረቀት የሚሰጥ ሲሆን ኮሌጃችን ከ16...
28/06/2026

የዲላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከሰኔ 23-ሐምሌ 16 ለሚካሄደው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዝግጅቱን አጠናቋል። ፈተናው በሀገር አቀፍ ደረጃ በበይነ መረብና በወረቀት የሚሰጥ ሲሆን ኮሌጃችን ከ160 በላይ የመፈተኛ ኮምፒውተሮችን በማዘጋጀት የፈተና አገልግሎት ይሰጣል።

 የዲላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከነገ 22/10/2018ዓ.ም ጀምሮ እስከ 15/11/2018ዓ.ም ድረስ በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ምክንያት ፍቃድ ከተሰጣቸው የፈተና ባለሙያዎችና ሰራተኞች ውጪ ወደ...
28/06/2026



የዲላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከነገ 22/10/2018ዓ.ም ጀምሮ እስከ 15/11/2018ዓ.ም ድረስ በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ምክንያት ፍቃድ ከተሰጣቸው የፈተና ባለሙያዎችና ሰራተኞች ውጪ ወደ ተቋሙ ቅጥር ጊቢ መግባት የተከለከለ ሲሆን ይህንን ማሳሰቢያ ጥሶ በሚገኝ ማንኛውም ግለሰብ ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን።

ከዚህም በተጨማሪ በኮሌጁ ስር አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ ዲጅታል ሲስተሞችና የኢንተርኔት አገልግሎትም ተቋርጦ የሚቆይ ይሆናል።

በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና አሰጣጥ ወቅት ፈተና ለመስረቅም ይሁን ለማሰረቅ የሚሞክሩ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ ይወሰዳል። - ትምህርት ሚኒስቴርትምህርት ሚኒስቴር ከሰኔ 23 እስከ ሐ...
26/06/2026

በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና አሰጣጥ ወቅት ፈተና ለመስረቅም ይሁን ለማሰረቅ የሚሞክሩ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ ይወሰዳል። - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም በበይነ መረብ እና በወረቀት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አካሒዷል።

የፈተናው አጠቃላይ ሂደት ደህንነቱ የተጠበቀና ውጤታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተቀናጀ ሁኔታ መሰራት እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል፡፡

ፈተናውን ለመስረቅም ይሁን ለማሰረቅ የሚሞክሩ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወሰድ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል።

ብሔራዊ ፈተናውን ለመስጠት በመሠረተ ልማት፣ ደህንነት እና ሌሎች መስኮች ተገቢው ዝግጅት መደረጉ ተመላክቷል።

ፈተናውን ለመውሰድ 563,501 ተፈታኞች (306,456 የተፈጥሮ ሳይንስ እና 257,045 የማኅበራዊ ሳይንስ) ተፈታኞች መመዝገባቸው ተገልጿል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በስኬት ለማከናወን የሚያስችል የማስፈፀሚያ እቅድ ላይ ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ...
23/06/2026

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በስኬት ለማከናወን የሚያስችል የማስፈፀሚያ እቅድ ላይ ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ ያዘጋጀው በክልሉ የ2018ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የማስፈፀሚያ እቅድ ላይ በአርባ ምንጭ ከተማ ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል ፈተና በተቀናጀ መንገድ በመስራት እንከን የለሽ አድርጎ ለመምራት የሚያስችል የምክክር መድረክ መሆኑን ገልፀዋል።

መንግስት እንደ ሀገር የጋጠመውን የትምህርት ስብራት ለመጠገን ሪፎርሞችን በማካሄድ፥ በርካታ የትምህርት እና የስልጠና ፖሊስ በመተግበር ተጨባጭ ለውጥ በማምጣት ላይ መሆኑን አስረድተዋል።

የፈተና የሚመራበት ሂደት የትምህርት ጥራት ላይ የራሱን አሉታዊ እና አውንታዊ ተፅኖዎች እንዳሉት ገልፀው የፈተናን ሂደቶች በመግባቡ በመምራት ለውጤት መስራት እንደሚገባ አፅኖት ሰጥተዋል

የዲጂታል 2030 አካል የሆነው ተማሪዎችን በዲጂታል መንገድ በመስጠት የተሻለ ውጤት በመመዝገብ ላይ እንደሚገኝ ገልፀው በትምህርት ቤቶችን ግበዓት በሟሟላት በቂ ዝግጅት በማድረግ ከተወሰኑ አካባቢዎች በስተቀር በበይነ መረብ እንዲፈተኑ የሚያስችል የተሻለ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

የፈተና ግዜ ሂደቱን በአግባቡ በመምራት ተማሪዎች ሳይረበሹ በተረጋጋ እና ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮላቸው በራስ በመተማመን እንዲፈተኑ ቅንጅታዊ አሰራር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

አክለው በወረቀት የሚሰጥ ፈተናም ከስርቆት እና ከተለያዩ ችግሮች ነፃ በማድረግ እንከን የለሽ የፈተና አሰጣጥ ስረዓት ለማስኬድ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት ተናግረዋል።

የዘንድሮ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ የማጠቀለያ የፈተና አሰጣጥ ሂደት በሰላም ተካህዶ በስኬት እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካሉ፥ መምህራን እና የትምህርት ዘርፍ አመራሩ ትልቅ ድርሻ እንደነበራቸው በመግለፅም ምስጋና አቅርበዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በቀጣይ የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና በሰላም እና በስኬት እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት እና በክልሉ የሚገኙ አራቱ ዩንቨርሲቲዎች ተቀናጅተው በተረጋጋ ሁኔታ መስራት ይጠበቅባቸዋልም ብለዋል።

የክልሉ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዮት ደምሴ በበኩላቸው፥ በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ ለመስጠት እቅድ ተይዞ በበርካታ አካባቢዎች በበይነ መረብ ለመስጠት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ገልፀው በግበዓት እና የመሰረተ ልማት እጥረቶች በተወሰኑ ዞኖች ብቻ በወረቀት እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

በ2018ዓ/ም በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና 33 ሺህ 989 ( 64%) ተማሪዎች በ42 የበይነ መረብ ማዕከላት የሚፈተኑ ሲሆን ፥ ቀሪ 18ሺህ 865 36% ተፈታኞች በወረቀት ፈተናውን እንደሚወስዱ አብራርተዋል።

በመድረኩ ከርዕሰ መስተዳድሩ በተጨማሪ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የአራቱ ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንቶች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

Address

Dilla
0000

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00
Saturday 08:00 - 17:00
Sunday 08:00 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dilla Polytechnic College Official posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share