Dawit Mengesha Mekuria/ዳዊት መንገሻ መኩሪያ

Dawit Mengesha Mekuria/ዳዊት መንገሻ መኩሪያ መቼም በተቸገሩት ጎን መቆም ይገባናል

10/10/2025
ዛሬም አለሁ በጌታ ቸርነት!!
26/07/2025

ዛሬም አለሁ በጌታ ቸርነት!!

18/07/2024

GABAGABA BALLU INNIDAMAMET 100%. | Check out Abiy Ahmed official LIVE videos on TikTok! Watch, follow, and discover the latest content from Abiy Ahmed official.

ለእናታችን እትዬ ፋጤ ተባብረን ቤት እንገንባበዳምቦያ ከተማ እትዬ ፋጤን የማያውቃቸው የለም ተወዳጅም ናቸው ። ህፃን ይሁን አዋቂ እትዬ ይላቸዋል ፤ ከአፋቸው የሚወጠው ሁሌም ምርቃት ነው ። ...
11/07/2024

ለእናታችን እትዬ ፋጤ ተባብረን ቤት እንገንባ

በዳምቦያ ከተማ እትዬ ፋጤን የማያውቃቸው የለም ተወዳጅም ናቸው ። ህፃን ይሁን አዋቂ እትዬ ይላቸዋል ፤ ከአፋቸው የሚወጠው ሁሌም ምርቃት ነው ። ሁሉንም ልጆቼ ይላሉ አቅፈው ይስማሉ ።

እንግዲህ እኝህ እናት ምንም በሌለበት የሚያኖራቸው ፈጣሪ ነው ። እናቴ ብሎ የሚደግፋቸው ልጅ በጎናቸው ባይኖርም ብዙ እንደ ልጅ ከጎናቸው የሚቆሙ ግን አልጠፉም ።

እናታችን ፋጤ በዚህ ዕድሜያቸው ማረፍያ ቤት የላቸውም እጅግ ተቸግራዋል ። ለእናታችን ፋጤ ሀፋ በጎ አድራጎት ማህበርም ይሁን ሌሎች ወጣቶች በየጊዜው በሀገር ውስጥና ውጭ ያሉትን በማስተባበር አንዳንድ ድጋፎች እንደሚያደርጉላቸው ይታወቃል። አሁን ደግሞ ብዙወቻችሁ ስትጠይቁ በነበረው መሰረት ለእናታችን ቤት ለመገንባት እቅድ ይዘናል።

እቅዳችን የሚሳከው ደግሞ በደጋግ የኢትዮጵያ ልጆች በመሆኑ በሀገር ውስጥና ውጭ ያላችሁ በግልም ሆነ በቡድን ለቤት መስሪያ የሚሆን ድጋፍ እንድታደርጉ እየጠየቅን ለምታደርጉት ቀና ትብብር ከወድሁ እያመሰገንን ተባረኩ ማለት እንወዳለን ።

➣የድጋፍ አካውንት ቁጥር 1000517478532 ንግድ ባንክ።

➣ስለመልካምነታችሁ ፈጣሪ ይባርካችሁ!!

➣ሀፋ በጎ አድራጎት ማህበር!!

ለበለጠ መረጃ፡- 0917187821/0974759094/0953775124 ይደውሉልን።

ባለፉት ጊዜያት በተባበረ ክንድ በርካቶችን ከብርድ፣ከዝናብና ከአውሬ ማዳን ችለናል።ሀፋ በጎ አድራጎት ማህበር በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ ልበ-ቅኖችን በማስተባበር ለተለያየ ማህበራዊና ኢ...
09/06/2024

ባለፉት ጊዜያት በተባበረ ክንድ በርካቶችን ከብርድ፣ከዝናብና ከአውሬ ማዳን ችለናል።

ሀፋ በጎ አድራጎት ማህበር በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ ልበ-ቅኖችን በማስተባበር ለተለያየ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር የተጋለጡ ወገኖችን ዘር፣ሀይማኖትና ብሄር ሳይለይ እየደገፈ አሳልፏል።

ይህንን መልካምነት እግዚአብሔር ጤናና ሰላም እስከሰጠን ድረስ እናስቀጥላለን።

እናታችን ሞምነ መኪሶ ይባላሉ (የበሪሶ እናት) ነዋርነታቸው በዳምቦያ ወረዳ የቡ ቀበሌ ሲሆኑ ያላቸው አንድ ልጅ (በሪሶ) በወጣትነት ዕድሜው በህመም ጎዳና ከወጣ ቆየት ብሏል። ምናልባትም ይህ ልጃቸው ከሁኔታወች አለመመቻት አንስቶ በጭንቀት ታሞባቸው ልሆንም ይችላል። በዝህ ችግር ውስጥም ሆነው ያገኙትን ለልጃቸው እስከ ጎዳና ሄደው ያቀብሉለታል የእናት ሆድም አይደል።

እንግዲህ እኝህ እናት የሚኖሩት ከታች በፎቶው በሚታየው ቤት በሚመስል ዝናብና ብርዱን በማይከላከል ዳስ ውስጥ ነው።

ሁሉም ብተባበር ለእናታችን ቤት ሰርተን በዚህ ዕድሜያቸው አንዴ ከብርድና ዝናብ እፎይ ብሉ ይመርቁናል። በሀገር ውስጥና ውጭ ያላችሁ ደጋጎች የተለመደ ትብብራችሁን በማድረግ ለእናታችን እንድረስላቸው።

ድጋፍ ማድረግ የምትሹ የአቅማችሁን ከታች ባለው አካውንት ቁጥር ማስገባት ትችላላችሁ።

1000517478532 ንግድ ባንክ

በእናታችን ጎን በመቆም አጋርነታችንን እናሳይ!!

ሀፋ በጎ አድራጎት ማህበር

Address

Durame

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dawit Mengesha Mekuria/ዳዊት መንገሻ መኩሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Dawit Mengesha Mekuria/ዳዊት መንገሻ መኩሪያ:

Share