Assosa University

Call Website Contact the university

Assosa University This is an official page of Assosa University.

ማስታወቂያከትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ወደ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ
14/10/2026

ማስታወቂያ
ከትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ወደ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ም/ፕሬዝዳንት ዘርፍ የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ገመገመ(አሶሳ ዩኒቨርሲቲ፣ ጥቅምት 03/2019 ዓ.ም) የአሶሳ ዩኒ...
13/10/2026

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ም/ፕሬዝዳንት ዘርፍ የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ገመገመ

(አሶሳ ዩኒቨርሲቲ፣ ጥቅምት 03/2019 ዓ.ም) የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ም/ፕሬዝዳንት ዘርፍ የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ገምግሟል።

በሪፖርት ግምገማው የዘርፉ የሥራ አፈጻጸም፣ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት የተከናወኑ ተግባራት፣ ከዕቅድ አንጻር የተመዘገቡ ውጤቶችና ቀጣይ ሥራዎች ላይ ውይይት ተደርጓል።

በግምገማው የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብዮት አበጀ እንደገለጹት፣ በዚህ ሩብ ዓመት በርካታ ስራዎች ተሰርተው የተሻለ ዉጤት የታየበት መሆኑን በመግለፅ ሪፖርት መገምገም የታዩ ጥንካሬዎችን ለማጠናከርና ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት የቀጣይ ሥራዎችን በተሻለ መልኩ ለማከናወን ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

በተጨማሪም የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ የሥራዎችን ተጠያቂነት በማጠናከር፣ የሀብት አጠቃቀምን በማሻሻልና ተቋማዊ ግቦችን በተቀመጠው ጊዜ ለማሳካት የሚያግዝ መሆኑን ዶ/ር አቢዮት ገልፀዋል።

በግምገማው የዘርፉ የሥራ አስፈጻሚዎች የተሳተፉ ሲሆን በሪፖርቱ ላይ ያላቸውን ሙያዊ አስተያየት በመስጠት፣ በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራት የበለጠ ውጤታማና ከተቋሙ አጠቃላይ ዕቅድ ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል።

የሪፖርት ግምገማው የዘርፉን የሥራ አፈጻጸም በተከታታይ ከመከታተልና ከመገምገም ባሻገር፣ የቀጣይ ሩብ ዓመታት ተግባራት በተሻለ ቅንጅት፣ በተጠያቂነትና በውጤታማነት እንዲፈጸሙ መሠረት የሚጥል መሆኑንም ተጠቁሟል።

ስለ ዩኒቨርሲቲዉ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የማህበራዊ ገፆቻችን ይከተሉ!
Twitter:Assosa University () / X
Website: www.asu.edu.et
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: [email protected]

የልዩ አዳሪ ተማሪዎች በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ************//******************(ጥቅምት 3/2019 ዓ.ም ) አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በትምህ...
13/10/2026

የልዩ አዳሪ ተማሪዎች በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ************//******************

(ጥቅምት 3/2019 ዓ.ም ) አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር በጊዜያዊነት የተመደቡለትንና ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የመጡ የ9ኛ ክፍል የልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ተቀብሎ የመማር ማስተማር ሂደቱን በአግባቡ በማስኬድ ላይ ይገኛል።

የአዳሪ ትምህርት ቤቱ ምክትል ርዕሰ መምህር ሀቢብ ሀጂ እንደገለጹት፤ ለተማሪዎቹ ምቹ የመኖሪያና የምግብ አገልግሎት እየቀረበላቸው ትምህርታቸውን በስነ-ስርዓት እየተከታተሉ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ምክትል ርዕሰ መምህሩ አክለውም፣ ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን በተሟላ ሁኔታ እንዲከታተሉ ለማስቻል የመማሪያ መጻሕፍትና የሰው ኃይል ክፍተቶች መኖራቸውን ጠቁመው፤ እነዚህን ለማሟላት ከሚመለከታቸው አካላት ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚስፈልግ አሳስበዋል።

ከሀረርጌ የመጣችው የ9ኛ ክፍል ተማሪ ዱረቲ መሀመድ በበኩሏ፤ የተሻለ ዕውቀት ለማግኘት ወደ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በመምጣቷ የተሰማታቸውን ደስታ ገልፃ፣ አሁን ላይ በምቹ የትምህርት አካባቢ ውስጥ ትምህርቷን እየተከታተለች መሆኗን ተናግራለች።

ተማሪዋ አክላም በቀጣይ ከፍተኛ ትምህርቷን በብቃት አጠናቃ ለሀገሯ የሚጠቅም በጎ ሥራ የመሥራት ትልቅ ምኞት እንዳላት ገልፃለች።

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ — ጥበብን በተግባር!

ስለ ዩኒቨርሲቲዉ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የማህበራዊ ገፆቻችን ይከተሉ!
Twitter:Assosa University () / X
Website: www.asu.edu.et
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: [email protected]

ማስታወቂያ ለትምህርት ፈላጊዎች
12/10/2026

ማስታወቂያ
ለትምህርት ፈላጊዎች

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ 19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን  ተከበረ***********//************( አሶሳ ዩኒቨርሲቲ፣ ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም) በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ 19ኛው ብሔራዊ...
12/10/2026

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ 19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ***********//************

( አሶሳ ዩኒቨርሲቲ፣ ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም) በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ 19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን “ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችና የፌደራል ፖሊስ አባላት የተገኙ ሲሆን ሠንደቅ ዓላማ የኢትዮጵያውያን የጋራ መገለጫ እንዲሁም የነጻነትና የሉዓላዊነት ምልክት መሆኑ ተገልጿል። ይህም ለአገራዊ አንድነትና ለብሔራዊ መግባባት መጠናከር ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተነግሯል።

ስለ ዩኒቨርሲቲዉ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የማህበራዊ ገፆቻችን ይከተሉ!
Twitter:Assosa University () / X
Website: www.asu.edu.et
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: [email protected]

ዉድ የዚህ ገጽ ተከታታዮቻችን በመስከረም ወር የተከናወኑ ዋና ዋና ሁነቶችና አዳዲስ መረጃዎችን በወርሃዊ የኤሌክትሮኒክስ ዜና መጽሄት ቅፅ 25 2019 ዓ/ም ያዘጋጀን በመሆኑ የሚከተለዉን ማስ...
12/10/2026

ዉድ የዚህ ገጽ ተከታታዮቻችን በመስከረም ወር የተከናወኑ ዋና ዋና ሁነቶችና አዳዲስ መረጃዎችን በወርሃዊ የኤሌክትሮኒክስ ዜና መጽሄት ቅፅ 25 2019 ዓ/ም ያዘጋጀን በመሆኑ የሚከተለዉን ማስፈንጠሪያ በመጫን
https://sway.cloud.microsoft/wAFiffJhrfpRrC15?ref=Link ዜና መጽሄታቸንን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ለቀጣይ ስራዎቻችን መሻሻል የእናንተ የአንባቢያን ሀሳብ፣ አስተያየትና ተሳትፎ ትልቅ ሚና አለዉና አስተያየታችሁን እንድትጋሩ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

ስለ ዩኒቨርሲቲዉ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የማህበራዊ ገፆቻችን ይከተሉ!
Twitter:Assosa University () / X
Website: www.asu.edu.et
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: [email protected]

የኢፊዲሪ ትምሀርት ሚኒስቴርን በአመራርነት እንዲመሩ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የተሾሙ ከፍተኛ አመራሮች ባላቸው እውቀትና ባካበቱት ልምድ እንደ ሀገር የተጀመረውን የትምህር...
10/10/2026

የኢፊዲሪ ትምሀርት ሚኒስቴርን በአመራርነት እንዲመሩ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የተሾሙ ከፍተኛ አመራሮች ባላቸው እውቀትና ባካበቱት ልምድ እንደ ሀገር የተጀመረውን የትምህርት ሪፎርምን በተሳካ ሁኔታ እንደሚመሩ ዩኒቨርሲቲያችን በሙሉ ያምናል።

በመሆኑም ዩኒቨርሲቲያችን ለአመራሮቹ መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው እየተመኘ ፣ ቷቋማችንም በጎናቸው መሆኑን ይገልጻል።

ማሳሰቢያበአሶሳ ዪኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች በሙሉ
10/10/2026

ማሳሰቢያ
በአሶሳ ዪኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች በሙሉ

በዩኒቨርሲቲው የሥነ-ጽሑፍና የኪነ-ጥበብ ምሽት  ተካሄደ*******************//***************(አሶሳ ዩኒቨርሲቲ፣ መስከረም 29/2019 ዓ.ም ) በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-...
09/10/2026

በዩኒቨርሲቲው የሥነ-ጽሑፍና የኪነ-ጥበብ ምሽት ተካሄደ*******************//***************

(አሶሳ ዩኒቨርሲቲ፣ መስከረም 29/2019 ዓ.ም ) በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ጽሑፍና የኪነ-ጥበብ ምሽት በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል።በምሽቱ ግጥም ፣ ተውኔት እና ሙዚቃን ጨምሮ የተለያዩ የሥነ-ጽሑፍና የኪነ-ጥበብ ሥራዎች ቀርበዋል።

በዝግጅቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው የሀገር በቀል ጥናት ኦፊሰር ዶ/ር ፈንታነሽ ኃይሌ ሲሆኑ ሥነ-ጽሑፍ ስሜትን ከመግለጽ ባለፈ የማኅበረሰብን ታሪክና ባህል የሚያስቀምጥ፣ ሰዎችን የሚያገናኝና አዳዲስ ሐሳቦችን የሚያፈልቅ ወሳኝ መሣሪያ መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይም በዩኒቨርሲቲ ደረጃ የሥነ-ጽሑፍና የኪነ-ጥበብ ምሽቶችን ማዘጋጀት የተማሪዎችን የፈጠራ ችሎታና ለማዳበር፣ ባህላዊ እሴቶችን ለማስተዋወቅና አዳዲስ የኪነ-ጥበብ ተሰጥኦዎችን ለማበረታታት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አስረድተዋል።

በስነ ጹህፍና ኪነ- ጥበብ ምሽቱ የቀረቡት የተለያዩ ሥራዎች ተማሪዎች ከትምህርታቸው ባለፈ በሥነ-ጽሑፍና በኪነ-ጥበብ ዓለም እንዲዝናኑና አዳዲስ ሐሳቦችን እንዲያያገኙ እንደሚያግዝ ተገልጿል።

የሥነ-ጽሑፍና የኪነ-ጥበብ መድረኮች የተማሪዎችን ፈጠራ ከማበረታታት ባለፈ የዩኒቨርሲቲውን የአካዳሚክና የባህል ሕይወት ለማጠናከር ወሳኝ መሆኑንም ተነግሯል።

ማስታወቂያ  #ለትምህርት ዘመኑ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ መደበኛ የ1ኛ ዓመት አዲስ ገቢ እና በሪሚዲያል ትምህርት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ዉጤት ላመጣችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን እያሳወቅን ...
09/10/2026

ማስታወቂያ
#ለትምህርት ዘመኑ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ መደበኛ የ1ኛ ዓመት አዲስ ገቢ እና በሪሚዲያል ትምህርት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ዉጤት ላመጣችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን እያሳወቅን ለአዲስ የሪሚዲያል ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ በሌላ ማስታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል

Address

Ethiopia, Benishangul Gumuz
Gondar
18

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Assosa University posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Assosa University:

Shortcuts

Share