የመተማ ወረዳ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ቡድን መምሪያ ጣቢያ

  • Home
  • Ethiopia
  • Gondar
  • የመተማ ወረዳ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ቡድን መምሪያ ጣቢያ

የመተማ ወረዳ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ቡድን መምሪያ ጣቢያ ስለ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ግንዛቤ መፍጠር ወይም ጠቀሜታ ማሳወቅ

22/07/2025
23/03/2023

የክብር መዝገብ ሹም ፊት የሚፈጸም ጋብቻ አፈፃፀም ቅደም ተከተል
የክብር መዝገብ ሹሙ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎችና ደጋፊ ማስረጃዎች መሟላታቸውን በመጠየቅ ያረጋግጣል፡፡
ጋብቻው ሁለቱ ተጋቢዎች እና ከእያንዳንዱ ተጋቢ በኩል ሁለት ሁለት ምስክሮች በተገኙበት በግልጽ ይፈፀማል፡፡
ተጋቢዎችና ምስክሮቹ የመሃላ ቃል ከመስጠታቸው በፊት የሚሰጡት ቃል ስለሚያስከትለው ሃላፊነት የክብር መዝገብ ሹሙ በግልጽ ማስረዳት አለበት፡፡
ተጋቢዎችና ምስክሮቹ ጋብቻ ለመፈጸም አስፈላጊ ሁኔታዎች አለመጣሳቸውን በጽሁፍ በሰፈረ ቃለ መሃላ ያረጋግጣሉ፡፡
ሁለቱም ተጋቢዎችና ምስክሮቻቸው በክብር መዝገብ ላይ መፈረም አለባቸው፡፡
የክብር መዝገብ ሹሙ ተጋቢዎቹ በህጋዊ ጋብቻ የተሳሰሩ መሆናቸውን አስታውቆ ለተጋቢዎቹ የጋብቻ ምስክር ወረቀት ይሰጣቸዋል፡፡

የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአት
21/03/2023

የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአት

21/03/2023
17/11/2021

የነዋሪነት መታወቂያን ጨምሮ ሐሰተኛ ሰነዶችን በመኖሪያ ቤቱ ሲያዘጋጅ የነበረ የወረዳ አስተዳደር ሰራተኛ ተያዘ
****************

በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ የነዋሪነት መታወቂያን ጨምሮ የተለያዩ ሃሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጅ የነበረ የወረዳ አስተዳደር ሰራተኛ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ፡፡

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል እና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዲቪዚዮን ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ዘሪሁን ተፈራ እንደገለፁት አንድ ግለሰብ ሃሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ ይዞ ሲንቀሳቀስ ህዝብ በሰጠው ጥቆማ በፖሊስ አባላት ተደርሶበት በተደረገ ምርመራ ሃሰተኛ መታወቂያውን ያዘጋጀውን ግለሰብ ማወቅና በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል፡፡

እንደ ኃላፊው ገለፃ ሃሰተኛ ሰነዶቹን የሚያዘጋጀው ተጠርጣሪ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ወሳኝ ኩነት ምዝገባ የስራ መደብ ላይ ይሰራ የነበረ እና በአሁኑ ወቅት በሌላ የስራ መደብ ላይ የሚገኝ ሲሆን ሃሰተኛ ክብ ማህተም እና ቲተሮችን በማስቀረፅ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ህገ-ወጥ ሰነዶችን ሲያዘጋጅ ቆይቷል፡፡

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ህዳር 04 ቀን 2014 ዓ.ም ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 የረር በር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው የተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት ባደረገው ብርበራ የተለያዩ ንግድ ፈቃዶች፣ የትምህርት ማስረጃዎች፣ መሸኛ ደብዳቤዎች፣ የጋብቻ ማስረጃዎች እና ሌሎች ልዩ ልዩ ሰነዶች ተገኝተዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ማህተሞች እና ቲተሮች፣ ፍላሾች፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተር እና ፎቶግራፍ የተለጠፈባቸውን ጨምሮ ተጠርጣሪው ለሃሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ መስሪያ የሚገለገልባቸው በርካታ ካርዶች እና ሃሰተኛ ሰነድ ሊዘጋጅባቸው የተሰጡ የበርካታ ግለሰቦች ፎቶ ግራፎች በብርበራ ተይዘዋል፡፡

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
የመዝናኛ ቻናላችን የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት የዩቲዩብ የመዝናኛ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCp9pS23Vw1n8WpcpZBDJNmA
በምስል የሚገኙ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የኢንስታግራም ገፃችንን ይከተሉ
https://www.instagram.com/ebcnews1/
አጫጭርና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
https://twitter.com/ebczena

19/08/2021

ወ/ኩ/ም/መ/ኤጀንሲ
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ /14 2013.ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ በማዕከል ከሚሰጡ አገልግሎቶች አንዱ ያላገባ ማስረጃ /Non-marital/ማረጋገጥ ሲሆን ባለ ጉዳዮች ያላገባ ማስረጃውን ለማረጋገጥ ወደ ኤጀንሲው ሲመጡ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን እንደሚከተለው ተቀምጠዋል ፡፡
ዜግነታቸው ኢትዮጵያዊ ለሆኑ
1. የታደሰ በቡድን መሪ የተፈረመ ያላገባ ምስክር ወረቀት ዋናዉ እና ፎቶ ኮፒ ፣
2. የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ዋናዉ እና ፎቶ ኮፒ እና
3. በወረዳዉ ተሞልቶ በቡድን መሪ እና ስራ አስኪያጅ የፈረሙበት ማረጋገጫ ፎርም፣ ከኢትዮጵያ ውጭ ላሉ ኢትዮጵያውያን እና ለትውልደ ኢትዮጵያውያን
1. የታደሰ ያላገባ ምስክር ወርቀት ፣
2. ያላገባ የምስክር ወረቀቱ ከሀገር እስከ ወጡበት ድረስ የተገደበ መሆን አለበት ፣
3. ያላገባ ምስክር ወረቀቱ እንዳይገደብ ከፈለጉ ካሉበት ሀገር አለማግባታቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ፣
4. የታደሰ ፓስፖርት ፣ትራቨል ዶክመንት ወይም የስደተኞች መታወቂያ እንዲሁም
5. በወረዳዉ ተሞልቶ በቡድን መሪ እና ስራ አስኪያጅ የፈረሙበት ማረጋገጫ ፎርም ፣ ማሳሰቢያ
በውክልና ለሚስተናገዱ
1. ስለ ጉዳዩ የሚገልፅ ልዩ ውክልና
2. ውክልናው ከውጭ የተላከ ከሆነ በውጭ ጉዳይ ተረጋግጦ እና በሰነዶች ማረጋገጫ የተመዘገበ (ሀገር ውስጥ የተሰጠ ከሆነ በሰነዶች ማረጋገጫ የተመዘገበ) መሆን አለበት
3. የወካይና የተወካይ የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም ትራቨል ዶክመንት እንዲሁም
4. ያላገባ ማስረጃው በወረዳው እንደተሰጠ የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

Address

አማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ
Gondar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የመተማ ወረዳ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ቡድን መምሪያ ጣቢያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share