Hawassa College of Health Sciences - የሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

  • Home
  • Ethiopia
  • Hawassa
  • Hawassa College of Health Sciences - የሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

Hawassa College of Health Sciences - የሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ Forever to outshine!!

የሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ  ለመላዉ  የኦርቶዶክስ  እምነት ተከታዮች  በሙሉ እንኳን  ለ2018 ዓ.ም የከተራ እና ጥምቀት በዓላት በሰላም አደረሳችሁ በማለት  በዓሉ የፍቅር:የደስታ: የአንድ...
18/01/2026

የሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለመላዉ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ2018 ዓ.ም የከተራ እና ጥምቀት በዓላት በሰላም አደረሳችሁ በማለት በዓሉ የፍቅር:የደስታ: የአንድነት እና የበረከት ይሆንላችሁ ዘንድ የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፋል‼
ጥር 11 /2018 ዓ.ም
ሀ.ጤ.ሳ.ኮ

የሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ  የብልጽግና  ህብረት የግማሽ ዓመት ኮንፍረንስ አካሂዷል ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።የሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የመምህራንና አስተዳ...
17/01/2026

የሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የብልጽግና ህብረት የግማሽ ዓመት ኮንፍረንስ አካሂዷል ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የመምህራንና አስተዳደር ሠራተኞች የብልጽግና ህብረት የ2018 ዓ.ም የ 6 ወር የአባላት ኮንፍራንስ በደማቅ ሁኔቴ አካሂዷል። በመድረኩ የሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መስፍን አየለ እና ም/ሀላፊ አቶ ተመስገን ጴጥሮስ የተሳተፉ ሲሆን የህብረቱ የስድስት ወር አፈፃፀም ሪፖርት በዝርዝር ቀርቦ ሰፊ ውይይት በማድረግ በቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ላይ በመግባባት መድረኩ ተጠቃሏል።

ጥር 08 ,2018 ዓ.ም
ሀ.ጤ.ሣ.ኮ

የሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ታህሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም  የ2018 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደየሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ...
01/01/2026

የሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ታህሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም የ2018 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ
የሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል። መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሌጁ ዲን ወ/ሮ ትሁን ፈለቀ እንደገለጹት፤ ኮሌጁ በመማር ማስተማር፣ በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት፣ በተማሪዎች አገልግሎት እንዲሁም በአስተዳደር ዘርፎች ውጤታማ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል በማለት ይህ የግምገማ መድረክ ያሉንን ጥንካሬዎች የምናስቀጥልበት ክፍተቶችን ደግሞ በመለየት ለቀጣዩ ግማሽ ዓመት ዝግጁነታችንን የምናረጋግጥበት መድረክ እንደሚሆን ያላቸውን ተስፋ በመግለፅ፣ የጋራ ተልዕኳችንን ለማሳካት የሁላችንም ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ ነው ብለዋል።

በመቀጠልም በዕለቱ በሁሉም ዘርፎች ዝርዝር የአፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን በተጨማሪም መድረኩ የላቀ አፈጻጸም ላሳዩ የትምህርት ክፍሎች ዕውቅና የተሰጠበትም ነበር።በዚህም መሠረት በሙያ ማሻሻያ (Post-Basic) የድግሪ ፕሮግራም መውጫ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገበው የሕክምና ላቦራቶሪ ሳይንስ ትምህርት ክፍል እና በደረጃ 4 የብቃት ምዘና (COC) የላቀ ውጤት ላመጣው የፋርማሲ ትምህርት ክፍል የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል። እንዲሁም ኮሌጁን በቅንነትና በታማኝነት ለረዥም ዓመታት አገልግለው በክብር ለተሰናበቱ ሰራተኞቻችን ምስጋና እውቅና ተሰቷቸዋል፡፡ በመቀጠልም በኮሌጁ ሰፋፊ የልማት ሥራዎች ላይ በንቃት ለተሳተፉ ሠራተኞች የዕውቅና ሰርተፍኬት ተሰጥቷቸዋል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የኮሌጁ ዲን ወ/ሮ ትሁን ፈለቀ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የተገኘው ውጤት የሁላችንም የጋራ ጥረት መሆኑን ጠቁመው፣ ዕውቅና የተሰጣቸው ክፍሎችና ግለሰቦች ለሌሎች አርአያ እንዲሆኑ አሳስበዋል። በቀጣይ ስድስት ወራትም የተጀመሩ የለውጥ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና የተቋሙን ሁለንተናዊ ተልዕኮ ለማሳካት ሁሉም በቁርጠኝነት እንዲረባረብ አደራ ብሏል። በመጨረሻም መድረኩ ለቀጣይ ሥራዎች ግልጽ አቅጣጫ በማስቀመጥና በሠራተኛው መካከል የጋራ መግባባትን በመፍጠር በስኬት ተጠናቅቋል።

ታህሳስ 23/2018 ዓ.ም
ሀ.ጤ.ሳ.ኮ

የሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ታህሳስ 22,2018 ዓ.ም  የደም ልገሳ  መርሀ ግብር ተጠናቀቀ።                                                     በሀዋሳ ጤና ሳ...
31/12/2025

የሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ታህሳስ 22,2018 ዓ.ም የደም ልገሳ መርሀ ግብር ተጠናቀቀ።

በሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ታህሳስ 20-22,2018 ዓ.ም "ደሜን እለግሳለሁ - ሕይወት አድናለሁ" በሚል መሪ ቃል ለሦስት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ የነበረው የደም ልገሳ መርሃ-ግብር በስኬት ተጠናቋል።
ከሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ደም ባንክ ጋር በመተባበር በተዘጋጀው በዚህ መርሃ-ግብር ላይ የኮሌጁ ማህበረሰብ በከፍተኛ ተነሳሽነት የተሳተፉ ሲሆን፤ በአጠቃላይ 181 ከረጢት ደም መሰብሰብ ተችሏል።
በልገሳው ላይ በመሳተፍ ወገናዊነታችሁን ላሳያችሁ የኮሌጁ ማህበረሰብ በሙሉ ምስጋናችን የላቀ ነው። ታህሳስ 22,2018 ዓ.ም ሀ.ጤ.ሣ.ኮ

የሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ  ታህሣሥ 17,2018 ዓ.ም ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች Orientation ሰጠ ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።በ2018  ዓ.ም የነርሲን...
26/12/2025

የሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ታህሣሥ 17,2018 ዓ.ም ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች Orientation ሰጠ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በ2018 ዓ.ም የነርሲንግ ፣ሚድዋይፈሪ፣ፋርማሲ ፣ህክምና ላቦራቶሪ እና ፖብሊክ ሄልዝ ዲፓርትመንት ተመልምለው ወደ ኮሌጃችን የገቡ ተማሪዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት በኮሌጃችን የሚኖራቸዉ ቆይታ ስኬታማ እንዲሆን በመመኘት በአካዳሚያዊ ፣የምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት እና ተማሪዎች አገልግሎት ዙሪያ በቂ ገለጻ ተደርጓል ።
መልካም የትምህርት ዘመን!

ታህሳስ፣2018
ሀ.ጤ.ሣ.ኮ

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ምንነት፣ መተላለፊያ መንገዶችና መከላከያ ዘዴዎች
27/11/2025

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ምንነት፣ መተላለፊያ መንገዶችና መከላከያ ዘዴዎች

ጥንቃቄ እናድርግ! እራሳችንን ከማንበርግ ቫይረስ እንጠብቅ !
26/11/2025

ጥንቃቄ እናድርግ! እራሳችንን ከማንበርግ ቫይረስ እንጠብቅ !

ወቅታዊ የጤና ጉዳይን(Hemorrhagic Fever) አስመልክቶ የተሰጠ መረጃተጨማሪ መረጃዎችን """"""""""""""""""""""""""""የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትነፃ የስልክ መስ...
14/11/2025

ወቅታዊ የጤና ጉዳይን(Hemorrhagic Fever) አስመልክቶ የተሰጠ መረጃ

ተጨማሪ መረጃዎችን
""""""""""""""""""""""""""""
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: https://www.sphi.gov.et/

 #ጥንቃቄወቅታዊ የጤና ጉዳይን አስመልክቶ ከኢፌዲሪ ጤና ሚኒስቴር የተሰጠ መግለጫ
12/11/2025

#ጥንቃቄ

ወቅታዊ የጤና ጉዳይን አስመልክቶ ከኢፌዲሪ ጤና ሚኒስቴር የተሰጠ መግለጫ

በስነምግባር የታነፀ ብቁ የጤና ባለሙያ መሆን ይፈልጋሉ ? እንግዲያዉስ በአንጋፈዉ ኮለጃችን ፈጥነው  ይመዝገቡ!27/02/2018 ዓ.ምሀ.ጠ.ሳ.ኮ
06/11/2025

በስነምግባር የታነፀ ብቁ የጤና ባለሙያ መሆን ይፈልጋሉ ? እንግዲያዉስ በአንጋፈዉ ኮለጃችን ፈጥነው ይመዝገቡ!

27/02/2018 ዓ.ም
ሀ.ጠ.ሳ.ኮ

በስነምግባር የታነፀ ብቁ የጤና ባለሙያ መሆን ይፈልጋሉ ? እንግዲያዉስ በአንጋፈዉ ኮለጃችን ፈጥነው  ይመዝገቡ!18/02/2018 ዓ.ምሀ.ጠ.ሳ.ኮ
28/10/2025

በስነምግባር የታነፀ ብቁ የጤና ባለሙያ መሆን ይፈልጋሉ ? እንግዲያዉስ በአንጋፈዉ ኮለጃችን ፈጥነው ይመዝገቡ!

18/02/2018 ዓ.ም
ሀ.ጠ.ሳ.ኮ

በሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሐረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከፍተኛ አመራሮች  በኮሌጃችን ተገኝተው የልምድ ልውውጥ አደረጉ::ጥቅምት 14/2018 ዓ.ምየሐረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ  ከፍተኛ አመራሮች ...
24/10/2025

በሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
የሐረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከፍተኛ አመራሮች በኮሌጃችን ተገኝተው የልምድ ልውውጥ አደረጉ::

ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም
የሐረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከፍተኛ አመራሮች በኮሌጃችን የልምድ ልውውጥ ለማድረግ የተገኙ ሲሆን እኛም ተቀብለን በመማር ማስተማርና በምረምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ጉዳይ ላይ ያለንን ልምድ አካፍለናል።

ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም
ሀ.ጤ.ሳ.ኮ

Address

Hawassa: Next To Snnprs Health Bureau
Hawassa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hawassa College of Health Sciences - የሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Hawassa College of Health Sciences - የሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ:

Share