Tokkichaa Nolee

Tokkichaa Nolee Welcome.Bagaa gamaa rayyaa Paartii badhaadhiinatii nagahan dhuftaan.���������

14/07/2025
በምርጫ ያልተቻለውን በ’YouTube’አቶ ልደቱ አያለው እድሜውን ሁሉ በወሬና አሉባልታ የጨረሰ ፣ አንድ ጠብ የሚል ነገር ያላበረከተ አውርቶ -አደር ነው ። በማንም የማይደገፍ እንደመጣለን የ...
26/05/2025

በምርጫ ያልተቻለውን በ’YouTube’

አቶ ልደቱ አያለው እድሜውን ሁሉ በወሬና አሉባልታ የጨረሰ ፣ አንድ ጠብ የሚል ነገር ያላበረከተ አውርቶ -አደር ነው ። በማንም የማይደገፍ እንደመጣለን የሚያወራ ፣ ግችር በማውራት ብቻ መፍትሔ የሚገኝ የሚመስለው ከንቱ ፖለቲከኛ ነው 😂።

አሁን ደግሞ ትዕይንተ ህዝብ በሚል በ"You Tube" ቀጥታ ስርጭት መንግስትን ከስልጣን እናወርዳለን በማለት እየዶለቱ ነው😂 ። በምርጫ የተመረጠ መንግስት ስልጣን የሚለቀው በምርጫ ብቻ ነው ።
እነ ልደቱ ሁሌ " የሽግግር መንግስት " የሚሉት አሸናፊ የሚያደርጋቸው ሀሳብ የሌላቸው ፣ በቅናት ብቻ ፖለቲከኛ ነን የሚሉ ሀሳብ አልባ ናቸው። ተወዳዳሪ መሆን ከፈለጋቹ ሀገር ቤት በመግባት በሰላማዊ መንገድ መፎካከር እንጂ በ’YouTube’ ምንም ስጣን አይገኝም የዩቱብ ብር እንጂ 😂😂 ።

01/04/2025

ብልፅግና ፓርቲ ኢትዮጵያን ከተረጅነት ለማላቀቅ የሚያስችሉ በርካታ ስኬቶችን አስመዝግቧል
አቶ አደም ፋራህ

ብልፅግና ፓርቲ በአጭር ጊዜያት ወስጥ ኢትዮጵያን ከተረጅነት በማላቀቅ ወደ ተሟላ ሉዓላዊነት ለማሸጋገር የሚያስችሉ በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ተናገሩ።

ፓርቲው ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግስት ለመገንባት ችግሮች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

አቶ አደም ፋራህ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በተገኙ ስኬቶች እና የወደፊት ትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህም ህዝብ ሲያነሳቸው የነበሩ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች ለውጡ እንዲመጣ ያደረጉ ገፊ ምክንያቶች ስለመሆናቸው አብራርተዋል።

በብልፅግና ፓርቲ መሪነት የለውጡ መንግስት የኢትዮጵያን ታሪካዊና አሁናዊ ችግሮች በመለየት ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት በቂ ትንተና አድርጎ ወደ ስራ ስለመግባቱም አስረድተዋል፡፡
በተለይ አሳታፊና አካታች የፖለቲካ ምህዳር እንዲፈጠር ፓርቲው በግንባር አርአያ በመሆን ጭምር በርካታ ስራዎችን ማከናወኑንም አንስተዋል።

ለአብነትም በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ብልጽግና ፓርቲ በአብላጫ ድምጽ አሸንፎ መንግስት የመመስረት ህገ-መንግስታዊ መብት ቢያገኝም የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በተለያዩ የአመራር ደረጃዎች ላይ ማሳተፉን አስታውሰዋል።

ይህም በኢትዮጵያ የፖለቲካ ስርዓት ውስጥ አዲስ ምእራፍ የከፈተ ስለመሆኑም አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ በብልፅግና ፓርቲ መሪነት ባለፉት ጥቂት ዓመታት የዴሞክራሲ ተቋማትን በማጠናከር፣ ማህበራዊ ልማትን በማጎልበት፣ ለጎረቤት ሀገራት ቅድሚያ የሰጠና ትብብር ላይ የተመሰረተ ዲፕሎማሲን ተግባራዊ በማድረግ ተጨባጭ ውጤቶችን ማስመዝገብ መቻሏንም ተናግረዋል።
ከልመናና ተረጅነት በመላቀቅ የተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ይገባል በሚል መርህም ተስፋ ሰጪ የኢኮኖሚ ልማት ስራዎች መከናወናቸውንም አብራርተዋል።

በሌላ በኩል ብልፅግና ፓርቲ ለማህበራዊ ልዕልና፣ ለተረጋጋ የፖለቲካ ስርዓት እንዲሁም ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግስት ለመገንባት ችግሮች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ቅድሚያ ሰጥቶ መስራቱን ተናግረዋል።

በዚህም ፓርቲው ለሰላማዊ መፍትሄ ያለውን ቁርጠኝነት በተደጋጋሚ በተግባር ማረጋገጡን ጠቅሰው፤ የፕሪቶሪያውን ስምምነት በማሳያነት አንስተዋል፡፡

በአፍሪካ ግዙፍ ፓርቲ የሆነው የብልጽግና ፓርቲ ከኢትዮጵያ አልፎ አፍሪካዊ እና ዓለም አቀፋዊ ግንኙነቶችን በማጠናከር ለፍትሃዊ እና የጋራ ተጠቃሚነት እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

Address

Hirna

Telephone

+251991827291

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tokkichaa Nolee posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Tokkichaa Nolee:

Share