05/09/2025
የቀይ እንባ ወተት
የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት መምህር ምስጋና ተመስገን በህገወጥ ስደት እና አስከፊነት ላይ የተመሠረተ "Kashar "Indiixxi Ado" "የቀይ እንባ ወተት" በሚል ርዕስ በሀዲይሳና በአማርኛ ቋንቋ የተጻፈው የገሐዱ ዓለም ነጸብራቅ የሆነው መጽሐፍ በዘሬው ዕለት በቪክቲሪ ሆቴል የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል፣ የዞን ም/ቤት አባላት፣ የዞን መምሪያ ኃላፊዎች፣ የወረዳ አስተዳዳሪዎች ነጋዴዎች፣ የዩኒቨርስቲው ምሁራንና የሐዲይሳ ቋንቋ ትምህርት ክፍል ተማሪዎች የደራሲው ቤተሰቦች እና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል።
እኔም በመጽሐፉ የአማርኛው እትም ላይ በተወሰነ ደረጃ ተሳትፎ ያደረኩት በመሆኑ በምረቃው ሥርዓት በመታደሜ በእጅጉ ደስ ብሎኛል።