Ayehu Guagusa Education Office

Ayehu Guagusa Education Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ayehu Guagusa Education Office, College & University, Injibara.

የትምህርት ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ ነዉ !!  ህጻናት ይማሩ! የአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገት እና ብልጽግና ማምጣት የሕዝቦቿን ኑሮ ማሳደግ የሚቻለው በሚኖራት የተማረ የሰው ኃይል እምቅ አቅ...
22/09/2025

የትምህርት ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ ነዉ !!
ህጻናት ይማሩ!

የአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገት እና ብልጽግና ማምጣት የሕዝቦቿን ኑሮ ማሳደግ የሚቻለው በሚኖራት የተማረ የሰው ኃይል እምቅ አቅም ነዉ።

እንደሀገር ለመጽናት እንደ ህዝብ ለመኖርም ትምህርት ላይ መስራት ብቸኛዉ መዉጫ መንገድ መሆኑ ሀቅ ነዉ።

ትምህርት ዘላቂ የአስተሳሰብ ለውጥን በማምጣት ፣ የአንድን ሀገር ሰላም፣ እድገትና ብልጽግና በማረጋገጥ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ከቤተሰብ ጀምሮ ማህበረሰቡ በጋራ መስራት ይኖርበታል።

በክልላችን ሁሉም እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናትና ወጣቶች ወደ ትምህርት ተቋማት እንዲገቡና ያለአንዳች የጊዜ ብክነት ማግኘት ያለባቸውን የትምህርት ፍሬ እንዲያገኙ ማስቻል ይጠበቅብናል።

በዚህ ረገድ በትምህርት ዘመኑ ያለው አጀማመር ካለፉት ጊዜያት ለውጦች ቢኖሩትም አሁንም ፈጣን ጥረትና እገዛ ከሁላችንም ይጠበቃል።

!
!
!
!

🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊
•~•~•

"የጎርጎራ ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
•~•~

የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች የሚያገኙበት አድራሻዎች ይፋ ሆኑአዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ...
15/09/2025

የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች የሚያገኙበት አድራሻዎች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች የሚያገኙበት አድራሻዎች ይፋ ሆነዋል፡፡

የ2017 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተፈተኑ ተፈታኞች በሚከተሉት አድራሻዎች ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ፡፡

ዌብ ሳይትና ቴሌግራም አድራሻ የሚጠቀሙ ተፈታኞች ጊዜያዊ ሰርቲፊኬታቸውን ወዲያውኑ አውርደው (download አድርገው) መውሰድና መጠቀም ይችላሉ፡፡

አድራሻዎቹ፡

1. ዌብ ሳይት፡ https://result.eaes.et

2. ቴሌግራም፡ https://t.me/EAESbot

3. አጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS)፡ 6284

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

በአየሁ ጓጉሳ ወረደ ትም/ጽ/ቤት ሁሉም ምዝገባ የጀመሩ  ት/ቤቶች የ2018 ዓ/ም የትም/ት አጀማመር (Day one class one) በጥሩ ንቅናቄ ተጀምሯል። የትም/ት አጀማመር የወረዳው አስ...
15/09/2025

በአየሁ ጓጉሳ ወረደ ትም/ጽ/ቤት ሁሉም ምዝገባ የጀመሩ ት/ቤቶች የ2018 ዓ/ም የትም/ት አጀማመር (Day one class one) በጥሩ ንቅናቄ ተጀምሯል። የትም/ት አጀማመር የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ገበየሁ በሪሁን ጭምር ት/ቤቶችን ጭምር ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

2017 ም.አ 12ንቲ ቤኑ ዩንቨርስቴ ሚፅፂ ፍታኒ  8 ትኩሚ 4 ታፋ ክንታንትካ 50 ታፋስታ ጃላ ዋይሜ ያጌካ - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋባርዳር፡ ሜስኬሩም 04/2018 ም.አ(አሚኮ አውጚ) 20...
14/09/2025

2017 ም.አ 12ንቲ ቤኑ ዩንቨርስቴ ሚፅፂ ፍታኒ 8 ትኩሚ 4 ታፋ ክንታንትካ 50 ታፋስታ ጃላ ዋይሜ ያጌካ - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

ባርዳር፡ ሜስኬሩም 04/2018 ም.አ(አሚኮ አውጚ) 2017 ም.አ ክንቲው ዝቤንዳ 12ንቲ ቤኖ አሊዲው ፍታኒዳ 8 ትኩሚ 4 ታፋ ክንታንትካ 50 ታፋስታ ጃላ ዋይሜ ሜዜጌብፅጞ ክንቲው ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጌሌፅካ፡፡

ክንቲው ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ክንቲው ዝቤኑ 12ንቲ ቤኑ ዩንቨርስቴ ሚፅፄ ፍታኒውሳ ዋይሜ ካንትኹስ ጊሊፄ እይካ።

50 ታፋስታ ጃላ ዋይሜ ሜዜጌብፁንኩ ክቻዴስ ማይቤራዊ ሳይንስ ፌቴንስታንትካ 5. ትኩሚ 2 ታፋ፣ ፍትሬት ሳይንስ ፌቴንስታንትካ ዴሜካ 11 ትኩሚ 4 ታፋ አኽጞ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ቶኬምካ፡፡585 ሻይ 882 ክንታንትካ ፍታኔ ፌቴንስትጞኪላ ጌሊፂዳ ቶኬምካ፡፡

እምልፕታቑ ኪሲስ ቲጊኔ

የ2018 ዓ/ም የትምህርት ስራ ቅድመ ዝግጅት ተገመገመ።አየሁ ጓጉሳ ትም/ጽ/ቤት መስከረም 04/2018 ዓ/ም (አዘና)ዛሬ በቀን  መስከረም 04/2018 ዓ/ም ሁሉም የትምህርት ባለድርሸ አካላ...
14/09/2025

የ2018 ዓ/ም የትምህርት ስራ ቅድመ ዝግጅት ተገመገመ።
አየሁ ጓጉሳ ትም/ጽ/ቤት መስከረም 04/2018 ዓ/ም (አዘና)
ዛሬ በቀን መስከረም 04/2018 ዓ/ም ሁሉም የትምህርት ባለድርሸ አካላት (ር/መ/ራን፣ ሱ/ሮችና የጽ/ቤት ባለሙያዎች) በተገኙበት
1.መስከረም 05/2018 ዓ/ም የትም/ት አጀማመር (Day one class one) ቅድመ ዝግጅት ስራ ምን እንደሚመስ፤
2.የተማሪ ምዝገባ ያለው አፈፃፀም እና ጎን ለጎን ተማሪ ምዝገባ
3.የተዘጉ ተቋማት እንዴት ወደስራ መግባት እንዳለባቸው
4.አጠቃላይ የመርሱ ስምሪት ያለበት ሁኔታ በመገምገምና በመግባባት የስራ ስምሪት ተይዟል።

የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይሆናልአዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2017 የትምህርት ዘመን የተሰጠው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት በነገው ዕ...
13/09/2025

የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2017 የትምህርት ዘመን የተሰጠው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት በነገው ዕለት ይፋ ይሆናል።

የትምህርት ሚኒስቴር ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳስታወቀው፤ የፈተና ውጤቱን አስመልክቶ በነገው ዕለት ከ10 ሰዓት ጀምሮ ለመገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ ይሰጣል።

የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ መሰጠቱ ይታወሳል።

በተፈጥሮ ሳይንስና በማህበራዊ ሳይንስ በአጠቃላይ 608 ሺህ 742 ተማሪዎች ተመዝግበው 581 ሺህ 905 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል።

ከተፈታኞቹ መካከል 134 ሺህ 828 ተማሪዎች በበይነ መረብ የተፈተኑ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ ተማሪዎች ደግሞ በወረቀት ተፈትነዋል።

ፈተናው በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በተቋቋሙ 216 የመፈተኛ ማዕከላት በበይነ መረብ በአራት ዙር እንዲሁም በወረቀት በሁለት ዙር መሰጠቱ የሚታወስ ነው።

በመሳፍንት እያዩ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/ በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

ዕድሜው ለትምህርት የደረሰ ልጅን ወደ ትምህርት ቤት አለመላክ ያስጠይቃል - ትምህርት ሚኒስቴርየአንደኛ ደረጃ ትምህርት ነጻና ግዴታ መሆኑን በመገንዘብ ወላጅ ወይም አሳዳጊ ዕድሜው ለትምህርት ...
12/09/2025

ዕድሜው ለትምህርት የደረሰ ልጅን ወደ ትምህርት ቤት አለመላክ ያስጠይቃል - ትምህርት ሚኒስቴር

የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ነጻና ግዴታ መሆኑን በመገንዘብ ወላጅ ወይም አሳዳጊ ዕድሜው ለትምህርት የደረሰ ልጅን ወደ ትምህርት ቤት መላክ እንዳለበት ትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ።

በኢትዮጵያ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ከ7 ሚሊዮን በላይ ህጻናት በተለያዩ ምክንያቶች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ መግለጹ ይታወቃል።

እንግዲያውስ እነዚህን ልጆች ወደ ትምህርት ቤት የማስገባት ሀገራዊ ንቅናቄን በመቀላቀል የዜግነት ግዴታን በመወጣት ሁሉንም ወደ ትምህርት ቤት እንዲገቡ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም አመላክቷል።

በሚኒስቴሩ የትምህርት ፕሮግራሞችና ሥርዓት ማሻሻል ዴስክ ኃላፊ ዳዊት አዘነ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ከቅድመ መደበኛ እስከ 8ኛ ክፍል ከተመዘገቡት ውስጥ ለ60 በመቶው የትምህርት ቤት ምገባ ተደራሽ ይደረጋል።

የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ነጻ እና ግዴት መሆን በትምህርት ሕጉ መደንገጉን አስታውቀው፤ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ልጆችን ወደ ትምህርት ቤት አለመላክ በሕግ እንደሚያስጠይቅም አሳስበዋል።

ወላጆች፣ አሳዳጊዎች፣ ሕብረተሰቡና ባለድርሻ አካላት ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ልጆች ከትምህርት ገበታ ውጭ እንዳይሆኑ ሊረባረቡ ይገባል ነው ያሉት።

በ2018 ከቅድመ መደበኛ እስከ 12ኛ ክፍል 31 ነጥብ 9 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለማስተማር መታቀዱን እና ከእነዚህ መካከል 15 ሚሊዮኑ ሴቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ሰላም ባልተረጋገጠባቸው አካባቢዎች፣ በኢኮኖሚ እጥረት እና የልጆችን ጉልበት በመፈለግ ምክንያት በ2017 የትምህርት ዘመን ከ7 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ እንደነበሩም አውስተዋል።

በ2018 የትምህርት ዘመን በትምህርት ገበታ ላይ እንዲገኙ የታቀደው 31 ነጥብ 9 ሚሊዮንም ባለፈው ዓመት ከትምህርት ገበታ ውጭ የነበሩትን እንደሚያጠቃልል አስታውቀዋል።

ዕቅዱን ለማሳካትም ሚኒስቴሩ በሦስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የተማሪዎች ተሳትፎ የንቅናቄ ሠነድ አዘጋጅቶ ከክልሎች እና ባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ በማድረግ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም መሠረት ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ልጆች ወደ ትምህርት ቤት እንዲሄዱ ለማስቻል ለማኅበረሰቡና ባለድርሻ አካላት ግንዛቤ መፍጠር አንዱ የሠነዱ ትኩረት መሆኑን ጠቅሰዋል።

የተማሪ ተሳትፎ ዕቅድን ለማካካስ የሚያስችሉ ሁነቶችን ማዘጋጀት ሁለተኛው የሠነዱ ትኩረት መሆኑን ጠቁመው፤ የምዝገባ ሳምንት፣ የግቢ ጽዳት ሳምንት፣ የቤት ለቤት ቅስቀሳ እንዲሁም የትምህርት ቁሳቁስ የማሰባሰቢያ ሳምንት እንዲዘጋጁ ማድረግ መሆኑን አብራርተዋል።

ሦስተኛው ሰላምን የማጽናት ስራ እየተከናወነባቸው ባሉ አካባቢዎች ተማሪዎች በሚፈለገው ልክ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ በዋናነት የአካባቢው ማኅበረሰብ፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂና ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ትምህርት ቤቶችን ለመማር ማስተማር ምቹ እንዲሆኑ እንዲሠሩ ማድረግ ነው ብለዋል።

ከነሐሴ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ የትምህርት ምዝገባ እና ተጓዳኝ ተግባራት በጥሩ ሁኔታ እየተከናወኑ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ሁሉም ትምህርት ቤቶች ከመስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለትምህርት ክፍት ሆነው ማስተማር እንደሚጀምሩም አስታውቀዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

በ2018 ዓ/ም አንድም ህፃን ከትምህርት ገበታ ውጭ አይሆንም!!
10/09/2025

በ2018 ዓ/ም አንድም ህፃን ከትምህርት ገበታ ውጭ አይሆንም!!

ስለ ጳጉሜ _5 ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ መልዕክት!!የነገው ቀንዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግትናንትን በመጠቀምና በማረም፣ ዛሬ ላይ ተግተን በመሥራት፣ ነገን እጅግ የተሻለ ለማድረግ...
10/09/2025

ስለ ጳጉሜ _5 ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ መልዕክት!!
የነገው ቀን

ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ

ትናንትን በመጠቀምና በማረም፣ ዛሬ ላይ ተግተን በመሥራት፣ ነገን እጅግ የተሻለ ለማድረግ ተነሥተናል፡፡ በአናሎግ ዘመን የነበሩ ችግሮች በዲጂታል ዘመን አይደገሙም፡፡ ነገ “ዲጂታል ኢትዮጵያ” ፕሮጀክት ከመሆን አልፎ ባህል ይሆናል፡፡ ንግድ እና አገልግሎታችንን በማቀላጠፍ፣ መረጃዎቻችንን ተደራሽ በማድረግ፣ አንድ ሰው አንድ እንዲሆን በማስቻል፣ የፋይናንስ ሥርዓታችንን ይበልጥ ተደራሽ ቀልጣፋ እንዲሆን በማድረግ፣ የትምህርትና የጤና አገልግሎቶችን በየአቅጣጫው በማስፋፋት፣ ዲጂታል ኢትዮጵያ እንዲሳካ የሁላችንን ጥረትና ትኩረት ይፈልጋል፡፡

በፕ/ር ጌትነት ታደለ አስተባባሪነት ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች የተገኙና ለመማር ማስተማር የሚያገለግሉ የትምህርት መሳሪያዎች በአየሁ ጓ/ወረዳ ለሚገኘው ለፕ/ር ጌትነት ታደለ 2ኛ ደ/ትም/ቤት ...
08/09/2025

በፕ/ር ጌትነት ታደለ አስተባባሪነት ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች የተገኙና ለመማር ማስተማር የሚያገለግሉ የትምህርት መሳሪያዎች በአየሁ ጓ/ወረዳ ለሚገኘው ለፕ/ር ጌትነት ታደለ 2ኛ ደ/ትም/ቤት ድጋፍ ተደረገ።

አዘና ጰጉሜ 03/2017 ዓ.ም (አየሁ ጓ/ኮሙኒኬሽን)
በዛሬው ዕለት ለትም/ቤቱ ድጋፍ የተደረጉ የትምህርት መሳሪያዎችም 30 ላፕ ቶፕ፣ 1 ፕሮጀክተር፣ 3 ስታቭላይዘር ሲሆኑ 12 ፓኔል ሶላር ከነሙሉ አክሰሳሪው ደግሞ የኢንስታሌሽን ስራው አልቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ነው።

6.6KW ሀይል የሚያመነጨው 12 ፓኔል ሶላር 11KWh ሀቅም ማንቀሳቀስ የሚችል ኢንቨርተር/inverter/ የተገጠመለት ሲሆን አገልግሎቱም በትም/ቤቱ ላይ 24:ዐዐ ሰዓት ሙሉ ለመብራት አገልግሎት የሚውልና ኮምፒውተርን ማንቀሳቀስ የሚችል ነው።

አነዚህ መሳሪያዎች ተማሪዎቹ ቲዎሪን በተግባር በማቀናጀት ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያግዙ ናቸው።

ይህንን የትምህርት መሳሪያ ድጋፍ ያደረጉት ወንድም ፋውንዴሽን ከአምስታርደም፣ ዋይልድ ጋይዝ፣ ፓርትነርስ ኢን ኢዱኬሽን ኢትዮጵያና ፕ/ር ጌትነት ታደለ ሲሆኑ ይህንን ድጋፍ ተረክበው ለትም/ቤቱ ያስረከቡት የወረዳው ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አሳዬ ተረፈ ትምህርት የሁሉም መሠረት መሆኑን ተረድተው ይህንን ድጋፍ ላደረጉ ድርጅቶችና ለፕ/ር ጌትነት ታላቅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የ2018 ዓ.ም. ትምህርት ቤቶች ከመስከረም 05/2018 ዓ.ም ጀምሮ የመማር ማስተማር ሥራ ይጀምራሉ ፤ትምህርት ሚኒስቴር             ከ2018 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም ትምህርት...
06/09/2025

የ2018 ዓ.ም. ትምህርት ቤቶች ከመስከረም 05/2018 ዓ.ም ጀምሮ የመማር ማስተማር ሥራ ይጀምራሉ ፤ትምህርት ሚኒስቴር

ከ2018 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ሞባይል ስልክ ፣ ታብሌትና ኤሌክትሮኒክስ ቁሰቀቁሶችን ይዞ ትምህርት ቤት መምጣት ተከልክሏል፡፡

(ጳጉሜን 01/2017 ዓ.ም) የ2018 የትምህርት ዘመን የትምህርት ቤቶች አከፋፈት አስመልክቶ ትምህርት ሚኒስቴር ከክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር የበይነ-መረብ ምክክር ባደረገበት ወቅት የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ እንደገለጹት የ2018 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ ሰኞ መስከረም 5/ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ይጀመራል።

በትምህርት ካሌንደሩ መሠረት ዓርብ መስከረም 2 / 2018 ዓ.ም. ትምህርት ቤቶች ክፍት ሆነው መምህራንና ተማሪዎች ውይይት የሚያደርጉበትና መስከረም 5/2018 ዓ.ም ደግሞ በይፋ ለሚጀመረው የትምህርት ስራ ቅድመ ዝግጅት የሚያደርጉበት ቀን መሆኑንም ክብርት ወ/ሮ አየለች አስታውቀዋል፡፡

በ2018 የትምህርት ዘመን ባለፈው ዓመት ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ተማሪዎችን ጨምሮ ሁሉም እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናትና ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ወላጆች፣ መምህራንና የዘርፉ ባለድርሻዎች የጀመሩትን የንቅናቄ ተግባር አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባና የትምህርት ቤት ምዝገባም እስከ መጨረሻው ቀን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የተማሪዎችን ሥነ ምግባር በተመለከተም ከ2018 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በየትኛውም ክልልና የከተማ አስተዳደር የሚገኝ ተማሪ ተንቀሳቃሽ ስልክ ፣ ታብሌትና ማናቸውንም የትምህርት ስራ ላይ ተጽእኖ ሚያሳድሩና አዋኪ የሆኑ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶችን ይዞ መገኘት ክልክል መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ አስገንዝበዋል፡፡

በበይነ መረብ በተካሄደው ምክክር የትምህርት ጥራትና ፕሮግራሞች መሻሻል መሪ ስራ አስፈጻሚ ዩሀንስ ወጋሶ (ዶ/ ር) የ2018 የትምህረትት ዘመን የትምህርት ቤቶችን አከፋፈት ጋር ተያይዞ የባለድርሻ አካላት ሚና ፣የትምህርት ቤቶች ዝግጅት፣ ምቹና ደህንነቱ የተጠበቀ የትምህርት አካባቢ በመፍጠር፣ በትምህርት ለትውልድና በሌሎችም ዙሪያ ስትራቴጂክ እቅድ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በምክክር መድረኩ የተሳተፉ የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችና ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች በበኩላቸው ለ2018 የትምህርት ዘመን አከፋፈት ፣በተማሪዎች ምዝገባ ፣ በትምህርት አጀማመር፣ በመማር ማስተማር ስራውና በተማሪዎች ስነ ምገባር ዙሪያ አፈጻጸሞቻቸውን አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።

# ትምህርት ሚኒስትር

Address

Injibara

Telephone

+251918058133

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ayehu Guagusa Education Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Ayehu Guagusa Education Office:

Share