23/02/2023
[የእመቤታችን የየካቲት 16 ቃል ኪዳኗን አስመልክቶ በሊቃውንት የቀረበላት ውዳሴ (ቅዱስ ያሬድ፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፣ አባ ዘመለኮት፣ አባ ጽጌ ድንግል)]
✍️ አዘጋጅ፡- መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥 ቅዱሳን ሊቃውንት የአምላክን እናት አመስግነው በቃኝ አይሉም ነበር በተለይ ከኢትዮጵያ ሊቃውንት ቅዱስ ያሬድ፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፣ አባ ጽጌ ድንግልና አባ ዘመለኮትን በዚህ ክፍል ላይ ስጠቅሳቸው በተለይ የክብር ባለቤት ልጇ በጎልጎታ የምሕረት ቃል ኪዳንን የገባላትን የየካቲት 16 ክብረ በዓሏን አስመልክቶ ከጻፉት ከብዙው በጣም ጥቂቱን የእመቤቴን በረከት ለመሳተፍ ስል አስፍሬዋለሁ፡፡
💥በቅዱስ ያሬድ💥
❤ ቅዱስ ያሬድ በድጓው በተለይ በዐጫብር ድጓ ዘኪዳነ ምሕረት ውስጥ ከተጻፈው፡-
✍️ “ለብእሲ ዕሩቅ እምልብሰ ምግባር
ታዕድዊዮ እምገሃነም ባሕር
ኦ ድንግል በኪዳንኪ ሐመር”
(ድንግል ሆይ በቃል ኪዳንሽ መርከብ ከምግባር ልብስ የተራቈተውን ሰው ከገሃነመ እሳት ባሕር ታሻግሪዋለሽ)
✍️ “ብእሲ ቅሩብ ለሙስና
ለድንግል በኪዳና
በመንግሥተ ሰማይ ዘኢይጸልም ብርሃና
ይረክብ ሕይወተ ዕረፍት ወጥዒና”
(ለጥፋት የቀረበ ሰው ለድንግል በተሰጣት ኪዳን፤ ብርሃኗ በማይጨልም በመንግሥተ ሰማይ ዕረፍትና ጤንነትን ያገኛል)
✍️ “ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር ወገበዋቲሃኒ በሐመልማለ ወርቅ
አንቲ ምሥራቅ ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ
አማን ኪዳንኪ ኢየሐልቅ”
(በብር የተሠራች የርግብ ክንፍ ጐኖቿ በወርቅ ዐመልማሎ የተሸለመች አንቺ በምሥራቅ ስትመሰዪ ልጅሽ የእውነት ፀሐይ ነው፡፡ በእውነት ቃል ኪዳንሽ አያልቅም)፡፡
✍️ “አዕረግዋ መላእክት እምድር ውስተ ሰማያት በክብር ወበስብሐት
በእንቲኣነ ከመ ትስአል እምወልዳ ኪዳነ ምሕረት”
(ስለ እኛ ከልጇ የምሕረት ኪዳንን ትለምን ዘንድ በክብር በምስጋና መላእክት ከምድር ወደ ሰማያት አሳረጓት፡፡)
✍️ “ይቤላ ለእሙ ማርያም እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ተካየድኩ ምስሌኪ ኪዳነ ምሕረት ከመ አድኅን ዘተአመነኪ መሐልኩ ለኪ በርእስየ ዘመሐልኩ አነ ለኖኅ ገብርየ ወለአብርሃም ፍቁርየ፤ ዘመሐልኩ አነ ለዳዊት ኅሩይየ ብእሲ ምእመን ዘከመ ልብየ መሐልኩ ለኪ በርእስየ በቅዱስ ሥጋየ ወበክቡር ደምየ መሐልኩ ለኪ በርእስየ ከመ ኢይሔሱ ማእኰትየ”
(ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ ማርያምን እንዲኽ አላት በምልጃሽ ያመነብሽን አድን ዘንድ ካንቺ ጋራ የምሕረት ቃል ኪዳንን ተጋባኊ፤ ለአገልጋዬ ለኖኅና ለወዳጄ ለአብርሃም ቃል የገባኊ እኔ በራሴ ማልኹልሽ፤ እንደ ልቤ ለምለው ለታመነው ለዳዊት የማልኊ እኔ በራሴ ማልኹልሽ፤ በቅዱስ ሥጋዬና በክቡር ደሜ የማልኊ እኔ ምዬ እንደማልከዳ ማልኹልሽ)
💥💥💥
💥 አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ💥
✍️ድካመ ጌጋይየ ትማእ ማርያም ጽድቀ ዚኣኪ በጽንዓ
መዳልወ ጥበብ ሶበ መልኣ ሰማኒተ ነፍሳተ ወሰብዓ
ሕፍነ ማይ ኀየለ ወሞአ”
(ማርያም የአንቺ ጽድቅ የበደሌን ድካም ድል ትነሣ ዘንድ የጥበብ (የምስጢር) ሚዛኖች በመሉ ጊዜ እፍኝ ውሃ ሰባ ስምንት ነፍሳትን ፈጽሞ ድል ነሣ፡፡)
✍️ “በከመ ልማድኪ በሊ ኀበ ወልድኪ ከሃሊ
ኦ ርኅሩኅ ኢተበቃሊ
ያጠፍኦኑ ለሥዕሉ ሠዓሊ
ኪነተከ ዘትካት ኀሊ”
(እንደ ልማድሽ ኹሉን የሚችል ወደሚኾን ልጅሽ የማትበቀል ቸር ሆይ፤ ሠዓሊ ሥዕሉን ያጠፋዋልን? የቀድሞ ፍጥረትኽን ዐስብ በዪ)።
✍️ “ጊዜ ጸልዮትኪ በጽሐ ከመ ኢይሙት ገብርኪ
ቅድሜሁ ስግዲ ወአስተብርኪ
እንዘ ታዘክሪዮ እምጻማ ንግደትኪ
ርግብየ የዋሂት ለየዋህ ወልድኪ”
(ደገኛዪቱ ርግቤ ለደገኛው ልጅሽ የእንግድነትሽን ድካም እንደ እናት እያሳሰብሺው፤ በፊቱ ፍጹም ስገጂ፤ አገልጋዪሽ እንዳይሞት የጸሎትሽ ጊዜ ደረሰ)።
✍️ “እሙ በሊዮ በእንቲኣየ ለፍሬ ከርሥኪ እብኖዲ
ላዕሌሁ ምሕረተ ኢታጐንዲ
እመ አሕዘነከ ብእሲ አባዲ
ቤዛ ነፍሱ ንጽሕየ እፈዲ”
(የጌታዬ እናት የማሕፀንሽ ፍሬ እብኖዲን ስለ እኔ እንዲኽ በዪው በርሱ ላይ ይቅርታን አታዘግዪ፤ ሰነፍ ሰው ቢያሳዝንኽም የነፍሱን ምትክ ንጽሕናዬን ዋጋ አድርጌ እከፍልለታለኊ)።
✍️ “አንቲ ውእቱ ለእግዚአብሔር አትሮኑሱ
ለአዳም ክብረ ሞገሱ
በኪዳንኪ ኃጥኣን መንግሥተ ሰማያት ይወርሱ"
(የእግዚአብሔር አትሮንሱ (ዙፋኑ) የአዳም የግርማው ክብር አንቺ ነሽ፤ ኃጥኣንም በቃል ኪዳንሽ መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉ)።
💥💥💥
💥 አባ ጽጌ ድንግል 💥
✍️ “ሚ ሠናይ ከመ ጼና ጽጌ ልሑይ
በኲሉ ጊዜ ምሒረ ነዳይ
በእንተ ኪዳንኪ ድንግል ለበላዔ ሰብእ ጊጉይ
ሶበ ዐብየ እምኀጢአቱ ክበደ መድሎቱ ለማይ
ለተአምርኪ በሰማይ ተገብረ ግናይ”
(ኹል ጊዜ ለደኻ መራራት መመጽወት እንደ ለመለመ አበባ ያማረ ነው (ምን ያምር?) ድንግል በቃል ኪዳንሽ ምክንያት ከበላዔ ሰብእ ኀጢአት የውሃ ሚዛን በልጦ በመታየቱ ለተአምርሽ በሰማይ ምስጋና ኾነ)።
✍️ “በከመ ይቤ መጽሐፍ ማእከለ ፈጣሪ ወፍጡራን
ለዕረፍት ዘኮንኪ ትእምርተ ኪዳን
ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ዕለተ ብርሃን
ብኪ ይትፌሥሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን
ወብኪ ይወጽኡ ኃጥኣን እምደይን”
(መጽሐፍ እንደተናገረ በፈጣሪና በፍጡራን መካከል ለዕረፍት የኪዳን ምልክት የሆንሽ የብርሃን ዕለት የሰንበታት ሰንበት ማርያም በአንቺ የገነት አበባ ጻድቃን ይደሰታሉ፡፡ ኃጥአንም በአንቺ ምልጃ ከሲኦል ይወጣሉ)፡፡
💥💥💥
💥የመልክአ ኪዳነ ምሕረት ደራሲ አባ ዘመለኮት💥
✍️ “ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘአስተማሰልዎ በኮከብ
ሶበ ብርሃኖ ተከድኑ ጽልሙታነ ራእይ ሕዝብ
ኪዳነ አምላክ ማርያም ወተስፋ መድኀኒት ዘዐርብ
ተናዘዘ ብኪ አኮኑ ኅሊና ቀዳማይ አብ
አመ እምገነቱ ተሰደ በሐዘን ዕጹብ”
(ለጨለመባቸው ወገኖች ብርሃኑን ባሳየ ጊዜ በኮከብ የመሰሉት ለኾነ ለስም አጠራርሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ የዐርብ የመድኀኒት ተስፋ የአምላክ ኪዳን ማርያም ሆይ በሚያስጨንቅ ሐዘን ከገነቱ በተሰደደ ጊዜ የመዠመሪያው ሰው ኅሊና ባንቺ ተረጋጋብሽ እኮን)።
✍️ “ሰላም ለአእዛንኪ እለ ተበሥራ ኪዳነ
እምአፈ ፈጣሪ ወልድኪ ዘባሕርየኪ ተከድነ
አምሕለኪ ማርያም ከመ ኢታርእዪኒ ደይነ
እንበለ ምግባር ባሕቱ እመ ኢይጸድቅ አነ
ቦኑ ለከንቱ ኪዳንኪ ኮነ”
(ባሕርይሽን ከተዋሐደ ከፈጣሪ ልጅሽ አንደበት የኪዳን ምሥራችን ለተበሠሩ ጆሮዎችሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ ያለምግባር የማልጸድቅማ ከኾነ በውኑ ኪዳንሽ ለከንቱ ይኾናልና ማርያም ሆይ ፍርድን እንዳታሳዪኝ አምልሻለኊ)።
✍️ “ማርያም ኅሪት እምነ መላእክት ወሰብእ
ተዝካረኪ ለእመ ገብረ በተአምኖ ጽኑዕ
በመንግሥተ ሰማይ ምስሌኪ ይነግሥ ኃጥእ”
(ከመላእክትና ከሰዎች ይልቅ የተመረጠሸ ማርያም ሆይ መታሰቢያሽን በብርቱ መታመን ያደረገ በመንግሥተ ሰማይ ካንቺ ጋር ይነግሣል) በማለት አወድሰዋታል፡፡
💥 እኛም በረከቷ ይደርብን ጸሎቷ ይጠብቀን፡፡
✍️ መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ