Tocha Construction & Industrial College

Contact the university

Tocha Construction & Industrial College Training

15/04/2023

እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ በአል በሰላም አደረሳችሁ።

ዛሬ በቶጫ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ  በ6 ወር ሥራ አፈፃፀም ግብረመልስ ዙሪያ እና በሶስተኛ ሩብ ዓመት ሥራ አፈፃፀም ዙሪያ ከዞን ክህሎትና ቴክኖሎጂ መምሪያ እና ከኮሌጁ ማኔጅመን...
12/04/2023

ዛሬ በቶጫ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በ6 ወር ሥራ አፈፃፀም ግብረመልስ ዙሪያ እና በሶስተኛ ሩብ ዓመት ሥራ አፈፃፀም ዙሪያ ከዞን ክህሎትና ቴክኖሎጂ መምሪያ እና ከኮሌጁ ማኔጅመንት አባለት ጋር ውይይት ተካሂዱዋል።
ውይይቱን የመሩት የመምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ አድሴ ዘለቀ እና የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ጌድዮን ኤርሚያስ ሲሆኑ በመምሪያ ልመት ዕቅድ ባለሙያ በሆኑት ወ/ሮ አበዛሽ ኩራቱ የኮሌጁ 6 ወር ሥራ አፈፃፀም ግብረ መልስ ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በኮሌጁ በጠንካራ ጎን የታዩትን ለማስቀጠልና መሻሻል ባለባቸው ጉዳዮች ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጡዋል።
በውይይት ወቅት በርካታ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን
በዋናነት:-@ግንባታን በተመለከተ የክልሉ መንግስት ትኩረት አንዲሰጥ እንዲደረግ።
@አሁን ካለው አድስ ቅበላ ጋር ተያይዞ የተመዘገቡ ሰልጣኞች ቁጥር በዚህ ዓመት እንደኮሌጅ ከፍ ያለ ስለሆነ የአሰልጣኝ ቅጥር እና አድስ የሙያ መስመር የሚፈቀድበት ሁነታ እንዲመቻች።
@አሁን ባለው ሁነታ ከነውስንነቱም ቢሆን ወደ አድሱ ግቢ የተገባ ስለሆነ ለግቢ የጥበቃ ሠራተኛ እጥረት እና አትክልተኛ የለሌ ስለሆነ የሚፈቀድበት ሁነታ እንዲመቻች።
@በመምሪያ በኩል ኮሌጁ ወደፊት የሚደገፊበት ሁነታና የኮሌጁ ሰራተኞች ልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበት ሂደት ቢፈጠር የሚሉ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን በአጠቃላይ የዛሬ ዓይነት ውይይት በኮሌጁና በመምሪያ መካከል ሲደረግ የመጀመሪያ በመሆኑ የተሳካ እና ቀጣይ በጋራ ለሚሰሩ ስራዎች ብዙ ግብአት ያስገኘ እንደሆኔ የኮሌጁ ዲን የሆኑት አቶ ጌድዮን ኤርሚያስ ገልፀዋል።
በመጨረሻም ግቢ ያለበት ነባራዊ ሁነታ ጉብኝት ተደርጎ ውይይቱ ተጠናቅቁዋል።

የቶጫ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ለኮሌጁ አሰልጣኛች፣ ሰራተኞችና ለኮሌጁ ሰልጣኞች እንዲሁም ለመላዉ የኢትዮጲያ ህዝብ በሙሉ እንኳን ለ2015 ዓ.ም ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ...
05/01/2023

የቶጫ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
ለኮሌጁ አሰልጣኛች፣ ሰራተኞችና ለኮሌጁ ሰልጣኞች እንዲሁም ለመላዉ የኢትዮጲያ ህዝብ በሙሉ እንኳን ለ2015 ዓ.ም ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡
በዓሉ የሰላም ፣ የጤናና የብልፅግና ይሁንላችሁ።

የኮሌጃችን የ2015 ዓ፡ም 1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም የዳውሮ ዞን ክህሎትና ቴክኖሎጂ መምሪያ ም/ሀላፊ  የወረዳ አስ/ርና የቦርድ ሰብሳቢ የወረዳው ክህሎትና ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ሀላፊየወረዳው ኢን...
11/11/2022

የኮሌጃችን የ2015 ዓ፡ም 1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም
የዳውሮ ዞን ክህሎትና ቴክኖሎጂ መምሪያ ም/ሀላፊ
የወረዳ አስ/ርና የቦርድ ሰብሳቢ
የወረዳው ክህሎትና ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ሀላፊ
የወረዳው ኢን/ዝና ኢንዱስትሪ ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ እና አጠቃላይ የኮሌጁ ሠራተኞች በተገኙበት ገምግመናል።

24/10/2022
የቶጫ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የ2015 ዓ.ም ስልጠና ማስጀመሪያ እና የአዲስ ሠራተኞች ትውውቅ መድረክና እንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮግራም ጥቅምት 14 2015 ዓ.ም ተካሄደ።ኮሌጃች...
24/10/2022

የቶጫ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የ2015 ዓ.ም ስልጠና ማስጀመሪያ እና የአዲስ ሠራተኞች ትውውቅ መድረክና እንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮግራም ጥቅምት 14 2015 ዓ.ም ተካሄደ።

ኮሌጃችን ያለውን የስልጠና መስክና ስልጠና ሙያን ለማስፋፋት ኮሌጁ የሚያሰለጥናቸውን ሙያ ዘርፍ ለማስፋፋት በ2015 ዓ.ም ተጨማሪ አሠልጣኛችን መቅጠሩ ይታወቃል። አዲስ የተቀጠሩት አሰልጣኞች በኮሌጁ ሲሰጡ ለነበሩ ዲፓርትመንት ተጨማሪ አሰልጣኝ ና እንዲሁም አካባቢው ካለው ዘጋና ሃብት/resource / ለመጠቀም አዳዲስ ዲፓርትመንት ለመክፈት አዲስ አሠልጣኞችን ቀጥሯል።
በውይይት መድረክ አዲስ ለተቀጠሩ አሰልጣኞች በጥቅምት 14/2015 ዓ.ም ከኮሌጁ ማህበረሰብና ከነባር አሠልጣኞች ጋር ትዉዉቅ መድረክና እንዲሁም ስለ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ግንዛቤ የቴክኒክና ሙያ ዓላማ :ራዕይና ተልዕኮ በተመለከተ የግንዛቤ መፍጠሪያ ሰነድ በኮሌጁ ዲን አቶ ጌዲዮን ኤርሚያስ በኩል የተሰጠ ሲሆን የ2015 ዓ.ም ስልጠና ስራ በይፋ እንዲጀመር ተደርጓል።
በኮሌጁ ከተቀጠሩት አዲስ አሰልጣኞች መካከል
በእንጨት ስራ/Furniture Making/ ኢንስትራክተር ተስፋዬ እንደተናገሩት በኮሌጁ ማህበረሰብና አሰልጣኞች የተደረገዉን እንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮግራም መደሰታቸዉንና ስለቴክኒክና ሙያ ስልጠና የተሰጠዉ ግንዛቤ ጥሩና ወደፊት ለማሰለጥነው ሙያ ዘርፍ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። እንዲሁም ኮሌጁ ያለበት አካባቢ በተፈጥሮ በቀርካሃ እንጨት በስፋት ያለበትና ምንም ያልተሰራበትና በዚህ አካባቢ ማህበረሰቡንና ለወጣቶች በቀካርሃ ስራ በማደራጀትና በመስራት የኑሮ ሁኔታን በማሻሻል የተሻለ ገቢ ማግኘትና የሀገራችንን ኢኮኖሚ ወደ ተሻለ የደረጃ እድገት ከፍ ለማድረግ ያግዛል ብለዋል።

01/07/2022

ማስታወቂያ

https://t.me/TochaTVETour telegram pageplease join it.
11/06/2022

https://t.me/TochaTVET
our telegram page
please join it.

use for only Tocha construction and lndustrial college workers

Address

Mi`irab Abaya

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tocha Construction & Industrial College posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Tocha Construction & Industrial College:

Shortcuts

Share