Mizan Agricultural TVET College/የሚዛን ግ/ቴ/ሙ/ስ/ኮሌጅ ፌስቡክ ገፅ

  • Home
  • Mizan Agricultural TVET College/የሚዛን ግ/ቴ/ሙ/ስ/ኮሌጅ ፌስቡክ ገፅ
Call Website Contact the university

Mizan Agricultural TVET College/የሚዛን ግ/ቴ/ሙ/ስ/ኮሌጅ ፌስቡክ ገፅ Agricultural skills Training

ለሚዛን እና አከባቢዋ ነዋሪዎች በሙሉ የሚዛን ግ/ቴ/ሙ/ስ /ኮሌጅ ለስጋ የሚሆኑ ዶሮዎችን በመሸጥ ላይ ይገኛል።ስለዚህ መግዛት የምትፈልጉ አካላትም በኒያላ ግቢ ውስጥ በመገኘት ግዥ መፈፀም የ...
17/08/2026

ለሚዛን እና አከባቢዋ ነዋሪዎች በሙሉ የሚዛን ግ/ቴ/ሙ/ስ /ኮሌጅ ለስጋ የሚሆኑ ዶሮዎችን በመሸጥ ላይ ይገኛል።ስለዚህ መግዛት የምትፈልጉ አካላትም በኒያላ ግቢ ውስጥ በመገኘት ግዥ መፈፀም የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን ።

በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት  የሚዛን ቅርንጫፍ  ፅ/ቤት " ዕምርታ  በስታቲስቲክስ  ልማት" በሚል መሪ ቃል  ለሠራተኞች በሚዛን ግ/ቴ/ሙ/ስ/ኮሌጅ ስልጠና ተሰጥቷል። በስልጠናው  ላይ...
12/08/2026

በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የሚዛን ቅርንጫፍ ፅ/ቤት " ዕምርታ በስታቲስቲክስ ልማት" በሚል መሪ ቃል ለሠራተኞች በሚዛን ግ/ቴ/ሙ/ስ/ኮሌጅ ስልጠና ተሰጥቷል።

በስልጠናው ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ካሳሁን ናይክን በተቋማዊ ዕድገት ምልከታ ውስጥ የአመራርም ሆነ የፈፃሚ ውጤታማነት ዕውን የሚሆነው በተጠናከረና በተደመረ አቅም የሚከናወኑ ተግባራት የላቀ ፋይዳና ዕሴት ያላቸው መሆኑን ገልፀዋል።

የሚዛን አማን ስታቲስቲክስ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ሽመልስ መጂቶ ተቋማችን ከመሰል ዓለም አቀፍ የስታቲስቲክስ ተቋማት ጋር ያለውን ተወዳዳሪነትና እኩል የመራመድ አቅም በማሳደግ የስታቲስቲክስ ልማት አቅጣጫ በውል በመገንዘብ በጋራ፣ በአንድነት ለመተግበር የተሟላ ግንዛቤና ዕውቀት እንዲኖረን የሚያስችለን ስልጠና በመሆኑ ሰልጣኞች ስልጠናውን በትኩረትና በዲሲፕሊን በመከታተል ለቀጣይ ተልዕኮ ራሳቸውን ማዘጋጃት እንደሚጠበቅባችው የስራ መመሪያ በመስጠት ስልጠናውን አስጀምረዋል።

የቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ አክለውም ሥልጠናዉ በዲጂታል መረጃ አሰባሰብ ሂደት ላይ የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማጎልበት፣ ከ2019 እስከ 2021 ዓ.ም. ለሚተገበረው አዲስ ስትራቴጂክ ዕቅድ ሠራተኛውንና የመስክ መረጃ ሰብሳቢዎችን በዕውቀትና በሥነ-ምግባር ለማዘጋጀት ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር አብራርተዋል።

ስልጠናውም ከነሐሴ 4_6/2018 ዓ.ም በቅ/ጽ/ቤቱ ለሚገኙ ለ 70 ሠራተኞች በሰፊው ገለፃ የተደረገላቸው ሲሆን ስልጠናውም የሠራተኞችን የእውቀትና ክህሎት ልማት ያሳድጋል ተብሎ ይጠበቃል ።

ለወቅታዊና ትኩስ መረጃ

Official website:- https://www.mizan-atvet.edu.et/
Facebook:- http://www.facebook.com/mizan.atvet.facebook
Telegram:-
https://t.me/mizanatvt ይጎብኙ ።

የህዝብ ግንኙነት ስራ አሰፈፃሚ
ነሀሴ 06 : 2018

አረንጓዴ አሻራ ከፌደራል ስራና ክህሎት ከመጡ ከፍተኛ አመራሮች እና ከቤንች ሸኮ ዞን  አመራሮች ጋር በመቀናጀት "ተስፋን እንትከል " በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀንበር ሲከናወን በዋለው የችግኝ...
03/08/2026

አረንጓዴ አሻራ ከፌደራል ስራና ክህሎት ከመጡ ከፍተኛ አመራሮች እና ከቤንች ሸኮ ዞን አመራሮች ጋር በመቀናጀት "ተስፋን እንትከል " በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀንበር ሲከናወን በዋለው የችግኝ ተከላ መረሀ ግብር ከ10.000 በላይ ችግኞች ተተክለዋል ።

በዕለቱም የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ዶክተር አብይ አንደሞ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም በጎ ስራ የዛሬን ህይወት እንደሚያሻሽል እና የነገን ትውልድንም እንድሚገነባ ተናግረዋል ።

የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩም እንደተጠናቀቀም በሚዛን ግ/ ቴ/ሙ/ስ/ኮሌጅ ውስጥ እየተገነቡ የሚገኙትን የለውጥ ስራ እና የልማት ስራዎች ላይ የመስክ ምልከታ ተካሂዷል ።

በመጨረሻም በዛሬው ዕለት ተገኝተው ይህ ታላቅ ስኬት እውን እንዲሆን የራሳቸውን አሻራ ላስቀመጡ የተለያዩ አመራሮች እና ነዋሪዎችም ምስጋና አቅርበዋል ።

አስደሳች ዜና ለሚዛንና አከባቢዋ ማህበረሰብ በሙሉ ፦የሚዛን ግብርና ቴክኒክ ሙያ ስልጠና ኮሌጅ  ያፈላቸውን የተለያዩ የቡና ችግኝ ዝርያዎች፣ የደን ችግኞች   በተመጣጣኝ ዋጋ  መሸጥ ስለሚፈል...
20/07/2026

አስደሳች ዜና ለሚዛንና አከባቢዋ ማህበረሰብ በሙሉ ፦
የሚዛን ግብርና ቴክኒክ ሙያ ስልጠና ኮሌጅ ያፈላቸውን የተለያዩ የቡና ችግኝ ዝርያዎች፣ የደን ችግኞች በተመጣጣኝ ዋጋ መሸጥ ስለሚፈልግ ማንኛውም ግለስብ/ድርጅቶች በማስታወቂያው መሠረት ከተጠቀሰበት ቀን ጀምሮ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን ፡፡

የሚዛን ግ/ቴ /ሙ/ሥ/ኮሌጅ  ለተቋሙ  አመራሮች   በFuture   Thinking  and strategic  foresight , በአመራርነት እንዲሁም   በስነምግባራዊ ውሳኔ አሰጣት ዙሪያ  ስ...
04/07/2026

የሚዛን ግ/ቴ /ሙ/ሥ/ኮሌጅ ለተቋሙ አመራሮች በFuture Thinking and strategic foresight , በአመራርነት እንዲሁም በስነምግባራዊ ውሳኔ አሰጣት ዙሪያ ስልጠና ተሰቷል።

በመጀመሪያ ምዕራፍ ላይ የኮሌጅ ዲን አቶ ካሳሁን ናይክን በ future thinking and strategic foresight እና አጠቃላይ ተቋምን የማዘመን ርዕስ ጉዳይ ዙሪያ ላይ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን በተቋማችን ውስጥ የዕለት ተዕለት ስራዎችን ብቻ ከመስራት ባለፈ ተቋሙ በአጠቃላይ እንዴት እየታጓዘ እንደሆነ እንዲሁም ዓለም ላይ በቴክኖሎጂ በፖለቲካ በኢኮኖሚ የሚታዩ የለውጥ ምልክቶችን በማንበብ ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ የተለያዩ ሁነቶችን (Scenarios) አስቀድሞ በመተንተን፣ ዛሬ ላይ ሊወሰዱ የሚገባቸውን ስልታዊ ውሳኔዎች መቅረፅ አስፈላጊ ነው ብለዋል ።

ይህ አካሄድ በአንድ ወጥ እቅድ ላይ ብቻ ከመንጠልጠል ይልቅ፣ ተለዋዋጭ የሆኑ አማራጭ መንገዶችን ዝግጁ ማድረግ ተገቢ እንደሆነ አስቀምጠዋል ።

የኮሌጅ አስተዳደር ዘርፍ ም/ዲን እንደገለጹት በኮሌጁ በአዲሱ መዋቅር የተመደቡ አመራሮች ወደ ስራ ከተሰማሩ ጀምሮ የአመራርነት ብቃትና አቅምን ለማሳደግ የሚያስችል ስልጠና ለመስጠት በተዘጋጀው መድረክ ላይ በንቃት በመሳተፍ የተቋሙን መልካም አፈጻጸሞችን ለማስቀጠልና በቅጣይ የተሻለ እውቀትን በመውሰድ ለውጥ ለማምጣት የጋራ ግንዛቤ እንዲኖር ለማድረግ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ገልጸዋል።

የተቋሙ ስራ አስፈጻሚዎችና አመራሮች አሁን ላይ እያደረጉት ያለውን መነቃቃትና እንቅስቃሴ መልካም መሆኑን ገልጸው በኮሌጁ ውስጥ ያለንን አቅም በመጠቀም በተሻለ መልኩ ለመስራት እና የአመራር ስርአታችን ይበልጥ ለማሳደግ እንድንችል የአመራር ክህሎት ስልጠና በመዘጋጀቱ የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ ሰልጣኞች በተጨማሪ ራሳቸውን ለማብቃት መጣር እንደሚያስፈልግ እና ይህም ለኮሌጁ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል ።

በሶስተኛውም ምዕራፍ በኮሌጁ የስነምግባር መከታተያ ስራ አስፈፃሚ በስነ ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ እና የጥቅም ግጭት መከላከልና ማስተዳደር የቀረበ ሲሆን በኮሌጁ አመራሮች ዘንድ የስነ ምግባር ዕሴቶችን በማስረፅ የጥቅም ግጭቶችን በአግባቡ ለማስተዳደር ትልቅ አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል ።

ስልጠናውም እንደተጠናቀቀ በኮሌጁ እና በሲፍ ፕሮጀክት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች በኮሌጅ አመራሮች ምልከታ ተካሂዷዋል።

ለወቅታዊ ትኩስ መረጃ
Official website:- https://www.mizan-atvet.edu.et/
Facebook:- http://www.facebook.com/mizan.atvet.facebook
Telegram:-
https://t.me/mizanatvt

የህዝብ ግንኙነት ስራ አሰፈፃሚ
ሰኔ : 22/2018

26/05/2026
የሚዛን ግብርና ቴ/ሙ/ስ/ኮሌጅ በደረጃ IV  ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞች አሰመረቀ  ።  🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓ኮሌጁ በሰብል ልማት፣ በእንስሳት ሳይንስ  እና ...
23/05/2026

የሚዛን ግብርና ቴ/ሙ/ስ/ኮሌጅ በደረጃ IV ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞች አሰመረቀ ።

🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓
ኮሌጁ በሰብል ልማት፣ በእንስሳት ሳይንስ እና ተፈጥሮ ሀብት ያሰለጠናቸውን በመደበኛ 327 በቅዳሜና እሁድ ፕሮግራም 172 በድምሩ 499 ሰልጣኞችን ዛሬ ግንቦት15/2018 ዓ.ም አስመረቀ።

በምረቃ ሰነ ሥርዓቱ ላይ የፌደራል ስራና ክህሎት ሚ/ር አመራሮች : የኮሌጁ ከፍተኛ አመራሮች፣ የአስተዳደር ሠራተኞች መምህራንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

የኮሌጁ ዲን አቶ ካሳሁን ናይክን በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት እንግዶችን እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ ከብዙ ልፋትና ጥረት በኋላ ለዛሬ ቀን ስለበቃችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለው። በሀገራችን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የአንበሳውን ድርሻ የምትወጡት እናንተ ስለሆናችሁ የተጣለባችሁን ከፍተኛ ሀላፊነት እንድትወጡ አደራ እላለሁ ብለዋል ።

እንደ ዲኑ ገለፃ ኮሌጁ ከመማር ማስተማር ባሻገር ገቢውን ለማሳደግ የእንተርፕራይዝ ስራዎችን በመስራት የአከባቢውን ማህበረሰብ ችግሮች መፍትሔ ማፈላለግ፣ ለሀገራዊ ፖሊሲ ጠቃሚ ጥቆማዎችና ሳይንሳዊ ግኝቶችን ማቀበል፣ ፕሮጀክቶች ቀርጾ የማኅበረሰብ ጉድኝት ሥራዎች መተግበርን በትኩረት እያከናወነ ይገኛል፡፡

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጸጵያ ክልል የፍይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ሀላፊ ተመራቂዎችን እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።

አክለውም እናንተ የዛሬ ተመራቂዎች ለሀገራችሁ ልማትና እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላችሁ በመሆኑ ተግታችሁ እንድትሰሩ ሲሉ አሳስበዋል።

በስራና ክህሎት ሚንስቴር የቴክኒክና ሙያ መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት የተከበሩ አቶ ጌታቸው ደምሴ በበኩላቸው ተመራቂዎችን እንኳን ደስ ያላችሁ ካሉ በኋላ የወደፊት የስራ አቅጣጫ በመስጠት አጠቃለዋል።

በምረቃ መርሐ ግብሩ ከእንስሳት ሳይንስ 3.98 በማምጣት ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበው ተማሪ አለማየሁ አርቸቦ የወርቅ ሜዳሊያ የተሸለመ ሲሆን በ3.8 ውጤት ከኮሌጁ ከፍተኛ ውጤት ያመጣችው ሴት ምሩቅ ቅድስት ደመቀ ጋንታ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ለወቅታዊ ትኩስ መረጃ
Official website:- https://www.mizan-atvet.edu.et/
Facebook:- http://www.facebook.com/mizan.atvet.facebook
Telegram:-
https://t.me/mizanatvt

ግንቦት 15/2018 ዓ.ም
የኮሌጁ ህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ

21/05/2026
የሚዛን ግ/ቴ/ሙ/ስ/ኮሌጅ  ለአዲስ እና ለነባር አሰልጣኝ መምህራን የማስተማር   ስነ ዘዴ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል ።ስልጠናውን አስመልክቶ የኮሌጁ ዲን አቶ ካሳሁን ናይክን የመክፈቻ ን...
09/05/2026

የሚዛን ግ/ቴ/ሙ/ስ/ኮሌጅ ለአዲስ እና ለነባር አሰልጣኝ መምህራን የማስተማር ስነ ዘዴ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል ።

ስልጠናውን አስመልክቶ የኮሌጁ ዲን አቶ ካሳሁን ናይክን የመክፈቻ ንግግር ያድረጉ ሲሆን ስልጠናው የመምህራንን ክህሎት ልማት የሚያሳድግና አጠቃላይ እንደሀገር የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅ ረገድ የማይተካ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡

በንግግራቸውም ተቋማችንም የግብርና ተቋም እንደመሆኑ መጠን ውጤታማ የመማር ማስተማር ስነ ዘዴ ከሚከናወንባቸው መንገዶች አንዱና ዋነኛው ተግባር ተኮር የማስተማር ስነዘዴን ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡

በተጨማሪም የኮሌጅ ስልጠና ዘርፍ ምክትል ዲን የሆኑት ወ/ሮ ብዙአየው ታሪኩ እንደገለፁት ሰልጣኝ መምህራን ተግባር ተኮር ማስተማር ስነ-ዘዴ ተጠቅመው ሲያስተምሩ የሰልጣኞችን የትምህርት ውጤት ከማሳደጉም በላይ ሰልጣኞች እራሳቸውን በመማር ማስተማር ሂደት ዋነኛ ተዋናይ እንዲሆኑም ያደርጋል፡፡

ይህም የሰልጣኙን ተፈጥሮዊ ዕምቅ ኃይል በማልማት በወደፊት የህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ሊገጥሙ የሚችሉ ችግሮችን በመጋፈጥ ችግሮችን በሳይንሳዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል ዕውቀት ፣ክህሎትና ችሎታ ከወዲሁ እንዲኖራቸውም ያስችላቸዋል።

ስልጠናውም የመማር ማስተማሩን ስራ ስኬታማ በማድረግ የሰልጣኞቹን ውጤት በላቀ ደረጃ ለማሻሻል ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል ፡፡

ለወቅታዊ ትኩስ መረጃ
Official website:- https://www.mizan-atvet.edu.et/
Facebook:- http://www.facebook.com/mizan.atvet.facebook
Telegram:-
https://t.me/mizanatvt

የህዝብ ግንኙነት ስራ አሰፈፃሚ
ሚያዝያ : 30/2018

የሚዛን ግብርና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ የISO 21001 :2018 (Educational  organazational Managment System) ትግበራን በይፋ አስጀመረ ።           ...
01/05/2026

የሚዛን ግብርና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ የISO 21001 :2018 (Educational organazational Managment System) ትግበራን በይፋ አስጀመረ ።
****
የሚዛን ግብርና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ የአገልግሎት አሰጣጡን ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችለውን የቴክኒክ ድጋፍ ስምምነት ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር ተፈራርሞ ከተቋሙ ከተለያዪ ስራ ክፍሎች ለተወጣጡ አባላት(Task force) በሰነድ ዝግጅት ዙሪያ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል ።

የኮሌጁ ዲን አቶ ካሳሁን ናይክን እንደገለጹት፣ የትምህርት ጥራት ማኔጅመንት ሥርዓትን መተግበር ተቋሙ የተገልጋይ እርካታን በተጨባጭ እንዲያረጋግጥ ከመርዳቱም በላይ ተቋሙ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆንም ያስችለዋልም ብለዋል።

በተያዘው በጀት ዓመትም ኮሌጁ የትምህርት ጥራት ሥራ አመራር ስርዓት ማረጋገጫ ባለቤት ለማድረግ ዝግጅቶች ተጠናቅቀው ወደ ሰነድ ዝግጅት ምዕራፍ መገባቱን የተቋሙ ማኔጅመንት ሪፕረዘንቴቲቭ የሆኑት ወ/ሮ ብዙአየሁ ታሪኩ ገልፀዋል።

Official website:- https://www.mizan-atvet.edu.et/
Facebook:- http://www.facebook.com/mizan.atvet.facebook
Telegram:-
https://t.me/mizanatvt

የህዝብ ግንኙነት ስራ አሰፈፃሚ
ሚያዝያ : 21/2018 ዓ.ም

Address

Mizan Teferi

0

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mizan Agricultural TVET College/የሚዛን ግ/ቴ/ሙ/ስ/ኮሌጅ ፌስቡክ ገፅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Mizan Agricultural TVET College/የሚዛን ግ/ቴ/ሙ/ስ/ኮሌጅ ፌስቡክ ገፅ:

Shortcuts

  • Want your university to be the top-listed university?

Share