ድጎ ጽዮን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ Digo Tsion TVT College

  • Home
  • Ethiopia
  • Motta
  • ድጎ ጽዮን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ Digo Tsion TVT College
Website Contact the university

ድጎ ጽዮን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ Digo Tsion TVT College Everyone has a role in quality TVT training!!!

📢የነባር ሰልጣኞች ያለ ቅጣት ምዝገባ 2ቀናት ብቻ ቀሩት።ውድ ነባር ሰልጣኞቻችን የጀመራችሁትን የሙያ ጉዞ በትጋት፣ በስልጠና ተግታችሁ እና በተግባር ልምምድ በማጠናከር ወደ ስኬት እንድትደርሱ...
24/09/2026

📢የነባር ሰልጣኞች ያለ ቅጣት ምዝገባ 2ቀናት ብቻ ቀሩት።

ውድ ነባር ሰልጣኞቻችን የጀመራችሁትን የሙያ ጉዞ በትጋት፣ በስልጠና ተግታችሁ እና በተግባር ልምምድ በማጠናከር ወደ ስኬት እንድትደርሱ ኮሌጃችሁ ከጎናችሁ መሆኑን እየገለፅን በማስታወቂያ የተጠቀሱት ቀናት እየተገባደዱ ስለሆነ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን።

📢የአዲስ ሰልጣኞች ምዝገባ በቅርቡ ማስታወቂያ የምናወጣ ይሆናል።

💥 እንኳን ለ2019 በጀት ዓመት የስልጠና ዘመን አደረሳችሁ! 🎂የድጎ-ጽዮን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅእውቀትን ወደ ክህሎት፣ ክህሎትን ወደ ዕድል!ውድ ነባር ሰልጣኞቻችን፣ አዲስ ተመዝጋቢ ሰልጣኞቻች...
16/09/2026

💥 እንኳን ለ2019 በጀት ዓመት የስልጠና ዘመን አደረሳችሁ! 🎂
የድጎ-ጽዮን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ
እውቀትን ወደ ክህሎት፣ ክህሎትን ወደ ዕድል!
ውድ ነባር ሰልጣኞቻችን፣ አዲስ ተመዝጋቢ ሰልጣኞቻችን እና የሙያ ቤተሰባችን፤ እንኳን ለ2019 በጀት ዓመት የስልጠና ዘመን በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!
የአዲሱ የስልጠና ዘመን አዲስ ዕድሎችን፣ አዲስ ህልሞችን እና የተሻለ የስኬት ጉዞን ይዞ መጥቷል።
🎓 ነባር ሰልጣኞቻችን
የጀመራችሁትን የሙያ ጉዞ በትጋት፣ በስልጠና ተግታችሁ እና በተግባር ልምምድ በማጠናከር ወደ ስኬት እንድትደርሱ ኮሌጃችሁ ከጎናችሁ መሆኑን እየገለፅን በማስታወቂያ በተጠቀሱት ቀናት እንድትመዘገቡ እናሳስባለን።
🎉 አዲስ ሰልጣኞቻችን
የሙያ ምርጫችሁን ወደ ተግባራዊ ክህሎት የምትቀይሩበት አዲሱ ጉዞ እዚህ ይጀምራል። ዛሬ የምትማሩት ክህሎት ነገ የራሳችሁን የሥራ ዕድል ለመፍጠር፣ ለሀገራችሁ የተሻለ አስተዋፅኦ ለማበርከት እና የተሻለ ሕይወት ለመገንባት መሠረት ይሆናል።
📢 የምስራች ለሁሉም!
ሙያ ይምረጡ! ክህሎት ይማሩ ወደፊትዎን በራስዎ ይገንቡ!
ወላጆችና የሰልጣኞች ቤተሰቦች፤ ልጆቻችሁ በሥራ ዓለም ተፈላጊ የሆነ ክህሎት እንዲያገኙ ዛሬውኑ የሙያ ትምህርትን ይምረጡ።
የድጎ-ጽዮን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ
የተግባር ስልጠና
🛠️ የሙያ ክህሎት
💡 ፈጠራና ኢኖቬሽን
🚀 ለሥራና ለራስ ሥራ የሚያዘጋጅ ስልጠና
የወደፊትዎን በዛሬው ውሳኔዎ ይገንቡ!
🌟 ድጎ-ጽዮን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ — ክህሎት ለስኬት! 🌟
እንኳን ለ2019 በጀት ዓመት የስልጠና ዘመን አደረሳችሁ!

16/09/2026

Wise use of resources

የሪሚዲያል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲ ቅበላ መቁረጫ ነጥብ2019 ዓ/ም ሪሚዲያል ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ሚኒስቴሩ የሚከተለውን መቁረጫ ነጥብ ይፋ አደረ፡ዋናው መቁረጫ ነጥብ (ከ600...
14/09/2026

የሪሚዲያል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲ ቅበላ መቁረጫ ነጥብ

2019 ዓ/ም ሪሚዲያል ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ሚኒስቴሩ የሚከተለውን መቁረጫ ነጥብ ይፋ አደረ፡

ዋናው መቁረጫ ነጥብ (ከ600)
1. ተፈጥሮ/ማህበራዊ ሳይንስ ወንዶች፡ 240 (40%)
2. ተፈጥሮ/ማህበራዊ ሳይንስ ሴቶች፡ 228 (38%)

በልዩ ድጋፍ የሚታይ ምድቦች
1. ከአፋር፣ ሶማሌ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ የሚመጡ ተፈጥሮ/ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች፡ 222 (37%)
2. ከአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር የሚመጡ ተማሪዎች፡ 222 (37%)
3. ማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ ዓይነ ስውሮች፡ ከ500 ውስጥ 185 (37%)
4. ተፈጥሮ/ማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ መስማት የተሳናቸው፡ 222 (37%)

14/09/2026

📢 የነባር ሰልጣኞች የምዝገባ ማስታወቂያ
በቅድሚያ እንኳን ለ2019 ዓ.ም የትምህርትና ሥልጠና ዘመን አደረሳችሁ እያልን፣ የ2019 ዓ.ም የትምህርትና ሥልጠና ዘመን ምዝገባ የሚካሄደው ከ04/01/2019 ዓ.ም እስከ 15/01/2019 ዓ.ም ድረስ ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት ብቻ መሆኑን አውቃችሁ የ3 ወር የወጭ መጋራት ክፍያ በፀደይ ባንክ በመክፈል ሬጅስትራር ፅ/ቤት በአካል በመምጣት ምዝገባ እንድታከናውኑ ኮሌጁ ያሳስባል፡፡
➣ማሳሰቢያ
🌻ለምዝገባ ስትመጡ የወጪ መጋራት ክፍያ ለቀን ሰልጣኞች የሶስት ወራት 450 ብር እና መመዝገቢያ 100 ብር፣ በድምሩ 550 ብር በፀደይ ባንክ መክፈልና ደረሰኝ ማቅረብ እና መመዝገብ ይኖርባችኃል፡፡
🌻ከተጠቀሰው የምዝገባ ቀን ውጭ በቅጣት የምናስተናግድ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
🌻ሥልጠና የሚጀመርበት 18/01/2019 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የኮሌጁ ሬጅስትራር ፅ/ቤት

14/09/2026
🌟🎉 እንኳን ለ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመት አደረሳችሁ! 🎉🌟 እያለን ኮሌጃችን በ2019 ዓመተ ምኅረት ስልጠና የሚሰጥባቸው ሙያዎች፤1. Industrial Development (ኢንዱስትሪ ልማት)...
10/09/2026

🌟🎉 እንኳን ለ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመት አደረሳችሁ! 🎉🌟 እያለን ኮሌጃችን በ2019 ዓመተ ምኅረት ስልጠና የሚሰጥባቸው ሙያዎች፤
1. Industrial Development (ኢንዱስትሪ ልማት)

👗Garment Production (ልብስ ስፌት)
🛌 Wood Work (እንጨት ስራዎች)
⚙️ Machining (ማሽኒግ)
🔩 Mechanics (ሜካኒክስ)
🛷 Welding (ብየዳ)

2. Economic Infrastructure (ኢኮኖሚ መሰረተ-ልማት)

🖥 Web Development & Database Administration (ዌብ ዲቨሎፕመንት እና ዳታቤዝ)
🚗 Automotive (አውቶሞቲቭ )
🎬 Electrical & Electronics (ኤሌክትሪካል እና ኤሌክትሮኒክስ)
🏠 Building Electrical Installation (የሕንፃ ኤሌክትሪክ ገመድ ዝርጋታ)
🏘 Plumbing & Construction Work (ቧንቧ ሥራ እና የግንባታ ሥራዎች)

3. Agriculture (ግብርና)
🥗 Crop Production (የሰብል ልማት) እና
🍚 Animal Production (የእንስሳት እርባታ እርባታ) ሙያዎች መሆናቸውን እየገለፅን🙏 አዲሱ ዓመት
🌻የሰላም
🌻የፍቅር
🌻የጤና
🌻የበረከት እና
🌻 የስኬት
ዓመት ይሁንልን!
✨ አሮጌውን ዓመት በምስጋና፣
✨ አዲሱን በተስፋ፣
✨ መጪውን በእምነት እንቀበል!
በአዲሱን ዓመት
ቤታችን በሰላም፣ ልባችን በደስታ፣
ሕይወታችንንም በበረከት ይሙላ! 🙏❤️
🇪🇹 መልካም አዲስ ዓመት! 🇪🇹
የድጎ-ጽዮን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ

📢 ሰሚ ያጣንበትና ‎መፍትሔ የሚሻ ጉዳይ‎‎በዛሬው የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን የሞባይልና የኢንተርኔት ኔትወርክ እንደ ቅንጦት የሚታይ አገልግሎት አይደለም። ለንግድ፣ ለትምህርት፣ ለጤና፣ ለባንክ...
06/09/2026

📢 ሰሚ ያጣንበትና ‎መፍትሔ የሚሻ ጉዳይ
‎
‎በዛሬው የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን የሞባይልና የኢንተርኔት ኔትወርክ እንደ ቅንጦት የሚታይ አገልግሎት አይደለም። ለንግድ፣ ለትምህርት፣ ለጤና፣ ለባንክና ዲጂታል ክፍያ፣ ለመረጃ ልውውጥና ለማህበራዊ ግንኙነት መሠረታዊ የልማት መሣሪያ ሆኗል።
‎
‎ይሁን እንጅ በምስራቅ ጎጃም ዞን ቢቡኝ ወረዳ በድጎ ፅዮን ከተማ የድጎ-ፅዮን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በ2011 ዓ.ም ከ200 ሽህ ብር በላይ ወጭ በማድረግ ለEthio Telecom ክፍያ ከፍሎ ይጠቀምበት የነበረው የ7G.B ኢንተርኔት ፣ የ05 ቢሮ ስልኮች፣ የቴሌገመድና የፖል መሰረተልማት ላይ በ2015 ዓ.ም መገባደጃ የደረሰውን ዝርፊያና ብልሽት ከዚህ ቀደም ኮሌጁ ክፍያውን ሲከፍል Ethio telecom በገባው ውል መሰረት ጉዳዩን ተከታትሎ አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ሲገባ ይህው እስከዛሬ ሰሚ ጠፍቶ ከነችግራችን 2019 ዓ.ም ልንቀበለው ነው።
ከዚህ በተጨማሪ በወረዳ ባሉ ቀበሌዎች ከዘመኑ የቴሌኮሙኒኬሽን እድገት ጋር የማይመጣጠን የኔትወርክ ችግር እያጋጠማቸው ነው። በወረዳዋ አንዳንድ አካባቢዎች ያለው አገልግሎት ከ2G&3G ደረጃ እንኳን በተግባር የማይጠቅም እስኪመስል ድረስ ደካማ መሆኑ የሕብረተሰቡን ዕለታዊ ኑሮ እየጎዳ ነው።
‎
‎ይህን ችግር በሳይንሳዊ የኔትወርክ አስተዳደር አንፃር ስንመለከተው፣ የሲግናል ሽፋን (coverage) ብቻ መኖሩ በቂ አይደለም። የሲግናል ጥንካሬ፣ የኔትወርክ አቅም (capacity)፣ የዳታ ፍጥነት፣ የጥሪ ጥራት፣ የኔትወርክ መቋረጥ መጠንና በአንድ ጊዜ የሚጠቀሙ ደንበኞች ብዛት በሙያዊ መንገድ መመዘን ያስፈልጋል።
‎
‎በተለይ በንግድ ስራ የተሰማሩ ነዋሪዎች እና ተቋማት የተሻለ ዲጂታል ግንኙነት ማግኘታቸው ለአምራቾች፣ ለነጋዴዎች፣ ለሠራተኞችና ለአካባቢው ኢኮኖሚ እድገት ቀጥተኛ ጠቀሜታ አለው።
‎
‎ከዚህም በላይ ደንበኞች ለድምፅና ለዳታ አገልግሎት ገንዘብ ከፍለው ፓኬጅ ከገዙ በኋላ፣ በቂ ኔትወርክ ባለመኖሩ ሳይጠቀሙበት የገዙት ፓኬጅ ጊዜው የሚያልቅበት ሁኔታ በቁም ነገር ሊታይ ይገባል። ክፍያ እየተቀበሉ በተመጣጣኝ ጥራት አገልግሎት አለመስጠት የደንበኞችን እምነት ይጎዳል።
‎
‎ስለዚህ ለኢትዮ ቴሌኮም የዲስትሪክት ኃላፊዎች፣ የክልልና የፌዴራል የዘረፍ አመራሮች፣ የምስራቅ ጎጃም ዞን ስራና ክህሎት መምራያ እና የአብክመ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊዎች የኮሌጁን የዓመታት ጥያቄ ጀሮ ሰጥቶ በመስማትና ችግሩን በውል በመረዳት ጥያቂያችን እንድትፈቱልን እየገለፅን የዘርፉ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች
በአካባቢው የቴክኒክ የመስክ ጥናት (network survey) እንዲካሄድ፣ የአንቴናና የቤዝ ስቴሽን ሽፋን እንዲገመገም፣ የደንበኞች ብዛትና የዳታ ፍላጎት እንዲለካ፣ በቅርቡ የተገነባው ተጨማሪ የቴሌኮም መሠረተ ልማት (4G )የተሻለ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ እየሰጠ ስላልሆነ እንዲታይ።
‎
‎በየደረጃው ያላችሁ አመራሮችም ጉዳዩን እንደ ተራ የስልክና ኢንተርኔት ችግር ሳይሆን እንደ አንድ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በዚህ በቴክኖሎጅ ዘመን በኮሌጁ የመረጃና ሪፖርት ልውውጥ፣ የመደበኛ ሰልጣኞች የሲስተም ምዝገባ፣ የቴክኖሎጅና ፈጠራ ተግባራት እና በዲጅታል ስራዎቻችን ላይ የሚያደረሰውን ከፍተኛ ችግር በመመልከት ከኢትዮ ቴሌኮምና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በተቋማዊና በዲፕሎማሲያዊ አካሄድ በመነጋገር ዘላቂ መፍትሔ እንዲመጣ ጠንካራ ስራና ክትትል ሊያደርጉ ይገባል።
‎
ኮሌጁም ሆነ የወረዳው ‎ሕብረተሰቡ ልመና አያቀርብም፤ ለከፈለበት በቂ አገልግሎት የማግኘት መብት አለው።

ድጎ ጽዮን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ
01/13/2018ዓ.ም
ድጎ-ጽዮን

የድጎ-ፅዮን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በቅድሚያ እንኳን ለ2019 ዓ.ም የስልጠና ዘመን አደረሳችሁ እያለ በ2019 ዓ.ም የስልጠና ዘመን በልዩ ልዩ የስልጠና ሙያዎችና የሰልጠና መረሐ ግብሮች መደበ...
04/09/2026

የድጎ-ፅዮን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በቅድሚያ እንኳን ለ2019 ዓ.ም የስልጠና ዘመን አደረሳችሁ እያለ በ2019 ዓ.ም የስልጠና ዘመን በልዩ ልዩ የስልጠና ሙያዎችና የሰልጠና መረሐ ግብሮች መደበኛና አጫጭር ሰልጣኞችን ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚሂ በታች በተዘረዘሩት ሙያዎች በቀጣይ በምናወጣው የመደበኛ ሰልጣኞች የምዝገባ ማስታወቂያ መሰረት የምናስተናግድ መሆኑን ስንገልፅልዎ በታላቅ ደስታ ነው።
1. Industrial Development (ኢንዱስትሪ ልማት)

➣Garment Production (ልብስ ስፌት)

➣Wood Work (እንጨት ስራዎች)

➣Machining (ማሽኒግ)

➣Mechanics (መካኒክስ)

2. Economic Infrastructure (ኢኮኖሚ መሰረተ-ልማት)

➣Web Development & Database Administration (ዌብ ዲቨሎፕመንት እና ዳታቤዝ)

➣Automotive (ኦቶሞቲቭ )

➣Electrical & Electronics (ኤሌክትሪካል እና ኤሌክትሮኒክስ)

➣Building Electrical Installation (የሕንፃ ኤሌክትሪክ ገመድ ዝርጋታ)

➣Plumbing & Construction Work (ቧንቧ ሥራ እና የግንባታ ሥራዎች)

3. Agriculture (ግብርና)

➣Crop Production (የሰብል ልማት)

➣Animal Production (የእንስሳት እርባታ እርባታ)

🛠 ወደ ኮሌጃችን ጎራ ብለው የሙያ ባለቤት በመሆን ወደፊት ዕድልዎን አሁኑኑ ይወሰኑ::

02/09/2026

Address

Debre Markos Erbu Gebiya Wabirr Digotsion Woynwuha Motta
Motta

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ድጎ ጽዮን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ Digo Tsion TVT College posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to ድጎ ጽዮን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ Digo Tsion TVT College:

Shortcuts

Share