አለም አቀፍ ትምህርት ነክ መረጃዎች Global Education informations

  • Home
  • Ethiopia
  • Sebeta
  • አለም አቀፍ ትምህርት ነክ መረጃዎች Global Education informations

አለም አቀፍ ትምህርት ነክ መረጃዎች Global Education informations ለትምህርት ጥራት አበክረን እንሰራለን
(2)

"ትምህርት ገንዘብ ዝም ብሎ የሚሰበሰብበት ተራ ንግድ አይደለም!" አሉ ዶ/ር ነገሬ ሌንጮበኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ላይ የተጋረጠው የጥራት ቀውስ እና በመንግሥት ቁጥጥርና በግል ተቋ...
19/08/2026

"ትምህርት ገንዘብ ዝም ብሎ የሚሰበሰብበት ተራ ንግድ አይደለም!" አሉ ዶ/ር ነገሬ ሌንጮ

በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ላይ የተጋረጠው የጥራት ቀውስ እና በመንግሥት ቁጥጥርና በግል ተቋማት ነጻነት መካከል ያለው ፍጥጫ አደባባይ ወጥቷል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዳራሽ ነሐሴ 08 /2018 ዓ.ም የተካሄደው የቋሚ ኮሚቴ ውይይት፣ በዘርፉ ላይ ለዓመታት ታፍነው የቆዩ ቅሬታዎችና የፖሊሲ መገፋፋቶች የፈነዱበት መድረክ ነበር።

ውይይቱን በንግግር የከፈቱት ዶ/ር ነገሬ ሌንጮ፣ ወደ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች ጣታቸውን በመቀሰር መረር ያለ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።

"ትምህርት ገንዘብ ዝም ብሎ የሚሰበሰብበት ተራ ንግድ አይደለም!" ያሉት ሰብሳቢው፣ ዘርፉ ከፍተኛ ኃላፊነትና ተጠያቂነት የሚጠይቅ ስልታዊ ኢንቨስትመንት መሆኑን አስምረውበታል።

እንደ እሳቸው አገላለጽ፣ መንግሥት የሚፈልገው ተቋማት ተዘግተው ሥራ አጥነት እንዲነግስ ሳይሆን፣ "ሰርተፊኬት ብቻ ተሸክሞ የሚዞርና ለሀገር ሸክም የሚሆን ዜጋ" የማፍራቱ ሂደት እንዲቆም ነው። ይህ ንግግር በትርፍ ላይ ብቻ ለሚያተኩሩ ባለሀብቶች የተላከ ግልጽና መራራ መልእክት ይመስላል።

በሌላ በኩል፣ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሞላ ፀጋዬ፣ በመንግሥት በኩል የሚወጡ መመሪያዎች "አሰራሪ ሳይሆኑ አሳሪ" መሆናቸውን በምሬት ገልጸዋል።

ተቋማቱ በዳግም ምዝገባ ወቅት የሚገጥማቸው ፍትሐዊ ያልሆነ መመዘኛ፣ ለመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች የፒ.ኤች.ዲ (PhD) መምህራንን ቅጠሩ የሚለው አስገዳጅ ሕግ፣ እና ስለ ግቢ ስፋትና በግቢ ውስጥ ስለሚኖሩ አገልግሎቶች የተቀመጡት "ጠባብ" መመሪያዎች ዘርፉን አጣብቂኝ ውስጥ ከትተውታል ብለዋል።

"ባንክ በሌለበት ዩኒቨርሲቲው አይታደስም" የሚሉ አይነት ጥብቅ መመሪያዎች ተቋማቱን ለኪሳራና ለሥራ ማቆም እየዳረጓቸው መሆኑን በዝርዝር አቅርበዋል።

የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አህመድ አብተው ግን ለቅሬታዎቹ እጅ አልሰጡም።
መመሪያዎቹ የወጡት ለተቋማቱ ማነቆ ለመሆን ሳይሆን የኢትዮጵያን ተማሪዎች መብት ለማስከበር መሆኑን በጽኑ ተከራክረዋል።

"ተማሪው ጥራት ያለው ትምህርት፣ ቤተ-ሙከራና ቤተ-መጽሐፍት በአቅራቢያው የማግኘት መብት አለው" ያሉት ዳይሬክተሩ፣ የትምህርት ጥራት ላይ ምንም አይነት ድርድር እንደሌለ አሳውቀዋል። ይሁን እንጂ፣ መመሪያዎቹ ከነባራዊ ሁኔታው ጋር እንዲጣጣሙ ዳግም ለመመልከት ዝግጁ መሆናቸውን በመግለጽ ለውይይት በሩን ክፍት አድርገዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ውይይቱ በሁለቱ አካላት መካከል ያለውን ጥርጣሬና የጎሪጥ መተያየት በከፊል የቀነሰ ቢሆንም፣ አሁንም ድረስ "ጥራት" እና "ትርፍ" የሚሉት ሁለት ጽንፎች ሳይታረቁ ቀርተዋል።

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ወደ እውነተኛ የእውቀት ማዕከልነት ይሸጋገራል ወይስ በቁጥጥርና በቅሬታ አዙሪት ውስጥ እንደታሰረ ይቀጥላል? የሚለው ጥያቄ የብዙዎችን ትኩረት እንደሳበ ይገኛል።

ለዓለም አሰፋ

በ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከ80 በመቶና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎችን በአዳሪ ትምህርት ቤቶች ለመቀበል ምዝገባ መጀመሩን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡የአዳሪ ትምህርት ቤቶች የተማሪ ምዝገባ...
19/08/2026

በ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከ80 በመቶና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎችን በአዳሪ ትምህርት ቤቶች ለመቀበል ምዝገባ መጀመሩን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የአዳሪ ትምህርት ቤቶች የተማሪ ምዝገባን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የሚኒስትሩ አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ክንድዬ ገብረሕይወት (ፕ/ር)፤ በ8ኛ ክፍል ከ80 በመቶና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎችን በማወዳደር ምዝገባ የተጀመረ ሲሆን፤ ከገጠራማ እና ከአርብቶ አደር አካባቢዎች ለሚመጡ ተማሪዎች ልዩ ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ምዝገባው በሚኒስቴሩ በይነ-መረብ በኩል ያለምንም ክፍያ እንደሚከናወን ጠቁመው፤ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ውጤታቸውን በፒዲኤፍ (PDF) ስካን በማድረግና የፈተና መለያ (ID) ቁጥራቸውን በመጠቀም ባሉበት ሆነው በመመዝገብ ወደ አዲስ አበባ ሳይመጡ ባሉበት ክልል ሆነው በበይነ-መረብ ፈተናውን ይወስዳሉ ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በአምስት አካባቢዎች (ጂጂጋ፣ ጋምቤላ፣ ቦንጋ፣ ቡኢ እና ወሊሶ) አገልግሎት እየሰጡ ካሉት አራት አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ማለትም በባህር ዳር፣ አርባ ምንጭ፣ ድሬደዋና አሶሳ መቀበል እንደሚጀምሩ ጠቁመዋል፡፡

በሁሉም ክልሎች የተገነቡ 13 የፌደራል አዳሪ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት ሲጀምሩ፣ እያንዳንዱ አዳሪ ትምህርት ቤት እስከ 1,000 ተማሪዎችን በመቀበል በየዓመቱ 13 ሺህ አዳዲስ ተማሪዎችን የማስተናገድ አቅም ይኖራቸዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ለትምህርት ቤቶቹ የሚያስፈልጉ ዳይሬክተሮችና መምህራንም በፌደራል ደረጃ በልዩ ሁኔታ ተመርጠው እየተቀጠሩ ይገኛሉ ሲሉ ገልጸዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፕሮግራሙ ከፍተኛ አገራዊ ሀብት እየፈሰሰበት የሚገኝ በመሆኑ፣ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ብቁ ተማሪዎች የዚህ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ፕሮግራሞች ጥራት ማሻሻል መሪ ስራ አስፈፃሚ ዮሐንስ ኦጋሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች በተግባር የተደገፈ ትምህርት በመስጠት በፈጣራ የጎለበተ ዜጋ እያፈሩ ነው፡፡

"አዳሪ ትምህርት ቤት ላይ የሚማሩ ልጆች መጀመሪያውንም በጣም ጎበዝ፣ ፈጣን የመማር ችሎታና ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ልጆች የሚማሩ በመሆኑ በቀጣይ እነዚህ ልጆች የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው" ብለዋል፡፡

ባለፈው ዓመት በአምስት አዳሪ ትምህርት ቤቶች በእያንዳንዱ 250 ተማሪዎች፣ በአጠቃላይ 1,250 ተማሪዎች የ9ኛ ክፍል ትምህርታቸውን አጠናቀዋል።
(ኢትዮ ፕረስ ድርጅት)

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ለ2019 የትምህርት ዘመን አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ተማሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዷል፡፡ - የክልሉ ትምህርት ቢሮ ለ2019 የትምህርት ዘመን ከቅድመ 1ኛ እስ...
19/08/2026

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ለ2019 የትምህርት ዘመን አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ተማሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዷል፡፡ - የክልሉ ትምህርት ቢሮ

ለ2019 የትምህርት ዘመን ከቅድመ 1ኛ እስከ 2ኛ ደረጃ 992,732 ተማሪዎችን ለመመዝገብ መታቀዱን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አልማው ዘውዴ ገልፀዋል።

በክልሉ የተማሪዎች ምዝገባ ከነሐሴ 18 እስከ ጳጉሜን 05/2018 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑ ተገልጿል፡፡

ወላጆች፣ የትምህርት ባለድርሻ አካላት፣ ማኅበረሰቡ እና ተቋማት ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናት ምዝገባ አድርገው ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲሔዱ የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

19/08/2026

ትምህርት መረጃ/Academic information #ትምህርትመረጃ/academicinformationmoment

19/08/2026

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Tamagne Haile, Wotaro Balta Dana, Dagne Chere, Nigatu Ayele, Mekoro Arega, Markos Oda, Tarekegn Habte, Molla Sugebo, Zelalem Paulos, Kebede Belachew, Biruke Beyene, Wogayehu Woldegiorgis, Sami Tafe, Geletaw Nigus, Kiyya Tamru, Ayano Abera Gage, አለም ነህ, Jemal Drmulo Shafiko, Evana Abenob, Admasu Abebe, Adi Eyayu, Yasie Habtie, Sayid Mahamed, Muzekir Ali Ahmed, Bine Jhon, Mathewos Feleke, Bezabih Fikire, መልካሙ ዘለቀ ኢትዮጵያዊ, Melese Tefera Bunare, Tigist Tesema, Bellachew Bache, Pecoke Gojamaw, Demelew Tadele, Hagos Wele, Afework Wolde, ኢየሱስ ይመጣል, Teramaj Wongel, Sh*taye Yohannis, ሳሙኤል ጫርሻ ጫልቤ ጫጨ, Yigrem Lakew Talargachew, Gizachew Kebede, Biruk Fola, Tokkitti Birqqii, Hanis Haftu Hadera, ዱድያሌብ ነኝ, Ghion Abay, Nehmya Shambel, Fassikaw Kebede Bizuneh, Shakir Usmail, Tesfaye Motuma

 #የፌዴራል ትምህርት ሚኒስቴር ወደ ራስ ገዝ አስተዳደር በመሸጋገር ላይ ባሉ ዘጠኝ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የንብረትና የፋይናንስ እንቅስቃሴ እገዳ ጣለ። #በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ...
18/08/2026

#የፌዴራል ትምህርት ሚኒስቴር ወደ ራስ ገዝ አስተዳደር በመሸጋገር ላይ ባሉ ዘጠኝ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የንብረትና የፋይናንስ እንቅስቃሴ እገዳ ጣለ።

#በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ዶ/ር) የተፈረመው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው፤ ዩኒቨርሲቲዎቹ የተቋማቱን ዝግጅት የሚገመግመው የገለልተኛ ባለሙያዎች ኮሚቴ ግኝት ታይቶ እስኪረጋገጥ ድረስ ንብረቶቻቸውን መሸጥ፣ በንብረቶቻቸው ማስያዣነት ብድር መውሰድ፣ መጠነ ሰፊ የግንባታ ሥራዎችን ማስጀመር እና ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁ ግዢዎችን መፈጸም አይችሉም።

#እገዳው የተጣለባቸውና በቀጣዮቹ ሦስት ወራት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ወደ ራስ ገዝ አስተዳደር ይሸጋገራሉ ተብለው የሚጠበቁት የጎንደር፣ ባህር ዳር፣ መቐለ፣ ሀዋሳ፣ ጅማ፣ ሐረማያ፣ አርባ ምንጭ፣ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ (ASTU) እንዲሁም አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ (AASTU) ዩኒቨርሲቲዎች ናቸው።

#​በተያያዘም በጅማ፣ በጎንደር እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች አዳዲስ ጊዚያዊ ፕሬዚዳንቶች የተሾሙ ሲሆን፤ ሹመቱ የተከናወነው ከአካዳሚክ ማህበረሰቡ ውጭ አዲስ ሰዎችን ከመቅጠር ይልቅ በነባር የሥራ ኃላፊዎች መካከል ሽግሽግ በማድረግ ነው።

​ዩኒቨርሲቲዎቹ ወደ ራስ ገዝነት ለመሸጋገር በአራቱ ዋና ዋና መሥፈርቶች ላይ የተመሠረተውን የዝግጅት ምዘና ቢያንስ 60 በመቶ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል። ይህ እርምጃ ቀደም ሲል ከተተገበረውና በተደረገው መዋቅራዊ ማስተካከያ ምክንያት በርካታ ሠራተኞችን ያለ መደብ አስቀርቶ ከነበረው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተሞክሮ በመቀጠል የመጣ ነው።

​ወደ ራስ ገዝነት መሸጋገር የተቋማት ነፃነትን እና የገቢ ምንጭን በራስ የማሳደግ ዕድል የሚያስገኝ ቢሆንም፤ ተችዎች ግን ተቋማቱ በትምህርት ክፍያ (ቱሽን) ላይ ጥገኛ መሆናቸው አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ተማሪዎች ሊያገለል ይችላል ሲሉ ሥጋታቸውን ይገልጻሉ።

#ምንጭ Addis fortune
ለተጨማሪ መረጃዎች 👇
https://t.me/Meinfo2018

 #መምህርነት የትውልድ ቀረጻ እና የማህበረሰብ ግንባታ ሙያ1. መግቢያመምህር ማለት ዕውቀትን፣ ክህሎትን፣ ሞራልንና ሥነ-ምግባርን ለትውልድ የሚያስተላልፍ፣ ሰዎችን የሚያበቃና ትክክለኛ አቅጣጫ...
18/08/2026

#መምህርነት የትውልድ ቀረጻ እና የማህበረሰብ ግንባታ ሙያ

1. መግቢያ

መምህር ማለት ዕውቀትን፣ ክህሎትን፣ ሞራልንና ሥነ-ምግባርን ለትውልድ የሚያስተላልፍ፣ ሰዎችን የሚያበቃና ትክክለኛ አቅጣጫ የሚያሳይ ባለሙያ ነው። መምህርነት ከመማርና ከማስተማር ተግባር በላይ ሰብአዊነትን፣ አስተሳሰብን፣ እሴትንና የማህበረሰብን መሠረት የሚገነባ ክቡር ሙያ ነው።

የአንድ ሀገር የትምህርት ጥራት፣ የሰው ሀብት ልማትና የወደፊት ዕድገት በከፍተኛ ደረጃ ከመምህራን ብቃትና ቁርጠኝነት ጋር ይያያዛል። ስለሆነም መምህርን ማብቃትና ማክበር ማለት የትውልድን የወደፊት ዕድል ማስጠበቅ ማለት ነው።

2. የመምህር ዋና ዋና ሚናዎች

2.1 ዕውቀትን ማስተላለፍ
መምህር ተማሪዎች የትምህርት ይዘትን እንዲረዱ፣ እንዲተነትኑና በተግባር እንዲጠቀሙበት ያግዛል። የመምህር ሚና መረጃን በቃል ማስተላለፍ ብቻ ሳይሆን ተማሪዎች የሚማሩትን እንዲገነዘቡና እንዲተገብሩ ማስቻል ነው።

2.2 ክህሎትን ማዳበር
ዘመናዊ ትምህርት ዕውቀት ብቻ አይደለም። ችግር መፍታት፣ በራስ መተማመን፣ ቡድን ሆኖ መሥራት፣ መግባባትና ፈጠራ የመሳሰሉ ክህሎቶችን ማዳበርም የመምህር ኃላፊነት ነው።

2.3 ሥነ-ምግባርንና እሴትን ማስተማር
መምህር በቃሉ ብቻ ሳይሆን በተግባሩም ምሳሌ ይሆናል። ታማኝነት፣ ኃላፊነት፣ አክብሮት፣ ፍትሃዊነትና ትጋትን በማስተማር የተሻለ ዜጋ እንዲገነባ ያግዛል።

2.4 የተማሪዎችን ችሎታ ማውጣት
እያንዳንዱ ተማሪ የተለየ ችሎታና ፍላጎት አለው። ጥሩ መምህር የተማሪዎችን ጠንካራ ጎን በመለየት ተማሪው ችሎታውን እንዲያውቅና እንዲያሳድግ ያበረታታል።

2.5 አቅጣጫ መስጠት
ተማሪዎች በትምህርት፣ በሙያና በሕይወት የሚወስዷቸውን ውሳኔዎች በተገቢው እንዲመሩ መምህር ምክርና መመሪያ ይሰጣል።

3. መምህር ለተማሪ ያለው አስፈላጊነት

መምህር የተማሪን የትምህርት ውጤት ብቻ አይወስንም፤ የተማሪውን ራስን የማመን፣ የመማር ፍላጎትና የወደፊት ራዕይ ለመገንባትም ወሳኝ ሚና አለው።

ተማሪ ከመምህሩ የሚያገኘው ዕውቀት በፈተና ውጤት ብቻ አይለካም። የሚያገኘው የማሰብ ችሎታ፣ ችግርን በመፍታት ብቃት፣ በራስ መተማመንና ለሌሎች አክብሮት የመስጠት ባህሪም የመምህሩ ተጽዕኖ ውጤት ነው።

4. መምህር ለማህበረሰብ ያለው ሚና

መምህር የሚያስተምረው ተማሪ የነገ ሐኪም፣ መሐንዲስ፣ መምህር፣ ተመራማሪ፣ መሪ፣ ሠራተኛ ወይም ሥራ ፈጣሪ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ መምህር የሚያደርገው ሥራ የአንድ ክፍል ተማሪዎችን ብቻ አይመለከትም፤ በረጅም ጊዜ የማህበረሰብን አቅም ይቀርጻል።

ጥራት ያለው መምህር በትምህርት ቤት የሚያስተምራቸውን ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን በእነርሱ በኩል ቤተሰብንና ማህበረሰብን ይነካል። በዚህም መምህርነት የሀገር ግንባታ ሙያ ይሆናል።

5. የዘመናዊ መምህር ባህሪያት

የዘመኑ መምህር፦

- በሙያው ብቁና ቀጣይነት ያለው ራስን ማሻሻል የሚፈልግ መሆን፤
- የዲጂታል ቴክኖሎጂንና ዘመናዊ የማስተማሪያ ዘዴዎችን መጠቀም፤
- ተማሪን የሚያከብርና ልዩነቶችን የሚቀበል መሆን፤
- በተግባር ምሳሌ መሆን፤
- የተማሪን ችሎታ ማወቅና ማበረታታት፤
- ከወላጆችና ከማህበረሰቡ ጋር በትብብር መሥራት፤
- ተማሪዎች በራሳቸው ማሰብና መወሰን እንዲችሉ ማብቃት ይገባዋል።

6. መምህርን ማብቃት ለምን ያስፈልጋል?

የተማሪ ትምህርት ጥራት ከመምህር ብቃት ጋር በቀጥታ ስለሚያያዝ፣ መምህራን በተከታታይ ስልጠናና የሙያ ልማት እንዲያገኙ ማድረግ ያስፈልጋል። የማስተማር ስልቶች፣ ቴክኖሎጂ፣ የተማሪ ግምገማ፣ የክፍል አመራርና የልዩ ፍላጎት ተማሪዎችን ማገዝ በመሳሰሉ ዘርፎች የሚደረግ ቀጣይ ሙያዊ ልማት የመምህራንን ብቃት ያጠናክራል።

7. የሚጠበቁ ዋና ውጤቶች

መምህራንን በብቃትና በሙያዊ አቅም ማጠናከር፦

1. የተማሪዎችን የመማር ውጤት ለማሻሻል፤
2. የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ፤
3. የተማሪዎችን የፈጠራና የችግር መፍታት ችሎታ ለማዳበር፤
4. ሥነ-ምግባርና ኃላፊነት ያለው ዜጋ ለማፍራት፤
5. የሰው ሀብት ልማትን ለማጠናከር፤
6. የሀገርን የዕውቀትና የልማት አቅም ለማሳደግ ያግዛል።

8. ማጠቃለያ

መምህር የመማሪያ መጽሐፍን ወደ ተማሪ የሚያስተላልፍ ባለሙያ ብቻ አይደለም። የሰውን ልጅ የሚያበቃ፣ የሚያነሳሳ፣ የሚመራ፣ እሴትን የሚያስተላልፍና የወደፊት ትውልድን የሚቀርጽ የሀገር ግንባታ ባለሙያ ነው።

“መምህርን ማብቃት ትውልድን ማብቃት ነው፤ መምህርን ማክበር የሀገርን ነገ ማክበር ነው።”

 #ኮከብ ተማሪ መተግበሪያ ለሁሉም ክልሎች እንዲዳረስ ተጠየቀከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ትምህርትን በቀላሉ ለመማር የሚያግዝ መተግበሪያ ተዘጋጀ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህ...
18/08/2026

#ኮከብ ተማሪ መተግበሪያ ለሁሉም ክልሎች እንዲዳረስ ተጠየቀ

ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ትምህርትን በቀላሉ ለመማር የሚያግዝ መተግበሪያ ተዘጋጀ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና መሰረተ ልማት ዳይሬክቶሬት ከግራችሰም ቴክኖሎጂ ጋር በመተባበር ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ “ኮከብ ተማሪ” የተሰኘ የማስተማሪያ መተግበሪያ አዘጋጅቷል።

#መተግበሪያው ተማሪዎች የሚማሯቸውን ትምህርቶች በቀላልና ለልጆች ተስማሚ በሆነ ዘዴ እንዲረዱና እንዲያጠናክሩ ለማገዝ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

በመተግበሪያው አጠቃቀምና በተያያዙ ጉዳዮች ላይ የክፍለ ከተማ የዘርፉ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱንም ቢሮው ገልጿል።

#በተለይም መተግበሪያው ከአዲስ አበባ ባሻገር በመላ ኢትዮጵያ ላሉ ተማሪዎች ተደራሽ እንዲሆን የሚያስችሉ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ ጥያቄ ቀርቧል።

“ኮከብ ተማሪ” መተግበሪያ በሁሉም ክልሎች ለሚገኙ የ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል ተማሪዎች ተደራሽ ከሆነ፣ የዲጂታል ትምህርት አጠቃቀምን በማስፋፋት የተማሪዎችን የመማር ሂደት ለማጠናከር የሚያበረክት ሚና እንደሚኖረው ተጠቁሟል።

18/08/2026
  #የምዝገባ ጊዜ መራዘሙ ተገለጸ! #አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም አመልካቾች የምዝገባ ጊዜ እስከ እሑድ ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም መራዘ...
18/08/2026



#የምዝገባ ጊዜ መራዘሙ ተገለጸ!

#አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም አመልካቾች የምዝገባ ጊዜ እስከ እሑድ ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም መራዘሙን ገልጿል፡፡

ለድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች ዝርዝር 👇https://admission.aau.edu.et/GraduatePrograms

አመልካቾች በቅድሚያ በዩኒቨርሲቲው የሚሰጠውን የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (G*T) ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃዎች 👇
https://t.me/Meinfo2018

Address

Sebeta

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አለም አቀፍ ትምህርት ነክ መረጃዎች Global Education informations posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to አለም አቀፍ ትምህርት ነክ መረጃዎች Global Education informations:

Shortcuts

Share