ወቅታዊ መረጃ

ወቅታዊ መረጃ Ethiopia

ድርጊቱ በጥቅምት ወር የተፈፀመ ነው‼በድብደባ ቪዲዮው ላይ ፖሊስ ምርመራ አጠናቆ መዝገቡን ለፍትህ አካል መላኩን ገለፀ‼​በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ በነበረው የድብደባ ቪዲዮ ላይ አስፈላጊው ማጣ...
17/08/2026

ድርጊቱ በጥቅምት ወር የተፈፀመ ነው‼

በድብደባ ቪዲዮው ላይ ፖሊስ ምርመራ አጠናቆ መዝገቡን ለፍትህ አካል መላኩን ገለፀ‼

​በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ በነበረው የድብደባ ቪዲዮ ላይ አስፈላጊው ማጣራት ተጠናቆ የምርመራ መዝገቡ ለፍትህ አካል መላኩን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

​የፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ቶማስ እሸቴ ለብስራት ሬድዮ እንዳረጋገጡት፣ ድርጊቱ ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በጓደኛሞች መካከል በ”ሀሜት” ምክንያት የተፈጸመ ነው።

ፖሊስ ጥቆማ ይድረሰው እንጂ ቪዲዮው በማህበራዊ ሚዲያ ከሰራጨቱ በፊት ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ውለው ለሶስት ሳምንታት ምርመራ ሲደረግባቸው ቆይቷል።

​ኮማንደር ቶማስ አክለውም፡​ህብረተሰቡ ላደረገው ጥቆማ ምስጋና አቅርበዋል።

​ምስሉን ቀርፆ ማሰራጨት ህገ-ወጥ በመሆኑ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስበዋል።

​ወላጆች በልጆቻቸው የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ላይ አስፈላጊውን ክትትል እንዲያደርጉ መክረዋል።

3 ሚሊዮን ብር የሚገመት የሀበሻ አረቄ ተደፋበምዕራብ ኦሞ ዞን ቤሮ ወረዳ በህገ-ወጥ መንገድ ተዘጋጅቶ ለዝውውር የቀረበው ይህ አረቄ በገበያ ግምቱ ከ3 ሚሊየን ብር በላይ እንደሚገመት ተገልጿ...
17/08/2026

3 ሚሊዮን ብር የሚገመት የሀበሻ አረቄ ተደፋ

በምዕራብ ኦሞ ዞን ቤሮ ወረዳ በህገ-ወጥ መንገድ ተዘጋጅቶ ለዝውውር የቀረበው ይህ አረቄ በገበያ ግምቱ ከ3 ሚሊየን ብር በላይ እንደሚገመት ተገልጿል።

ህገ-ወጥ ምርቱ እንዲደፋ እና እንዲወገድ በተደረገበት ወቅት ግልጽነትና ህጋዊ አሰራርን በተከተለ መልኩ የሂደቱ ታዛቢዎች ተገኝተዋል።

በቦታውም የወረዳው ፖሊስ መርማሪዎች የወረዳው አቃቤ ህግ የአካባቢውም የቀበሌ ስራ አስኪያጅ የከተማዋ ነዋሪዎችና ታዛቢዎች በተገኙበት በይፋ እንዲደፋ ተደርጓል።

የወረዳው ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍላ ኃላፊ ሳጅን ጌታሁን ክፍሌ እንደገለጹት ህገ-ወጥ አረቄ ማዘጋጀትና ማሰራጨት በማህበረሰቡ ጤና ላይ ከሚያደርሰው የጎንዮሽ ጉዳት ባለፈ በወረዳው የሚታየውን የወንጀል ድርጊት የሚያበዛና በህጋዊ የንግድ ስርዓት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድር በመሆኑ ቁጥጥሩ አሁንም ተጠናክሮ ይቀጥላል።

በተጨማሪም ህብረተሰቡ መሰል ህገ-ወጥ ድርጊቶችን በመጠቆም እና ከጸጥታ አካላት ጋር የሚያደርገውን አጋርነት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል ሲል ከወረዳው ኮሙኒኬሽንን ጠቅሶ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግኝኙነትና ኮሙኒኬሽን ዘግቧል

ሰበርአቶ ክርስቲያን ታደለ የመንግሥትን የምሕረት ቅድመ ሁኔታ ተቀበሉ! ከአማራ ክልል ቀውስ ጋር በተያያዘ በሽብር ተከስሰው በእስር ላይ የሚገኙ በርከት ያሉ ታሳሪዎች መንግሥት ያቀረበላቸውን ...
17/08/2026

ሰበር

አቶ ክርስቲያን ታደለ የመንግሥትን የምሕረት ቅድመ ሁኔታ ተቀበሉ!

ከአማራ ክልል ቀውስ ጋር በተያያዘ በሽብር ተከስሰው በእስር ላይ የሚገኙ በርከት ያሉ ታሳሪዎች መንግሥት ያቀረበላቸውን በቅድመ ሁኔታ የታሠረ የምኅረት መጠየቂያ ሠነድ መፈረማቸውን ዋዜማ ራድዮ ዘግቧል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ ክርሰቲያን ታደለን፣ ረዳት ፕሮፌሰር ማዕረጉ ቢያበይንን ጨምሮ በርካታ እስረኞች የምኅረት መጠየቂያውን በመሙላት ስምምነታቸውን እንደገለጡ ምንጮች እንደነገሩት ዘገባው ጠቅሷል። አምስት ጋዜጠኞችንና ፖለቲከኞችን ጨምሮ 30 ያህል እስረኞች ግን ሠነዱን 'አንፈርምም' ማለታቸው ታውቋል።

ሠነዱን አንፈርምም ካሉት መካከል፤ የአማራ ክልል ምክር አባሉ ዮሐንስ ቧያለው፤ ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው፣ ዶ/ር ወንደወሠን አሠፋ፣ መስከረም አበራ እና ጎበዜ ሲሳይ ይገኙበታል ተብሏል። የምኅረት ሠነዱን እንዲፈርሙ የቀረበላቸው እስረኞች 300 ገደማ እንደሚጠጉ ታውቋል፡፡

አዳነች ኩምሳ የሁለት ልጆች እናት ስትሆን፤ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) ውስጥ በ አለልቱ ቅርንጫፍ  ትሰራ ነበር። ታህሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም (ዲሴምበር 15, 2025) ምሽት ላይ አ...
14/08/2026

አዳነች ኩምሳ የሁለት ልጆች እናት ስትሆን፤ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) ውስጥ በ አለልቱ ቅርንጫፍ ትሰራ ነበር።
ታህሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም (ዲሴምበር 15, 2025) ምሽት ላይ አዳነች እና ወንጀለኛው ፀጋዬ አሰላፈው ጎነቴ ሰንዳፋ በሚገኝ አንድ ምግብ ቤት ውስጥ ተገናኝተው ነበር። እዚያም በነበራቸው ከባድ አለመግባባት ምክንያት አዳነች ቦታውን ጥላ ወጣች። ፀጋዬም በስተጀርባዋ ተከትሎ በመውጣት በሃይል ወደ መኪና ውስጥ ካስገባት በኋላ በጥይት መትቶ ገድሏታል። በመጨረሻም አስከሬኗን በአካባቢው ባለ የፍሳሽ ማስወገጃ ቦይ ውስጥ ጥሎታል።
አስከሬኗ ከቀናት በኋላ ሲገኝ ከ ጭንቅላቷ በቀር አካሏ በ አብዛኛው በዱር አራዊት ተበልቶ ነበር።
ተጠርጣሪው ወንጀሉን ከፈጸመ በኋላ የተጠቀመበትን መኪና እና የነፍስ ማጥፊያ መሳሪውን አለልቱ አካባቢ ጥሎ በመሰወር ለወራት ሲፈለግ ቆይቷል። በወቅቱ የተለያዩ የሐሰት መታወቂያዎችን በመጠቀም በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ውስጥ ተሸሽጎ ነበር።

በግንቦት ወር 2018 ዓ.ም (ሜይ 2026) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት (NISS) ጋር በመተባበር ባደረጉት ጥብቅ ክትትል ተጠርጣሪውን ፀጋዬ አሰላፈው ጎነቴን በደብረ ብርሃን ከተማ ውስጥ በቁጥጥር ስር አውለውታል።
በበይነ መረብ ላጣራ ብዙ ብሞክርም የ ክሱ እና የ ፍርድ ሒደቱን መጨረሻ መረጃ ማግኘት አልቻልኩም።
የ አዳነች ትንንሽ ሁለት ልጆች ፍትህን ይሻሉ ሊሰሙም ይገባል።

በዋቢነት Borkena.com ን ተጠቅሜያለሁ።

Via:- Feben Fancho

"በአዲስ አበባ ጉዳይ ስምምነት አልተደረሰም" ኮሚሽኑ በአዲስ አበባ ጉዳይ የኦሮሚያ መቀመጫ እንዲትሆን ስምምነት ላይ ተደርሷል መባሉን ኮሚሽኑ አስተባብሏል።መናኸሪያ ኤፍ ኤም ትላንት ያሰራጨው...
14/08/2026

"በአዲስ አበባ ጉዳይ ስምምነት አልተደረሰም" ኮሚሽኑ

በአዲስ አበባ ጉዳይ የኦሮሚያ መቀመጫ እንዲትሆን ስምምነት ላይ ተደርሷል መባሉን ኮሚሽኑ አስተባብሏል።

መናኸሪያ ኤፍ ኤም ትላንት ያሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ኮሚሽኑ፣ ዘገባው ባሰራጨው ሚዲያ በኩል በሰጠው ማስተባበያ አስታውቋል።

"የአዲስ አበባ ከተማ የፌደራል እና የኦሮሚያ ክልል መቀመጫ እንድትሆን 500 አባላት ያሉት የተመካካሪዎች ቡድን ተስማምተዋል" በሚል የተሰራጨው መረጃ አሳሳች መሆኑን ኮሚሽኑ አረጋግጧል።

ኮሚሽኑ መረጃውን ላሰራጨው መናኸሪያ ኤፍ ኤም በሰጠው ማብራሪያ "በአገራዊ ምክክር ጉባኤ የአዲስ አበባ አጀንዳ የመጨረሻ ውሳኔ አላገኘም" ብሏል።

በፌደራል መቀመጫ ከተሞች አጀንዳ ላይ በነበረው የምክክር ሂደት የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች ሚከተሉት ናቸው 👇

🎯አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ መዲና እና የፌደራል መንግሥት መቀመጫ እንጂ ለአንድ አካል ብቻ የማትሰጥ ናት የሚል አቋም ተንጸባርቋል።

🎯አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ በፌደራል ተጠሪነት እንዲቀጥሉ እንዲሁም አዲስ አበባ ራሷን በራሷ እንድታስተዳድር የምክር ሀሳብ ስምምነት ተደርጓል።

🎯የኦሮሚያ ክልል መቀመጫነት በልዩነት ተይዞ በአስማሚ ቡድን እንዲታይ፣ ቀደም ሲል ይነሳ የነበረው "ልዩ ጥቅም" የሚለው ሐረግ ቀርቶ "የጋራ ጥቅም" እንዲሆን ተገልጿል።

ይህ ሂደት በ500 ሰዎች የተከናወነ ቢሆንም፣ ጉዳዩ ገና በኮሚቴዎች እና በ4 ሺህ የምክክር ተሳታፊዎች በይፋ እስከሚወሰን ድረስ የመጨረሻ ውሳኔ እንዳልተሰጠው የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ አስታውቋል።

#ኢትዮጵያ #አዲስአበባ #ምክክር

ሰበር ❗️ተላላኪው ህወሃት በግዳጅ ወደ ግምባር ከወሰዳቸው 250 የሚሆኑ ወጣቶች እኛ ለናንተ ስልጣን ለማስጠበቅ አንሰዋም በማለት በራያ በኩል ከነ ትጥቃቸው የትግራይ ሰላም ሃይል ተቀላቅለዋል...
08/08/2026

ሰበር ❗️

ተላላኪው ህወሃት በግዳጅ ወደ ግምባር ከወሰዳቸው 250 የሚሆኑ ወጣቶች እኛ ለናንተ ስልጣን ለማስጠበቅ አንሰዋም በማለት በራያ በኩል ከነ ትጥቃቸው የትግራይ ሰላም ሃይል ተቀላቅለዋል። የተወሰነ የህወሃት ሀይሎች ትጥቅ ፈታችሁ ትሄዳላችሁ በማለት በሀይል ትጥቅ ለማስፈታት ቢሞክሩም እንዳልቻሉ ታውቋል። ቀሪው ወጣት ለነተቡ የሻዕቢያ ተላላኪዎች ብላችሁ ውድ ህይዎታችሁን አትለግሱ በተገኘ አጋጣሚ ወደ ትግራይ ሰላም ተቀላቀሉ።

Ahmed Habib Alzarkawi

አሳዛኝ ዜና======= #በአለታ ወንዶ ከተማ በተከሰተ የትራፍክ አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡በቀን 02/2018, ዓ.ም ከሌሊቱ 2፤30 ከቦረና መስመር ፌዴራል ፖሊስ ጭኖ ወደ ሀዋሳ እየ...
08/08/2026

አሳዛኝ ዜና
=======
#በአለታ ወንዶ ከተማ በተከሰተ የትራፍክ አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

በቀን 02/2018, ዓ.ም ከሌሊቱ 2፤30 ከቦረና መስመር ፌዴራል ፖሊስ ጭኖ ወደ ሀዋሳ እየመጣ ያለው ታርጋ ቁጥር 1190 EFP የሆነ ተሽከርካሪ በአለታ ወንዶ ከተማ ቡልቱማ ቀበሌ በደረሰው የመንገድ ላይ ትራፊክ አደጋ ምክንያት የአምስት ወንድና የአንድ ሴት በድምሩ የስድስት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

በተጨማሪም አንድ ሲኖትራክ መስመር ስቶ መኖሪያ ቤት ሰብሮ በመግባቱ የአንድ እግረኛ ህይወትም ልያልፍ ችሏል፡፡

የሌሊት ጉዞ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያሻው በመሆኑ አሽከርካሪዎች በሌሊት ጉዞ በሚያደርጉበት ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል።
የትራፊክ አደጋን በጋራ እንከላከል!!

 #ትዝብት 1ጥላቻ ልክ እንደ መርዝ ነው! መጀመሪያ ተሸካሚውን ይመርዝና ሞልቶ ሲፈስ በአቅራቢያው የተገኘውን ሁሉ ይበክላል:: ከዚያም ዕድል ከተሰጠው ልክ እንደ ምግብ ሰንሰለት ከግለሰብ ወደ...
08/08/2026

#ትዝብት 1
ጥላቻ ልክ እንደ መርዝ ነው! መጀመሪያ ተሸካሚውን ይመርዝና ሞልቶ ሲፈስ በአቅራቢያው የተገኘውን ሁሉ ይበክላል:: ከዚያም ዕድል ከተሰጠው ልክ እንደ ምግብ ሰንሰለት ከግለሰብ ወደ ማህበረሰብ፣ ብሎም ተቋም፣ ከፍ ሲል ደግሞ ሃገር ይዛመታል!

የጥላቻ ዋነኛ መሳሪያ ደግሞ እርቃኗን የምትሄደው ሃፍረተቢሷ ውሸት ናት! ሁለቱ ሲቀናጁ ውጤታቸው አስከፊ ይሆናል::

ዛሬ ላይ ሀገራችንን ከሰፈር እስከ ድንበር የሚያውኳት እነዚህ የትውልድ ጠንቆች ተቀናጅተው የፈጠሩት ከባድ ሁኔታ ነው::

እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥር ለፍቅር ነበር:: ዳሩ ግን እውነት ተከናንባ ውሸት አደባባይ ወጥታ እዩኝ እዩኝ እያለች ነው:: ምንም እንኳን ፀሐይ መውጣቷ ባይቀር ውሸት ሲደጋገም እውነት መስሎት የምያልቅሰው ሰው ብዛት ያሳስበኛል::

ብቻ ፈጣሪ ወደ ቀልባችን ይመልሰን ዘንድ እንፀልይ!

መልካም ቀዳሚት ሰንበት!

‎አስቸኳይ የህይወት አድን ጥሪ📢😥‎‎ይሄ ከታች በፎቶ የሚታዩት ወጣት መላኩ ነቢዩ ይባላል። ህይወቱን ለማሻሻል እና የተሻለ ስራ ፍለጋ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ስራ ላይ እያለ ባጋጠመው ከባድ...
07/08/2026

‎አስቸኳይ የህይወት አድን ጥሪ📢😥

‎ይሄ ከታች በፎቶ የሚታዩት ወጣት መላኩ ነቢዩ ይባላል። ህይወቱን ለማሻሻል እና የተሻለ ስራ ፍለጋ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ስራ ላይ እያለ ባጋጠመው ከባድ የመኪና አደጋ ምክንያት በተለያዩ ሆስፒታሎች ህክምና ስከታተል ቆይቶ ወደ ትውልድ ቀየው ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን ጌና ወረዳ ተመልሶ በመምጣት ህይወትን መምራት የጀመረ ቢሆንም መጀመሪያ በደረሰው አደጋ ጉዳት እንደገና በማገርሸቱ ምክንያት በታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል ኦፊራሰዪን ከተደረገ በኋላ ወደ ጅማ ሆስፒታል ሪፌር የተደረገ ቢሆንም በገንዘብ እጦት የተነሳ ወደ ጅማ ሆስፒታል ሄዶ መታከም ተስኖት ከፍተኛ ህመምና ስቃይ ውስጥ ይገኛል ።

‎የህክምና ባለሙያዎች ህይወቱን ለማዳን ሌሊት ከቀን ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። ሆኖም ግን፣ ህክምናው ቀጣይነት ያለው በመሆኑና ከፍተኛ ሀኪሞች፣ መድኃኒቶች እንዲሁም የህክምና መሳሪያዎችን የሚጠይቅ በመሆኑ ወጪው እጅግ በጣም አሳሳቢ ሆኗል። ‎እስከ አሁን ያለው ህክምና በቤተሰብና በቅርብ ወዳጆች አቅም ሲሸፈን የቆየ ቢሆንም፣ አሁን ግን የህክምና ወጪው ከአንድ ቤተሰብ አቅም በላይ ሆኖ ተደቅኗል።

አሁን ለ‎ህክምናውን ጠቅላላ ወጪ 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺ) ብር አስፈልጓል። እናንተ ደጋግ ኢትዮጵያዊያን እጃችሁን እንዲትዘረጉ በፈጣሪ ስም እንለምናለን።

የኢትዮጵያ ንግድ አካውንት ቁጥር
CBE: 1000428180511 Melaku Nebiyu

መረዳት ባትችሉ እንኳን ለደጋግ ኢትዮጵያዊያን እንዲደርስ ሼር በማድረግ ተባበሩ🤲

የእዮሃ የሚዲያ ፕሮግራም ታገደበአለምሰገድ እየተዘጋጀ የሚቀርበው ፕሮግራም የታገደው ለበርካታ ቤተሰቦች መበተን ምክንያት በመሆኑ ነው ። DNA እያስመረመሩ የሚቀርቡ መሰል የቤተሰብ ህይወት ላ...
07/08/2026

የእዮሃ የሚዲያ ፕሮግራም ታገደ
በአለምሰገድ እየተዘጋጀ የሚቀርበው ፕሮግራም የታገደው ለበርካታ ቤተሰቦች መበተን ምክንያት በመሆኑ ነው ። DNA እያስመረመሩ የሚቀርቡ መሰል የቤተሰብ ህይወት ላይ ያተኮሩ ፕሮግራሞች በየትኛውም የማህበራዊ ሚዲያም ይሁን ቴሌቪዥን እግድ ተጥሎባቸዋል ።

Address

Addis Abeba
Shashemene
ERR

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ወቅታዊ መረጃ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share