Adigrat university Evangelical Chirstian Graduates Fellowship page

  • Home
  • Adigrat university Evangelical Chirstian Graduates Fellowship page

Adigrat university Evangelical Chirstian Graduates Fellowship page Re united in jesus

እሁድ ማለዳ በሱሉልታ ፕራይቶርየም የክርስቶስ ቤተክርስቲያን እግዘብሔር እንደ ህብረት መልካም የአገልግሎት ጊዜን ሰቶናል። ክብር ለእርሱ ይሁን።
07/09/2026

እሁድ ማለዳ በሱሉልታ ፕራይቶርየም የክርስቶስ ቤተክርስቲያን እግዘብሔር እንደ ህብረት መልካም የአገልግሎት ጊዜን ሰቶናል። ክብር ለእርሱ ይሁን።

05/08/2026

BkI ምዝገባ ለ10 ቀን ብቻ ተራዝሟል!

ለማመልከት የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ያስፈልጋል፦
✔️ በኢቫሱ አገልግሎት የተሳተፉ እና የኢቫሱ ሰርተፊኬት ያላችሁ
✔️ ከ2008 እስከ 2018 ዓ.ም. የተመረቃችሁ
✔️ የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ ወይም ቴምፖ ያላችሁ
✔️ የንግድ እቅድ ማቅረብ የምትችሉ
✔️ በስልጠናዎቹ ሙሉ በሙሉ መሳተፍ የምትችሉ
✔️ የምዝገባዉ ቀን የሚጠናቀቀዉ ነሀሴ 7/2018 ዓ.ም.

በየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል የምትገኙ የኢቫሱ ምሩቃን ማመልከት ትችላላችሁ።
ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ያመልክቱ!
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfTFFk1xbQ_qOhP506Pv7aVbeCcUqCd5tztS124wYYlvqY9Qg/viewform?usp=header

05/08/2026
ሰላም እንዴት ናችሁ?በሀዋሳ እና በአካባቢው የምትገኙ የቀድሞ የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ክርስቲያን ተማሪዎች ፌሎሽፕ (ADUECGF) አባላት የነበራችሁ፣ ዛሬ በጌታ ፈቃድ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ...
15/07/2026

ሰላም እንዴት ናችሁ?
በሀዋሳ እና በአካባቢው የምትገኙ የቀድሞ የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ክርስቲያን ተማሪዎች ፌሎሽፕ (ADUECGF) አባላት የነበራችሁ፣ ዛሬ በጌታ ፈቃድ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች እና አገልግሎተቶች ውስጥ የምትገኙ ውድ የADUECGF ቤተሰቦች፤

ባለፈው ወር ግንቦት 23/09/2018 ዓ.ም. በሀዋሳ መሰባሰባችን ይታወሳል።

የሰኔ ወር ፕሮግራማችንን ለሰኔ 28 ቀጥረን ነበር፤ ሆኖም በተለያዩ ፕሮግራሞች መደራረብ ምክንያት የቀን ለውጥ ማድረግ አስፈልጓል።

ስለዚህ በሐምሌ 12/11/2018 ዓ.ም. እሁድ 8:00 ሰዓት ሁላችንም በጊዜ እንድንገናኝ በጌታ ፍቅር እናሳስባችኋለን።

አድራሻ: ቱሩፍት
ለበለጠ መረጃ አስተባባርዎችን ያናግሩ::

እግዚአብሔር ይባርካችሁ፤ እንጠብቃችኋለን!



Join us on

የ Adigrat university graduated fellowship የአምልኮ ህብረት የስብሰባ ሪፖርትየስብሰባ ቦታ፡በማንያዘዋል ግቢቀን፡ግንቦት 30፣ 2018 ዓ.ምየስብሰባ ሰዓት፡ከቀኑ 8:00...
08/06/2026

የ Adigrat university graduated fellowship የአምልኮ ህብረት የስብሰባ ሪፖርት
የስብሰባ ቦታ፡በማንያዘዋል ግቢ
ቀን፡ግንቦት 30፣ 2018 ዓ.ም
የስብሰባ ሰዓት፡ከቀኑ 8:00 ሰዓት
1. መግቢያ
የአምልኮ ህብረታችን የውይይት መድረክ በታቀደው መሰረት ተካሂዷል። የስብሰባው ዋና ዓላማ የህብረቱን መነሻ ሀሳብ ማጽናት፣ አላማውን መግለጽ እና ለወደፊት ግቦች ስኬት የሚረዱ ተግባራዊ እርምጃዎችን መወሰን ነው።

2. ዋና ዋና የውይይት አጀንዳዎች
የመክፈቻ ፕሮግራም፡ስብሰባው በዘማሪት ሊኖራ በንግግር የተጀመረ ሲሆን፤ በንግግሯም ህብረቱ የአዲግራትን ከተማ አልፎ በወንጌል ለመድረስ በትግራይ ክልል ደረጃ ለሚደረገው የትልቅ እንቅስቃሴ ወሳኝ ግብአት መሆኑን አጽንኦት ሰጥታለች።
የህብረቱ ዓላማ፡ወንድም ሀብትሽ በህብረቱ መቋቋም ላይ ዝርዝር ማብራሪያ የሰጠ ሲሆን፣ ህብረቱ የተቋቋመበትን የጋራ ግብ እና የቤተክርስቲያን አገልግሎትን በማጠናከር ረገድ ያለውን ሚና አብራርቷል።
የአባላት አስተያየትና ተስፋ፡
አባላት የሆኑት ኤማ፣ አብዲ እና በረከት በህብረቱ ላይ ያላቸውን ጥልቅ ስሜት የገለጹ ሲሆን፣ ህብረቱ በወደፊት የአገልግሎት ጉዞ ላይ ሊጫወት የሚችለውን አወንታዊ ሚና በተመለከተ ገንቢ ሀሳቦችን አቅርበዋል።
የስትራቴጂያዊ ድጋፍ፡ወንድም ሎጲሶ በሰጡት ማብራሪያ፣ የዚህ ህብረት አስፈላጊነት ከዋናው "Graduated Fellowship" ጋር ያለውን ትስስር አብራርተዋል። በተለይም ዋናው ህብረት ለዚህ የአምልኮ ቡድን የገጠመው ከፍተኛ ድጋፍና እምነት ለስኬታችን መሰረት እንደሚሆን ተጠቅሷል።3. የተወሰኑ የቀጣይ እርምጃዎች
ሙዚቀኞችን መሰባሰብ፡ሀብትሽ እና ኤማ ሙዚቀኞችን በመለየት ወደ ህብረቱ ለማምጣት ኃላፊነት ተረክበዋል። ይህ ተግባር በቀጣዩ ስብሰባ ላይ ውጤት ይጠበቅበታል።
የአባላት ተሳትፎና መስፋፋት፡ እያንዳንዱ የህብረቱ አባል ቀድሞ የነበሩ ወንድሞችንና እህቶችን በማስተባበር፣ ቢያንስ እያንዳንዱ ሰው ሁለት ተጨማሪ ሰዎችን ይዞ በሚቀጥለው ስብሰባ ላይ እንዲገኝ ቃል ተገባብቷል።

4. የጊዜ ሰሌዳዎች
የጸሎትና የውይይት መድረክ፡በየ 15 ቀኑ በቴሌግራም ግሩፕ በኩል ቅዳሜ ምሽቱ 3:00 እስከ 4:00 (በአዲስ አበባ ሰዓት) ይካሄዳል።

የአንድነት ጊዜ (Physical Fellowship): ለቀጣይ ወር ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም (እሁድ) የአንድነት ፕሮግራም ተይዟል።

5. ማጠቃለያ
ስብሰባችን በወንድም አብዲ የመዝጊያ ጸሎት በድል የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ሁሉም አባላት በተጣለባቸው ኃላፊነትና ለጋራ ግብ በቆራጥነት ለመንቀሳቀስ ተስማምተዋል።
ቀን፦ ግንቦት 30፣ 2018 ዓ.ም

01/06/2026

በአዲግራት ዩንቨርስቲ ክርስቲያን ተማርዎች ህብረት የመጀመርያዋ ሰብሳቢት የሆነችው ዘማሪት ቤተልሔም ታምራት አዲስ አልበም ይዛልን መታለች ከዝማሬዎቿ መካከል እርዳኝ የሚለዉ እነሆ ተባረኪ!

የቀድሞ የአዲግራት ዩንቨርስቲ ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት አገልጋዮች በሀዋሳ በዘማሪ ሞኬ እና ማሬ መኖርያ ቤት በመገኘት መልካም የአድነት ጊዜ አሳልፈዋል:: ተባረኩ!
01/06/2026

የቀድሞ የአዲግራት ዩንቨርስቲ ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት አገልጋዮች በሀዋሳ በዘማሪ ሞኬ እና ማሬ መኖርያ ቤት በመገኘት መልካም የአድነት ጊዜ አሳልፈዋል:: ተባረኩ!

For your information 📌ማስታወቅያ ===============================ዋናዉን ዲግሪ (Original Degree) ላልወሰዳችሁ የቀድሞ ተማሪዎች በሙሉ፥ ➡️ ከዓዲግራት...
29/05/2026

For your information
📌ማስታወቅያ
===============================
ዋናዉን ዲግሪ (Original Degree) ላልወሰዳችሁ የቀድሞ ተማሪዎች በሙሉ፥

➡️ ከዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተመርቃችሁ ዋናዉን ዲግሪ (Original Degree) ያልወሰዳችሁ እና እንዲሰራላችሁ የምትፈልጉ ትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት ዋናዉን ዲግሪ (Original Degree) ከማተሚያ ቤቱ በቀጥታ ታትሞ የሚመጣ በመሆኑ ከዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተመርቃችሁ ዋናዉን ዲግሪ (Original Degree) ያልወሰዳችሁ እና እንዲሰራላችሁ የምትፈልጉ ከታች በተቀመጠዉ ማስፈንጠሪያ (Link) እንድትመዘገቡ እያሳሳብን እስከ ጉንበት 28, 2018 ዓ/ም የተመዘገቡትን ብቻ ለመጀመሪያ ዙር የምናሳትም ሲሆን ከዚያ በኋላ የተመዘገባችሁት በሁለተኛ ዙር የሚታተምላችሁ መሆኑን እናሳዉቃለን።

👉🏻 Link: https://forms.gle/2AUWjV2pF6nrzDxi6

ማሳሰቢያ፦
በወጪ መጋራት (Cost-Sharing) የተማራችሁ አመልካቾች ኦሪጅናል ዲግሪ ሰርተፊኬታችሁን ለመውሰድ የክፍያ ግዴታችሁን መፈጸማችሁን ወይም በአገልግሎት መወጣታችሁን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ እና ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባችኋል።

Please fill out this form carefully and correctly. Incomplete or incorrect information may delay or result in rejection of your request. Eligibility Instructions: 1. This form is intended for graduates requesting their Original Degree Certificate. 2. Graduates under Cost-Sharing or sponsorship progr...

የህብረቱን አላማ ከግብ ለማድረስ በቀድሞ የአዲግራት ዩንቨርስቲ የዝማሬ ቡድን(Worship team) በኩል የአገልግሎት እንቅስቃሴዎች ተጀምሯል። Singer Israel, Singer Habitsh...
28/05/2026

የህብረቱን አላማ ከግብ ለማድረስ በቀድሞ የአዲግራት ዩንቨርስቲ የዝማሬ ቡድን(Worship team) በኩል የአገልግሎት እንቅስቃሴዎች ተጀምሯል። Singer Israel, Singer Habitsh, Singer Abigya, Singer Wede. ተባረኩ!

Betty Momy God bless you!  Share it for others.
23/05/2026

Betty Momy God bless you! Share it for others.

🎉 NOW RELEASED 🎉“YINSA KENE - ይነሳ ከእኔ”by Betelhem Tamirat 🎶🙏Wa...

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Adigrat university Evangelical Chirstian Graduates Fellowship page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Want your university to be the top-listed university?

Share