Wolkite Poly Technic College & Satellite Institute

Call Contact the university

Wolkite Poly Technic College & Satellite Institute Transferring up to date information about training ,technology transfer and industry extension activ

 !!🙏❤
27/09/2026

!!🙏❤

27/09/2026

!!🙏❤🙏

✝️✝️✝️  ! ✝️✝️✝️===========================መስከረም 15/2018 (ወልቂጤ)፡ የወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ ለመላው የኮሌጁ ማህበረሰብ፣ ለወላጆች፣ ...
25/09/2026

✝️✝️✝️ ! ✝️✝️✝️
===========================
መስከረም 15/2018 (ወልቂጤ)፡ የወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ ለመላው የኮሌጁ ማህበረሰብ፣ ለወላጆች፣ ለተማሪዎች፣ ለአሰልጣኞችና ሰራተኞች፣ ለአጋር ተቋማት፣ ለወዳጆችና እንዲሁም የሀገራችን የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ2019 ዓ.ም. የመስቀሉ በዓል አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የተስፋና የሰላም እንዲሆንላችሁ ከልብ ይመኛል!!✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

በድጋሚ መልካም በዓል! እንኳን አደረሳችሁ! ✝️✝️✝️

 ።==============================መስከረም 12/2019 (ወልቂጤ)፡ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲና ከቼቼ የቴክኖሎጂ ኩባንያ የመጡ የልዑካን ቡድን አባላት በወልቂጤ ...
22/09/2026

።
==============================
መስከረም 12/2019 (ወልቂጤ)፡ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲና ከቼቼ የቴክኖሎጂ ኩባንያ የመጡ የልዑካን ቡድን አባላት በወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ በመገኘት ጉብኝት አደረጉ።

የልዑካን ቡድኑ ጉብኝት የተዘጋጀው በጉራጌ ዞን ሳይንስና ቴክኖሎጂ መምሪያና በወልቂጤ ከተማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት አስተባባሪነት ሲሆን፣ በልዑካን ቡድኑ ውስጥ በፈጠራና በቴክኖሎጂ ስራዎች ከፍተኛ እውቅና ያተረፉ በርካታ ወጣቶችም ተካተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ልዑካን ቡድኑ በኮሌጁ የሚገኙ የተለያዩ የት/ት ክፍሎችን የተግባር ማሰልጠኛ ቦታዎችን እና የፈጠራ ስራዎች የሚከናወኑባቸውን ክፍሎች በመዘዋወር ጎብኝተዋል። በዚህም ወቅት በኮሌጁ ዲን አቶ ኸይሩ አህመዲን እንዲሁም በየት/ት ክፍሎቹ ኃላፊዎች አማካኝነት ገለፃና ማብራሪያ ተሰጥቷል። በዚህም ጉብኝት በስልጠና፣ በፈጠራ፣ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ለወጣቶቹ የልምድ ልውውጥና የትብብር መድረክ መፍጠር ችሏል።

በመጨረሻም ጉብኝቱ ከተጠናቀቀ በኋላ የልዑካን ቡድኑ አባላት በኮሌጁ ባዩት የስልጠና፣ የፈጠራና የቴክኖሎጂ ስራ እንዲሁም የስራ አቅም በማድነቅ በጉብኝቱ መደሰታቸውን እና በቀጣይ ከኮሌጁ ጋር በቅንጅት ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።
-----------------------------
!
!
፦
Tiktok tiktok.com/
Facebook https://w.facebook.com/wolkite poly technic college & satellite institute
Website:- https://wptc.gov.et/
Telegram:- https://t.me/wptc2000
!

 ።=============================መስከረም 12/2019 (ወልቂጤ)፡ የወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ የ2018 የሥራ ዘመን የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 ...
22/09/2026

።
=============================
መስከረም 12/2019 (ወልቂጤ)፡ የወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ የ2018 የሥራ ዘመን የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 የሥራ ዘመን ዕቅድ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ አካሄደ።

በመድረኩ የ2018 የሥራ ዘመን የተቋሙ ዕቅድ አፈጻጸም በጥልቀት የተገመገመ ሲሆን፣ በተገኙ ውጤቶች፣ በተለዩ ጥንካሬዎችና ክፍተቶች እንዲሁም በቀጣይ የሥራ ዘመን ሊሻሻሉ በሚገባቸው ጉዳዮችና የ2019 የሥራ ዘመን ዕቅድ የትኩረት ነጥቦች ላይ ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

በመድረኩ የጉራጌ ዞን ቴ/ሙ/መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ስርገማ፣ የኮሌጁ ዲን አቶ ኸይሩ አህመዲን፣ የዕለቱ የክብር እንግዳ የፌደራል ቴ/ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት መምህር ዶ/ር ፊጣ አያሌው፣ ም/ዲኖች፣ መምህራንና የአስ/ሠራተኞች ተገኝተዋል።

በመድረኩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የዞኑ ቴ/ሙ/መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ስርገማ እና የኮሌጁ ዲን አቶ ኸይሩ አህመዲን በቅደም ተከተል የመክፈቻ ንግግራቸውን አድርገዋል። በንግግራቸውም የተቋሙን የሥራ አፈጻጸም በየጊዜው መገምገም፣ የተገኙ ውጤቶችን ማጠናከር፣ የታዩ ክፍተቶችን በመለየት የማሻሻያ እርምጃ መውሰድና የቀጣይ የሥራ ዘመን ዕቅድን በተጨባጭ የሥራ አቅጣጫዎች ላይ መመስረት እንደሚገባ አፅንዖት ሰጥተዋል።

በመቀጠል የኮሌጁ የልማት ዕቅድ የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ሀብቴ አገዘ የ2018 የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 ዕቅድ እንዲሁም በመቀጠል አቶ ዳንኤል አስፋው የISO ኦዲት ግብረ-መልስን በቅደም ተከተል በዝርዝር አቅርበዋል።

የሪፖርትና የግብረ-መልስ ተከትሎ በኮሌጁ ዲኖች መሪነት አጠቃላይ ውይይት ተካሂዷል። ተሳታፊዎችም በ2018 የሥራ ዘመን የተገኙ ስኬቶችን በማስቀጠል፣ የታዩ ክፍተቶችን በመፍታትና የ2019 ዕቅድን በተቀናጀ መልኩ በመተግበር የኮሌጁን የሥራ አፈጻጸም የበለጠ ለማሻሻል እንደሚሰሩ ሀሳቦችን አንስተዋል። በተለይም ደግሞ የISO ትግበራ ላይ የተገኘውን ውጤታማነት የማስቀጠልና የማሳደግ ተግባር በትኩረት መሰራት እንዳለበት መግባባት ላይ ተደርሷል።

በመጨረሻም በ2018 የሥራ ዘመን የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ መምህራን፣ የአስተዳደር ሠራተኞች፣ የዲፓርትመንት ተጠሪዎች እና የISO ትግበራ Task Force አባላት እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል። በልዩ ሁኔታ ደግሞ በኮሌጁ ውስጥ ባሳዩት የሥራ ትጋት፣ በISO ትግበራ ሂደት ያበረከቱት አስተዋጽኦ ለስኬት በማብቃት እና ለተቋሙ የነበራቸውን አገልግሎት ለማድነቅ ወደ አዲሱ የሥራ ቦታቸው ሲሸጋገሩ የተቋሙን ምስጋናና መልካም ምኞት በሚገልጽ ለበርካታ ዓመታት የኮሌጁ አባል በመሆን ላገለገሉት በአሁኑ ወቅት ወደ ፌደራል ቴ/ሙ/ስልጠና ኢንስቲትዩት ለተዘዋወሩት ዶ/ር ፊጣ አያሌው ልዩ እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል። በተጨማሪም ለሁሉም የት/ትና የስራ ክፍሎች የISO ሰርተፍኬት ርክክብ ተደርጓል። ከእውቅናና ሽልማቱ በተጨማሪ የኮሌጁ ማህበረሰብ በየወሩ በሚያዋጣው መዋጮ በቋሚነት ለሚያስተምራቸው የአቅመ-ደካማ ቤተሰብ ልጆችም የትምህርት ቁሳቁስና አልባሳት ድጋፍ ተደርጎላቸዋል

በአጠቃላይ መድረኩ በተቋሙ የ2018 ልምዶችንና ውጤቶችን በመነሻነት የ2019 ዕቅድን በተቀናጀ መልኩ ለመፈጸም የጋራ መግባባት በመፍጠር በስኬት ተጠናቋል።
-----------------------------
!
!
፦
Tiktok tiktok.com/
Facebook https://w.facebook.com/wolkite poly technic college & satellite institute
Website:- https://wptc.gov.et/
Telegram:- https://t.me/wptc2000
!

 !! !!
22/09/2026

!!
!!

 #ማስታወቂያ!! !!
21/09/2026

#ማስታወቂያ!!
!!

🏆🎉🌷  !!🌷🎉🏆============================የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ ባዘጋጀው የሴክተር ጉባኤ ላይ በ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈ...
18/09/2026

🏆🎉🌷 !!🌷🎉🏆
============================
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ ባዘጋጀው የሴክተር ጉባኤ ላይ በ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም መሠረት ኮሌጃችን በየዘርፉ 2ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫ፣ ሰርተፍኬት፣ የላፕቶፕ ተሸላሚ መሆን የቻለ ሲሆን የISO 21001፡2025 የትምህርት ድርጅት ማኔጅመንት ሲስተም(EOMS) በአግባቡ በመተግበርና በተቀመጠው ቀነ-ገደብ በማጠናቀቅ ሰርተፍቱን በማግኘት በሀገርም ሆነ በክልል ደረጃ ብቸኛ ኮሌጅ መሆን በመቻሉ በተጨማሪ በልዩ ተሸላሚነት የዋንጫ፣ ሰርተፍኬት፣ የላፕቶፕ፣ ኮምፒውተር ከነፕሪንተሩ ተሸላሚ መሆን ችሏል።

🌷🏆 💐ይህም የመላው የኮሌጁ አመራር፣ መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች የጋራ ስኬት የተገኘው በትጋት፣ በቁርጠኝነት፣ በቡድን ሥራ እና በጥራት ባለው አመራርነት ውጤት በመሆኑ ለመላው የኮሌጁ ማህበረሰብ እንኳን ደስ አላችሁ/አለን በማለት ደስታችንን ለመግለፅ እንወዳለን! 🎊🌷🏆
-----------------------------
!
!
፦
Tiktok tiktok.com/
Facebook https://w.facebook.com/wolkite poly technic college & satellite institute
Website:- https://wptc.gov.et/
Telegram:- https://t.me/wptc2000
!

Address

Near To Wolkite Stadium
Welk'it'e

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+251113301590

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolkite Poly Technic College & Satellite Institute posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Wolkite Poly Technic College & Satellite Institute:

Shortcuts

Share