17/08/2026
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሳይበር ደህንነት ስርዓቱን ይበልጥ ለማጠናከር እና የደንበኞችን ገንዘብ ከዘራፊዎች ለመጠበቅ የሚያስችል ዘመናዊ የ AI ቴክኖሎጂ ማስተዋወቁን አስታውቋል።
ይህ የተገለጸው የባንኩ የኢንፎርሜሽን ሲስተም ደህንነት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ስዩም ዳምጠው ሰሞኑን በአዲስ አበባ በተካሄደው 29ኛው የ'Connected Banking Summit' ላይ ባቀረቡት ሪፖርት ነው።
የቴክኖሎጂው ዋና ዋና ጥቅሞች፦
🤖 የግብይት ማጭበርበርን በቅጽበት መለየት፦ ቴክኖሎጂው የደንበኞችን መደበኛ የገንዘብ ዝውውር ባህሪ በማጥናት፣ ያልተለመደ እና አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ሲፈጠር በቅጽበት ይለያል። አደጋ (Risk) መኖሩን ሲያረጋግጥም ዝውውሩን ያገዳል ወይንም ተጨማሪ ማረጋገጫ (Verification) ይጠይቃል።
📱 የሞባይል ባንኪንግ ደህንነት ጥበቃ (RASP)፦ በደንበኞች ስልክ ላይ ሊኖሩ የሚችሉ አደገኛ ቫይረሶችን (Malware) እና ያልተፈቀዱ የጠላፊዎች አፕሊኬሽኖችን በመለየት፣ ስጋት ሲፈጠር አጠራጣሪ ዝውውሮችን ወዲያውኑ ያቋርጣል።
🔒 'Zero Trust' (ማንንም አለማመን) መርህ፦ ሲስተሙ የትኛውንም ተጠቃሚም ሆነ መሳሪያ በዘፈቀደ ከማመን ይልቅ፣ በእያንዳንዱ የኔትዎርክ እንቅስቃሴ ላይ ተከታታይ እና ጥብቅ ማረጋገጫዎችን ይጠይቃል።
ከዚህ በተጨማሪም ባንኩ ከሶስተኛ ወገን (Third-party) አቅራቢዎች ጋር በሚኖረው የቴክኖሎጂ ትስስር ላይ ጥብቅ የደህንነት ፍተሻዎችን እና የዳታ ልውውጥ ቁጥጥሮችን ተግባራዊ ማድረጉ ተገልጿል።