ትምህርት መረጃ/Academic information

ትምህርት መረጃ/Academic information education information
(3)

ወቅታዊና ታማኝ መረጃወች @ትምህርት መረጃ( academic info)
Telegram: https://t.me/academic_info
Facebook: https://www.facebook.com/share/1EqNsbE4CN/
email: [email protected]
Instagram:https://www.instagram.com/academicinfor?igsh=ZW8xc2J0MXdxdDVj

05/27/2026

ሰኞ ግንቦት 24 ሥራ ዝግ ነው።

ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ/ም በፌዴራል እና ክልል መንግሥታዊ ተቋማት እንዲሁም የግል ተቋማት ሥራ ዝግ ሆኖ ይውላል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚካሄደውን የ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥቷል።

ቦርዱ፦

- ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ የፌዴራል እና የክልል መንግሥታዊ ተቋማት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ሥራ ዝግ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

- ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ በፌዴራል እና በክልሎች የሚገኙ ማንኛውም መንግሥታዊ ያልሆኑ እና የግል ተቋማት በተመሳሳይ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ዝግ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

- የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት፣ ሆስፒታሎች፣ የዕለት ተዕለት አገልግሎት ሰጪዎችም (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፓርት አገልግሎት) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ እንዲያከነውኑ ፤ የመተባበር ግዴታው እነዚህን ተቋማት እንቅስቃሴ መዘጋት እንደማያስገድድ አሳውቋል።

- የትራንስፓርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ የሚቀጥል ቢሆንም፤ ዜጎች ድምፅ ከመስጠት ውጪ ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚፈልጉ ሁነቶችን እና ዕቅዶችን እንዳይይዙ እና እንቅስቃሴያቸውን ድምፅ ለመስጠት ብቻ እንዲያደርጉ አረበታቷል።

የተከለሰ ካሌንደር አአ ከተማ አስተዳደር
05/26/2026

የተከለሰ ካሌንደር አአ ከተማ አስተዳደር

 ሀገር አቀፍ ፈተናዎች በሚሰጥባቸው የጊዜ መርሐግብር ላይ ማሻሻያ መደረጉን ሰምተናል። በዚህም፥➫ የሪሚዲያል ፈተና ከግንቦት 27/2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 03/2018 ዓ.ም ➫ የቅድመ-ምረቃ...
05/21/2026



ሀገር አቀፍ ፈተናዎች በሚሰጥባቸው የጊዜ መርሐግብር ላይ ማሻሻያ መደረጉን ሰምተናል።

በዚህም፥
➫ የሪሚዲያል ፈተና ከግንቦት 27/2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 03/2018 ዓ.ም

➫ የቅድመ-ምረቃ የመውጫ ፈተና ከሰኔ 04-12/2018 ዓ.ም

➫ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23/2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም የሚሰጡ መሆኑ ተገልጿል።

🔔 አስቸኳይ!የፊታችን ሰኞ መሠጠት የሚጀምረውን የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ለመውሰድ የተመዘገባቹ በአስቸኳይ የማረጋገጥ ሥራ እንድታደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።የማረጋገጥ ሥራው (Self...
05/21/2026

🔔 አስቸኳይ!

የፊታችን ሰኞ መሠጠት የሚጀምረውን የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ለመውሰድ የተመዘገባቹ በአስቸኳይ የማረጋገጥ ሥራ እንድታደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

የማረጋገጥ ሥራው (Self Verification) ከ2-3 ደቂቃዎች ብቻ የሚወስድና የተፈታኞችን የትምህርት ሰነዶች ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ለማስተሳሰር የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል።

ተከታዩን ሊንክ (https://verify.ethernet.edu.et/) ከተጫኑ በኋላ Remedial Examination የሚለውን ይጫኑ፣ Start Verification የሚለውን በመጫንና የሚያስፈልገውን በመሙላት ያረጋግጡ።

የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ከግንቦት 17-20/2018 ዓ.ም እእንደሚሰጥ ይታወቃል።

የ2018ዓም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና
05/21/2026

የ2018ዓም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና

05/19/2026

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመስጠት 667 የፈተና ማዕከላት ተዘጋጁ

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በ667 የፈተና ማዕከላት ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ገለፀ።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለፋና እንደገለጹት÷ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናን በ97 ዩኒቨርሲቲዎች እና በ570 የክልል ማዕከላት ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚሰጠው ፈተና መደበኛ ተማሪዎችን ጨምሮ በሁሉም ፕሮግራሞች በተፈጥሮ ሳይንስ 306 ሺህ 964 እንዲሁም በማህበራዊ ሳይንስ 257 ሺህ 255 በድምሩ 564 ሺህ 219 ተማሪዎች መመዝገባቸውን ገልጸዋል፡፡

ፈተናውን በሙሉ አቅም በበይነ መረብ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ÷ በተለያዩ ምክንያቶች ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ በወረቀት የሚፈተኑ ተማሪዎች እንደሚኖሩም ጠቁመዋል።

ከባለፈው አርብ ጀምሮ ለተፈታኞች የበይነ መረብ የሙከራ ፈተና መሰጠት መጀመሩንም አንስተዋል።

ፈተናው በ6 ዙር እንደሚሰጥና በማህበራዊ ሳይንስ በሶስት ዙር በተመሳሳይ በተፈጥሮ ሳይንስ ደግሞ በሶስት ዙር በመሆኑ አንድ ኮምፒዩተር ስድስት ተማሪን ያስተናግዳል ነው ሉት።

Ethiopia Statistical Service (ESS)Position: National Data collectors Workplace: Nationwide (in all regions and city admi...
05/17/2026

Ethiopia Statistical Service (ESS)

Position: National Data collectors

Workplace: Nationwide (in all regions and city administrations)
Requirements and Qualifications
We are looking for candidates who meet the following requirements:
Work Experience: No work experience is required. Selected candidates will receive full comprehensive training.
Age: Candidates must be under 45 years old.
Language: Must be able to speak the local language of the region or district where they will work.
Education: Must have at least a diploma or degree in any field of study.
Digital Knowledge: Must be comfortable using smartphones or tablets for data recording.
Physical Ability: Especially for those in rural or remote areas, must be able to travel from house to house and conduct interviews.
Application Process
Candidates can submit their applications only through the official Google Form link below. Applications submitted in person at the main office will not be accepted.

Application Link:
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSe4XM3uuUVM33hrVPKKQ7XZXmFfoxnbgMvsX2YHnyn9lUVW_Q/viewform?usp=publish-editor

05/17/2026

አካውንታችሁ ዝግ ነው ዲጂታል መታወቂያ ያላስተሳሰረ ብር ማንቀሳቀስ አይችልም ስለዚህ አስተሳስሩ በቀጣይ አይከፈታል

 የቅድመ-ምረቃ ትምህርት የመውጫ ፈተና በድጋሚ በግል ለመፈተን እየተጠባበቃችሁ የምትገኙ አመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ ግንቦት 08/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ይካሔዳል፡፡በመሆኑ...
05/16/2026



የቅድመ-ምረቃ ትምህርት የመውጫ ፈተና በድጋሚ በግል ለመፈተን እየተጠባበቃችሁ የምትገኙ አመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ ግንቦት 08/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ይካሔዳል፡፡

በመሆኑም የመመዝገቢያ ሊንኩን https://exam.ethernet.edu.et በመጠቀምና የተዘረዘሩ መስፈርቶችን በማሟላት ከግንቦት 08-12/2018 ዓ.ም መመዝገብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የአገልግሎት ክፍያ 750 ብር በቴሌብር በኩል መክፈል የሚጠበቅባችሁ ሲሆን፤ ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ የግድ የሚያስፈልግ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የ2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ከሰኔ 02-12/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወሳል፡፡

የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች የሚለማመዱባቸው  አድራሻዎች ይፋ ሆኑ። (ግንቦት 6/2018 ዓ.ም) የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 ትምህር...
05/15/2026

የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች የሚለማመዱባቸው አድራሻዎች ይፋ ሆኑ።

(ግንቦት 6/2018 ዓ.ም) የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች የሚለማመዱባቸው አድራሻዎች ይፋ አድርጋል።

የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በበይነ መረብ (CBT) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ የሚገኝ ሲሆን ሁሉም ተፈታኞች በተደለደሉበት ክልል ወይም ከተማ አስተዳደር ትይዩ ባለው ማስፈንጠሪያ በመጠቀም USER Name በሚለው ላይ የፈተና አዳራሽ መግቢያ ካርድ ላይ ያለውን አድሚሽን ቁጥር በማስገባት እና Pass word በሚለው ላይ 1234 በማስገባት በዴስክቶፕ ኮምፕዩተር፣ በላፕቶፕ ኮምፕዩተር፣ በታብሌት፣ በስልክና በመሰል የኤልክትሮኒክስ መሣሪያዎች ማንኛውንም ዓይነት ኢንተርኔት አማራጭ በመጠቀም ከግንቦት 07/2018 ዓ/ም ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከፈተናው ድረስ መለማመመድ ይችላሉ ተብላል።

ተፈታኞች አዲሚሽን ካርድ ከየትምህርት ቤቶቻቸው ማግኘት የሚችሉ ሲሆን በየጊዜው የተለያዩ የሚለማመዱባቸውን ፈተናዎች በተከታታይ የሚሰጥ መሆኑን ፈተናዎች አገልግሎት ገልፃል።

ስለሆነም መምህራን ፣ የትምህርት ቤት አመራርና ወላጆች ተፈታኞቹ እንዲለማመዱ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንዲያደርጉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ጥሪ አቅርባል።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc

Address

Edmonton, AB

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ትምህርት መረጃ/Academic information posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to ትምህርት መረጃ/Academic information:

Share