Ayase tube - አያሴ ቲዩብ

Ayase tube - አያሴ ቲዩብ እየተዝናኑ ቁም ነገር የሚያገኙበት ድረ ገጽ ነው .....

15/04/2022
ቤተሰብ ይሁኑኑኑኑኑኑ ከታች ያለውን lïñķ በመጠቀም ...https://youtu.be/E42hZfpaoxwከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግንሃለን
09/04/2022

ቤተሰብ ይሁኑኑኑኑኑኑ ከታች ያለውን lïñķ በመጠቀም ...
https://youtu.be/E42hZfpaoxw

ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግንሃለን

09/04/2022
06/04/2022

እግዚኦ....የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጉድ!! ስለ ሴክስ ፓርትነር ምን ያውቃሉ? | Ethiopia | Addis Ababa University us on the following links http://yegna.abyssi...

06/04/2022
31/03/2022

🌀✅ የሶቅራጠስ 3ቱ ጠቃሚ ጥያቄዎች ✅🌀

አንድ ሠው ሶቅራጠስ ወዳረፈበት እልፍኝ ሄዶ እንዲህ አለው፡፡

‹‹ሶቅራጠስ ወዳጄ፣ እገሌ ስለተባለው ወዳጅህ ዛሬ የሠማሁት ነገር ምንም ደስ አይልም›› አለው፡፡

ሶቅራጦስ መከዳው ላይ እንደተደገፈ መልስ ሳይሰጠው ዝም አለ፡፡

ሠውየውም እንደገና ‹‹ይገርማል ከእርሱ አይጠበቅም፤ በጣም ገርሞኛል›› ሲል ተናገረ፡፡

ሶቅራጦስ፣ ይህ ሠው በቀላሉ እንደማይፋታው ስለተረዳ አንድ መደራደሪያ አቀረበለት፡፡ ‹‹ስለ ወዳጄ ልትነግረኝ የፈለግከውን እንድሠማህ ከፈለግህ ሶስት ጥያቄዎች አሉኝ፤ እነርሱን በቅድሚያ ልትመልስልኝ ይገባል! ይህ ሲሆን ብቻ ነው የምሰማህ›› አለው፡፡

ሠውየው ለወሬው ቢቸኩልም አማራጭ ስላልነበረው በሶቅራጠስ ሀሳብ ተስማማ፡፡

‹‹የመጀመሪያው ጥያቄዬ የእውነት ጥያቄ ነው" አለ ሶቅራጠስ። "ስለወዳጄ የሠማኸው መቶ በመቶ እውነት ነው ወይ?›› ሲል ጠየቀ፡፡

ሠውየውም፡- ‹‹መቶ በመቶ እንኳን እርግጠኛ መሆን አልችልም›› ሲል እያመነታ መለሰለት፡፡

‹‹በጣም ጥሩ! ልትነግረኝ የፈለግከው እርግጠኛ ያልሆነ ነገር ነው ማለት ነው፡፡ እሺ ሁለተኛው ጥያቄዬ የመልካምነት ነው፡፡ የምትነግረኝ መልካም ነገር ነው ወይ?›› ሲል ሶቅራጠስ አቀረበ ጥያቄውን፡፡

ሠውየውም፡- ‹‹እርሱማ መልካም አይደለም›› አለ ቱግ ብሎ፡፡ የሶቅራጠስ ጥያቄዎች ለማውራት የቋመጠለትን ወሬ እንዳያወራ እንቅፋት መስለው ታዩት።

ሶቅራጦስም ‹‹እውነትነቱ ያልተረጋገጠና መልካም ያልሆነ ነገር ልትነግረኝ ፈልገሃል፡፡ እሺ ሶስተኛውና የመጨረሻው ጥያቄዬን ልጠይቅህ?›› አለው፡፡

ሠውየውም ጥያቄውን ለመስማት ፈጥኖ ‹‹እሺ›› አለ፡፡

ሶቅራጦስ ጠየቀ፤ ‹‹የምትነግረኝ ነገር ለእኔ የሚጠቅመኝ ነገር አለው ወይ?››

‹‹የለም! የለም! መጥቀም እንኳን አይጠቅምህም። ብቻ ብትሰማኝ...›› ብሎ ሰውዬው መቅለስለስ ጀመረ።

ይሄን ጊዜ ሶቅራጦስ ‹‹ታዲያ እንደምን አድርጌ እውነትነቱ ያልተረጋገጠ፤ መልካም ያልሆነ እና ለእኔ ምንም ጥቅም የሌለው ነገር ልንገርህ ስትለኝ እንዴት እሰማሃለሁ። ዞር በል ካጠገቤ አልሰማህም!!›› አለው ይባላል፡፡

ስንቶቻችን ነን ሰው የሚነግረን ነገር እውነት፣ መልካምና ጠቃሚ መሆኑን አጣርተን የምንሰማው? ስንቶቻችን ነን ለሰው ቁምነገር ብለን ልንናገር ስንል ከሶስቱ አንዱን ማሟላቱን የምናረጋገጠው? አሁን እኮ ሰው ዝም ብሎ የተነገረውን ስለሚሰማ በቀላሉ እንደ እንስሳ የሚነዳ ሆኗል፡፡ በየሶሻል ሚዲያው ላይ ፖስት የሚደረጉት ብዙዎቹ መረጃዎች እውነት ያልሆኑ፣ መልካምነት የሌላቸው እና ለእኛ ምንም ጥቅም የማይሰጡ ናቸው፡፡ በተቃራኒው የውሸት መረጃዎች ሆነው ስንቱን ያጭበረበሩ፣ ሰይጣናዊ ርምጃ ለመውሰድ የሚገፋፉ ሆነው ሳለ ያለማቅማማት እንሰማቸዋለን፡፡

አሁን አሁን እውነት ከሚናገሩት ሰዎች በላይ በመርዝ የተለወሰ ውሸት የሚናገሩ ሰዎች የተሻለ ብዙ ተከታይ አላቸው፡፡ መልካም መልካሙን ከሚሰብኩ ሰዎች ይልቅ የጥፋት ሰባኪዎች ብዙ ደጋፊ አላቸው፡፡ ፍለጠው/ቁረጠው ባዮች ናቸው የጀገኑት፡፡ እነሱን ማስቆም አይቻል ይሆናል፤ ነገር ግን እነሱን አለመስማት/አለመከተል ቀላል ነው፡፡ እነዚህን የሶቅራጠስ 3ቱ ጥያቄዎችን እንደ ወንፊት ተጠቅመን ማጣራት ብቻ በቂ ነው፡፡ ✳✴✳

🚺🚹 ፅሁፉን ፣ጠቃሚ ሆኖ ካገኛችሁት ሼርርርር አድርጉት
ምርጥ መጣጥፎች

26/03/2022

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ayase tube - አያሴ ቲዩብ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Ayase tube - አያሴ ቲዩብ:

Share