11/06/2026
የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ወቅታዊ መረጃ
ለፈተና ተቀማጭ ተማሪዎች የተሰጡ መመሪያዎችና ደንቦች
የፈተና ተፈታኞች ኃላፊነቶች
ፈተናው ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ በፊት የማንነት መታወቂያዎን (ID) በመያዝ በፈተና ክፍሉ ውስጥ ይገኙ።
ፈተናው ከተጀመረ ከ15 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው!
ፈተናው በጀመረ በመጀመሪያዎቹ 30 ደቂቃዎች ውስጥ ከፈተና ክፍል መውጣት አይፈቀድም።
በተሰጠዎት ነጭ ወረቀት ላይ የተጠቃሚ ስምዎን (Username) እና የይለፍ ቃልዎን (Password) ጽፈው በጥንቃቄ ይያዙ።
በፈተና ተቆጣጣሪዎች በተመደበልዎት ወንበር ላይ ብቻ ይቀመጡ።
የእርስዎን ኮምፒውተር ብቻ ይጠቀሙ እና ይክፈቱ።
በፈተና ክፍል ውስጥ ማውራትም ሆነ መዘዋወር በጥብቅ የተከለከለ ነው።
በአጠገብዎ ያለውን ተማሪ ኮምፒውተር ለማየት አይሞክሩ።
በፈተና ክፍሉ ውስጥ የሞባይል ስልክዎን ያጥፉ።
ማንኛውንም ዓይነት ወረቀት ወደ ፈተና ክፍል ይዞ መግባት አይቻልም።
ከማንኛውም ዓይነት የማጭበርበር ወይም የኩረጃ ተግባር ይቆጠቡ።
የፈተና ተቆጣጣሪዎችን እና አስተባባሪዎችን መመሪያዎች በትክክል ይከተሉ።
መልካም ዕድል! 🙏
Instructions and Guidelines for the Exit Exam
Responsibilities of Students Taking this Exam
1. Arrive at the exam room 30 minutes early with your ID.
2. Do not stop studying more than 15 minutes after the exam has started!
3. Do not leave the exam room within the first 30 minutes after the exam has started.
4. Write down and keep your Username and Password on the white paper provided.
5. Only sit in the seat assigned by the exam supervisors.
6. Use and open only your own computer.
7. Do not talk or move around the exam room.
8. Do not look at the computer of the student next to you.
9. Turn off your mobile phone in the exam room.
10. Do not bring any papers into the exam room.
11. Avoid and do not participate in any form of cheating or fraud.
12. Follow the instructions of the exam supervisors and coordinators.
Good luck 🙏