Ethiopian Academic Staffs Union of Universities-EASUU

Directions Contact the university

Ethiopian Academic Staffs Union of Universities-EASUU We aim to unite all academic staffs through out Ethiopian Universities.

12/08/2026

1. የባህር ዳር #ዩኒቨርሲቲ መፈክር (BDU): "Wisdom at the Source of the Blue Nile" (ከአባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ)

2· መቀሌ ዩኒቨርሲቲ: "We Really Care"

3· ራያ ዩኒቨርሲቲ: "Knowledge for Societal Change!" (እውቀት ለማህበረሰባዊ ለውጥ!)

4· አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ (AMU): "We grow in the esteem of future generation" (ወደፊት ትውልድ አክብሮት እያገኘን እናድጋለን)

5· ወሎ ዩኒቨርሲቲ (WU): "Knowledge for Sustainable Development" (እውቀት ለዘላቂ ልማት) ወይም "Striding for Quality" ("ለጥራት እንተጋለን")

6· ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ (DBU): "Practical education for better success" (ተግባራዊ ትምህርት ለተሻለ ስኬት)

7· ዲላ ዩኒቨርሲቲ: "The University of the Green Land" (የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ)።

8. ጎንደር ዩኒቨርሲቲ (UoG): የበፊቱ = "የሰላሙ ዩኒቨርሲቲ /University of Peace/ ነው፡፡ ያሁኑ = Devoted For Excellence/ለልህቀት እንተጋለን/ ነው፡፡

9· ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ (DMU): "Grow wiser at the water tower" / "የዕዉቀት አዉድማ ከጮቄ ማማ"

10. ሚዛን–ቴፒ ዩኒቨርሲቲ (MTU): "Light of The Green Valley" (የአረንጓዴው ሸለቆ ብርሃን) ።

11· ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ (WKU):
"ለጥበብ እንተጋለን/"We Strive for Wisdom"/

12· አሶሳ ዩኒቨርሲቲ (ASU): "Idol or Icon of excellence" (የልህቀት ምሳሌ)

13. ሰመራ ዩኒቨርሲቲ (SU): "We serve the community!" (ህብረተሰቡን እናገለግላለን!) ።

14· አክሱም ዩኒቨርሲቲ (AXU): "Excellence Through Perseverance" (በጽናት ወደ ልህቀት)

15. ጅማ ዩኒቨርሲቲ (JU): "We are in the Community" (እኛ በማህበረሰቡ ውስጥ ነን)

16. ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ፡ Let Your Light Shine in The Soceity (ብርሃናችሁ በማህበረሰቡ ዉስጥ ይብራ)

17. ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ፡ We Strive For Excellence/ለላቀ ለውጥ እንተጋለን/

18· አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU): "We are dedicated to innovative knowledge" (ለፈጠራ እውቀት የተሰጥን ነን)

19· ሃራማያ ዩኒቨርሲቲ (HU): Build Basis For Development

20. ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ፡ Historical duty to answer Tewodros quest knowledge

21. እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ፡ Explore Your Creative Potential (ያለህን እመቅ ሀይል ለይተህ ተጠቀም)

22. ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ፡ Knowledge in Action/እውቀት በተግባር/

23. አድግራት ዩኒቨርሲቲ፡ Hardwork Our Hall Mark

24. ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ፡ "አዕምሮ ሲከፈት ዓይኖች ይከፈታሉ/Open Mind Open Eyes/

25. ወለጋ ዩኒቨርሲቲ፡ Icon of Quality

26. አዲስ አበባ (AAU): "Honoring Our Past, Reimagining Our Future" (ያለፈውን አክብረን፣ የወደፊቱን እንደገና ማሰብ)

27. ማዳ ዋላቡ ዩኒቨርሲቲ: "Excellence through Diversity" (በብዝሃነት ወደ ልህቀት)

28. ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፡ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ – "Ever to Excel!" (ሁልጊዜ ወደ ላቀ ስኬት)

29. ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ፡ በጋራ እንችላለን/Together We Can/

30. Mettu University – "We Are Dedicated To Serve The Community"

31. Jigjiga University – "Knowledge for Peace and Development." "ዕውቀት ለሰላምና ለልማት")

32. የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ (GU): "Building Generations"

33. ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ (DU): "Our success mount on educational Quality"

34. የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ (MAU) ፡ "Striving for Change/ለለውጥ እንተጋለን/"

35. ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ (DDU): "Empowering Generation" (ትውልድን ማብቃት)

36. የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ (Salale U): "Co-Creating Quality" ( "ጥራትን በጋራ መፍጠር")

37. ዲሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ፡ "Striving to make a difference" (ልዩነት ለመፍጠር እንተጋለን)

38. አርሲ ዩኒቨርሲቲ፡ "Like Our Star Athletes, Excelling Professionals" (እንደ ኮከብ አትሌቶቻችን፣ የላቁ ባለሙያዎች)

39. አምቦ ዩኒቨርሲቲ፡ "Better Future Through Knowledge and Wisdom" (በእውቀትና በጥበብ የተሻለ የወደፊት)

40. ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ፡ "Education for Community Development" (ትምህርት ለማህበረሰብ ልማት)

41. ወራቤ ዩኒቨርሲቲ፡ "Knowledge for Excellence" (እውቀት ለልህቀት)

42. ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ (KUE)፡ "Committed to Excellence in Education"

43. ጂንካ ዩኒቨርሲቲ፡ Knowledge for Change

44. ቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ (KDU): _????

45. ቦረና ዩኒቨርሲቲ፡ __????

የዕለታዊ ትምህርት ዕቅድ ዝግጅት መመሪያ!
PDF እዚ ላይ ማግኘት ትችላላችሁ
👉 https://bit.ly/4g0N6hl

12/08/2026

ማስታወቂያ

የ ኢፌዴሪ የትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት በሚሰጥባቸው የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የ9ኛና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል። በመሆኑም በልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶቹ ተመዝግባችሁ ለመማር ፍላጎቱ ያላችሁና መስፈርቱን የምታሟሉ ተማሪዎች በዚህ ሊንክ https://sbs.moe.gov.et/apply መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

✍️ ነጻ የትምህርት እድሉ የሚሰጣቸው ጥቅሞች
👉 ሙሉ የትምህርት ክፍያ ሽፋን
👉 የመኝታና የምግብ አገልግሎት
👉 የተሟላ እና ልዩ ሥርዓተ ትምህርት የሚከተል ጥራት ያለው ትምህርት
👉 ምቹ የመማሪያ አካባቢ
✍️ትምህርት የሚሰጥባቸው ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች
✍️ 9ኛ እና 10ኛ ክፍል
👉 ቡኢ ልዩ አዳሪ
👉 ጅግጅጋ ልዩ አዳሪ
👉 ጋምቤላ ልዩ አዳሪ
👉 ወሊሶ ልዩ አዳሪ
👉 ቦንጋ ልዩ አዳሪ
✍️ 9ኛ ክፍል ብቻ
👉 አርባ ምንጭ ልዩ አዳሪ
👉 ድሬዳዋ ልዩ አዳሪ
👉 አሶሳ ልዩ አዳሪ
👉 ባህር ዳር ልዩ አዳሪ
የመመዝገቢያ መስፈርቶች
✍️ ለ9ኛ ክፍል ተመዝጋቢዎች
👉 የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና አማካይ ውጤት 85 በመቶ እና በላይ አማካኝ ውጤት ያለው/ያላት እንዲሁም በእንግሊዝኛና በሂሳብ ትምህርቶች 80 እና በላይ ያመጣ/ያመጣች ።
👉 ጥሩ ስነ -ምግባር ያለው/ያላት

✍️ ለ10ኛ ክፍል ተመዝጋቢዎች
👉በ2017 የትምህርት ዘመን በ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና 70 እና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች
👉በ9ኛ ክፍል ትራንስክሪብት 85 በመቶና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች እንዲሁም በእንግሊዝኛ እና ሂሳብ ትምህርት ዓይነት 80 በመቶና በላይ ያመጣ/ያመጣች።
✍️ የምዝገባ ሁኔታ
👉 ባሉበት በበየነ መረብ ( Online) ይመዝገቡ፡_ https://sbs.moe.gov.et/apply
✍️ መስፈርቱን የምታሟሉ ተማሪዎች ምዝገባችሁን ባላችሁበት ቦታ ሆናችሁ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የመመዝገቢያ ፖርታል በኦንላይን መመዝገብ እና አስፈላጊ የተባሉ መረጃዎችን ማያያዝ ይጠበቅባችኋል
✍️ ምዝገባው እስከ ነሃሴ 15/2018 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል።
✍️ ለፈተና የሚቀርቡ ተማሪዎች ዝርዝር እና የፈተና ጊዜ ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል
✍️ የመመልመያ መስፈርቱን አሟልተው ፈተናውን የሚያልፉ ተማሪዎች ባሉን ክፍት ቦታዎች በሚመደቡበት ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ለመማር ፈቃደኛ የሆኑ መሆን አለባቸው።

26/05/2026
26/05/2026
07/12/2025

All major Universities set to open new campus in all major cities in Ethiopia and even in east African countries. This will crash all 2nd, 3rd and 4th generation Universities, I don't know if there is 5th generation too, if there is say goodbye!

Now, universities have to open campuses everywhere and compete among each other. This pursuit is primarily about attracting more students to maximize profit and ensure Universities' survival. Welcome to Et-Autonomous Universities, this is often called the neoliberalism.

Time to support and develop an Et-Universities Artificial Intelligence (AI) use guideline for our Unis.
07/12/2025

Time to support and develop an Et-Universities Artificial Intelligence (AI) use guideline for our Unis.

14/08/2025

Credit, sheger FM
በሀላፊነት ላይ ያለ የመንግስት ሹመኛ ወይም ተመራጭ ለ እንዳይታጭ የሚከለክል መመሪያ የትምህርት ሚኒስቴር አወጣ፡፡
መመሪያው 8 ዙር ተማሪዎችን ያላስመረቁ እና ሶስተኛ ዲግሪ ወይም (PhD) የማያስተምሩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት እንዳይሰጡ ይከለክላል፡፡
በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ሃምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ተፈርሞ ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የተመራው ይህ መመሪያ በቅርብ ጊዜ የተመሰረቱ የትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት እንዳይሰጡ ይከለክላል፡፡
በመመሪያው ክፍል ሁለት ላይ የክብር ዶክትሬት የሚሰጡ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መስፈርትን በተመለከተ የተቀመጠው ድንጋጌ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት ለመስጠት ቢያንስ ከ8 ጊዜ በላይ ተማሪዎችን ያስመረቁ እና የሶስተኛ ዲግሪ የሚሰጡ መሆን እንዳለባቸው ያስገድዳል፡፡
በዚህም መሰረት ሰላሌ፣ ደምቢ ዶሎ፣ መቅደላ አምባ፣ ራያ፣ ደባርቅ እና መሰል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ስምንት ዙር ተማሪዎችን ስላላስመረቁ በመመሪያው መሰረት የክብር ዶክትሬት መሰጠት አይችሉም፡፡
በዚሁ ክፍል ስር ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት ማዕረግ ለመስጠት አገር እና አለም አቀፍ መስፈርቶችን ማሟላት እንዳለባቸው ሰፍሯል፡፡
በሞያ መስኩ የተለየ ስራ ያበረከተ ከሆነ ኢትዮጵያዊም ሆነ ሌላ ዜጋ የክብር ዶክትሬት ማዓረግ ማግኘት እንደሚችል የዘረዘረው መመሪያው መስፍርቱን ካሟሉ ለግለሰብም ይሁን ለቡድን መስጠት እንደሚቻል አመላክቷል፡፡
በሕይወት ላለም ይሁን ለሌለ ሰው ማዕረጉን መስጠት እንደሚቻል የሚፈቅደው ይህ መመሪያው የክብር ዶክትሬት ለማግኘት የማይቻልባቸውን ገደቦችም በክፍል ሁለት አንቀጽ 10 ስር ዘርዝሯል፡፡
በዚህም መሰረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ የሙሉ ሰዓት ተቀጣሪ ሰራተኛ፣ የሴኔት አባላት ወይም የአስተዳደር አካላት ከተቋሙ ጋር ያላቸው ቀጥተኛ ግንኙነት እስካላበቃ ድረስ ለክብር ዶክትሬት መታጨት እንደማይችሉ ደንግጓል፡፡
መመሪያው በስራ ላይ ያሉ የመንግስት ሹሞች ወይም ባለስልጣናት ለክብር ዶክትሬት እንዳይታጩም የሚከለክል ነው፡፡
የክብር ዶክትሬት የተሰጠው ግለሰብ ዶክተር፣ የክብር ዶክተር እና መሰል መጠሪያዎችን ከሰጪው ተቋም ውጪ በየትኛውም ድርጅት ውስጥ መጠቀም እንደማይችሉም ደንግጓል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር በለፈው ዓመት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሽምያ የሚሰጡ የክብር ዶክትሬት ማዕረጎች መመሪያ እስኪወጣ ድረስ እንዲያቆሙ ማዘዙ ይታወሳል፡፡

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Academic Staffs Union of Universities-EASUU posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Ethiopian Academic Staffs Union of Universities-EASUU:

Shortcuts

Share