እዚህ ሰፈር Gedeo

እዚህ ሰፈር Gedeo GedeoDhugatee miteefat✊👊 jabate

15/05/2026
በዲላ ከተማ አስተዳደር የምርጫ ምልክት የቀደደው ግለሰብ በ2 ወር የግዳጅ ስራ ቅጣት ተቀጣዲላ፡ግንቦት፣ 7/2018 ዓ.ምበዲላ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት ያለበትን ወረ...
15/05/2026

በዲላ ከተማ አስተዳደር የምርጫ ምልክት የቀደደው ግለሰብ በ2 ወር የግዳጅ ስራ ቅጣት ተቀጣ

ዲላ፡ግንቦት፣ 7/2018 ዓ.ምበዲላ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት ያለበትን ወረቀት በመቅደድ ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘው አማኑኤል አብርሃም የተባለ ግለሰብ በ2 ወር የግዳጅ ስራ ቅጣት እንዲቀጣ የዲላ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላለፈ።

ተከሳሹ ወንጀሉን የፈጸመው ግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 2 ሰዓት ገደማ በሴሳ ክፍለ ከተማ አንዲዳ ቀበሌ ልዩ ስሙ ዳላቻ ቀጠና ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑ በችሎቱ ተብራርቷል።

የዲላ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ አማኑኤል አብርሃም የምርጫ ምልክት በመቅደድ የፈጸመው ድርጊት በማስረጃ በመረጋገጡ ጥፋተኛ ነው ብሎታል።

በዚህም መሰረት ግለሰቡ ለ2 ወራት የሚቆይ የግዳጅ ስራ ቅጣት እንዲቀጣ ወስኗል።

ተከሳሹ ቀደም ሲል የቀረበበትን ክስ ሐሰት ነው በማለት የክህደት ቃል ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም የዲላ ከተማ ፖሊስ ከዐቃቤ ሕግ ጋር በመተባበር የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን አደራጅተው በማቅረባቸው ጥፋተኝነቱ ሊረጋገጥ ችሏል።

እንደ ፍርድ ቤቱ መግለጫ ከሆነ ተከሳሹ ጥፋተኛ የተባለው በኢትዮጵያ የምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 158 ሥር የተደነገገውን የተከለከለ ተግባር በመጣሱ ነው።

ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ ውሳኔ ሲያስተላልፍ ቅጣቱ ተከሳሹን የሚያርምና ሌሎች መሰል ድርጊት ከመፈጸም እንዲቆጠቡ ትምህርት የሚሰጥ መሆን አለበት በማለት የ2 ወር የግዳጅ ስራ ቅጣቱን መወሰኑን አስታውቋል።

ዘገባው፦ተስፋልደት ወርቁ
ምስል፦አቤኔዘር ስዩም

ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸው ተገለፀ እነዚህ ካልተባረሩ የትግራይ ህዝብ ሰላም አይኖረውም ሲሉ ጌታቸው ረዳ  ተናግረዋል ::​በትግራይ ክልል ለሦስ...
05/05/2026

ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸው ተገለፀ

እነዚህ ካልተባረሩ የትግራይ ህዝብ ሰላም አይኖረውም ሲሉ ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል ::

​በትግራይ ክልል ለሦስት ዓመታት ተቋርጦ የቆየው የክልሉ ምክር ቤት በድጋሜ በመሰባሰብ ባካሄደው ጉባኤ ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን የክልሉ ፕሬዝዳንት አድርጎ መምረጡ ተዘግቧል ።

ምክር ቤቱ ወ/ሮ ኪሮስ ሓጎስን አፈ ጉባኤ፣ ወ/ሮ ምህረት በርሄን ደግሞ ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ በመሾም ጉባኤውን አጠናቋል።

ሥልጣናቸውን በሰላም ካስረከቡ ችግር አይገጥማቸውም በሚል ከህወሓት በኩል ጫና የበረታባቸው ጀነራል ታደሰ፣ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከርዮት ጋር በነበራቸው ቆይታ በሰጡት ምላሽ፣ “እኔ የማስረክበው ነገር የለም ማለታቸው ይታወሳል ።

ይህ አጥፊ አካሄድ ተገቢ እንዳልሆነ እየገለጽኩ ነው። የለም በዛ መንገድ እንሄዳለን ካሉ ግን እንደፈለጉ ያድርጉ” ማለታቸው ይታወቃል::

"የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ለትግራይ ህዝብ የተስፋ ብርሃን ፈንጥቆ የነበረ ቢሆንም፣ የህወሓት አመራሮች ግን እንደገና የጦርነት ነጋሪት እየጎሰሙ ነው ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ እና የስምረት ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ መግለፃቸው ይታወቃል::

ጦርነት መፍትሄ ሳይሆን ለትግራይ ህዝብ ቀጣይ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ውድመት መሆኑን ሊገነዘቡት ይገባል ያሉትን መዘግባችን ይታወቃል::

ጌታቸው ረዳ ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያ በሰጡት አጭር ምላሽ "የሙሽሪት ጅራት የሚባለው የልጆች ጨዋታ፡ ልጆቹን ለመጨረስ የወሰኑ ደደቦች ዛሬ እየቀለዱ ደገሙት፡ እንሳቅ ወይንስ እናለቅስ?እነዚህ ካልተባረሩ የትግራይ ህዝብ ሰላም አይኖረውም ሲሉ አስቀምጧል ::

  👇👇👇👇
04/05/2026

👇👇👇👇

ዜና ችሎት የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በከሳሽ ዐቃቤ ህግ እና በተከሳሽ በአቶ ጸጋዬ ታደሰ መካከል የነበረዉን የወንጀል ክስ መነሻነት ክስ የመስማት ሂደት ለማካሄድ ለዛሬ ቀን ቀጠሮ መስጠ...
04/05/2026

ዜና ችሎት

የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በከሳሽ ዐቃቤ ህግ እና በተከሳሽ በአቶ ጸጋዬ ታደሰ መካከል የነበረዉን የወንጀል ክስ መነሻነት ክስ የመስማት ሂደት ለማካሄድ ለዛሬ ቀን ቀጠሮ መስጠቱን መዘገባችን ይታወሳል

ዲላ ሚያዝያ 26/2018 ዓ/ም ጌዴኦ ዞን ፖሊስ መምሪያ ህዝብ ግንኙነት

በተከሳሽ በአቶ ጸጋዬ ታደሰ ላይ ዐ,ህግ አቶ ተመስገን ዳንኤልን በአሰቃቂ ሁኔታ መግደሉን የሚገልጽ ክስ መመስረቱ ከችሎቱ ለመረዳት ተችሏል

ከሳሽ አቃቤ ህግ እንደ ክስ አመሰራረት ያስረዱልኛል ያላቸዉን የሰዉና የሰነድ ማስረጃ እንዲቀርብ ተደርጓል ፍ/ቤቱም የቀረቡትን አራት የዐ,ህግ ማስረጃዎችን በችሎት ዉስጥ አድምጧል

የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም ተከሳሹ እንዲከላከል በማለት የመከላከያ ምስክር ለመስማት ለግንቦት 05/2018 ዓ/ም ቀጠሮ መስጠቱን ከስፍራዉ የጌዴኦ ዞን ፖሊስ መምሪያ ህዝብ ግንኙነት ዘግቧል

በጉዳዩ ዙሪያ ልዩ ትኩረት በመስጠት የወንጀል ፈጻሚዎች ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወሰድባቸዉ በሚያስችል መልኩ እየተሰራ መሆኑንና ጉዳዩ የመጨረሻ ዉሳኔን ጭምር በመከታተል ለህዝባችን እናሳዉቃለን ሲሉ

የጌዴኦ ዞን ፖሊስ መምሪያ የታክቲክ ወንጀል ምርመራ ዲቪዥን ኃላፊ ረ/ኢንስፔክተር ዮሐንስ በቀለ ተናግረዋል

በረ/ኢንስፔክተር ሐብታሙ ወንዶ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when እዚህ ሰፈር Gedeo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share