07/08/2022
አንዳንዴ ህይወት የማትችለውን
እንድትጋፈጥ ታደርግሃለች ትልቁ ፈተና ግን 👇
⚡
👉 ትልቁ ፈተና መሞት አይደለም አለመኖር እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና መፀለይ አይደለም አለማመን እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና ማፍቀር አይደለም አለመፅናት እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና መደመር አይደለም አለማካፈል እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና ማጣት አይደለም ተስፋ መቁረጥ እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና ማግባት አይደለም አለመግባባት እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና መደሰት አይደለም ደስታን አለመቆጣጠር እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና ማሰብ አይደለም የሚያስቡትን አለማጤን እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና ችግር አይደለም ትዕግስት ማጣት እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና ማዘን አይደለም ማማረር እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና ሃይማኖተኛ መሆን አይደለም መንፈሳዊ መሆን እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና ስልጣን አይደለም አጠቃቀሙን አለማወቅ እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና እውቀት አይደለም እያወቁ መሳሳት እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና ስደት አይደለም የተሰደዱለትን አላማ መርሳት እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና ስኬታማ መሆን አይደለም ራዕዩን መርሳት እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና የፀለዩትን ማግኘት አይደለም ያገኙትን ማማረር እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና ዝምተኛ መሆን መቻል አይደለም በዝምታ ውስጥ መረጋጋት ማጣት እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና ቤተክርስትያን ወይም መስጊድ መሄድ አይደለም የሚሄዱበት ምክንያት መዛባት እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና ገንዘብ አይደለም በገንዘቡ የምናደርግበትን ነገር አለማስተዋል እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና ልጅ መውለድ አይደለም ልጅን መቅረፅ እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና መጣላት አይደለም ለበቀል ማቀድ እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና ይቅርታ ማድረግ አይደለም ይቅርታውን ማመን እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና መለያየት አይደለም እንደሚገናኙ አለማሰብ
እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና ፈጣሪን ማሰብ አይደለም ፈጣሪን ማመን እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና መጣላት አይደለም ክፉ ቃል መናገር እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና ተሰሚነትን መጨመር አይደለም ለሚሰሙን መልካም አርአያ መሆን እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና አብሮ ስራ መጀመር አይደለም አብሮ ስራውን መፈፀም እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና አለማቀድ አይደለም ለማቀድ አለመሻት እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና ሞክሮ መበላሸት አይደለም ድጋሚ አለመሞከር እንጂ
👉 ትልቁ ፈተና ጓደኛ ማጣት አይደለም ወዳጅ ማግኘት እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና ማሸነፍ መቻል አይደለም አሸንፎ መፅናት እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና ተመስገን ማለት አይደለም አመስግኖ መርካት እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና መደንገጥ አይደለም ግራ መጋባት እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና መሸነፍ አይደለም ተሸንፎ መቅረት እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና እንደ እዮብ መውደቅ አይደለም እንደ እዮብ መፅናት እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና ከልብ ማልቀስ አይደለም ተሰብሮ መቅረት እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና ሀገርን መውደድ አይደለም ሀገርን ማገልገል እንጂ!
👉 ትልቁ ፈተና ሰው ሆኖ መፈጠር አይደለም ሰው ሆኖ መኖር እንጂ! ✔
•••═• 🌼🍀🌹•••═•