Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) I feel I am still a student, a beginner journalist with a great zeal to learn more.

I am climbing up the ladder and register remarkable achievement in my profession. This page is dedicated to serve you with reliable news and voice for voiceless.

እናት መሆን ከባድ ነው!  | በሚስ ወርልድ የዓለም ዲዛይነሮች ውድድር ላይ የቀረበችው የኡጋንዳ ተወካይ በፋሽን መድረክ ላይ የተለመዱ ውበቶችን ብቻ ሳይሆን የተለየና ጥልቅ የሆነ ሰብአዊ ታሪ...
02/09/2026

እናት መሆን ከባድ ነው!

| በሚስ ወርልድ የዓለም ዲዛይነሮች ውድድር ላይ የቀረበችው የኡጋንዳ ተወካይ በፋሽን መድረክ ላይ የተለመዱ ውበቶችን ብቻ ሳይሆን የተለየና ጥልቅ የሆነ ሰብአዊ ታሪክ ይዛ በመቅረብ የብዙዎችን ቀልብ ስባለች።

"ኪሻ" በተሰኘው የኡጋንዳ የፋሽን ዲዛይን ተቋም የተቀረፀው ይህ ቀሚስ አንዲት እናት ለመውለድ ስለምታደርገው ቀዶ-ሕክምና ወቅት የምታልፍበትን አካላዊና መስዋዕትነት የተሞላበት ጉዞ ደረጃ በደረጃ የሚያሳይ አሰራር አለው።

​ይህ አልባሳት ከስብና ፋሺያ ንብርብር ተነስቶ ወደ ጡንቻ፣ በመቀጠልም የሆድ ዕቃ ሽፋን ፣ ማህፀን እና በመጨረሻም የፅንስ ከረጢት ድረስ ያሉትን የህክምና እና የአካላዊ ሁኔታ በጥበብ ያሳያል።

የቀሚሱ የጨርቅ ቀለም ከፒችና ወርቃማ ቀለሞች ተነስቶ ደረጃ በደረጃ ወደ ኮራል፣ ቀይ፣ ማሩን እና ጥቁራማ ቀይ የሚቀያየር ሲሆን፣ ይህም እናቶች ከፅንስ እንክብካቤ እስከ ልጅ መውለድ ድረስ የሚያልፉበትን ጥልቅ ስሜታዊ ሂደት እና የህይወት መፈጠር ጉዞን በግልጽ ይገልጻል።

​በተጨማሪም በሜርሜይድ ቅርፅ በተሰራውና ንብርብር በሆኑት የቱል ጨርቆች ላይ በጥንቃቄ የተረበቡት ሉሎች፣ የብርጭቆ ዶቃዎች እና ክሪስታሎች በእያንዳንዱ የልብሱ ክፍሎች ላይ ጥልቀትና ልዩ ውበት በመስጠት የፅንስ ጉዞውን በእይታ የተሞላ አድርገውታ።

ይህ የፈጠራ ስራ በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ እናቶች የሚያልፉበትን ጥልቅ የእናትነት ተሞክሮ በዓለማችን የውበት መድረክ ላይ የሚለበስ የጥበብ ስራ አድርጎ በመቀየር አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

የአፋልጉን ተማጽኖእባካችሁ ሼር በማድረግ እንተባበር!  | ወንድማችን ሚካኤል መለሰ ማክሰኞ፣ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 10:30 ሰዓት ከቤት ወጥቶ የደረሰበትን ስፍራ ማወቅ ተስኖ...
02/09/2026

የአፋልጉን ተማጽኖ
እባካችሁ ሼር በማድረግ እንተባበር!

| ወንድማችን ሚካኤል መለሰ ማክሰኞ፣ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 10:30 ሰዓት ከቤት ወጥቶ የደረሰበትን ስፍራ ማወቅ ተስኖናል።

እስካሁን ድረስ የት እንዳለ ስላልታወቀ፣ እባክዎ ሚካኤልን ያያችሁ ወይም ያለበትን አካባቢ የምታውቁ ሰዎች በእነዚህ ስልክ ቁጥሮች በአስቸኳይ እንድታሳውቁን በአክብሮት እንጠይቃለን።

+251 900 472 195
+251 911 138 460

እባካችሁ ይህንን መልዕክት ሼር በማድረግ ሚካኤል ወደ ቤተሰቡ እንዲመለስ እንተባበር።

🙏 በፈጣሪ ስም ትብብራችሁን እንጠይቃለን።

#የአፋልጉንጥሪ #ሚካኤልመለሰ

"ሜሲ" የሚለው የስም መጠርያ ለማንም እንዳይሰጥ!  | የሊዮኔል ሜሲ የትውልድ ከተማ የሆነችው ሮሳሪዮ ወላጆች ለልጆቻቸው "ሜሲ" የሚለውን ስም እንዳይሰጡ ከለከለች።በአርጀንቲናዋ ሮሳሪዮ ከተ...
02/09/2026

"ሜሲ" የሚለው የስም መጠርያ ለማንም እንዳይሰጥ!

| የሊዮኔል ሜሲ የትውልድ ከተማ የሆነችው ሮሳሪዮ ወላጆች ለልጆቻቸው "ሜሲ" የሚለውን ስም እንዳይሰጡ ከለከለች።

በአርጀንቲናዋ ሮሳሪዮ ከተማ ወላጆች ለልጆቻቸው "ሜሲ" የሚለውን ስም የመጀመሪያ ስም አድርገው እንዳይሰጡ መከልከሏ ተገለጸ።

አርጀንቲና "ሊዮኔል ሜሲ" የሚለውን ስም በእግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ለማንም የማይሰጥ እና ወደፊትም የማይደገም ልዩ አድርጋዋለች።

በ2014 ከሮዛሪዮ ውጪ የሚኖር አንድ አባት ልጁን "ሜሲ ዳንኤል ቫሬላ" ብሎ ለመሰየም ልዩ ፈቃድ ካገኘ በኋላ ነበር ይህ ክልከላ የወጣው።

ይህንን ተከተሎ የሮሳሪዮ ከተማ ባለሥልጣናት ተመሳሳይ ነገር በከተማቸው መደበኛ በሆነ መንገድ የማይፈቀድ መሆኑን የሚገልጽ መመርያ ያወጡት።

ይህ ለእሱ ያላቸውን ፍቅር እና አድናቆት መግለጫ ነው ተብሏል።

በሜሲ በትውልድ ከተማ ሮዛሪዮ አካባቢ ግራ መጋባትን ለመቀነስ የሕፃናትን ስም "ሜሲ" ብሎ መሰየምን የሚከለክል ሕግ በ2014 ነበር ተደንግጎ የወጣው።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል



ፖፑላር ኤሌክትሮኒክስ ቃሉን በተግባር አረጋገጠ!   | ፖፑላር ኤሌክትሮኒክስ ለኢትዮጵያ የስፖርት ተስፋ ረቢቅ ሳኒ ለማበርከት የገባውን 300,000 ብር የገንዘብ ድጋፍ ዛሬ አበርክቷል።ድርጅ...
02/09/2026

ፖፑላር ኤሌክትሮኒክስ ቃሉን በተግባር አረጋገጠ!

| ፖፑላር ኤሌክትሮኒክስ ለኢትዮጵያ የስፖርት ተስፋ ረቢቅ ሳኒ ለማበርከት የገባውን 300,000 ብር የገንዘብ ድጋፍ ዛሬ አበርክቷል።

ድርጅቱ ይህንን ድጋፍ ያደረገው ረቢቅ ሳኒ በቅርቡ በአድዋ ሙዚየም በተካሄደው የስፖርት ውድድር ያስመዘገበውን ድል ተከትሎ፣ ስፖርተኛውን ለማበረታታትና ለሀገር ክብር የሚያበረክቱ ወጣቶችን ለመደገፍ መሆኑን ገልጿል።

የፖፑላር ኤሌክትሮኒክስ ኃላፊዎች እንደገለጹት፣ ድርጅቱ የንግድ ሥራውን ከማስፋፋት ባሻገር ሀገራቸውን በተለያዩ መድረኮች ለሚወክሉ ወጣቶች ድጋፍ ማድረግን እንደ ማህበራዊ ኃላፊነት ይመለከቱታል።

በቀጣይም በትልልቅ ዓለም አቀፍ መድረኮች ሀገራቸውን ወክለው ለሚወዳደሩና ስኬትን ለሚያስመዘግቡ ወጣቶች ከጎናቸው በመቆም ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

ረቢቅ ሳኒ በበኩሉ ለተደረገለት ድጋፍና ማበረታቻ ለፖፑላር ኤሌክትሮኒክስ ምስጋና አቅርቧል። ይህ ዓይነቱ ድጋፍ ለቀጣይ ውድድሮች የበለጠ ተነሳሽነትና ጥንካሬ እንደሚሰጠውም ገልጿል።

ፖፑላር ኤሌክትሮኒክስ የተለያዩ ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን ከውጭ በማስመጣት በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቾች የሚያቀርብ ሲሆን፣ በቅርቡም በፒያሳ አዲስ ሾውሩም መክፈቱ ይታወሳል።

በተጨማሪም በTikTok ታዋቂ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆነውን አድናይ ብርሃኔን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ መሾሙ ይታወሳል።

👏 ቃል ገብቶ በተግባር ማሳየት — የሚደነቅ ነው!

አድራሻ
ፒያሳ፣ ኤሊያና ሞል አጠገብ

ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
09 88 77 77 11 / 09 88 77 77 22

በአጭር የመልዕክት መላኪያ (SMS)
6992

የታይሰን ፊዩሪ እና አንቶኒ ጆሹዋ ታላቅ የከባድ ሚዛን ፍልሚያ የሚካሄድበት ቀን እና ስፍራ ይፋ ሆነ  | ለረጅም ጊዜ በስፖርት አፍቃሪዎች ዘንድ ትልቅ ጉጉትን ፈጥሮ የነበረው የታይሰን ፊዩሪ...
02/09/2026

የታይሰን ፊዩሪ እና አንቶኒ ጆሹዋ ታላቅ የከባድ ሚዛን ፍልሚያ የሚካሄድበት ቀን እና ስፍራ ይፋ ሆነ

| ለረጅም ጊዜ በስፖርት አፍቃሪዎች ዘንድ ትልቅ ጉጉትን ፈጥሮ የነበረው የታይሰን ፊዩሪ እና አንቶኒ ጆሹዋ የከባድ ሚዛን ቦክስ ግጥሚያ የሚካሄድበት ቦታ ተለይቶ የመጨረሻ ስምምነት ላይ መደረሱ ተታውቋል።

የብሪታኒያውያን ፍልሚያ የሚል ስየሜ የተሰጠው ይህ ታላቅ የቦክስ መርሃ ግብር በመጪው ህዳር ወር በኒውዮርክ ማዲሰን ስኩዌር ጋርደን ውስጥ እንደሚካሄድ ታይሰን ፊዩሪ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አማካይነት ይፋ አድርጓል።

ሁለቱ የብሪታንያ ከባድ ሚዛን ስፖርተኞች የስምምነት ሰነዱን በሳዑዲ አረቢያ የተፈራረሙ ሲሆን ውድድሩ በሀገሪቱ የቦክስ ታሪክ ውስጥ እጅግ ግዙፉ እንደሚሆን ተገምቷል።

ዕድሜው 38 ዓመት የደረሰው ታይሰን ፊዩሪ በፈረንጆቹ 2024 ማጠቃለያ ላይ ከቦክስ ዓለም መገለሉን አስታውቆ የነበረ ቢሆንም በ2026 መጀመሪያ ላይ ወደ መድረኩ መመለሱን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

ፊዩሪ በሙያዊ የቦክስ ጉዞው 36 ጊዜ ማሸነፍ የቻለ ሲሆን ብቸኛ ሽንፈት የገጠመው ደግሞ በ2024 ከዩክሬኑ ኦሌክሳንደር ኡሲክ ጋር ባደረገው ፍልሚያ ነበር።

በ2021 ሁለቱ የከባድ ሚዛን ኮከቦች እንዲገናኙ ጥረት ተደርጎ በተለያዩ ምክንያቶች ሳይሳካ ቀርቶ የነበረ ቢሆንም የአሁኑ ስምምነት ግን የስፖርቱን አፍቃሪዎች የዓመታት ጥበቃ እውን አድርጎታል።

#ጌጡ #ጌጡተመስገን

"ያሳደገችኝን ሴት እንዴት እረሳለሁ!"  | ለ20 ዓመት ያሳደገችውን ሴት አስታውሶ በፍቅር የተሰናበተው አንበሳ ብዙዎችን ስሜታዊ አድርጓል።ይህ አንበሳ እንደ እናት ሆና ለሁለት አስርት ዓመታ...
02/09/2026

"ያሳደገችኝን ሴት እንዴት እረሳለሁ!"

| ለ20 ዓመት ያሳደገችውን ሴት አስታውሶ በፍቅር የተሰናበተው አንበሳ ብዙዎችን ስሜታዊ አድርጓል።

ይህ አንበሳ እንደ እናት ሆና ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል ስትንከባከበው የነበረችውን ሴት የሰጣት ፍቅር ብዙዎችን እንዲገረሙም አድርጓል።

ታማሚው አንበሳ ሕይወቱ ከማለፉ በፊት ስትንከባከበው የነበረችውን ሴት የመጨረሻው የፍቅር ሰላምታውን ሰጥቶ ተሰናብቷታል።

ጁፒተር በመባል የሚጠራው ይህ አንበሳ በኮሎሚቢያ የእንስሳት እንክብካቤ መስጫ ማዕከል ከልጅነቱ ጀምሮ ሲጠበቅ ቆይቷል።

ጁፒተር ወደ ማዕከሉ የመጣው እናቱ ከተገደለች በኋላ ገና በሕፃንነቱ ነበር።

ከልጅነቱ ጀምሮ እስከ እለተ ሞቱ ድረስ ስትንከባከበው የነበረችው ይህችው ሴት ብቻ እንደነበረች ተገልጿል።

ጁፒተር አና ጁሊያን ሲያያት በደስታ እቅፍ አድርጎ እንደመሳም አድርጎ ፍቅሩን በመግለፅ ይታወቃል።

ከእድሜ መግፋትና ከሕመም ጋር በተያያዘ ጁፒተር ሰውነቱ በጣም ከሳ።

ጁሊያ በመጨረሻ ከእርሱ ጋር ስትገናኝ ጁፒተር እጅግ ደክሞ ነበር ቢሆንም ግን ወዲያውኑ አውቋታል።

ጁፒተር ምንም እንኳ የመንቀሳቀስ አቅም ቢያጣም ሕይወቱን ሙሉ ከጎኑ የነበረችውን ጁሊያን ለማቀፍና ለመሳም በመሞከር ፍቅሩን ገልጾላታል።

ከዚህ ግኑኝነታቸው ሁለት ቀናት በኋላ በ20 ዓመት ዕድሜው ጁፒተር ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል።

ለዘመናት ያሳደገችውን እስከ መጨረሻው እስትንፋሱ ድረስ ያልረሳው ጁፒተር በእንስሳትና በሰዎች መካከል ያለውን ጥልቅ ቁርኝት እንደገና ያሳየ አጋጣሚ ሆኖ አልፏል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል





"ሀይድሮጅን ቦምብ ሳይሆን ሀይድሮጅን ባቡር ነው የሚያስፈልገው!"  | ጀርመን በሀይድሮጅን ነዳጅ የሚሰሩ ባቡሮችን ወደ ስራ አስገባች። ሀገሪቷ "ኮራዲያ አይሊንት" የተሰኙት እነዚህ ባቡሮች ...
02/09/2026

"ሀይድሮጅን ቦምብ ሳይሆን ሀይድሮጅን ባቡር ነው የሚያስፈልገው!"

| ጀርመን በሀይድሮጅን ነዳጅ የሚሰሩ ባቡሮችን ወደ ስራ አስገባች።

ሀገሪቷ "ኮራዲያ አይሊንት" የተሰኙት እነዚህ ባቡሮች ኤሌክትሪክ መስመሮችን ለመዘርጋት አስቸጋሪ በሆባቸው አካባቢዎች ነው አገልግሎት እንዲሰጡ አድርጋለች።

ባቡሮቹ አንድ ጊዜ ብቻ በተሞላ የሃይድሮጅን ነዳጅ እስከ 1,000 ኪሎ ሜትር ድረስ የመጓዝ አቅም አላቸው ተብሏል።

እነዚህ ባቡሮች የሃይድሮጅን ነዳጅ በመጠቀም ኤሌክትሪክ ያመነጫሉ።

ከባቡሩ የጭስ ማውጫ የሚወጣው የተለመደው ጭስ ሳይሆን የውሃ እንፋሎት እና የውሃ ጠብታዎች ብቻ ናቸው።

ባቡሮቹ በሚጓዙበት ወቅት ምንም ዓይነት ቀጥተኛ የካርቦን ዳይኦክሳይድ ጭስ አያወጣም ነው የተባለው።

በዚህም ጀርመን ሃይድሮጅን ባቡር ለመደበኛ የንግድ አገልግሎት ያዋለች በዓለም የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል




የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎችጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”
02/09/2026

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎች

ጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”

ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”

ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”

ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”

ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”

የህዝብ ክብረ በዓላት ባህላዊ እሴቶችንና አብሮነትን በሚያጠናክር መልኩ እንደሚከበሩ ተገለጸ‎‎  | ኢትዮጵያ የጥንታዊ ስልጣኔና የብዙሃ ባህል ባለቤት እንደመሆኗ መጠን ለዘመናት ያዳበረችውን ...
02/09/2026

የህዝብ ክብረ በዓላት ባህላዊ እሴቶችንና አብሮነትን በሚያጠናክር መልኩ እንደሚከበሩ ተገለጸ

‎ | ኢትዮጵያ የጥንታዊ ስልጣኔና የብዙሃ ባህል ባለቤት እንደመሆኗ መጠን ለዘመናት ያዳበረችውን አብሮ የመኖር እሴት አጠናክራ እንደምትቀጥል የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የባህል እና ቋንቋ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ነፊሳ አልማሃዲ ገለጹ።

‎ክብርት ሚኒስትሯ የህዝብ ክብረ በዓላትን አስመልከተው በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ፣ የሀገራችን የሃይማኖት፣ የቋንቋና የባህል ስብጥር የጥንካሬያችን ምስጢር በመሆኑ ይህንን ህብረ-ብሔራዊ አንድነት በአግባቡ ተቀብሎ ማስተናገድ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

‎ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የባህል ሀብቶችን በማልማትና በማስተዋወቅ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት የሚኖራቸውን ሚና ለማሳደግ ምቹ የህግ ማዕቀፎችንና መመሪያዎችን ዘርግቶ እየሰራ ይገኛል።

‎​እንደ ክብርት ሚኒስትሯ ማብራሪያ፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀውን የአዋጅ ቁጥር 1334/2016 እና የህዝብ ክብረ በዓላት ማስፈፀሚያ መመሪያ ቁጥር 1116/2018 መሠረት በማድረግ ዘርፉን በታቀደ መንገድ የመምራት ስራ ተከናውኗል።

‎በዚሁ መሠረት በ2018 በጀት ዓመት ለሶስት ወራት በዘለቀው የባህል ንቅናቄ ከ46 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ማሳተፍ የተቻለ ሲሆን፣ ሂደቱም በውጤቱ የላቀ ስኬት ያስመዘገበ ነበር። ይህ አፈፃፀም አገር በቀል እውቀቶችን በማጉላት፣ የማህበረሰቡን ሚና በማሳደግና ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ ማበርከቱን አብራርተዋል።

‎​ይህ የጀመረው ጥረት በ2019 በጀት ዓመትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የጠቆሙት ክብርት ነፊሳ አልማሃዲ፣ በአገር አቀፍና በክልል ደረጃ የሚከበሩ በዓላት በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበሩ ተናግረዋል።

‎በተለይም ለመጪው የጳጉሜ 4 «የህብር ቀን» እና በየክልሎቹ ለሚካሄዱ በዓላት ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል። ክብርት ሚኒስትሯ አክለውም፣ እነዚህ በዓላት የሰዎችን ልዩነት እንደ ፀጋ በመቀበል፣ መቻቻልንና አካታችነትን በማስፈን፣ እንዲሁም አንድ የጋራ ምጣኔ ሀብታዊና ፖለቲካዊ ማህበረሰብ ለመገንባት በሚደረገው ጉዞ ውስጥ እጅግ ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖራቸው አስረድተዋል።

‎​በመጨረሻም የህዝብ ክብረ በዓላት ማህበራዊ ትስስርን ከመፍጠር ባሻገር የቱሪዝም ፍሰትን በመጨመር፣ የስራ ዕድል በመፍጠርና የአካባቢውን ንግድ በማንቀሳቀስ ረገድ በርካታ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞች እንዳሏቸው ክብርት ሚኒስትሯ ጠቁመዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ እነዚህን በዓላት ባህላዊ ይዘታቸውን ሳይለቁ የአብሮነትና የሰላም መገለጫ አድርጎ እንዲያከብራቸው ጥሪ አቅርበዋል።

‎በጌትነት ተመስገን

‎Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

‎ #ጌጡ ​ ​ ​ ​ ​

2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመትን በድምቀት እንቀበል! ✨በSheraton Addis – Musical Fountain የሚካሄደውን የአዲስ ዓመት ዋዜማ ዝግጅት አያምልጥዎ!  የኢትዮጵያ ሙዚቃ አዶ አስቴ...
02/09/2026

2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመትን በድምቀት እንቀበል! ✨

በSheraton Addis – Musical Fountain የሚካሄደውን የአዲስ ዓመት ዋዜማ ዝግጅት አያምልጥዎ!

የኢትዮጵያ ሙዚቃ አዶ አስቴር አወቀ በተወዳጅ ዘፈኖቿ በመድረኩ ላይ ድምቀት ትፈጥራለች።

በተጨማሪም ዓለም አቀፉ ሱፐርስታር T.I. በዚህ ልዩ የአዲስ ዓመት ዋዜማ ዝግጅት ይታደማል!

መስከረም 10፣ 2019 ዓ.ም.
Musical Fountain, Sheraton Addis
ትኬቶች በDashen Super App ይገኛሉ!

✨ አዲሱን ዓመት ከሙዚቃ፣ ከደስታ እና ከልዩ ትዝታዎች ጋር እንቀበል!

Address

Gabon Avenue (Washington DC Square/Sterling Buildg)
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን):

Shortcuts

Share