የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት / FDRE TVT Institute

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት / FDRE TVT Institute

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት / FDRE TVT Institute Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት / FDRE TVT Institute, College & University, Addis Ababa.

FDRE TVTI is the leading capacity-building institute for the TVET sector, providing training for teachers, trainers, and leaders, while also conducting research, community service, and technology and enterprise development activities. Federal Technical and Vocational Education and Training Institute (FTVETI) were established in 2011 by The Council of Ministers Proclamation 245/2011 to produce high

ly professional and technically efficient TVET teachers and leaders. The driving force for establishing FTVETI , among other things , was that there were no institution to train competent and sufficient technical and vocational teachers and leaders based on the outcome based system and occupational standards. At the time of its inception, the institute ran degree programs in 5 occupational sectors namely: automotive, construction, electronics/electrical, information and communication technology and manufacturing technology, and two years later railways and surveying technology departments were opened. Those programs embraced ten specializations, namely, Automotive, Building, Road, Water, ICT, Electrical and Control, Electronics and Communications, Manufacturing, Rolling Stock and Surveying.

የቴክኒክና ሙያ በ5ዓመታት የተመዘገቡ ለውጦች
26/08/2026

የቴክኒክና ሙያ በ5ዓመታት የተመዘገቡ ለውጦች

የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ባለፉት አምስት ዓመታት ያስመዘገባቸው ለውጦች

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተቋቋመ አምስት ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡

በዚህ ጊዜ ውስጥ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የነበሩ ማነቆዎችን ለመፍታት አጠቃላይ የህግና የማዕቀፍ ለውጦችን አድርጓል፡፡

የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ተሻለ በሬቻ እንዳብራሩት፤ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ከዚህ በፊት ሲመራበት የነበረው የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በአዲስ መልክ ተከለሶ ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡

በተጨማሪም አዲስ የቴክኒክና ሙያ ስትራቴጂ እንዲሁም የቴክኒክና ሙያ፣ ከፍተኛ ትምህርት፣ የምርምር እና የኢንዱስትሪ ትስስር አዋጅ መሻሻላቸው በዚህ የአምስት ዓመት ጉዞ ውስጥ የሚጠቀሱ ዋና ዋና ማሻሻያዎች ናቸው፡፡

ይህንን የፖሊሲ ክለሳ ተከትሎ አዲስ ሀገራዊ የብቃት ማዕቀፍ የተዘጋጀ ሲሆን ከዚህ ቀደም ተቋማቱ እስከ ደረጃ 5 ብቻ ያሰለጥኑ የነበረውን አሰራር በመቀየር አሁን እስከ ደረጃ 8 (ፒ.ኤች.ዲ) ድረስ ማሰልጠን እንዲችሉ ወደ ትግበራ ተገብቷል፡፡

እነዚህ ለውጦች የተደረጉት የዘርፉንና የኢንዱስትሪውን ፍላጎት በማጣጣም ነው፡፡ የአዲሱ ቴክኒክና ሙያ እሳቤ አሰልጥኖ ሰርተፍኬት ከመስጠት ባለፈ ክህሎትን፣ ዕውቀትን የሚያስጨብጥ እና ጥሩ አመለካከትን በዜጎች ላይ የሚቀርጽ እንዲሆን ታስቦ የተሰራበት ነው፡፡

ከዚህ ቀደም ሁሉም የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ተመሳሳይ ስልጠናዎች የሚሰጡበት አሰራር ቀርቶ አሁን የገበያውን ፍላጎትና የአካባቢን ጸጋ መሰረት ያደረገ ስልጠና እንዲሰጡ ተቋማቱ ዘመኑ በሚዋጀው ሁኔታ እንዲደራጁ ተደርገዋል፡፡

ከዚህም ባሻገር ተቋማት ማሰልጠን ብቻ ሳይሆን አምራችና አገልግሎት የሚሰጡ ኢንተርፕሩኒያል መሆን እንዳለባቸው በማድረግ ስልጠናው ይበልጥ ተግባር ተኮር ለማድረግ ተችሏል፡፡

በጠቅላላው ከዛሬ አምስት ዓመት በፊት ከነበረው ሁኔታ ጋር ሲነጻጸር የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ተልዕኮ ግልጽነት የተፈጠረበት እና በብዛት ከማሰልጠን ባለፈ ጥራትንና ተወዳዳሪነትን ማዕከል ያደረገ ሥራ የሚከናወንበት ደረጃ ላይ መድረሱ ተገልጿል፡፡

ነሀሴ 20/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI

የኢንስቲትዩቱ ሀዋሳ ካምፓስ ለሁለተኛ ደረጃ  ተማሪዎች ልዩ ተግባር ተኮር ስልጠና እየሰጠ መሆኑ ተገለጸ።*****ነሐሴ 15/2018 ዓ/ም ****ይህ የክረምት የበጎ ተግባር ስልጠና ፕሮግራም ...
22/08/2026

የኢንስቲትዩቱ ሀዋሳ ካምፓስ ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ልዩ ተግባር ተኮር ስልጠና እየሰጠ መሆኑ ተገለጸ።
*****ነሐሴ 15/2018 ዓ/ም ****

ይህ የክረምት የበጎ ተግባር ስልጠና ፕሮግራም ተማሪዎች እረፍታቸውን በቴክኖሎጂ እውቀትና በፈጠራ ስራዎች ላይ እንዲያሳልፉ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ሀዋሳ ካምፓስ ሀላፊ አቶ ስንሻው ብርሃኑ እንደገለጹት፤ የስልጠናው ዋነኛ ግብ ተማሪዎች ከወረቀት ትምህርት ባለፈ ቀጥተኛ የተግባር ክህሎት እንዲያገኙ ማድረግ ነው።

ይህም ተማሪዎች በራሳቸው የሚተማመኑ፣ የፈጠራ ስራዎችን ማመንጨት የሚችሉ እና በቀጣይ በ Online ፈተና በሚወስዱበት ጊዜ የሚያግዛቸው እንደሚሆን ተናግረዋል።

ሀላፊው አክለውም ተማሪዎቹ በቆይታቸው ተግባራዊ እውቀት ከመቅሰማቸው ባለፈ፣ ስልጠናውን ሲያጠናቅቁ በትምህርት ህይወታቸው ትልቅ ዋጋ የሚኖረውንና ደረጃውን የጠበቀ ህጋዊ የስልጠና ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እንደሚረከቡ ተገልፀዋል።

ተማሪዎቹ ቀደም ሲል በንድፈ-ሐሳብ ቀለም ትምህርት ብቻ ያውቁት የነበረው የማስተማር ሥርዓት በቴክኒክና ሙያ ተቋም ውስጥ በተግባር የታገዘ ስልጠና መውሰዳቸው በቀጣይ በትምህርታቸው ላይ በራስ የመተማመን ስሜት በከፍተኛ ደረጃ እንዳሳደገባቸው ተናግረዋል።

ዘገባው የ(ኤስቢሲ) ነው።

Telegram; https://t.me/fdretvtinstitute
Website: https://www.ftveti.edu.et/
Youtube ;
https://www.youtube.com/fdretvtinstitute
Tiktok; www.tiktok.com/
Twitter (X); https://x.com/FDRETVTI
WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029Vb73e9cGOj9ooFTo2u1R

የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ሥራ ሀላፊዎች በስኪል ኢትዮጵያ ፕሮግራም የተመረቱ ቴክኖሎጂዎችን ጎበኙ።**********ነሀሴ 15/2018*****የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ሥ...
22/08/2026

የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ሥራ ሀላፊዎች በስኪል ኢትዮጵያ ፕሮግራም የተመረቱ ቴክኖሎጂዎችን ጎበኙ።
**********ነሀሴ 15/2018*****

የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ሥራ ሀላፊዎች በኢንስቲትዩቱ የተመረቱ ቴክኖሎጂዎችን የጎበኙ ሲሆን በስፋት አምርተው ለተጠቃሚዎች ለማድረስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከኢንስቲትዩቱ ሥራ ሀላፊዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል።

የኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂና ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፀዳለ ተክሉ በሰመርካምፕና በስኪል ኢትዮጵያ ፕሮግራም የተመረቱ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን በተለይም የግብርና ዘርፍ ላይ ያሉ ፈጠራዎችን አቅርበዋል።

በግብርና ላይ ትኩረት ያደረጉ በስድስት ምድብ የተፈጠሩ 45 ቴክኖሎጂዎች መኖራቸውን በገለጻቸው አብራርተዋል።

እነዚህ ቴክኖሎጂዎች ውጤታማነታቸው መረጋገጡን የገለጹት ም/ዋና ዳይሬክተሯ የአእምሯው ንብረት እውቅና፣ የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያገኙ መኖራቸውን አብራርተዋል።

የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ማንደፍሮ ንጉሴ በኢንስቲትዩቱ ያየናቸው ቴክኖሎጂዎች የግብርናውን ዘርፍ ችግር የሚፈቱ ናቸው ብለዋል።

ቴክኖሎጂዎችንም "እውነተኛውን ችግር የለዩ ችግሮችን ለመፍታት ያለሙ" ናቸው ብለዋቸዋል።

እነዚህ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎች በስፋት ተመርተው ወደ ተጠቃሚዎች እንዲደርሱ ተቋማቸው ከኢንስቲትዩቱ ጋር እንደሚሠራ አረጋግጠዋል።

በመጨረሻም ፈጠራዎቹን በብዛት በማምረት ወደገበያ የማውጣት ሥራ በሚሠራው ቴክኖቢዚያ የኢንዱስትሪ ውጤቶች ኢንተርፕራይዝ ውይይት ተካሂዷል።

Telegram; https://t.me/fdretvtinstitute
Website: https://www.ftveti.edu.et/
Youtube ;
https://www.youtube.com/fdretvtinstitute
Tiktok; www.tiktok.com/
Twitter (X); https://x.com/FDRETVTI
WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029Vb73e9cGOj9ooFTo2u1R

በስኪል ኢትዮጵያ ውድድር ወደ 2ኛ ዙር ያለፉ ቴክኖሎጂስቶች ተለዩ።*********ነሀሴ 13/2018******በስኪል ኢትዮጵያ ብሔራዊ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ውድድር ወደ 2ኛ ዙር ያለፉ 24 ተ...
20/08/2026

በስኪል ኢትዮጵያ ውድድር ወደ 2ኛ ዙር ያለፉ ቴክኖሎጂስቶች ተለዩ።
*********ነሀሴ 13/2018******

በስኪል ኢትዮጵያ ብሔራዊ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ውድድር ወደ 2ኛ ዙር ያለፉ 24 ተወዳዳሪዎች ውጤት ዛሬ ይፋ ሆኗል።

48 የፈጠራ ባለሙያዎችን ይዞ የጀመረው ስኪል ኢትዮጵያ ብሔራዊ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ውድድር በመጀመሪያ ዙር ውድድር ጠንካራ ፉክክር አድርገው 24 ተወዳዳሪዎች ወደ ሁለተኛ ዙር መሻገራቸው በዳኞች ተገልጿል።

የህብረተሰቡን ችግር የሚፈቱ፣ ዘመናዊነትን የሚያጠናክሩ፣የሥራ እድል የሚፈጥሩ ፈጠራዎች ያሏቸው ወጣቶች ሀሳባቸውን፣ የተሞከሩ ፕሮቶ ታይፖችን፣ ገበያ ላይ የዋሉ ምርቶቻቸውን ይዘው ተወዳድረዋል።

የውድድሩ ቋሚ እና ተጋባዥ ዳኞች የወጣቶችን ፈጠራ በጥልቀት ተከታትለው ሙያዊ ምክር በመለገስ፣ በማበረታታት፣ በማስተካከል ሙያዊ ሚናቸውን አበርክተዋል።

ስኪል ኢትዮጵያ ብሔራዊ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ውድድር ሁለተኛ ዙር ይበልጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

የስኪል ኢትዮጵያ ብሔራዊ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ውድድር በኢንስቲትዩቱ እና በበላይ መልቲሚዲያ ትብብር እየተዘጋጀ በሀገሬ ቴሌቪዥን የሚተላለፍ የፈጠራ ውድድር ነው።

Telegram; https://t.me/fdretvtinstitute
Website: https://www.ftveti.edu.et/
Youtube ;
https://www.youtube.com/fdretvtinstitute
Tiktok; www.tiktok.com/
Twitter (X); https://x.com/FDRETVTI
WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029Vb73e9cGOj9ooFTo2u1R

7 የክህሎት ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂዎች የጥራት ማረጋገጫ እውቅና አገኙ።*******ነሀሴ 13/2018*******የኢትዮጵያ የተስማሚነትና ምዘና ድርጅት የስድስት የሰመር ካምፕ እና ስኪል ኢትዮጵያ ...
19/08/2026

7 የክህሎት ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂዎች የጥራት ማረጋገጫ እውቅና አገኙ።
*******ነሀሴ 13/2018*******

የኢትዮጵያ የተስማሚነትና ምዘና ድርጅት የስድስት የሰመር ካምፕ እና ስኪል ኢትዮጵያ የፈጠራ ባለሙያዎች 7 የፈጠራ ሥራዎች የላብራቶሪ ፍተሻ ካካሄደ በኋላ ጥራታቸውን ፈትሾ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ሰጥቷቸዋል።

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ስታርታፖችን ከሚደግፉ ተቋማት ጋር በቅርበት እየሠራ ሲሆን የኢትዮጵያ የተስማሚነትና ምዘና ድርጅትም በዚሁ ትብብር ይህንን ከክፍያ ነጻ በሆነ ትብብር ሰርቶ ማስረከቡ ተገልጿል።

የፈጠራ ውጤቶችም የኢትኤል ዱቄት ​(Ethel Flour)፣ የአጓት ዱቄት (Whey powder)፣ የዶሮ መኖ ​Animal Feed (chicken): የወተት ላም መኖ ​Dairy cow feed: የቲማቲም ድልህ እና ቅመማ ቅመም (​Tomato Paste & Spice) የግብጦ ዱቄት (​Lupin Flour) አልሚ ምግብ
(​Complementary feed) መሆናቸው ተገልጿል።

እውቅና መገኘቱ ፈጠራዎቹ በስፋት ተመርተው ወደተጠቃሚ እንዲደርሱ እንደሚያስችል የተገለጸ ሲሆን ስታርታፖችን ለመደገፍ የቋማች ትብብር እየተጠናከረ መሆኑ ማሳያ ነው ተብሏል።

Telegram; https://t.me/fdretvtinstitute
Website: https://www.ftveti.edu.et/
Youtube ;
https://www.youtube.com/fdretvtinstitute
Tiktok; www.tiktok.com/
Twitter (X); https://x.com/FDRETVTI
WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029Vb73e9cGOj9ooFTo2u1R

"የነገ ኢኖቬተሮች- የኢትዮጵያን የፈጠራ ሥነምህዳር መገንባት"******ነሀሴ 12/2018********የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት 7ኛ ሳምንት የቴክኖሎጂ ባህል ግንባታ መድረክ...
19/08/2026

"የነገ ኢኖቬተሮች- የኢትዮጵያን የፈጠራ ሥነምህዳር መገንባት"
******ነሀሴ 12/2018********

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት 7ኛ ሳምንት የቴክኖሎጂ ባህል ግንባታ መድረክ "የነገ ኢኖቬተሮች- የኢትዮጵያን የፈጠራ ሥነምህዳር መገንባት" በሚል ርዕስ ተካሂዷል።

የኢንስቲትዩቱ የኢንኩቤሽን ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ብሩክ ሰለሞን ባለፉት የተለያዩ ፕሮገራሞች የቴክኖሎጂ ባህል ለመገንባት የሙያተኞች ሠፊ ውይይት ሲካሄድ መቆየቱን አቶ ብሩክ ገልፀዋል።

ወጣቶች ከዚህ የባህል ግንባታ መድረክ ትምህርት እያገኙ እንደሆነ ገልጸው ከዚህ መድረክም ትልቅ ትምህርት እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የኢንስቲትዩቱ የአይሲቲ ዳይሬክተር አቶ ናኦል አንበሴ ዲጂታል 2030 ላይ ትኩረቱን ያደረገ የውይይት መነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል።

ለሀገራችን ለፈጠራ ባለሙያ ባለሙያዎች የተመቸ የዲጂታላይዜሽን ሥራ እየተሠራ መሆኑን በጽሁፋቸው አንስተዋል።

እንደተቋም የዲጂታል መሠረተልማት ከማማሟላት ጀምሮ፣ በስልጠና በማብቃት ኢኖቬተሮችን ለመደገፍ እየተሠራ ይገኛል። በዚህም ሠፊ ውጤት እንደተመዘገበበት ማሳያዎችን አንስተው አቅርበዋል።

ዲጂታላይዜሽን ላይ ተግቶ መሥራት የዘመኑ አማራጭ ሳይሆን ግዴታ ነው።

የዕለቱ ተጋባዥ እንግዳ እና ፓናሊስት ሆነው የተገኙት የአይሲቲና ዲጂታይዜሽን አማካሪ- አቶ ኑረዲን መሐሙድ ሀገራችን "ዲጂታል ኢትዮጵያ" ስትራቴጂን ቀርጻ በትኩረት እየሠራች ስለመሆኑ አንስተዋል።

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ዲጂታይዜሽን ላይ የኢኖቬሽን ሥነምህዳር ላይ እየሠራ ያለውን ሥራ አብራርተዋል።

የስኪል ኢትዮጵያ የፈጠራ ባለሙያው ወጣት ሁነኛው ዘሩ በፓናሊስትነት ቀርቦ የዲጂታይዜሽን አጠቃቀም ከራሱ ተጨባጭ ህይወት አንጻር አቅርቧል።

ሀሳብ ይዞ ሀሳቡን ወደ ውጤት የቀየረበትን ሂደት ለወጣቶች በሚጠቅም መልኩ ተሞክሮውን አቅርቧል።

የፈጠራ ባለሙያው ከ5 በላይ የፈጠራ ሥራዎችን ፒች አድርጓል።

Telegram; https://t.me/fdretvtinstitute
Website: https://www.ftveti.edu.et/
Youtube ;
https://www.youtube.com/fdretvtinstitute
Tiktok; www.tiktok.com/
Twitter (X); https://x.com/FDRETVTI
WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029Vb73e9cGOj9ooFTo2u1R

Dezhou Engineering Vocational College and FTVTI Partner to Advance Electric Vehicle Skills in Ethiopia August 18,2018 AD...
18/08/2026

Dezhou Engineering Vocational College and FTVTI Partner to Advance Electric Vehicle Skills in Ethiopia
August 18,2018 ADDIS ABABA —

A high-level delegation from China’s Dezhou Engineering Vocational College, led by President Wei Rongqing, met with the Deputy Director General of FTVTI, Mrs. Tsedale Teklu, to explore strategic partnerships in the electric vehicle (EV) sector.

The bilateral discussions focused on driving technological innovation and capacity building within the automotive industry, aligning with Ethiopia’s national transition toward renewable energy and sustainable mobility.
During the engagement, Mrs. Tsedale highlighted FTVTI’s proactive steps in specialized curriculum and training programs designed to develop market-ready EV technicians.

President Wei underscored China’s global leadership in EV research and development, expressing Dezhou Engineering Vocational College’s intent to deepen institutional cooperation through three main pillars:
• Joint EV Academy: Establishing a dedicated institution to equip Ethiopian youth with technical skills, fostering entrepreneurship and employment.
• Advanced Automotive Service Center: Building a state-of-the-art repair and maintenance facility for modern vehicle fleets.
• Local EV Assembly Operations: Developing localized assembly capabilities to support domestic manufacturing.

Following the formal briefing, the delegation conducted an inspection tour of FTVTI’s training workshops, automotive repair infrastructure, and its commercial wing, the Technobizia Industrial Products Enterprise.

Telegram; https://t.me/fdretvtinstitute
Website: https://www.ftveti.edu.et/
Youtube ;
https://www.youtube.com/fdretvtinstitute
Tiktok; www.tiktok.com/
Twitter (X); https://x.com/FDRETVTI
WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029Vb73e9cGOj9ooFTo2u1R

18/08/2026

በየዓመቱ 250 የጎረቤት ሀገራት ዜጎችን በ'ስኮላርሺፕ' ተቀብሎ እያሰለጠነ እንደሆነ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት አስታወቀ

ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. (አሐዱ ሬዲዮ) ባለፉት 5 ዓመታት በየዓመቱ የሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሶማሌላንድን ጨምሮ የሌሎች ጎረቤት ሀገራት ዜግነት ያላቸውን 250 ተማሪዎች በነጻ የትምህርት እድል (ስኮላርሺፕ) ተቀብሎ እያሰለጠነ እንደሚገኝ የኢፌዴሪ ቴክኒክ እና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር እንደገለጹት፤ "መርሃ-ግብሩ ቅድሚያ ለጎረቤት ሀገራት የሚለውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በመከተል ቀጣናዊ ትስስርን በሰው ኃይል ማጠናከርን ታሳቢ ያደረገ ነው።"

ዋና ዳይሬክተሩ በማብራሪያቸው፤ "ሰልጣኞቹ ወደየሀገራቸው ከተመለሱ በኋላ የጋራ እድገትን ለማምጣት እና የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ" ብለዋል።

ኢንስቲትዩቱ ከጎረቤት ሀገራት ባለፈ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም ነጻ የትምህርት ዕድሎችን እየሰጠ መሆኑን ዶ/ር ብሩክ አንስተዋል።

የስኮላርሺፕ ፕሮግራሙ የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 አንዱ መሠረት የሆነውን የሰው ኃይል ልማት ለማሳደግ የሚያግዝ እንደሆነም አስረድተዋል።


በአበረ ስሜነህ

ፌስቡክ ገጽ፡- https://web.facebook.com/ahadutelevision
ቴሌግራም ገጽ፡- https://t.me/ahaduradio
ቲክቶክ ገጽ፡- tiktok.com/.official
ዌብሳይት፡- www.ahaduradio.com
ኢንስታግራም ፡- www.instagram.com/ahaduradio/

https://web.facebook.com/AhaduRadioTvLive/

.3

ቴክኖቢዚያ የኢንዱስትሪ ውጤቶች ኢንተርፕራይዝ አዲስ ብራንድ አስተዋወቀ።******ነሀሴ 10/2018*****የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ቴክኖቢዚያ የኢንዱስትሪ ውጤቶች ኢንተርፕ...
16/08/2026

ቴክኖቢዚያ የኢንዱስትሪ ውጤቶች ኢንተርፕራይዝ አዲስ ብራንድ አስተዋወቀ።
******ነሀሴ 10/2018*****

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ቴክኖቢዚያ የኢንዱስትሪ ውጤቶች ኢንተርፕራይዝ ለባለድርሻ አካላት አዲስ ብራንድ አስተዋውቋል።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር እና የኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂና ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፀዳለ ተክሉ የኢንተርፕራይዙን አዲስ ቢሮ መርቀው ከፍተዋል።

ዘመናዊና ለሥራ ምቹ ቢሮ ከማስመረቁ በተጨማሪ አዲስ ሎጎ እና ብራንድ አስተዋውቋል።

አዲሱ ሎጎ ኢንተርፕራይዙ የተቋቋመለትን እያመረተ የማሰልጠን፣ ከውጭ የሚገቡ ቴክኖሎጂዎችን በመተካት ፈጠራዎችን በብዛት አምርቶ ለተጠቃሚ የማድረስ ተልዕኮ እንደሚገልጽ የኢንተርፕራይዙ ተወካይ ሥራአስኪያጅ ኢንጂነር ሰለሞን ገልጸዋል።

ኢንተርፕራይዙ በተደራጀ መንገድ ራሱን ወደ ገበያው ለማስተዋወቅ የሚያስችል የተደራጀ የብራንዲንግ ሥራ መሆኑንም ጨምረው አብራርተዋል።

ሌላው ኢንተርፕራይዙ ራሱን በዘመናዊ አሠራር ውስጥ የሚያስገባውን Enterprise Resource Planning system (ERP) ሥራ አስጀምሯል።

ሲስተሙ የኢንተርፕራይዙን ሥራ የወረቀት አሰራርን በመቀነስ ዘመናዊነትን የተላበሠ ዲጂታል አሠራር ለመተግበር ያስችለዋል ተብሏል። ኢንተርፕራይዙ ያለውን ሰብአዊና ቁሳዊ ሀብት ለመቆጣጠር ያስችለዋል የተባለው ይህ ሲስተም ሠራተኞች በአሻራ የሚገቡበትን ሠዓት የሚመዘግብ ስርዓት እንደያዘ ተገልጿል።

ሲስተሙ በየትኛውም ቦታ እና በማንኛውም ሠአት ሥራዎችን እየተከታተሉ አቅጣጫ ለማስቀመጥ እንደሚያስችል የተገለጸ ሲሆነሰ ይህም ከ35% በላይ ምርታማነትን ማሳደግ ያስችላል ተብሏል።

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙ የቦርድ አባላት እና ሌሎች ባለድርሻዎች ኢንተርፕራይዙ በአጭር ጊዜ ያሳየውን ለውጥ አድንቀዋል።

ኢንስቲትዩቱ በዘርፉ ያለውን መሪነት ከሚያረጋግጥባቸው ለውጦች መካከል አንዱ ኢንተርፕራይዙ መሆኑን ያነሱት ተሳታፊዎች የብራንዲንግ ሥራው ይበልጥ ራሱን ለማስተዋወቅ እንደሚያስችለው ገልጸዋል።

Telegram; https://t.me/fdretvtinstitute
Website: https://www.ftveti.edu.et/
Youtube ;
https://www.youtube.com/fdretvtinstitute
Tiktok; www.tiktok.com/
Twitter (X); https://x.com/FDRETVTI
WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029Vb73e9cGOj9ooFTo2u1R

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 12:30
13:30 - 17:00
Tuesday 08:00 - 12:30
13:30 - 17:00
Wednesday 08:00 - 12:30
13:30 - 17:00
Thursday 08:00 - 12:30
13:30 - 17:00
Friday 08:00 - 11:30
13:30 - 17:00

Telephone

+251116465689

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት / FDRE TVT Institute posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት / FDRE TVT Institute:

Shortcuts

Share