በጋርዳ ማርታ ወረዳ ግብርና ጽ / ቤት የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Alem
  • በጋርዳ ማርታ ወረዳ ግብርና ጽ / ቤት የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ

በጋርዳ ማርታ ወረዳ ግብርና ጽ / ቤት የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ Garda Marta Woreda

"በክልሉ የዶሮ አቅርቦትና ግብይት ማነቆዎችን ለመፍታት እየተሠራ ነው!" ዶ/ር አባይነህ ኬዳበክልሉ ግብርና ቢሮ የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ ከደቡብ ኢትዮጵያ ዶሮ እርባታ ኢንተርፕራይ...
22/07/2026

"በክልሉ የዶሮ አቅርቦትና ግብይት ማነቆዎችን ለመፍታት እየተሠራ ነው!" ዶ/ር አባይነህ ኬዳ

በክልሉ ግብርና ቢሮ የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ ከደቡብ ኢትዮጵያ ዶሮ እርባታ ኢንተርፕራይዝ ጋር በመቀናጀት በክልሉ ዞኖች የፍላጎት ዳሰሳና የግንዛቤ መፍጠር ሥራዎችን በመገምገም ግብረ-መልስ ሰጥቷል።



በክልሉ ግብርና ቢሮ የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ በክልሉ የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ ግቦችን ለማሳካት ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል የዶሮ ሀብት ልማትን ማፋጠን አንዱ መሆኑ ይታወቃል።

በክልሉ ቀደም ሲል ሲስተዋል የነበረ የዶሮ አቅርቦት ተግዳሮትን በመሠረታዊነት ለመቅረፍ ይቻል ዘንድ ክልሉ የራሱን የዶሮ እርባታ ኢንተርፕራይዝ አቋቁሞ ወደ ትግበራ መገባቱ ይታወሳል።

ይህንኑ ተከትሎ በወላይታ ሶዶ የወላጅ ዶሮ እርባታና ማሰራጫ ማዕከል ተቋቁሞ የአንድ ቀን ዕድሜ የዶሮ ጫጩት፣ ቄብና ኮከኔ የማምረትና የማሰራጨት ሥራ እየተሠራ ይገኛል።

ኢንተርፕራይዙ በመስኩ ሲስተዋል የቆየውን የአቅርቦትና ግብይት ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የሚችል አቅም ቢገነባም አቅርቦቱ ከፍላጎቱ ከፍያለ ሆኖ በመገኘቱ ያለውን ክፍተቱን ለመሙላት ከእርባታ ኤክስቴንሽኑ ጋር በቅንጅት እንዲሠራ አቅጣጫ ተቀምጧል።

በዚሁ መሠረት በክልሉ ግብርና ቢሮ የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ የድጋፍና ክትትል ቡድን ከኢንተርፕራይዙ ጋር በመቀናጀት በክልሉ ዞኖች የሚስተዋለውን የዶሮ ፍላጎት ከመለየት በተጨማሪ ግንዛቤ የመፍጠር ተግባራትን በማከናወን በተገኙ ጭብጦች ዙሪያ የጋራ መድረክ በመፍጠር ግብረ-መልሶችን ሰጥቷል።

የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር አባይነህ ኬዳ በክልሉ ዶሮ አርቢ ኅብረተሰብ ዘንድ ሰፊ ፍላጎት ቢኖርም አቅርቦቱን ከግብይት ጋር ከማስተሳሰር አንፃር ተግዳሮቶች መስተዋላቸውን ገልፀዋል።

ዶ/ር አባይነህ ተግዳሮቱን ለመቅረፍ የእርባታ ኢንተርፕራይዙ ከኤክስቴንሽኑ ጋር ተሸናጅቶ ኤንዲሠራ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ዘርፉ ሥራዎችን እየከወነ እንደሚገኝ ገልፀው ለድጋፍና ክትትል ቡድኑ በተሰጠው ተልዕኮ መሠረት ተግባራት በቅንጅት ተፈፅመው ግብረ-መልስ በሠሰጠቱ ምስጋና አቅርበዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ዶሮ እርባታ ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር አዲሱ ኢዮብ በበኩላቸው ኢንተረፕራይዙ Tetra-H የተሰኘ የተሻሻለና ምርታማ የሆነ የወላጅ ዶሮ ዝርያ እርባታና ማሰራጫ ማዕከል በወላይታ ሶዶ ማዕከል በመክፈት የአንድ ቀን ዕድሜ የዶሮ ጫጩቶችን ጨምሮ ቄብና ኮከኔዎችን እያመረተ እንደሚገኝ ገልፀው ምርቱን ከማሰራጨት አንፃር ተግዳሮት ሲገጥም እንደቆዬ ተናግረዋል።

የገጠመውን ተግዳሮት ለመቅረፍ ይቻል ዘንድ ኢንተርፕራይዙ ከክልሉ እንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ ጋር በመቀናጀት ፍላጎትና ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እስከ ዞን ወርዶ ማከናወኑን አብራርተዋል።

የወላጅ ዶሮ እርባታ ማዕከሉ በአሁኑ ወቅት ለክልሉ ዶሮ አርቢ ኅብረተሰብ የሚበቃ አቅርቦት በእጁ እንደሚገኝ የጠቆሙት ዶ/ር አዲሱ ለማዕከሉ የሚቀርብ ማናቸውም ጥያቄ እንደሚስተናገድ አመልክተው የድጋፍና ክትትል ቡድኑን አመስግነዋል።

አክለውም የተሰጠው ግብረ-መልስ ቅቡልነት ያለውና በቀጣይ የሚያሠራ መሆኑን አመልክተው የተጀመረው ቅንጅታዊ አሠራር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

በመድረኩ ዶ/ር አባይነህ ኬዳን እና ዶ/ር አዲሱ ኢዮብን ጨምሮ የክልሉ እንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ እና የዶሮ እርባታ ኢንተርፕራይዙ ከፍተኛ ባለሙያዎች መሳተፋቸው ተዘግቧል።

በአያሌው ዘነበ

በጋሞ ዞን ጋርዳ ማርታ ወረዳ የ2018/19 መኸር ወቅት ለአርሶ አደሮች  የክህሎት ስልጠና በተለያዩ ቀበሌዎች መሰጠት ተጀምሯል።  Marta Woreda Agriculture_Office
21/07/2026

በጋሞ ዞን ጋርዳ ማርታ ወረዳ የ2018/19 መኸር ወቅት ለአርሶ አደሮች የክህሎት ስልጠና በተለያዩ ቀበሌዎች መሰጠት ተጀምሯል።

Marta Woreda Agriculture_Office

Shoat pox vaccination is being held in Gamo Zone Garda Marta Woreda Shakaro kebele.  Harsiso Haile(DVM) who is Animal He...
17/07/2026

Shoat pox vaccination is being held in Gamo Zone Garda Marta Woreda Shakaro kebele.

Harsiso Haile(DVM) who is Animal Health Coordinator in office of Agriculture.

Garda Marta,Gogale

💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪

👉በዶሮ እርባታ ሥራ ዘርፍ ለመሰማራት ለምትፈልጉ በሙሉ!!በግለሰብ ፡ በቡድን እንዲሁም በማህበር ለመስራት ፍላጎት ያላችሁ ከአሁኑ ፍላጎታችሁን ቢያሳውቁ ይመረጣል።
16/07/2026

👉በዶሮ እርባታ ሥራ ዘርፍ ለመሰማራት ለምትፈልጉ በሙሉ!!

በግለሰብ ፡ በቡድን እንዲሁም በማህበር ለመስራት ፍላጎት ያላችሁ ከአሁኑ ፍላጎታችሁን ቢያሳውቁ ይመረጣል።

በጋሞ ዞን ጋርዳ ማርታ ወረዳ ጎጋሌ ቀበሌ የበርበሬ ምርት አሰባሰብ በከፊል---በብዙ ዘርፍ ሞዴል አርሶአደር በአቶ ማርቃ ማሳ!!
15/07/2026

በጋሞ ዞን ጋርዳ ማርታ ወረዳ ጎጋሌ ቀበሌ የበርበሬ ምርት አሰባሰብ በከፊል---

በብዙ ዘርፍ ሞዴል አርሶአደር በአቶ ማርቃ ማሳ!!

በጋርዳ ማርታ ወረዳ "ከተረጂነት ወደ ምርታማነት፤ ለተሟላ ሀገራዊ ክብርና ሉዓላዊነት" በሚል መሪ ቃል  የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው።​ጋርዳ ማርታ፡ ሐምሌ 1/2018 ዓ.ም (ጋርዳ ማርታ...
09/07/2026

በጋርዳ ማርታ ወረዳ "ከተረጂነት ወደ ምርታማነት፤ ለተሟላ ሀገራዊ ክብርና ሉዓላዊነት" በሚል መሪ ቃል የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው።

​ጋርዳ ማርታ፡ ሐምሌ 1/2018 ዓ.ም (ጋርዳ ማርታ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት)፣

በጋሞ ዞን ጋርዳ ማርታ ወረዳ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት፤ ለተሟላ ሀገራዊ ክብርና ሉዓላዊነት፣ የሰብአዊ ድጋፍ ሉዓላዊነትን በወረዳ ለማብሰር የተዘጋጀ የንቅናቄ መድረክ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጋርዳ ማርታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግዛቸው በቀለ፥ ከተረጂነት አስተሳሰብና ልምድ ተላቆ ወደ ሙሉ ምርታማነት ለመሸጋገር የሚደረገው ጥረት አሁን ላይ ተጨባጭና ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን እያስመዘገበ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ዋና አስተዳዳሪው አያይዘውም፣ተረጂነትን በዘላቂነት ለማስቀረት የተጀመሩ የምርታማነት ሥራዎቻችን ይበልጥ ማጠናከርና የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ ረገድ ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የጋርዳ ማርታ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት፣አደጋ ስጋትና የምግብ ዋስትና ተጠሪ ተቋም ኃላፊ የሆኑት አቶ ነጋ ከድር በበኩላቸው፥ ባለፉት ጊዜያት ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ስራ ላይ በርካታ ተግባራት ተሰርቷል ያሉት ሲሆን፣በወረዳችን ካሉ አርሶ አደሩና ከአምራቹ ማህበረሰብ ክፍሎች ወረዳ ማዕከልን ጨምሮ በሁሉም ቀበሌያት በተዘጋጁ በ13ቱ መጋዘኖች 107.5 ኩ/ል እህል መሰብሰብ ተችሏል ብለዋል።

እንደ አቶ ነጋ ገለጻ፣ለመጠባበቂያ ፈንድ በመመደብና ከየማህበራዊ መሰረት አስተባብሮ ሀብት በማሰባሰብ በብር 53 ሺሕ 830 ወደ ተከፈተው ዝግ አካውንት እንዲገባ የማድረግ ስራ ተሰርቷል።

በመድረኩ፣የተጠሪ ተቋሙ ኃላፊ የሆኑት አቶ ነጋ ከድር፥ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ስራ ላይ የተከወኑ አፈጻጸም እና የቀጣይ ዕቅድ ዙሪያ የተዘጋጀውን ሰነድ በማቅረብ ላይ ናቸው።

ቀጥሎም በሚቀርበው ሰነድ ዙሪያ ሰፊ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በጋሞ ዞን ጋርዳ ማርታ ወረዳ የሐምሌ አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ የቅድመ ዝግጅት ሥራ በከፊል---
05/07/2026

በጋሞ ዞን ጋርዳ ማርታ ወረዳ የሐምሌ አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ የቅድመ ዝግጅት ሥራ በከፊል---

በጋሞ ዞን ጋርዳ ማርታ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በቀን 24/10/2018 ዓ/ም በማርታ ላዶ  በዘመቻ የበጎችና ፍየሎች የበሽታ(Shoat pox) መከላከያ ክትባት መጀመሩን አስታወቀ።የወረዳው ግብ...
02/07/2026

በጋሞ ዞን ጋርዳ ማርታ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በቀን 24/10/2018 ዓ/ም በማርታ ላዶ በዘመቻ የበጎችና ፍየሎች የበሽታ(Shoat pox) መከላከያ ክትባት መጀመሩን አስታወቀ።

የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ ሐሼ በመልዕክታቸው የእንስሳት አርቢው ማህበረሰብ በትኩረት የክትባት አገልግሎቱን በመጠቀም በየጊዜው የሚከሰቱ የእንስሳት በሽታዎችን ቀድሞ መከላከል እንዲችል አስገንዝበዋል።

03/05/2026
19/04/2026

Address

Gamo Zone
Addis Alem
YES

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በጋርዳ ማርታ ወረዳ ግብርና ጽ / ቤት የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share