22/11/2025
የእንስሳት ጤንነትና ደህንነትን በህግ ማዕቀፍ የመደገፍ ጉዞ
(አዳማ፣ ሕዳር 13 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር)
በኢትዮጵያ የእንስሳት ሃብቱ ባለው ሰፊ ፀጋ መነሻነት በርካታ አርሶና አርብቶአደሮች እንዲሁም በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች ምርታማነትን እያሳደጉ ከራሳቸው አልፈው ለሀገር ኢኮኖሚ ምሰሶ ሆነው ይገኛሉ፡፡
በዚህ ሂደት የእንስሳት ጤናና ደህንነትን መጠበቅ አንዱ ትኩረት ነው፡፡ የግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት ጤናና ደህንነት ችግሮችን ለመፍታት የእንስሳት ልየታ፣ ምዝገባ፣ ክትትል እና የእንስሳት ደህንነት ስርዓትን ዘርግቶ እየሰራ ይገኛል፡፡
የእንስሳት ደህንነትን በዘላቂነት ለመጠበቅም አሰራሮችና የህግ ማዕቀፎችን ከመተግበር ባለፈ የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎችን በተከታታይ መስራት ያስፈልጋል፡፡
ግብርና ሚኒስቴር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር አለም አቀፍ የእንስሳት ቀንን በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መንገዶች አክብሯል፡፡
በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) የእንስሳት ሀብቱ ለአገራዊ ኢኮኖሚ ከሚያበረክተው አስተዋፅኦ በተጨማሪ ለበርካታ አርሶና አርብቶአደሮች የክብርና የሃብት መገለጫዎች መሆናቸውን ጠቅሰው፣ የእንስሳት ደህንነትና ጤንነትን መጠበቅ ሃገራችን በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን እንደሚያስችላት ተናግረዋል፡፡
የእንስሳት ሀብቱን ለማሳደግ የእንስሳቱን ጤንነትና ደህንነት ሳይንሳዊ በሆነ አሰራር መጠበቅ ይገባል፡፡
ለዚህ አጋዥ የሆኑ የህግ ማዕቀፎች መውጣታቸው ደግሞ ዘርፉ ትልቅ ትኩረት ማግኘቱን አመላካች ናቸው፡፡
የእንስሳት ጤንነትና ደህንነት አዋጅን መሰረት በማድረግ የእንስሳት ልየታና ደህንነትን የሚያስጠብቁ የእንስሳትና የእንስሳት ውጤቶች ልየታ፣ ምዝገባና ክትትል እንዲሁም የእንስሳት ደህንነት ስትራቴጂዎች የስራ መመሪያዎች እንዲሆኑ ይፋ ተደርገዋል፡፡
ዘጋቢ፦ ተዋበ ጫኔ
ፎቶግራፈር፦ ጌታቸው ምትኩ
#ከማምረትበላይ
-------------------------
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ስለግብርና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት👇
📌ድረ-ገጽ፦ www.moa.gov.et
📌ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/MoAEthiopia
📌ዩቲዩብ፦ https://www.youtube.com/
📌ቴሌግራም፦ https://t.me/MoAEthiopianews
📌ቲዊተር፦ https://x.com/MoA_Ethiopia
📌ሊንክድኢን፡- https://shorturl.at/7O6cs
📌ቲክቶክ፦ http://www.tiktok.com/
📌ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/moa_ethiopia/
F.D.R.E Ministry of Agriculture is a Governmental Organization Headquartered in Bole sub-city Ethiopia,Addis Ababa