Agarfa ATVET College

Directions Website Contact the university

Agarfa ATVET College Agarfa Agricultural TVET College is one of the Federally administered colleges under the Ministry of
(1)

በአጋርፋ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ኮሌጅ በቡቃያ ላይ የፀረ-አረም ርጭት ተጀመረአጋርፋ፡ መስከረም 06/2019 ዓ.ም — በአጋርፋ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥሰልጠና ኮሌጅ...
15/09/2026

በአጋርፋ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ኮሌጅ በቡቃያ ላይ የፀረ-አረም ርጭት ተጀመረ

አጋርፋ፡ መስከረም 06/2019 ዓ.ም — በአጋርፋ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥሰልጠና ኮሌጅ ቡቃያዎችን ከአረም ውድድር በመጠበቅ፣ ጤናማ እድገታቸውንና ምርታማነታቸውን ለማሻሻል የፀረ-አረም ርጭት ሥራ ተጀምሯል።

የርጭት ሥራው በባለሙያዎች ክትትልና በተገቢው የአጠቃቀም መመሪያ መሠረት እየተከናወነ ሲሆን በቡቃያዎቹ ዙሪያ የሚገኙ አረሞችን በመቆጣጠር የተክሎቹን ጤናማ እድገት ለማረጋገጥ ያለመ ነው።

ኮሌጁ በተለያዩ የግብርና ተግባራት ላይ ተግባራዊ ሥልጠናን በማጠናከር፣ የተሻለ የግብርና ክህሎትና ምርታማነት ለማስገኘት በትኩረት እየሰራ ይገኛል።

የኮሌጁ ህዝብ ግንኙነት

የእንኳን አደረሳችሁ መልእክትየአጋርፋ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ዲን የሆኑት አቶ ፊራኦል ኤደኦ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብና ለኮሌጁ ማህበረሰብ  🎉🌼 እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ! 🌼🎉አዲሱ ዓ...
10/09/2026

የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት
የአጋርፋ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ዲን የሆኑት አቶ ፊራኦል ኤደኦ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብና ለኮሌጁ ማህበረሰብ 🎉🌼 እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ! 🌼🎉
አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤና፣ የደስታ፣ የተስፋና የስኬት ዓመት ይሁንላችሁ። ❤️
ያለፈውን በትዝታ፣ ያገኘነውን በምስጋና፣ መጪውን በተስፋ እንቀበል።
🌟 አዲሱ ዓመት ለሁላችንም አዲስ ዕድል፣ አዲስ ተስፋ እና አዲስ ስኬት ይዞ ይምጣ! 🌟
መልካም አዲስ ዓመት! 🎊🌼🇪🇹

በአጋርፋ የግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ የአዲስ ዓመት ድጋፍ ተደረገበአጋርፋ የግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ አዲስ ዓመትን አስመልክቶ አቅመ ደካሞችንና ተማሪዎችን ያማከለ የድጋፍ መርሃ ግብር ተካሄደ።የድጋፍ...
10/09/2026

በአጋርፋ የግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ የአዲስ ዓመት ድጋፍ ተደረገ

በአጋርፋ የግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ አዲስ ዓመትን አስመልክቶ አቅመ ደካሞችንና ተማሪዎችን ያማከለ የድጋፍ መርሃ ግብር ተካሄደ።

የድጋፍ መርሃ ግብሩ ዋና ዓላማ የአዲስ ዓመትን በደስታና በአብሮነት ለማክበር፣ በተለያዩ ምክንያቶች የእለት ተዕለት ኑሯቸው ፈታኝ ለሆኑ ወገኖች ድጋፍ ማድረግ እና የመረዳዳት ባህልን ማጠናከር ነው።

በመርሃ ግብሩ ለአቅመ ደካሞች ለእያንዳንዳቸው 5 ሊትር ዘይት እና 5 ኪሎ ግራም ዱቄት የተደረገ ሲሆን፣ ይህም በበዓሉ ወቅት የቤተሰብ ወጪን በመቀነስ በበዓሉ ደስታ ውስጥ እንዲካፈሉ ለማገዝ የሚያስችል ድጋፍ ነው።

በተጨማሪም ለኮሌጁ ተማሪዎች የደብተርና ብዕር ድጋፍ ተደርጓል። ይህም ተማሪዎች የትምህርት ጉዟቸውን በተሻለ ሁኔታ እንዲቀጥሉና በተለይም በበዓል ወቅት የሚኖራቸውን ተጨማሪ የኑሮ ጫና ለመቀነስ የሚያግዝ ተግባር ነው።

በመርሃ ግብሩ ላይ የኮሌጁ የማኔጅመንት አባላት ተገኝተው በድጋፍ ሥራው ተሳትፈዋል።

የማኔጅመንቱ ተሳትፎም ተቋሙ ከትምህርት ሥራው ባሻገር ለማህበረሰቡና ለተማሪዎቹ ያለውን ማህበራዊ ኃላፊነት የሚያሳይ ነው።

በአጠቃላይ፣ የአዲስ ዓመት ድጋፍ መርሃ ግብሩ የአብሮነት፣ የመረዳዳትና የማህበራዊ ኃላፊነት እሴቶችን በተግባር ያሳየ ሲሆን፣ አቅመ ደካሞችና ተማሪዎች በአዲሱ ዓመት የበዓሉን ደስታ እንዲጋሩ አስተዋፅዖ አድርጓል።

አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የአብሮነትና የብልጽግና ይሁን!

መልካም አዲስ ዓመት! 🎉

ጷግሜ 5/2018 ዓ.ም

የኮሌጁ ህዝብ ግንኙነትና ኮምዩኒኮሽን ሥራ አስፈጻሚ

የወደፊት እሳቤ ስልጠና በአጋርፋ ግ/ቴ/ሙ/ት/ኮሌጅበአጋርፋ ግ/ቴ/ሙ/ት/ኮሌጅ የኮሌጁን “የነገ ቀን” የሚለውን ስያሜ መሠረት በማድረግ “የወደፊት እሳቤ” በሚል ርዕስ ለኮሌጁ አመራር ስልጠና...
10/09/2026

የወደፊት እሳቤ ስልጠና በአጋርፋ ግ/ቴ/ሙ/ት/ኮሌጅ

በአጋርፋ ግ/ቴ/ሙ/ት/ኮሌጅ የኮሌጁን “የነገ ቀን” የሚለውን ስያሜ መሠረት በማድረግ “የወደፊት እሳቤ” በሚል ርዕስ ለኮሌጁ አመራር ስልጠና ተሰጠ።

ስልጠናውን የሰጡት የኮሌጁ ዲን አቶ ፊራኦል ኤደኦ ሲሆኑ፣ የስልጠናው ዋና ዓላማ ተሳታፊዎች ስለወደፊት ዕቅዳቸው፣ ስለራስ እድገት እና ስለተቋሙ የወደፊት አቅጣጫ በግልጽ እንዲያስቡ ማድረግ ነው።

በስልጠናው ወቅት የወደፊት ራዕይን መገንባት፣ የሚፈለገውን ግብ በግልጽ መለየት እና ያለውን አቅም በአግባቡ በመጠቀም ወደተፈለገው ውጤት መድረስ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ሀሳቦች ተነስተዋል።

“የነገ ቀን” የሚለው የኮሌጁ ስያሜ በራሱ የተሻለ ነገን ለመገንባት የሚያነሳሳ መልዕክት እንደሚያስተላልፍ የተጠቆመ ሲሆን፣ ይህንንም ራዕይ በተግባር ለመተርጎም የእያንዳንዱ የኮሌጁ ማህበረሰብ አባል የራሱን ድርሻ መወጣት እንደሚገባው ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም የወደፊት ስኬት በምኞት ብቻ የሚገኝ ሳይሆን፣ በዕቅድ፣ በትጋት፣ በተጠያቂነት፣ በትብብር እና በቀጣይነት በሚደረግ ሥራ እንደሚገነባ በስልጠናው ላይ አፅንዖት ተሰጥቷል።

በመጨረሻም ተሳታፊዎች የግል እና የተቋም የወደፊት ግቦችን በማስቀመጥ፣ ለእነዚህ ግቦች መሳካት የሚያስፈልጉ ተግባራትን በመለየት እና በተግባር በመተርጎም የተሻለ ነገን ለመገንባት ቁርጠኛ መሆን እንደሚገባ ተላልፏል።

“የነገ ቀን” የሚለውን ስያሜ በተግባር ለመግለጽ የዛሬ ውሳኔና ተግባር ወሳኝ መሆኑን ያስገነዘበው ይህ ስልጠና፣ ለኮሌጁ ማህበረሰብ የወደፊት ራዕይን በማጠናከር ረገድ ጠቃሚ መድረክ ሆኗል።

ጷግሜ 05/2019
የኮሌጁ ህዝብ ግንኙነትና ኮምዩኒኬሽን

በአጋርፋ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ የሚለማው የበርበሬ ሰብል በፈንገስ መጠቃቱን ተከትሎ የባለሙያዎች ምልከታ ተደረገአጋርፋ፣ ኢትዮጵያ — በአጋርፋ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ እየለማ ያለው የበርበሬ ሰ...
08/09/2026

በአጋርፋ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ የሚለማው የበርበሬ ሰብል በፈንገስ መጠቃቱን ተከትሎ የባለሙያዎች ምልከታ ተደረገ

አጋርፋ፣ ኢትዮጵያ — በአጋርፋ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ እየለማ ያለው የበርበሬ ሰብል በፈንገስ መጠቃቱን ተከትሎ ከሲናና እርሻ ምርምር ተቋም የመጡ ባለሙያዎች የመስክ ምልከታ አድርገዋል።

በኮሌጁ የሚለማው የበርበሬ ሰብል በተለያዩ የተክል ጤና ችግሮች መጠቃቱ ከታወቀ በኋላ፣ የችግሩን ምንነት ለመለየትና ተገቢውን የመፍትሔ አቅጣጫ ለማስቀመጥ የባለሙያዎቹ ምልከታ ተካሂዷል።

ባለሙያዎቹ የበርበሬ ተክሎችን በመመልከት፣ በተጎዱ የተክል ክፍሎች ላይ የሚታዩ ምልክቶችን በመመዝገብ እና የሰብሉን አጠቃላይ የእድገት ሁኔታ በመገምገም የመስክ ምልከታ አድርገዋል። ይህም የበሽታውን መነሻና ስርጭት በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት ጠቃሚ እንደሆነ ተገልጿል።

የበርበሬ ምርት በአገሪቱ የምግብ ፍጆታና የገበያ ፍላጎት ውስጥ ጠቃሚ ሚና ያለው ሲሆን፣ በሰብሉ ላይ የሚከሰቱ የፈንገስ በሽታዎች በተገቢው ጊዜ ካልተለዩና ካልተቆጣጠሩ በምርት መጠንና ጥራት ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ።

በመሆኑም በኮሌጁ የተከሰተውን የበርበሬ ችግር በሳይንሳዊ መንገድ መለየት፣ የበሽታውን ምንጭ ማጥናትና ተገቢውን የቁጥጥር ዘዴ መምረጥ አስፈላጊ ሆኗል። የእርሻ ምርምር ባለሙያዎች በመስክ ምልከታው ያገኙትን መረጃ በመመርመር ለቀጣይ የበሽታ ቁጥጥር ሥራ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጡ ይጠበቃል።

ከዚህ በተጨማሪም የኮሌጁ የተግባር ልምምድ መስክ በመሆኑ፣ የበርበሬው ሰብል በተማሪዎችና በኮሌጁ የሙያ ሥልጠና ሥራ ውስጥ ተግባራዊ የመማሪያ ዕድል ይፈጥራል። በዚህ ረገድ የተክል በሽታን በመለየት፣ በመከላከልና በመቆጣጠር ዙሪያ ተማሪዎች ተግባራዊ ልምድ እንዲያገኙ ያግዛል።

የባለሙያዎች ምልከታም በበርበሬ ሰብሉ ላይ የታየውን የፈንገስ ችግር በተገቢው ለመቆጣጠር ከሚደረጉ የቴክኒክ ድጋፎች አንዱ ሲሆን፣ በቀጣይ በሚሰጡ የባለሙያ ምክረ-ሃሳቦች መሠረት የተገቢው እርምጃ እንደሚወሰድ ይጠበቃል።

በአጠቃላይ፣ በአጋርፋ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ በበርበሬ ሰብል ላይ የታየውን የፈንገስ ችግር በቅርበት በመከታተልና በባለሙያ ድጋፍ በመታገዝ ሰብሉን ከተጨማሪ ጉዳት መከላከል እና የምርት ጥራቱን ማስጠበቅ የሚቻልበት አቅጣጫ መፍጠር ይቻላል።

ጷግሜ 2/2018 ዓ.ም
የኮሌጁ ህዝብ ግንኙነት

03/09/2026
የአምስት ዓመት ጉዞ የውይይት መድረክ መቋጫውን አገኘበሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሲካሄድ የሰነበተው “የአምስት ዓመት ጉዞ” የውይይት መድረክ በስኬት መቋጫውን አግኝቷል።በመድረኩ የአምስት ዓመቱ ...
03/09/2026

የአምስት ዓመት ጉዞ የውይይት መድረክ መቋጫውን አገኘ

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሲካሄድ የሰነበተው “የአምስት ዓመት ጉዞ” የውይይት መድረክ በስኬት መቋጫውን አግኝቷል።

በመድረኩ የአምስት ዓመቱ የሥራ አፈጻጸም፣ የተገኙ ውጤቶች፣ የተለዩ ስኬቶችና በቀጣይ የሚከናወኑ የሥራ አቅጣጫዎች በስፋት ተገምግመዋል።

በመድረኩ ጥሩ አፈጻጸም ላሳዩ ተቋማት የምስክር ወረቀትና የዋንጫ ሽልማት ተበርክቷል። ከተሸላሚ ተቋማት መካከልም አጋርፋ ኮሌጅ ይገኝበታል።

የሥራና ክህሎት አማካሪ ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ነቢሃ ሙሐመድ በመድረኩ የአምስት ዓመቱን ጉዞ በማጠቃለል በቀጣይ የሚከናወኑ ሥራዎችንና የሥራ አቅጣጫዎችን አቅርበዋል።

የመድረኩ መጠናቀቅ በተቋማት የተመዘገቡ ውጤቶችን ከመገምገም ባለፈ፣ በቀጣይ የሥራና ክህሎት ዘርፉን ለማጠናከር የሚያስፈልጉ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ የሚያግዝ መድረክ ሆኗል።

ነሀሴ 29/2018 ዓ.ም
የኮሌጁ ህዝብ ግንኙነት

የአጋርፋ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ምርትና አገልግሎቶች በ5 ዓመት የልማት ጉዞ መድረክ ላይ ቀረቡየአጋርፋ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ በስራና ክህሎት ሚኒስቴር በተዘጋጀው የ5 ዓመት የልማት ጉዞ የምክ...
31/08/2026

የአጋርፋ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ምርትና አገልግሎቶች በ5 ዓመት የልማት ጉዞ መድረክ ላይ ቀረቡ
የአጋርፋ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ በስራና ክህሎት ሚኒስቴር በተዘጋጀው የ5 ዓመት የልማት ጉዞ የምክክር መድረክ ላይ ምርትና አገልግሎቶቹን ማስተዋወቅ ጀምሯል።
ኮሌጁ በሰልጣኞች ክህሎት ልማት፣ በቴክኖሎጂ እና በሰብል ልማት ዘርፎች ያከናወናቸውን ስራዎችና ያፈራቸውን ምርቶች በመድረኩ ለእይታ አቅርቧል።
በተለይም በስልጠና፣ በቴክኖሎጂ ልማትና በሰብል ምርት ዘርፎች የተሰሩ ስራዎች ለተሳታፊዎች ቀርበው የኮሌጁን የልማት እና የሙያ ክህሎት አበርክቶ የሚያሳዩ ተግባራት ተገልጸዋል።
የምክክር መድረኩ በስራና ክህሎት ዘርፍ ባለፉት 5 ዓመታት የተከናወኑ ስራዎችን ለመገምገም፣ ልምዶችን ለመለዋወጥና ቀጣይ የልማት አቅጣጫዎችን ለመወያየት የተዘጋጀ ሲሆን፣ መድረኩ ለ5 ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።

ነሀሴ 25/2018ዓ.ም
የኮሌጁ ህዝብ ግንኙነት

በአጋርፋየግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ የክረምት በጎ አድራጎት ሥራ ተከናወነ።በአጋርፋ የግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ በክረምት ወቅት የበጎ አድራጎት ሥራ አከናውኗል። የበጎ አድራጎት ሥራው በወልተኢ ወገርጌ...
24/08/2026

በአጋርፋየግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ የክረምት በጎ አድራጎት ሥራ ተከናወነ።

በአጋርፋ የግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ በክረምት ወቅት የበጎ አድራጎት ሥራ አከናውኗል። የበጎ አድራጎት ሥራው በወልተኢ ወገርጌ ቀበሌ ለምትኖር አቅመ ደካማ እናት የመኖሪያ ቤት የመገንባት ሥራ እንደሆነ በምልከታችን ተገንዝበናል።

ኮሌጁ በተግባራዊ የበጎ ፈቃድ ተሳትፎ 32 ዚንጎ ቆርቆሮ በመጠቀመ የመኖሪያ ቤት በመሥራት ለተቸገረችው እናት የተሻለ የመኖሪያ ሁኔታ እንዲኖራት አስተዋፅዖ አድርጓል።

የቤቱ ዋጋም በብር ሲገመት 5,20,000 የሚያወጣ ሲሆን የተገነባው ቤት ለቤተሰቡ የተሻለ የኑሮ ሁኔታ ለመፍጠር የሚያግዝ ነው።

የኮሌጁ የክረምት በጎ አድራጎት ተግባር የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ፣ የማኅበረሰብ ተሳትፎን በማጠናከርና የወገን ተቆርቋሪነትን በተግባር በማሳየት የሚጠቀስ ሥራ ሆኗል።

እንደ ኮሌጁ የበጎ አድራጎት ሥራ ይህ ተግባር በተቸገሩ ወገኖች ላይ የሚደርሰውን ጫና ለማቃለል ከማገዙም በላይ፣ መምህራንና የኮሌጁ ማኅበረሰብ ለማኅበራዊ ኃላፊነት ያላቸውን ተሳትፎ በተግባር ያሳየ ነው።

በዚህም ኮሌጁ በትምህርትና ሙያ ሥልጠና ላይ ከማተኮሩ በተጨማሪ፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ የበጎ አድራጎትና የወገን ተቆርቋሪነት ባህልን ለማጠናከር ሚናውን እየተወጣ መሆኑን በዚህ ተግባር አሳይቷል።

በፕሮግራሙ ላይ የማኔጅመንት አባልትየት/ት ክፍል ሀላፊዎችና ስራ አስፈጻሚዎች የተገኙ ሲሆን ከቁሳቁስ በተጨማሪ በጉልበትም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል።

ነሀሴ 18/2018 ዓ.ም
የኮሌጁ ህዝብ ግንኙነትና

በአጋርፋ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ  የአረንጓዴ አሻራ መረሀ ግብር እንደቀጠለ ነው።በዛሬው እለት የኮሌጁ ዲን ተወካይና የቴክኖሎጂ ም/ዲን ከልጣኝ የቀበሌ የልማት ጣቢያ ሰራተኞች ጋር በደማቅ ሁኔ...
17/08/2026

በአጋርፋ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ የአረንጓዴ አሻራ መረሀ ግብር እንደቀጠለ ነው።
በዛሬው እለት የኮሌጁ ዲን ተወካይና የቴክኖሎጂ ም/ዲን ከልጣኝ የቀበሌ የልማት ጣቢያ ሰራተኞች ጋር በደማቅ ሁኔታ የችግኝ ተከላ አካሂደዋል።

" ተስፋን እንትከል"

ነሀሴ 11/2018 ዓ.ም

Address

Agarfa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Agarfa ATVET College posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Agarfa ATVET College:

Shortcuts

Share