25/01/2026
____________________//______________
አክሱም ዩኒቨርሲቲ ጥር _ 17/2018 ዓ/ም
ከዛሬ ጥር 17/2018 ዓ.ም እስከ የካቲት 01/2018 ዓ.ም የሚካሔደውን ውድድር በስኬት ለማከናወን አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጀማል አባፊጣ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
አስተናጋጁ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለውድድሩ ቅድመ ዝግጅት ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ ማውጣቱንና ውድድሩን በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ ዝግጅት ማጠናቀቁን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጀማል አባ ፊጣ (ዶ/ር) ገልጸው እንግዶችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ውድድሩም ለሚቀጥሉት 15 ቀናት እንደሚካሄድ ገልጸዋል።
ውድድሩ በጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ በጅማ ዞን አስተዳደር እና በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ማኅበር ትበብር የተዘጋጀ ነው ብለዋል።
የዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ፌስቲቫል በ2008 ዓ.ም ከተቋረጠ በኋላ ባሳለፍነው ዓመት በድጋሜ መጀመሩን የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ማኅበር ፕሬዝዳንት ዓባይ በላይሁን አስታውሰዋል።
የዕለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስትር መኪዩ መሐመድ እንደዚህ ዓይነት ፌስቲቫሎች የባህል ልውውጥ ከማድረግ ባለፈ ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትን ለማጠናከር ሚናው የጎላ መሆኑን በመግለጽ የውድድሩ በይፋ መጀመር አብስረዋል።
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ማህበር ፕሬዝደንት ዓባይ በላይሁን በበኩላቸው ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ይህ ውድድር አንዱ የመፍለቅያ መድረክ በመሆን እያገለገለ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በእግር ኳስ ጥር 18/2018 ዓ/ም አክሱም ዩኒቨርሲቲ ከኢንጂባራ ዩኒቨርሲቲ (Injibara University ) 8:00 ስአት ላይ የሚጫወት ይሆናል ።
መልካም ዕድል ለውድ የዩኒቨርስቲያችን የስፖርት ልኡካን!
ልህቀት በጥረት!
ኣክሱም ዩኒቨርሲቲ@