Hawassa University College Of Medicine And Health Sciences

Hawassa University College Of Medicine And Health Sciences This Page Is An Official page of Hawassa University College Of Medicine and Health Science.

24/08/2026

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በመደበኛና ተከታታይ ፕሮግራሞች በ2019 የትምህርት ዘመን በጤናው ዘርፍ ከመጀመሪያ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ በሚከተሉት የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ሙሉ ዝግጅት ማጠናቃቁን በደስታ ይገልፃል :-
የማመልከቻ ፖርታል(portal.hu.edu.et)
👉 MPH in Epidemiology (Regular and Weekend)
👉General Master Public Health (Regular and Weekend)
👉MSc in Adult Health Nursing
👉MPH in Reproductive Health (Regular and Weekend)
👉MPH in Environmental Health (Regular and Weekend)
👉MSc in Emergency Medicine and Critical Care Nursing
👉MSc in Paediatrics & Child Health Nursing
👉MSc in Medical Parasitology
👉MSc in Medical Microbiology
👉MPH in Hospital and Healthcare Administration
👉MSc in Pharmacology
👉MSc in Clinical Laboratory Science (Specialty: Diagnostic and Public Health Microbiology)
👉MSc in Clinical Anesthesia
👉MPH in Health Service Management (Regular and Weekend)
👉MSc in Clinical Midwifery
👉Gyn-Oncology Subspecialties
👉Oral and Maxillofacial Surgery Residency
👉MSc in Medical Biochemistry
👉PhD in Public Health

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ግንዛቤን ለማጎልበት ታትመው ከሚሠራጩ ትምህርት ሰጭ በሪር(flyers) ተለጣፍ (Stickers) የሕትመት ውጤቶች መ...
22/08/2026

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ግንዛቤን ለማጎልበት ታትመው ከሚሠራጩ ትምህርት ሰጭ በሪር(flyers) ተለጣፍ (Stickers) የሕትመት ውጤቶች መካከል የሚከተሉት ተመርጠዋል።

21/08/2026

Updates on the Upcoming NGAT
***//***

August 21, 2026

All applicants of the National Graduate Admission Exam (NGAT) assigned to Hawassa University,

Please, be informed that the exam is scheduled for Nehase 20 & 21, 2018 EC (August 26 & 27, 2026 GC).

NB: Those applicants who would join Hawassa university for their postgraduate study will get research budget for their graduate theses, a special support from the Office of Vice President for Research and Collaboration!

Hawassa University
Ever to Excel!

Check out the list of nationally accredited research journals of Hawassa University for your publication opportunity!Att...
19/08/2026

Check out the list of nationally accredited research journals of Hawassa University for your publication opportunity!

Attached here is the link to detailed information on our official website

https://journals.hu.edu.et/hu-journals/

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንስቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ''አንድ መስኮት''' ማዕከል በክልል ደረጃ ተሸላሚ ሆነ    ነሔሰ 13/2018ዓም      *****//********በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ...
19/08/2026

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንስቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ''አንድ መስኮት''' ማዕከል በክልል ደረጃ ተሸላሚ ሆነ
ነሔሰ 13/2018ዓም
*****//********
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንስቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ፆታዊ ጥቃት ደርሶባቸው ለህክምና የሚመጡ ሴቶችና ሕፃናት የጋራ ምላሽ መስጫ አንድ መስኮት ማዕከል ችግሩን ለማቃለል ላበረከተው የላቀ አስተዋጾኦ ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፊትህ መምሪያ የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ።

ወ/ሮ ፀሐይ አድማሱ በሲዳማ ክልል ፊትህ ቢሮ በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ልዩ ምርመራና ክስ ዳይሬክተር በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ፆቲዊ ጥቃትን ከመከላከል ባሻገር ተጎጅዎች ወደ ሕግ በሚቀርቡበት ወቅት ተገቢውን ድጋፍ እንድያገኙ ከማድረግ አንጻር የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንስቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት ተጎጅዎች የህክምናና የሕግ አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል እንድያገኙ በማድረግ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጾኦ አመሠግነዋል።

አቶ ፀጋዬ ቶርባ በሀዋሳ ከተማ ፊትህ መምሪያ ልዩ ልዩ ወንጀል ሂደቶች ስራ ሂደት አስተባባሪ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ያለውን አቅም ተጠቅሞ የችግሩን ውስብስብነት ቀድሞ በመረዳት በከፈተው የአንድ መስኮት ማዕከል ከከተማው ፊትህ መምሪያ ጋር ቀጥተኛ ግኑኝነት በመፍጠር ላበረከተው አስተዋጾኦ የዓመቱ የዋንጫ ሽልማትና የዕውቅና ምስክር ወረቀት ለመሸለም መብቃቱን ገልፀዋል።

በሌላ በኩል የማዕከሉ አስተባባሪ ስ/ር መታሰቢያ አሰፋ እና በሆስፒታሉ የክሊኒካል አገልግሎት ዳይሬክተር ዶ/ር አዳነ ቸርነት በፕሮግራሙ ላይ እንዳስታወቁት ፆታዊ ጥቃት ደርሶባቸው ከሲዳማ ክልልና አጎራባች ዞኖች ለሚሙጡ ሴቶችና ሕፃናት የህክምና፣ ስነ-ልቦና ምክር ማረፍያና ማጋገሚያ ስፍራ እንዲሁም ነፃ የሕግ ድጋፍና የፍርድ ቤት ክርክርና ክትትል የሚያደርግ ሲሆን የተሰጠው እውቅና ይህንኑን ተግባር አጠናክሮ እንድቀጥል ብርታት የሚሠጥ መሆኑን አስረድተዋል።

በኮሌጁ ውስጥ እየተሠራ ያለው ለተጎዎች ማቆያና እንክብካቤ የሚውል የማዕከሉ ማስፋፊያ ስራ ጉብኝትም ተደርጓል።

በፕሮግራሙ ላይ የማዕከሉና የከተማው ፖሊስ አባላትና አመራሮች: ዓቃቤያን ሕጎችና የሆስፒታሉ በጎ ፈቃደኛ ሀኪሞች መሳተፋቸው ታውቋል።

የአፍሪካ ቀንድ የጨቅላ ሕፃናት ልማት ተቋም (HANDS) ለሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንስቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተለያዩ ህክምና ቁሳቁሶችን ለገሠ ነሔሰ 12/2018ዓም*********//***...
18/08/2026

የአፍሪካ ቀንድ የጨቅላ ሕፃናት ልማት ተቋም (HANDS) ለሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንስቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተለያዩ ህክምና ቁሳቁሶችን ለገሠ
ነሔሰ 12/2018ዓም
*********//*****
ተቀማጭነቱ በአሜሪካን ሀገር የሆነ የአፍሪካ ቀንድ የጨቅላ ሕፃናት ልማት ተቋም(Horn of Africa Neonatal Development Services , (HANDS) ለሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንስቭ ሰፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶችን ለጨቅላ ሕፃናት ህክምና ክፍል ለገሠ።

የተቋሙ መስራችና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ዶ/ር መስፍን ወ/ሰንበት በእርዳታው ርክክብ ላይ እንደገለጹት በሆስፒታሉ እጅግ በርካታ ጨቅላ ሕፃናት አገልግሎት የሚያገኙ ከመሆኑ የተነሣ የጨቅላ ሕፃናትን ሕይወት ለማዳን በህክምና ግብአትና በአቅም ግንባታ ስልጠና ለመደገፍ መወሰናቸውን ገልፀዋል።

ተቋማቸው ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንስቭ ሰፔሻላይዝድ ሆስፒታል በተጨማሪ ለቡሽሎ እናቶችና ሕፃናት ጤና ማዕከል እንድሁም ለአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ተመሳሳይ ድጋፎችን በዓመት ሁሌት ጊዜ እንደሚለግስ ለማወቅ ተችሏል።

ዶ/ር ዘርሁን ተስፋዬ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህክምና ትምህርትና ጤና አገልግሎት ኮርፖሬት ዳይሬክተር በዚሁ ወቅት እንደገለጹት በመንግስት ከሚደረገው ጥረት በተጨማሪ ኮሌጁ ከተለያዩ ሀገር በቀልና ዓለም ከቀፍ ለጋሽ ተቋማት ጋር መልካም ግንኙነቶችን በመፍጠር ተጨማሪ ድጋፍ የማመቻቸት የቆየ ልምድ ያካበተ መሆኑን ገልፀው በተለይም የጨቅላ ሕፃናትን ሕይወት ለመታደግ HANDS እየሠጠ ያለው ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑን አብራርተዋል።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ማኅበረሰብ HANDS እና ሁሉንም አጋሮች ከልብ ያመሰግናል !!

ተላላፊ በሽታዎች እንዳይከሰቱ  አስቀድሞ ለመከላከልና ለመቆጣጠር  የሚያስችል ውይይት ተካሄደነሔሰ 11/2018ዓም*******//*********የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሆሃዮ ስ...
17/08/2026

ተላላፊ በሽታዎች እንዳይከሰቱ አስቀድሞ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ውይይት ተካሄደ
ነሔሰ 11/2018ዓም
*******//*********
የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሆሃዮ ስቴት ዩኒቨርስቲ(Ohio State University Global one Health): ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ : እንዲሁም ከሲዳማና ደቡብ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶች ጋር በመተባበር ማርበርግን ጨምሮ ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች እንዳይከሰቱ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያግዝ ውይይት ዛሬ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አካሄዷል።

በሀዋሳ ዪኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍጹም ወ/ገብርኤል በመክፈቻ ንግግራቸው ባለፈው ዓመት ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ በሽታን የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር ለማዋል መቻሉ ሀገራችን ተላላፊ በሽታዎችን በመቆጣጠር ረገድ ለደረሰችበት የተሻለ ደረጃ ማሳያ መሆኑንና በቀጣይም በሽታዎችን በመከላከልና መቆጣጠር ላይ ለተመሠረተ የጤና ስርዓት ግንባታ መሠረት መጣሉን ገልፀዋል።

አቶ አብርሃም ሙሉነህ በኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተላላፊ በሽታዎች ቁጥጥር አስተባባሪ በበኩላቸው የውይይቱ ዋነኛ ዓላማ ተላላፊ በሽታዎችን አስቀድሞ መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የባለድርሻ አካላትን ትብብር ከማጠናከር ባሻገር የላቦራቶሪ ባለሙያዎችን አቅም በማጎልበት ፈጣንና ውጤታማ ስራዎችን ለማስቀጠል መሆኑን ጠቁመዋል።

የሲዳማ ክልል ኅብሰተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ በበኩላቸው ያለፉት ጊዜያት ልምዶችን በመቀመር በቀጣይ ማንም ዜጋ በተላላፊ በሽታ እንዳይጎዳ ጥብቅ ክትትል ለማደረግ ከተለያዩ ባለድርሻዎች ጋር በመተባበር ሙሉ ዝግጅት የተደረገ መሆኑን አብራርተዋል።

ከትኩሳትና መድማት ጋር ተያያዥ ምልክቶች ያላቸው ማናቸውም ህሙማን ልዩ ትኩረትና ክትትል የሚደረግ ከመሆኑም በላይ ከተላላፊ በሽታ ምልክቶች ጋር ተያያዥነት ባለው ህመም ሕይወቱ ያለፈበት ማንም ዜጋ ቢኖር በዘርፉ ባለሙያዎች የአስከረን ምርመራ ጭምር ለማድረግ የሚያስችል ዝግጅት መኖሩን ከዶ/ር ዳመነ ገለፃ ለመረዳት ተችሏል።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አስተባባሪነት ለአንድ ቀን በተካሄደው የውይይት መድረክ 40 ያህል የሚሆኑ ከሲዳማና ደቡብ ክልሎች የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተወካዮች የላቦራቶሪ ከፍተኛ ባለሙያዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መሳተፋቸው ታውቋል።

16/08/2026
ሆስፒታሉ የአንጎልና ህብለሰረሰር ቀዶ ህክምና አገልግሎቱን  በአዲስና ዘመናዊ  መልክ ማሻሻሉን አስታወቀነሔሰ 9/2018ዓም********//******የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝ...
15/08/2026

ሆስፒታሉ የአንጎልና ህብለሰረሰር ቀዶ ህክምና አገልግሎቱን በአዲስና ዘመናዊ መልክ ማሻሻሉን አስታወቀ
ነሔሰ 9/2018ዓም
********//******
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከአሁን ቀደም ሲሠጥ የነበረውን የአንጎልና ህብለሰረሰር ቀዶ ህክምና አገልግሎቱን በአዲስና ዘመናዊ መልክ ማሻሻሉን አስታውቋል።

ዶ/ር ዳኛቸው ዮሐንስ በኮሌጁ የአንጎልና ህብለሰረሰር ስፔሻሊስት ሀኪም በአዲስ መልክ ተሻሽሎ የተዋቀረውን አገልግሎት አስመልክቶ ከኮሌጁ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጋር በተካሄደው ውይይት ላይ እንዳስታወቁት የማሻሻያ ስራው የተካሄደው ሪች አናዘር ፋውንዴሽን(Reach Another Foundation) ከተባለ ዓለም አቀፍ ግብረ ሠናይ ድርጅት በተገኘ የዘመናዊ መሣሪያዎችና ተጨማሪ ግብአቶች ድጋፍ ነው።

የሆስፒታሉ አጠቃላይ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስትና የማዕከላዊ ቀዶ ህክምና ክፍል ዳይሬክተር ዶ/ር ይድነቃቸው መኮንን በበኩላቸው ከተለያዩ ሀገሪቷ አከባቢዎች በጭንቅላት ዕጢና ህብለሰረሰር ከፍተኛ ህክምና ራፌር ተብለው የሚላኩ በርካታ ተገልገዮችን በማስተናገድ ላይ የሚገኝ ቢሆንም ባጋጠመው የግብአት እጥረት ለጥቂት ወራት በከፊል ተሰተጓጉሎ የነበረውን አገልግሎት በአሁኑ ወቅት ችግሩ ሙሉ በሙሉ በመቀረፉ ሁሉንም የሳምንት ቀናት ለ24 ሰዓታት ለመስራት ዝግጅት መደረጉን አስረድተዋል።

በውውይቱ ማጠቃለያ የኮሌጁ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍጹም ወ/ገብርኤል በሠጡት የስራ መመሪያ ከዩኒቨርሲቲው ተልዕኮ አንፃር ዘመኑን የዋጄና የጥራት ደረጃቸውን የጠበቀ ፈጣንና ጥራት ያለው አገልግሎት ለማኀበረሰቡ መስጠት የኮሌጁ ዋነኛ ትኩረት መሆኑን ገልዋል።

በመንግስት ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን በሆስፒታሉ የሚሰጠውን የአንጎልና ህብለሰረሰር ቀዶ ህክምና የተሻለ ለማድረግ ሪች አናዘር ፋውንዴሽን(Reach Another Foundation) ለሠጠው ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና ያቀረቡት ዶ/ር ፍጹም ታካሚዎች ጊዜያቸውን ሳያባክኑ ፈጣንና ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ በየደረጃው የተመደቡ ሠራተኞች ከምንጊዜውም በላይ ጠንክረው መስራት የሚጠበቅባቸው መሆኑን አስገንዝበዋል።

Hawassa University College of Medicine and Health Sciences Conducts Open Defense for Female Research Proposal Selection....
14/08/2026

Hawassa University College of Medicine and Health Sciences Conducts Open Defense for Female Research Proposal Selection.
August 14/2026
*******//*******
The Hawassa University College of Medicine and Health Sciences (HU-CMHS) successfully conducted an Open Defense for Female Research Proposal Selection under the 2026/2027 Academic Year research funding call.

During the event, 24 research proposals were presented by female researchers and research teams of the college before expert evaluation panels as part of a transparent and merit-based selection process.

The research proposals covered a broad range of priority health research areas, including oncology, sexual and reproductive health, maternal and neonatal health, child and adolescent development, mental health, food insecurity, autism, diabetes and HIV care, occupational health, and behavioral risk factors, reflecting the College’s commitment to generating evidence for Ethiopia’s pressing health challenges.

HU-CMHS sincerely thanks all researchers, evaluators, moderators, and Research Council members for their dedication to advancing high-quality, evidence-based research.

We congratulate all presenters and look forward to supporting impactful research that contributes to improving the health of communities in Sidama and across Ethiopia.
University - CMHs
In Research
Research
Excellence

Address

Awassa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hawassa University College Of Medicine And Health Sciences posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share