Department of Journalism & Communication, Hawassa University

Department of Journalism & Communication, Hawassa University Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Department of Journalism & Communication, Hawassa University, College & University, Awassa.

አሁን ✨በዛሬው የJCSA የበይነ መረብ እልፍኝ ከጋዜጠኛ ቱኦክ ሩዋች ጋር የምናደርገው የልምድ ማጋራት መርሃ ግብር ተጀምሯል።በውይይቱ ላይ ቱኦክ ሩዋች በሚዲያ ዘርፍ ባካበተው የ8 ዓመት የሥ...
23/08/2026

አሁን ✨

በዛሬው የJCSA የበይነ መረብ እልፍኝ ከጋዜጠኛ ቱኦክ ሩዋች ጋር የምናደርገው የልምድ ማጋራት መርሃ ግብር ተጀምሯል።

በውይይቱ ላይ ቱኦክ ሩዋች በሚዲያ ዘርፍ ባካበተው የ8 ዓመት የሥራ ልምድ፣ በዜና ሪፖርተርነትና አቅራቢነት ባለው ሙያዊ ተሞክሮ እንዲሁም በEBC ቆይታው ከሰበሰበው የሥራ ልምድ ጋር በተያያዘ ለተሳታፊዎች ልምዱን ያካፍላል።

በተጨማሪም በብሮድካስት ጋዜጠኝነት ያገኘውን የትምህርት ዕውቀት ከግሎባል ስተዲስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርቱ ጋር በማጣመር በሚዲያ ሙያው ያዳበራቸውን ክህሎቶችና ተሞክሮዎች ያካፍላል።

ከታች ባለው የGoogle Meet ሊንክ በመጠቀም በቀጥታ ይሳተፉ።

👇👇👇👇

https://meet.google.com/inh-gdoe-mnn

የJCSA ቴሌግራም ግሩፕ

https://t.me/HU_JCSA_Group

እውነቱን በኃላፊነትና በሚዛናዊነት እንነግራችኋለን!!

  በዚህ ሳምንት ✨ የዚህ ሳምንት የበይነ መረብ እልፍኝ እንግዳችን ቱኦክ ሩዋች ሲሆን፣ በሚዲያ ዘርፍ የ8 ዓመት የሥራ ልምድ ያካበተ ጋዜጠኛ ነው። በአሁኑ ወቅትም በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ...
22/08/2026

በዚህ ሳምንት

✨ የዚህ ሳምንት የበይነ መረብ እልፍኝ እንግዳችን ቱኦክ ሩዋች ሲሆን፣ በሚዲያ ዘርፍ የ8 ዓመት የሥራ ልምድ ያካበተ ጋዜጠኛ ነው። በአሁኑ ወቅትም በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC) በዜና ሪፖርተርነትና አቅራቢነት እያገለገለ ይገኛል።

✨ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በብሮድካስት ጋዜጠኝነት ያገኘ ሲሆን፣ ሁለተኛ ዲግሪውን ደግሞ ከኒው ጄኔሬሽን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በግሎባል ስተዲስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት አጠናቋል።

✨ በዚህ ሳምንት የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብራችን ከ8 ዓመታት የሚዲያ ልምዱ ያካበተውን ተሞክሮ፣ በዜና ሪፖርተርነትና አቅራቢነት የሰበሰበውን ሙያዊ ልምድ እንዲሁም በጋዜጠኝነት ሙያ ለሚሰማሩ ወጣቶች የሚጠቅሙ ምክሮችን ከእኛ ጋር ያካፍላል።

እሁድ ማለትም 17/12/18

ከምሽቱ 2:00
በ አይቀርም!

🎤 አቅራቢ፦ ሀናን ሙዘሚል
(የሶስተኛ ዓመት የጋዜጠኝነትና ሥነ ተግባቦት ተማሪ)

የGoogle Meet ሊንኩ የመወያያ ሰዓቱ ሲቃረብ በJCSA የቴሌግራም ግሩፕ ይጋራል።

👇👇👇

እውነቱን በኃላፊነትና በሚዛናዊነት እንነግራችኋለን!!

✨ እናመሰግናለን!በዛሬው የJCSA የበይነ መረብ እልፍኝ የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብራችን ላይ በመገኘት፣ ረጅሙን የሙያ ጉዞዎን፣ ያካበቱትን ዕውቀትና ልምድ ከእኛ ጋር ስላካፈሉን ለእንግዳችን ...
16/08/2026

✨ እናመሰግናለን!

በዛሬው የJCSA የበይነ መረብ እልፍኝ የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብራችን ላይ በመገኘት፣ ረጅሙን የሙያ ጉዞዎን፣ ያካበቱትን ዕውቀትና ልምድ ከእኛ ጋር ስላካፈሉን ለእንግዳችን ኤልያስ ተክለወልድ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

✨ ከጋዜጣ ሥራ እስከ ሬዲዮና ኮሚኒኬሽን ያለውን የሙያ ልምድ በማካፈል፣ በሚዲያ ዘርፍ ለሚሰማሩ ወጣት ጋዜጠኞች ያካፈሉት ልምድና ምክር ለመርሃ ግብራችን ትልቅ ጥቅም ነበረው። ለዚህም እናመሰግናለን።

በዛሬው መርሃ ግብር ላይ በመገኘት፣ ውይይቱን በንቃት በመከታተል እና ጥያቄዎቻችሁን በማቅረብ ላደረጋችሁት ተሳትፎ እናመሰግናለን።

እውነቱን በኃላፊነትና በሚዛናዊነት እንነግራችኋለን!!

 #አሁን ✨በዛሬው የJCSA የበይነ መረብ እልፍኝ ከሚዲያ ባለሙያው ኤልያስ ተክለወልድ ገብረጊዮርጊስ ጋር የምናደርገው የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር ተጀምሯል።በውይይቱ ላይ ኤልያስ ተክለወልድ ...
16/08/2026

#አሁን ✨

በዛሬው የJCSA የበይነ መረብ እልፍኝ ከሚዲያ ባለሙያው ኤልያስ ተክለወልድ ገብረጊዮርጊስ ጋር የምናደርገው የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር ተጀምሯል።

በውይይቱ ላይ ኤልያስ ተክለወልድ የሙያ ጉዞውን እንዴት እንደጀመረ፣ በሌቃ ጋዜጣ ላይ በአራት ወራት የሥራ ልምድ ያገኘበትን የመጀመሪያ የሙያ ልምዱን እና በሬዲዮ ፋና ለ11 ዓመታት ያካበተውን የሚዲያ ልምድ ያካፍላል።

በተጨማሪም በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ለ3 ዓመታት እና በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ለአንድ ዓመት በመስራት ያካበተውን የሥራ ልምድ ያካፍላል። በአሁኑ ወቅትም በአራዳ FM 95.1 እያገለገለ ይገኛል።

በውይይቱም ከጋዜጣ ሥራ እስከ ሬዲዮ እና ኮሚኒኬሽን ያለውን የሙያ ጉዞ፣ በረጅም የሥራ ዘመኑ ያካበተውን ተሞክሮ እና በሚዲያ ዘርፍ ለሚሰማሩ ወጣት ባለሙያዎች የሚጠቅሙ ምክሮችን ያካፍላል።

ከታች ባለው የGoogle Meet ሊንክ በመጠቀም በቀጥታ ይሳተፉ።

👇👇👇👇

https://meet.google.com/mzs-zkve-khz

የJCSA ቴሌግራም ግሩፕ፦

https://t.me/HU_JCSA_Group

እውነቱን በኃላፊነትና በሚዛናዊነት እንነግራችኋለን!!

  በዚህ ሳምንት✨ የዚህ ሳምንት የበይነ መረብ እልፍኝ እንግዳችን ኤልያስ ተክለወልድ ገብረጊዮርጊስ ሲሆን፣ በሚዲያና ኮሚኒኬሽን ዘርፍ ረጅም የሙያ ልምድ ያካበተ ባለሙያ ነው። በትውልድ እና ...
14/08/2026

በዚህ ሳምንት

✨ የዚህ ሳምንት የበይነ መረብ እልፍኝ እንግዳችን ኤልያስ ተክለወልድ ገብረጊዮርጊስ ሲሆን፣ በሚዲያና ኮሚኒኬሽን ዘርፍ ረጅም የሙያ ልምድ ያካበተ ባለሙያ ነው። በትውልድ እና እድገቱ ከአዲስ አለም ከተማ የሆነው ኤልያስ፣ ትምህርቱንም በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በጋዜጠኝነት ተከታትሏል። በዩኒቨርሲቲውም በተለያዩ የተማሪና ማህበራዊ ተሳትፎዎች በመሳተፍ የማስተባበር ክህሎቱን አዳብሯል።

✨ የኤልያስ የሙያ ጉዞ ግን ከሚዲያ ተቋማት በፊት በሌቃ ጋዜጣ ላይ በአራት ወራት የስራ ልምድ በመጀመር የተገነባ ነው። ከዚያም በዚያው ወቅት በሬዲዮ ፋና የተከፈተውን የስራ ዕድል ተወዳድሮ በማለፍ የሚዲያ ሙያዊ ጉዞውን በስፋት ጀምሯል።

✨ ኤልያስ በሬዲዮ ፋና ለ11 ዓመታት፣ በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ለ3 ዓመታት እና በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ለአንድ ዓመት ሰርቷል። በፋና ቆይታውም የማስተባበርና የመሪነት ክህሎቱን በተግባር አሳይቷል፤ ይህም በቀጣይ የሙያ ጉዞው ላይ ትልቅ መሠረት ሆኖለታል። በአሁኑ ወቅትም በአራዳ FM 95.1 እያገለገለ ይገኛል።

✨ በዚህ ሳምንት የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብራችን ኤልያስ ተክለወልድ ስለ ረጅሙ የሚዲያ ጉዞው፣ ከጋዜጣ ስራ እስከ ሬዲዮ እና ኮሚኒኬሽን ያለው የሙያ ልምዱን እንዲሁም በሙያው ያካበተውን ተሞክሮ የሚያካፍለን ይሆናል።

እሁድ ማለትም [ቀን] ከምሽቱ 2:00 በ አይቀርም!

🎤 አቅራቢ:- ነጃት መሀመድ (የአራተኛ ዓመት የጋዜጠኝነት እና ሥነ ተግባቦት ተማሪ)

መርሃ ግብሩ የሚካሄድበትን የGoogle Meet ሊንክ የመወያያ ሰዓቱ ሲቃረብ በJCSA የቴሌግራም ግሩፕ እናጋራችኋለን።

👇👇👇

እውነቱን በኃላፊነትና በሚዛናዊነት እንነግራችኋለን!!

 #እናመሰግናለን!በዛሬው የJCSA የበይነ መረብ እልፍኝ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት የሙያ ልምድህን፣ እውቀትህን እና ጠቃሚ ተሞክሮዎችህን ስላካፈልከን ለጋዜጠኛ አብርሃም ክብረአብ ከልብ እናመ...
09/08/2026

#እናመሰግናለን!

በዛሬው የJCSA የበይነ መረብ እልፍኝ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት የሙያ ልምድህን፣ እውቀትህን እና ጠቃሚ ተሞክሮዎችህን ስላካፈልከን ለጋዜጠኛ አብርሃም ክብረአብ ከልብ እናመሰግናለን።

በተለይም በመዝናኛ ጋዜጠኝነት የሙያ ጉዞህ፣ በዘርፉ ያሉ ተግዳሮቶች፣ የመዝናኛ ሚዲያ ሚና እና ለወጣት ጋዜጠኞች ያካፈልከው ጠቃሚ ምክር ለተሳታፊዎቻችን ትልቅ ትምህርት ነበር።

እንዲሁም በመርሃ ግብሩ ላይ ለተሳተፋችሁ ሁሉ በJCSA ስም ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን። ወደፊትም በሚዘጋጁ የልምድ ማጋራት መርሃ ግብሮቻችን ላይ እንደገና እንጠብቃችኋለን።

እውነቱን በኃላፊነትና በሚዛናዊነት እንነግራችኋለን!!

 #አሁን ✨በዛሬው የJCSA የበይነ መረብ እልፍኝ ከጋዜጠኛ አብርሃም ክብረአብ ጋር የምናደርገው የልምድ ማጋራት መርሃ ግብር ተጀምሯል።በውይይቱ ላይ ጋዜጠኛ አብርሃም ክብረአብ ከአዲስ አበባ ...
09/08/2026

#አሁን ✨

በዛሬው የJCSA የበይነ መረብ እልፍኝ ከጋዜጠኛ አብርሃም ክብረአብ ጋር የምናደርገው የልምድ ማጋራት መርሃ ግብር ተጀምሯል።

በውይይቱ ላይ ጋዜጠኛ አብርሃም ክብረአብ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጋዜጠኝነት ያገኘውን ትምህርት፣ በሬዲዮ ዘርፍ በሸገር FM “ጣዕም ልኬት” እና በዛሚ ሬዲዮ “ጉዞ በዜማ” ፕሮግራሞች በአቅራቢነት ያካበተውን ልምድ፣ እንዲሁም በEBS TV ለአምስት ዓመታት በስፖርት ፕሮግራሞች ላይ ያገኘውን የሥራ ልምድ ያካፍላል።

በተጨማሪም በ“EBS ቅዳሜ ከሰዓት” የመዝናኛ ፕሮግራም በአቅራቢነት ያካበተውን ተሞክሮ በማካፈል፣ በሬዲዮና በቴሌቪዥን ዘርፍ ለሚሰማሩ ወጣት ጋዜጠኞች ስለሚያስፈልጉ ሙያዊ ክህሎቶችና ልምዶች ይወያያል።

ከታች ባለው የGoogle Meet ሊንክ በመጠቀም በቀጥታ ይሳተፉ።

👇👇👇👇

https://meet.google.com/xhr-gyzg-yup

የJCSA ቴሌግራም ግሩፕ፦

https://t.me/HU_JCSA_Group

እውነቱን በኃላፊነትና በሚዛናዊነት እንነግራችኋለን!!

  በዚህ ሳምንት ✨ የዚህ ሳምንት የበይነ መረብ እልፍኝ እንግዳችን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጋዜጠኝነት የተመረቀ ሲሆን፣ በሬዲዮና በቴሌቪዥን ዘርፍ የተለያዩ የሙያ ልምድ ያካበተ ጋዜጠኛ ነ...
07/08/2026

በዚህ ሳምንት

✨ የዚህ ሳምንት የበይነ መረብ እልፍኝ እንግዳችን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጋዜጠኝነት የተመረቀ ሲሆን፣ በሬዲዮና በቴሌቪዥን ዘርፍ የተለያዩ የሙያ ልምድ ያካበተ ጋዜጠኛ ነው። በተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ውስጥ በስፖርትና በመዝናኛ ፕሮግራሞች ላይ በመስራት በብዙ ተመልካቾችና አድማጮች ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፏል።

✨እንግዳችን በሸገር FM “ጣዕም ልኬት”በተሰኘው ፕሮግራም እንዲሁም በዛሚ ሬዲዮ “ጉዞ በዜማ” በተሰኘው ፕሮግራም ላይ በአቅራቢነት ሠርቷል። በሁለቱም ተቋማት ባካበተው ልምድ በሬዲዮ ዘርፍ ሙያዊ መሠረት መገንባት ችሏል።

✨ ከዚያም በEBS TV የስፖርት ፕሮግራሞች ላይ ለአምስት ዓመታት ካገለገለ በኋላ፣ ባለፉት ዓመታት “EBS ቅዳሜ ከሰዓት” በተሰኘው የመዝናኛ ፕሮግራም ላይ በአቅራቢነት በማገልገል ይገኛል። በዚህ ሳምንት የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብራችን በሬዲዮ ና በቴሌቪዥን ያካበተውን ልምድና ተሞክሮ የሚያካፍለን አብርሃም ክብረአብ ነው።

እሁድ ማለትም 03/12/2018 ከምሽቱ 2:00 በ አይቀርም!

🎤 አቅራቢ:- ፌነን ተስፋዬ(የአራተኛ ዓመት የጋዜጠኝነት እና ሥነ ተግባቦት ተማሪ)

መርሃ ግብሩ የሚካሄድበትን የGoogle Meet ሊንክ የመወያያ ሰዓቱ ሲቃረብ በJCSA የቴሌግራም ግሩፕ እናጋራችኋለን።

👇👇👇👇👇👇

እውነቱን በኃላፊነትና በሚዛናዊነት እንነግራችኋለን!!

 #እናመሰግናለን!በዛሬው የJCSA የበይነ መረብ እልፍኝ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት የሙያ ልምድህን፣እውቀትህን እና ጠቃሚ ተሞክሮችህን ስላካፈልከን ለጋዜጠኛ ሰለሞን አባቡ ከልብ እናመሰግናለን...
02/08/2026

#እናመሰግናለን!

በዛሬው የJCSA የበይነ መረብ እልፍኝ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት የሙያ ልምድህን፣እውቀትህን እና ጠቃሚ ተሞክሮችህን ስላካፈልከን ለጋዜጠኛ ሰለሞን አባቡ ከልብ እናመሰግናለን።

ከተሳታፊዎቻችን ጋር ባደረከዉ ገንቢ ውይይት በተለይም በስፖርት ጋዜጠኝነት የሙያ ጉዞክ፣ በስፖርት ዘገባ አሰራር፣ በዘርፉ ያካበትከዉ ልምድ እና ለወጣት ጋዜጠኞች ያካፈልከዉ ጠቃሚ ምክር ለሁላችንም ትልቅ ትምህርት ነበር።

በተለይም ስፖርትን በሙያዊ እይታ፣ በኃላፊነትና በጥልቀት ለመዘገብ የሚያስፈልጉ ብቃቶችን እና ተሞክሮዎችን ከእኛ ጋር ስላጋራከን እናመሰግናለን።

እንዲሁም በመርሃ ግብሩ ላይ ለተሳተፋችሁ ሁሉ በJCSA ስም ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን። ወደፊትም በሚዘጋጁ ተመሳሳይ የልምድ ማጋራት መርሃ ግብሮቻችን ላይ ንቁ ተሳትፎ እንደምታደርጉ ተስፋ እናደርጋለን።

እውነቱን በኃላፊነትና በሚዛናዊነት እንነግራችኋለን!!

 #አሁን ✨በዛሬው የJCSA የበይነ መረብ እልፍኝ ከጋዜጠኛ ሰለሞን አባቡ ጋር የምናደርገው የልምድ ማጋራት መርሃ ግብር ተጀምሯል።በውይይቱ ላይ ጋዜጠኛ ሰለሞን አባቡ ለጋዜጠኝነት ሙያ ያለውን...
02/08/2026

#አሁን ✨

በዛሬው የJCSA የበይነ መረብ እልፍኝ ከጋዜጠኛ ሰለሞን አባቡ ጋር የምናደርገው የልምድ ማጋራት መርሃ ግብር ተጀምሯል።

በውይይቱ ላይ ጋዜጠኛ ሰለሞን አባቡ ለጋዜጠኝነት ሙያ ያለውን ፍቅር ከልጅነቱ ጀምሮ እንዴት እንደገነባ፣ በሚኒ ሚዲያ ያደረገውን ተሳትፎ፣ በስፖርት ውድድሮች ላይ ሽፋን በመስጠት ያካበተውን ተሞክሮ፣ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ያገኘውን ትምህርት፣ እንዲሁም ከ13 ዓመታት በላይ በዘለቀው የሙያ ሕይወቱ ያካበተውን ልምድና ወጣት ጋዜጠኞች ሙያቸውን ለማጠናከር ሊያዳብሯቸው ስለሚገቡ ክህሎቶች ከተሞክሮው በመነሳት ያካፍላል።

ከታች ባለው የGoogle Meet ሊንክ በመጠቀም በቀጥታ ይሳተፉ።

👇👇👇👇

https://meet.google.com/qdw-vysp-hmu

የJCSA ቴሌግራም ግሩፕ፦

https://t.me/HU_JCSA_Group

እውነቱን በኃላፊነትና በሚዛናዊነት እንነግራችኋለን!!

Address

Awassa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Department of Journalism & Communication, Hawassa University posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Department of Journalism & Communication, Hawassa University:

Shortcuts

Share