01/09/2025
በወታደሮች የተጠበቀው እስረኛ እግናቲዩስ ወደ ሮሜ ከደረሰ በኋላ ብዙ ጊዜ ሳይቆይ ወደ አደባባይ ቲያትር ተወሰደ ። በዚያም ራብ ያጠቃቸው አውሬወች ይጠብቁታል ። አሰፈፈሪውንም ትርእይት ለመመልከት ብዙ ሕዝብ ተሰበስቦአል ። የአረዊት ቤት ተከፍቶ ተለቀቁበት ። በአንድ አፍታም ሰውነቱን ቦጫጭቆው ጨረሱት ። በአደባባዩም መካከል የቀረው ጥቅት የተበታታነ አጥንት ብቻ ነው ። ክርስትያኖች ሰብስበው መታሰብያውን ለማክበር ሲሉ ወደ አንጾክያ የወሰዱት ከዚያም አኖሩት ። እግናቲዩስ በነፍቆት ይጠባብቅ የነበረውን ወደ እየሱስ ክርስቶስ ጋ ሄደ ። ልትቀበልው ያለህን መከራ አትፍራ ። እነሆ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው አሥር ቀንም መከራ ትቀበላላችሁ። እስከ ሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወት አክሊል እሰጣለሁ ። መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ ።