Werabe University

Werabe University Werabe University is a public higher education institution in Ethiopia under the Ministry of Education.
(1)

It offers undergraduate and postgraduate programs, conducts research, and provides community services. Vision
Werabe University /WRU/ aspires to be one of the best comprehensive universities in the country by the year 2022. Mission
Werabe \university is committed to providing quality education and training to produce well trained human power intellectually, morally, socially, and equip them with

critical and imaginative skills to face the real life challenges and play an active role in the development of the country to transform the innovation, discovery, and communication, and application of knowledge, through different activities in a wide range of academic and professional fields for the highest economic development of the citizens in Ethiopia. Core values
• Quality and Excellence
• Commitment
• Culture of integrity for team work
• Mutual respect of diversity
• Ethics
• Always open for learning
• International out look

በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የ2018 ትምህርት ዘመን መውጫ ፈተና ስኬታማ ሆኖ መሰጠቱን ቀጥሏልሰኔ 10፣ 2018 (ወራ/ ዩ /ህ /አ /አ /ግ) በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የ2018 የትምህርት ዘመን የከፍተኛ...
17/06/2026

በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የ2018 ትምህርት ዘመን መውጫ ፈተና ስኬታማ ሆኖ መሰጠቱን ቀጥሏል

ሰኔ 10፣ 2018 (ወራ/ ዩ /ህ /አ /አ /ግ) በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የ2018 የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ስኬታማ ሆኖ መሰጠቱን ቀጥሏል።

የመውጫ ፈተናው እስከ ሰኔ 12/2018 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

ዕውቀት ለልህቀት
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ

መረጃዎቻችንን በሚከተሉት የሚዲያ አማራጮቻችን ይከታተሉ!

• Website: https://www.wru.edu.et/

• Telegram:https://t.me/werabeuniversitywru

• YouTube: https://www.youtube.com/

በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የ2018 ትምህርት ዘመን መዉጫ ፈተና መሰጠት ጀመረ  ሰኔ 4፣ 2018 (ወራ/ ዩ /ህ /አ /አ /ግ) በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የ2018 የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት መው...
11/06/2026

በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የ2018 ትምህርት ዘመን መዉጫ ፈተና መሰጠት ጀመረ

ሰኔ 4፣ 2018 (ወራ/ ዩ /ህ /አ /አ /ግ) በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የ2018 የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ዛሬ መሰጠት ተጀምሯል።

ዛሬ የተጀመረው ይሀው የመውጫ ፈተና እስከ ሰኔ 12/2018 ዓ.ም ይቆያል።

ዕውቀት ለልህቀት
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ

መረጃዎቻችንን በሚከተሉት የሚዲያ አማራጮቻችን ይከታተሉ!

• Website: https://www.wru.edu.et/

• Telegram:https://t.me/werabeuniversitywru

• YouTube: https://www.youtube.com/

በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ለመውጫ ፈተና ተፈታኞች ኦሬንቴሽን ተሰጠሰኔ 4፣ 2018 (ወራ/ ዩ /ህ /አ /አ /ግ) በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ከሰኔ 4 እስከ  12/2018 ዓ.ም ለተመራቂ ተማሪዎች እና በድ...
11/06/2026

በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ለመውጫ ፈተና ተፈታኞች ኦሬንቴሽን ተሰጠ

ሰኔ 4፣ 2018 (ወራ/ ዩ /ህ /አ /አ /ግ) በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ከሰኔ 4 እስከ 12/2018 ዓ.ም ለተመራቂ ተማሪዎች እና በድጋሚ ለሚፈተኑ ተማሪዎች የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና አስመልክቶ ኦሬንቴሽን ተሰጥቷል።

የወራቤ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መ/ር ሙሀባ ኑረዲን ተፈታኞች ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲፈተኑ አሳስበዋል

ከትምህርት ሚኒስቴር የመጡት አቶ ነሲቡ ሀይሌ በበኩላቸው በፈተና ሂደት ወቅት ለተፈታኞች የተፈቀዱና የተከለከሉ ተግባራትን አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ ምረቃ፣ ድህረ ምረቃና ተከታታይ ትምህርት አስተባባሪ መ/ር ያረጋል አወቀ የፈተና ደንቦችን እና ደንብ ጥሰቶች የሚያስከትሏቸውን ውጤቶች በዝርዝር አብራርተዋል።

ዕውቀት ለልህቀት
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ

መረጃዎቻችንን በሚከተሉት የሚዲያ አማራጮቻችን ይከታተሉ!

• Website: https://www.wru.edu.et/

• Telegram:https://t.me/werabeuniversitywru

• YouTube: https://www.youtube.com/

10/06/2026

#ማስታወቂያ

ለመውጫ ፈተና (Exit Exam) ተፈታኞች በሙሉ ከዚህ በፊት በማስታወቂያ የመውጫ ፈተና መፈተኛ የጊዜ ሰሌዳ ማስታወቃችን ይታወሳል። ስለሆነም የተመደባችሁበትን መፈተኛ ክፍል እና የመፈተኛ ሰዓት እንዲሁም ሌሎች መረጃዎችን ለማወቅ ከዚህ በታች ያለውን የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ኦፊሻል ቴሌግራም ሊንክ 👇
https://t.me/werabeuniversitywru ይጫኑ፡



ዕውቀት ለልህቀት!
የወራቤ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት

የ2018 ሀገር አቀፍ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፈተና ሰላማዊ እና ስኬታማ ሆኖ ተጠናቀቀሰኔ 3፣ 2018 (ወራ/ ዩ /ህ /አ /አ /ግ) በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሲሰጥ የቆየው የ2018 ሀገ...
10/06/2026

የ2018 ሀገር አቀፍ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፈተና ሰላማዊ እና ስኬታማ ሆኖ ተጠናቀቀ

ሰኔ 3፣ 2018 (ወራ/ ዩ /ህ /አ /አ /ግ) በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሲሰጥ የቆየው የ2018 ሀገር አቀፍ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፈተና ሰላማዊ እና ስኬታማ ሆኖ ተጠናቋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኢንጂነር ተውፊቅ ጀማል በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የተሰጠው የ2018 ሀገር አቀፍ የአቅም ማሻሻያ ፈተና የፈተና አሰጣጥ መመሪያ በአግባቡ የተተገበረበት፣ ሰላማዊና ስኬታማ እንደነበር ገልጰዋል።

ፈተናው ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ድረስ ስኬታማ ሆኖ ሊጠናቀቅ የቻለው ፈተናውን ሲያስተባብሩና ሲያስፈጽሙ የነበሩ አካላት በሙሉ ተናበውና ተቀናጅተው በመስራታቸው መሆኑን ተናግረዋል።

በባለቤትነት፣ በቁርጠኝነት፣ በትጋትና በቅንጅት ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረጉት ለሁሉም አካላት ዶ/ር ኢንጀነር ተውፊቅ ጀማል ምስጋና አቅርበዋል።

የሪሜዲያል ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተናው ውጤታማ እንዲሆኑም ፕሬዚዳንቱ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ዕውቀት ለልህቀት
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ

መረጃዎቻችንን በሚከተሉት የሚዲያ አማራጮቻችን ይከታተሉ!

• Website: https://www.wru.edu.et/

• Telegram:https://t.me/werabeuniversitywru

• YouTube: https://www.youtube.com/

 #ማስታወቂያ
10/06/2026

#ማስታወቂያ

09/06/2026

#ማስታወቂያ
ለመውጫ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ

የ2018 ትምህርት ዘመን ከሠኔ 04 እስከ 12/2018 የሚሠጠው የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተዘጋጅቶ የተላከ ሲሆን የጊዜ ሰሌዳውን በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ኦፊሻል ቴሌግራም ሊንክ https://t.me/werabeuniversitywru በመግባት ተጭናችሁ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ዕውቀት ለልህቀት!
የወራቤ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት

ዶ/ር ኢንጂነር ተወፊቅ ጀማል እና አቶ ኡስማን ስሩር በወራቤ ዩኒቨርሲቲ  አረንጓዴ አሻራቸውን አሳረፉግንቦት 30፣ 2018 (ወራ/ ዩ /ህ /አ /አ /ግ)ዶ/ር ኢንጂነር ተወፊቅ ጀማል እና አ...
07/06/2026

ዶ/ር ኢንጂነር ተወፊቅ ጀማል እና አቶ ኡስማን ስሩር በወራቤ ዩኒቨርሲቲ አረንጓዴ አሻራቸውን አሳረፉ

ግንቦት 30፣ 2018 (ወራ/ ዩ /ህ /አ /አ /ግ)
ዶ/ር ኢንጂነር ተወፊቅ ጀማል እና አቶ ኡስማን ስሩር በወራቤ ዩኒቨርሲቲ አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።

የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኢንጂነር ተወፊቅ ጀማል እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርናና ገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ የግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ኡስማን ስሩር በወራቤ ዩኒቨርሲቲ አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።

በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብሩ የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት አባላት፣ የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙበራ ከማል እና የክልሉ ግብርና ቢሮ አመራሮች ተሳተፈዋል።

በመርሃ-ግብሩ በዩኒቨርሲቲው የጃክ ፍሩት ችግኝ ተተክሏል።

ዕውቀት ለልህቀት
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ

መረጃዎቻችንን በሚከተሉት የሚዲያ አማራጮቻችን ይከታተሉ!

• Website: https://www.wru.edu.et/

• Telegram:https://t.me/werabeuniversitywru

• YouTube: https://www.youtube.com/

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የማጠናከሪያ ትምህርት ሲሰጣቸው ለቆዩ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የስነ-ልቦና ዝግጁነት ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጠግንቦት 29፣ 2018 (ወራ/ ዩ /ህ /አ /አ /ግ) ወራቤ ዩኒቨ...
06/06/2026

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የማጠናከሪያ ትምህርት ሲሰጣቸው ለቆዩ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የስነ-ልቦና ዝግጁነት ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጠ

ግንቦት 29፣ 2018 (ወራ/ ዩ /ህ /አ /አ /ግ) ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የማጠናከሪያ ትምህርት ሲሰጣቸው ለቆዩ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የስነ-ልቦና ዝግጁነት ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጥቷል።

የዩኒቨርሲቲው ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መ/ር ጀማል ሬድዋን ተማሪዎች ያገኙትን ዕውቀት በመጠቀምና እራሳቸውን በስነ-ልቦና በማዘጋጀት ለውጤታማነት መትጋት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ተማሪዎቹ ውጤታማ ሆነው እራሳቸውንና ማህበረሰቡን ለመጥቀም መስራት እንዳለባቸውም አመላክተዋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የማጠናከሪያ ትምህርቱን ያስተባበሩት አቶ አድማሱ ዳንኤል ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስማር ለሰራው ስራ ምስጋና አቅርበዋል።

የስነልቦና ዝግጁነት ላይ ያተኮረው ስልጠና በትምህርትና ስነ-ባህሪ ት/ቤት ዲን መ/ር ሱልጣን ሁልጫፎ ተሰጥቷል።

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ መምህራንን በመመደብ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለተውጣጡ 195 የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የትምህርት፣ የማደሪያ፣ የምግብ፣የቤተ ሙከራ፣የቤተ መጽሀፍትና እና የህክምና ድጋፍ በማድረግ የማጠናከሪያ ትምህርት ሲሰጥ መቆየቱ ይታወቃል።

ዕውቀት ለልህቀት
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ

መረጃዎቻችንን በሚከተሉት የሚዲያ አማራጮቻችን ይከታተሉ!

• Website: https://www.wru.edu.et/

• Telegram:https://t.me/werabeuniversitywru

• YouTube: https://www.youtube.com/

Address

Werabie, Central Ethiopia
Awassa
46

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Werabe University posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share