01/03/2026
እስራኤል የክርስትያን ሀገር አይደለችም ኢራንም አረብ ሀገር አይደለችም !
👉ኢራን አረብ ሀገር አይደለችም ።ፐርሺያን ናት።በፐርሺያንና በአረብያን መሀል ሰፊ ልዩነት አለ
👉እስራኤል የክርስትያን ሀገር አይደለችም።ይልቁንም የጂውሾች ሀገር ናት።
👉በእስራኤል ክርስትናም እስልምናም ማይኖሪቲ ናቸው።ግን የሙስሊም ቁጥር ከክርስትያን ይበልጣል።ጅውሽ ባይኖር እስራኤል የሙስሊም ሀገር ትሆን ነበር።
👉ኢራን በአንፃሩ ከእስራኤል በላይ ብዙ ቁጥር ያላቸው ክርስቲያን ዜጎች አሏት።
👉እስራኤል ውስጥ ካሉ ክርስትያኖች ይልቅ አረቦች በቂጥር ይበዛሉ።
👉ክርስቲያንነትን መስበክ ከእስራኤል ይልቅ ኢራን ውስጥ መስበክ እጅግ ቀላል ነው።
👉ኢራኖች ፐርዥያን ወይም ፋርሲን ይናገራሉ እንጂ ጆሯቸው ቢቆረጥ አረቢክ ኣይችሉም።ትንሽ ናቸው ሚችሉት።
👉ኢራን የሙስሊም ሀገር ብትሆንም የሽኣ ሙስሊም ሀገር ናት።እነ ሳውዲ እና ብዙ የእስልምና ሀገራት ሚከተሉት የሱኒ እስልምና ተቃራኒ ናት።በሀገራቱም እንደጠላት ትፈረጃለች።እንደእስልምና ስጋትም ትታያለች
👉እስራኤል ካሉ የክርስትያን ቤ/ክ በላይ ፍልስጤም ውስጥ ብዙ ቤ/ክ ኣለ።እየሱስም የተወለደው ፍልስጤም ውስጥ ነው።
እና ምን መሰለህ እዚ social media ላይ ሆነህ ክርስትያን ስለሆን እስራኤልን ሙስሊም ስለሆንክ ኢራንን አትደግፍ።መደገፍ ካለብህ ተበዳይን ብቻ ደግፍ ።ሲጀመር ጦርነት ሚባል ነገር አትደግፍ።የሰው እልቂት እንጂ ምንም ሚያመጣው ነገር ስለሌለ።
Via፦NBC AFAR