Dessalegn Maru

Dessalegn Maru ድምፅ ለተጎዳዉ የአማራ ህዝብ
ፋኖ ያሸንፋል
ድል ለአማራ ህዝብ
ላንጨርስ አልጀመርንም
ድል ለአማራ ፋኖ

ሚያዝያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. 85ኛውን የአርበኞች ድል በዓል አስመልክቶ ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የተሰጠ መግለጫሚያዝያ 27 ቀን 1928 ዓ.ም ኢትዮጵያን የወረረው የጣሊያን...
05/05/2026

ሚያዝያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም.

85ኛውን የአርበኞች ድል በዓል አስመልክቶ ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የተሰጠ መግለጫ

ሚያዝያ 27 ቀን 1928 ዓ.ም ኢትዮጵያን የወረረው የጣሊያን ፋሽስታዊ አገዛዝ ከአምስት ዓመታት ተጋድሎ በኋላ በተመሳሳይ ቀን ተሸንፎ የወጣበት ዕለት በመሆኑ በሀገራችን የነፃነት ታሪክ ውስጥ ጉልህ ድርሻ ያለው ዕለት ነው።

ይህ እለት ፋሽዝም የተሸነፈበት ብቻ ሳይሆን በተመሳሳይ ቀን የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የተረጋገጠበት ታሪካዊ ቀንም ነው። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ለመላው ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለአርበኞች ቀን አደረሳችሁ ይላል።

የብልፅግና አገዛዝ የሀገሩን የፖሊሲ ሉዓላዊነት ከማከራዬት አልፎ አዬር ኃይሉን እና መሰል ተቋማትን ለውጭ ኃይሎች መፈንጫ በማድረግ በአርበኞች መስዋዕትነት የተገኘውን የሀገር ነፃነት ለርካሽ ስልጣን ሲል አሳልፎ በመስጠቱ ሀገራችን ያልተነገረ ቅኝ ግዛት ውስጥ እንድትገባ አድርጓታል።

የብልፅግና አረመኔ አገዛዝ በአምስቱ የአርበኝነት ዘመን ጣሊያን ኢትዮጵያዊያን ላይ ከፈፀመው ግብ በብዙ እጥፍ የራቁ የዘር ማጥፋት እና ሰብአዊነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን በአማራ ህዝብ ላይ እየፈፀመ ነው።

የአባቶቹን ታሪክ የወረሰው ሰራዊታችን የአማራን ህዝብ ህልዉና ለማስከበር እና የኢትዮጵያን አንድነት ለማስጠበቅ ከዘመኑ ጥቁር ፋሽስቶች ጋር በመተናነቅ ላይ ይገኛል።

ዘር አጥፊዉን አገዛዝ ታግለን በማሸነፍ የተነጠቅነዉን ሀገር ማስመለስ ግባችን እንደመሆኑ መጠን ንቅናቄው አሁን ላይ እያደረገ ያለው ትግል የቀድሞ አርበኞች ካደረጉት የነፃነት ተጋድሎ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው።

ፅናትን፣ አይበገሬነትን፣ ቁርጠኝነትን በሚጠይቀው ተጋድሎ ውስጥ በመስዋዕትነት ድል እያስመዘገበ ያለው ሰራዊታችን በአማራ ህዝብ ጠላቶች ላይ የጀመረውን የህልውና ትግል አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ እናረጋግጣለን።

የባርነት ቀንበር የተሰበረበት የአርበኞችን ቀን ስናከብር የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህልዉና አደጋ ለማስወገድ የሚከፈለዉን ማንኛዉንም መስዋዕትነት በመክፈል ትግሉን በድል ለማጠናቀቅ ቃል በመግባትም ጭምር ነው።

ሚያዝያ 03 ቀን 2018 ዓ.ም ለሰራዊቱ እና ለአመራሩ ከአፋብን የተሰጠ ማሳሰቢያበአስደናቂ ተጋድሏችን እየተሰባበረ ያለው የአገዛዙ ሰራዊት የወገን ኃይል ላይ የተደራጀ ማጥቃት እንዲፈፅም ተደ...
11/04/2026

ሚያዝያ 03 ቀን 2018 ዓ.ም
ለሰራዊቱ እና ለአመራሩ ከአፋብን የተሰጠ ማሳሰቢያ

በአስደናቂ ተጋድሏችን እየተሰባበረ ያለው የአገዛዙ ሰራዊት የወገን ኃይል ላይ የተደራጀ ማጥቃት እንዲፈፅም ተደጋጋሚ ስምሪት ቢሰጥም እግረኛው ስራዊት የተሰጠውን ስምሪት መፈፀም አልቻለም። አንድም የሚደርስበትን ምት በመፍራት ሁለትም የብልፅግና ጦርነት ዓላማ የሌለው መሆኑን በመረዳት።

በዚህ ምክንያት የወገን ሰራዊት ከበዓል ጋር የሚያደርጋቸውን እንቅስቃሴወች እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም አገዛዙ የጅምላ ጥቃት ለመፈፀም በሁሉም አካባቢወች የድሮን ስምሪቶች ሰጥቷል።

የዩናይትድ አረብ ኢምሬት አየር ኃይል አባላት የድሮን እና የጀት ጥቃት ለመፈፀም ከሌላው ጊዜ በተለዬ ሁኔታ የወትሮ ዝግጁነት ላይ ይገኛሉ።

በመሆኑም መላው ሰራዊታችን እና አመራሩ ይህንን የድሮን እና የአየር ኃይል ስምሪት ታሳቢ ያደረጉ እንቅስቃሴወች እንዲያደርጉ እና በተለይም በዓል ለማክበር የሚደረጉ ክንውኖች እጅጉን ጥንቃቄ የተሞላባቸው እንዲሆኑ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ በጥብቅ ያሳስባል!

እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።____የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት____የስቅለት በዓል የሚያስ...
10/04/2026

እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
____
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት
____
የስቅለት በዓል የሚያስተምረን ጽናትና ለዓላማ መሞት ያለውን ትልቅ ትርጉም ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እውነትና ስለ ሰው ልጆች ፍቅር ሲል እስከ ቀራንዮ እንደተጓዘ ሁሉ፣ የአማራን ህዝብ ክብርና ህልውና ለማስጠበቅ የተጀመረው ጉዞ የተፀነሰው በመንገዳችን በድንገት በተቀላቀሉ እና እየወረዱ ባሉት ይሁዳዎች ሳይሆን ውድ ህይወታቸውን ለመክፈል በማይሰስቱ በቁርጠኛ ልጆቹ ልብ ያለ እስከ ቀራንዮ ለመጓዝ የተቆረጠ የማያወላውል ጉዞ ነው።

ስቃይና መከራ ለክብር፣ ሞት ደግሞ ለትንሳኤ መንገድ እንደሆኑ ሁሉ፤ ዛሬ የምናልፍበት መከራና የምንከፍለው መሥዋዕትነትም ለታላቅ ድልና ለሕዝባችን ሰላም መሠረት መሆኑ አይቀሬ መሆኑን በመተማን ነው።
የአፋብን አመራሮችና መላው የሰራዊት አባላትም ይህ ጉዞ የሕዝባችንን ነጻነትና ደህንነት እስኪያረጋግጥ ድረስ በፅናት እና በሙሉ ልብነት ለማስቀጠል በዚህ ለመላው የሰው ልጆች ሲባል ዋጋ በተከፈለበት ቀን በድጋሜ ቃል እንገባለን።

በዓሉን ስናከብር ለአማራ ሕዝብ ህልውና ሲሉ ውድ ሕይወታቸውን የገበሩ ጀግኖቻችንን እና በየበረሃው ደማቸውን ያፈሰሱ ልጆቻችንን ቤተሰቦች በመጠየቅና በመደገፍ፣ በማንነታቸው ምክንያት ከቀያቸው ተፈናቅለው በችግርና በስደት የሚገኙ ወገኖቻችንን በማሰብ፣ "አማራነት ወንጀል" ተደርጎባቸውና በፖለቲካ አመለካከታቸው ምክንያት በየእስር ቤቱ የሚማቅቁ የሕዝብ ልጆችንና ቤተሰቦቻቸውን በማስታወስ፣ ድምፅ በመሆንና በመጠየቅ ከጎናቸው መሆናችንን በማሳየት እንዲሆን ጥሪ እናቀርባለን።

በድጋሜ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል አደረሳችሁ!
ሚያዝያ ፪ ቀን ፪፼፩፰ ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)

ለሴተሰብና ወዳጅ ዘመዶቹ:– እኛ ጋ ነው ተብላችኋል! የስድስተኛ ዕዝ 601ኛ ኮር 25ኛ ክፍለ ጦር 6ኛ ሻለቃ ምክትል አዛዥ መቶ አለቃ አንተነህ ገመቹ ከእኛ ጋር ነው። ዛሬ ሰዴ ላይ አፋብን...
08/04/2026

ለሴተሰብና ወዳጅ ዘመዶቹ:– እኛ ጋ ነው ተብላችኋል!
የስድስተኛ ዕዝ 601ኛ ኮር 25ኛ ክፍለ ጦር 6ኛ ሻለቃ ምክትል አዛዥ መቶ አለቃ አንተነህ ገመቹ ከእኛ ጋር ነው። ዛሬ ሰዴ ላይ አፋብን በከፈተዉ ውጊያ በመሮጥ ላይ እያለ ቀላል ጉዳት ስለደረሰበት የቴወድሮስ ዕዝ ዘመቻ ኃላፊ መቶ አለቃ አበበ ሰው መሆን ወደ ህክምና ልኮታል።
አስረስ ማረ ዳምጤ

06/04/2026
በአንድ በኩል እየማረክን በሌላ በኩል ኮማንዶ  እያስመረቅን እንገኛለን። ነባሩ የኢትዮጵያ መከላከያ የአገዛዙ የቀውስ ፕሮጀክት አስፈፃሚ በመሆኑ ምክንያት ፖለቲካዊ ዓላማውን ከማጣቱ በተጨማሪ ...
04/04/2026

በአንድ በኩል እየማረክን በሌላ በኩል ኮማንዶ እያስመረቅን እንገኛለን። ነባሩ የኢትዮጵያ መከላከያ የአገዛዙ የቀውስ ፕሮጀክት አስፈፃሚ በመሆኑ ምክንያት ፖለቲካዊ ዓላማውን ከማጣቱ በተጨማሪ የቴክኖሎጅ ጥገና የሆነ ፀረ ህዝብ ሰራዊት ሆኗል። በየማዕዘኑ የምናሰለጥነው ሰራዊት ይህንን ሰራዊት የሚያሸንፍ ብቻ ሳይሆን ለመላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ተስፋ የሆነ ኃይል ነው።

በዛሬው ዕለት የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ የ206ኛ ኮር፣ 24ኛ ክፍለ ጦር ለተከታታይ ሰባት ወራት ያሰለጠናቸውን ብቁ ኮማንዶወች አስመርቀናል።
@የህግ ጠበቃ አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ

በሆሣዕና የተፈታውን አህያ መልሶ ሊያሥረው የሞከረ ማን ነው?የታሠረውን አህያ የፈቱት አሁን የትኛውን አህያ እየፈቱ ነው?"ፈትታችሁ አምጡልኝ"የሚለው ቃል ሕያው ነውና ለፈቺዎችምለተፈቺዎችም እ...
04/04/2026

በሆሣዕና የተፈታውን አህያ መልሶ ሊያሥረው የሞከረ ማን ነው?
የታሠረውን አህያ የፈቱት አሁን የትኛውን አህያ እየፈቱ ነው?
"ፈትታችሁ አምጡልኝ"የሚለው ቃል ሕያው ነውና ለፈቺዎችም
ለተፈቺዎችም እስከ ዘለዓለሙ ድረስ ይሠራል። ማቴ.፳፩፥፪

ታላቅ ሰበር ዜና!!
02/04/2026

ታላቅ ሰበር ዜና!!

Address

Bahir Dar

Telephone

+251915926958

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dessalegn Maru posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share