07/07/2022
ዓረፋ ዙልሒጃ 9‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
✍የአረፋ እለት አላህ ዲናችንን ያሟላበትና ፀጋውንም የተሟላ ያደረገበት እለት ነው።
✅ያቺ እለት አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ
ﺍﻟﻴَﻮﻡَ ﺃَﻛﻤَﻠﺖُ ﻟَﻜُﻢ ﺩﻳﻨَﻜُﻢ ﻭَﺃَﺗﻤَﻤﺖُ ﻋَﻠَﻴﻜُﻢ ﻧِﻌﻤَﺘﻲ ﻭَﺭَﺿﻴﺖُ ﻟَﻜُﻢُ ﺍﻹِﺳﻼﻡَ ﺩﻳﻨًﺎ
«ዛሬ ሃይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ፣ ፀጋዬንም በናንተ ላይ የተሟላ አደረግኩኝ፣ ኢስላምንም በሃይማኖትነት ወደድኩላችሁ»። በማለት የገለፀበት እለት ናት።
የአላህ መልእክተኛም (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዎል:-
"ﺻﻴﺎﻡُ ﻳﻮﻡِ ﻋﺮﻓﺔَ ، ﺃَﺣﺘﺴﺐُ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪِ ﺃﻥ ﻳُﻜﻔِّﺮَ ﺍﻟﺴﻨﺔَ ﺍﻟﺘﻲ ﻗﺒﻠَﻪ، ﻭﺍﻟﺴﻨﺔَ ﺍﻟﺘﻲ ﺑﻌﺪﻩ"
«የዐረፋ እለት ፆም ከዚህ አመት ቀድሞ ያለውንና የቀጣዩን ኣመት እንደሚያስምርልን ከአላህ ኣስባለሁ»።
📒📙📕ሙስሊም ዘግበውታል
በተጨማሪም የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዎል:-
"ﺧﻴﺮُ ﺍﻟﺪﻋﺎﺀِ ﺩﻋﺎﺀُ ﻳﻮﻡِ ﻋﺮﻓَﺔَ ...."
"ከዱዓኦች በላጩ የዐረፋ እለት ዱዓእ ነው"።
ማሳሰቢያ:-
--------------
"የዐረፋ ቀን" ማለት ከዒድ በፊት ያለው ቀን ወይም ነገ ጁሙዓ ነው ሁላችንም የነገውን ቀን እንፁም ለማለት እወዳለሁ።
መልክቱ እናንተ ጋር እንዳይቀር አስተላልፉ።