የጋዜጠኝነት መርሆች/ Principles of Journalism

የጋዜጠኝነት መርሆች/ Principles of Journalism Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የጋዜጠኝነት መርሆች/ Principles of Journalism, College & University, Bahir Dar.

05/11/2025

ለአዳዲሶቹ ዋና አድናቂዎቼ ታላቅ ምስጋና! ሚሚ ቦሌ, Argaw Soressa Beketa

29/11/2024

"ሁሉም ያልፋል፤ አንተ ብቻ ነህ በኛ ሠፈር የማታልፍ ..." ጥሩ አባባል።

07/02/2023

ቀጥሎ ያለውን you tube ቻነል በመጠቀም የተለያዩ አጋዥ ሰነዶች ላቀርብላችሁ ተዘጋጅቻለሁ።
https://youtube.com/
"The Journalist's View / የጋዜጠኛው ዕይታ" የተሰኜ ቻናሌን subscribe በማድረግ በቀላሉ ታገኙኛላችሁ።

19/01/2022

ሰበር-ዜና ወይም Breaking News ምንድነው?
ስለሰበር ዜና ምንነት በብዙዎች ዘንድ የተዛነፈ አረዳድ ስላለ የሚከተለዉን ማብራሪያ አቀርባለሁ፡፡
ሰበር-ዜና በሬዲዮና ቴሌቪዥን ወይም በኦንላይን የቀጥታ ስርጭት የሚቀርብ የዜና ዓይነት ነው፡፡
በዜናው ክብደት ልክ ብቻ ለታዳሚ የሚቀርብ ሳይሆን ባልታቀደ የዜና ሽፋን መሃል የተከሰተ ድርጊትን ይመለከታል፡፡ በተጨማሪም በሂደት ላይ ያለ (ያልተጠናቀቀ) ክስተት ሲያጋጥም ዜናው ተሟልቶ እስኪሰናዳ ድረስ ተቀንጭቦ የሚቀርብ ጉዳይ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- በፋና ቴሌቪዥን ቀጥታ ዜና እየተላለፈ፤ በመሃል ስለ እሳተ-ጎመራ መከሰት ከሪፖርተሮቹ መረጃ ቢደርሰው ‹ሰበር ዜና› ብሎ በመሃል ሊያስገባው ይችላል፡፡ የተሟላ መረጃ እስከሚገኝ ዜናውን በአጭሩ ያስተላልፋል፡፡ ከጥቅም አንፃር በፍጥነቱ ከሌሎች የሚዲያ ተቋማት ይልቅ ተመራጭ እንዲሆን ያስችለዋል፡፡
ሌላ ምሳሌ ለመጥቀስ ያክል፤- በጥምቀት በዓል አከባበር ላይ የአንድ ታዋቂ ሰዉ ሕፃን ልጅ አድራሻ ቢጠፋና የሕፃኑን መጥፋት አስመልክቶ የቴሌቪዥን ጣቢያው መረጃውን ለሕዝብ አሰራጨ እንበል፡፡ በዚያው የዜና ሰዓት ወይም በሌላ የፕሮግራም ስርጭቱ መሃል ሕፃኑ እንደተገኘ ጣቢያው ቢደርስበት ጉዳዩን ‹ሰበር ዜና› ብሎ ያቀርባል፡፡ መረጃው በሌሎች የብዙኃን መገናኛ ተደጋግሞ ቢቀርብና ጉዳዩን ከማቅረብ ቢዘገይ ‹ሰበር ዜና› ሊሠራ አይችልም፡፡
በዕያዩ ሞላ
ጥር 11፣ 2014 ዓ.ም

01/01/2022

ቀደም ሲል ስለአጀንዳ ቀረፃ (Agenda setting) ምንነት ላስነብባችሁ እየተሰናዳሁ ነበር።
አያሌው ደጀን የተባለ ባለሙያ በጥሩ ሁኔታ ያጠናቀረውን እነሆ።
በጋዜጠኝነትና ኮሚኒኬሽን ሳይንስ አስተምህሮ ትልቅ የጥናት ትኩረት ከሚስቡ እና የሚዲያ አሰራር ላይ የጎላ ተፅዕኖ ካላቸው ፅንሰ-ሀሳቦች የአጀንዳ ቀረፃ ንድፈ-ሀሳብ (agenda setting theory) ፍልስፍና ዋነኛው ነው። ይሄ መሰረታዊ ሀሳብ የሚያጠነጥነው የማህበረሰብን አስተሳሰብ መያዝ ወይም ቅርፅ ማስያዝ ላይ ነው።
ይህ ፅንሰ ሀሳብ የማህበረሰብን እሳቤ የሚቀርፀው በሚዲያ ዘገባዎች ውስጥ አንድን ርዕሰ ጉዳይ በተለየ ትኩረት ደጋግሞ በመዘገብ የሚዲያው ቀዳሚና ጠቃሚ አጀንዳ እንደሆነ በማስቀመጥ ነው። ለሚዲያው ጠቃሚ የሆነ አጀንዳ በድግግሞሽ ወደ ማህበረሰቡ ወይም አንባቢ፣ ተመልካችና አድማጭ አእምሮ እንዲሰርፅ በማድረግ ጉዳዩ ለህዝቡም የበለጠ ጠቃሚ አጀንዳ እንደሆነ አድርጎ ማስረፅ ነው።ጨበዚህም አሰራር መሰረት በብዛት የሚዲያ ሽፋን ያገኘ ወይም ዜና የሆነ ጉዳይ በሚዲያው ተጠቃሚው ዘንድም የበለጠ ጠቃሚ አጀንዳ ተደርጎ የመወሰድ እድሉ ከፍተኛ ይሆናል።
ለዚህ ግብ መሳካት ሚዲያዎች የሚጠቀሙበት አንዱ መንገድ ድግግሞሽ ነው። ማለትም በጋዜጠኛው ወይም በኢዲቶሪያል ቡድኑ አጀንዳ እንዲሆን የተፈለገውን ርዕሰ-ጉዳይ በተደጋጋሚ ሁኔታ አውዱን ወይም የጭብጥ አቅጣጫውን (Angle) እየለወጡ መዘገብ ወይም ሽፋን መስጠት ነው። ይህም ድግግሞሹ አጀንዳውን ወደ ሚዲያ ተጠቃሚው አእምሮ የማስረጊያ ስልት በመሆኑ ሲሆን ድግግሞሹ ተጠቃሚው ሌላ አማራጭ አጀንዳ እንዳይኖረውና በሚዲያው የተቀመጠለትን አጀንዳ ብቻ እውነት አድርጎ እንዲረዳ ያደርገዋል።
ይህ አንድን አጀንዳ ወይም ርዕሰ-ጉዳይ መርጦ የመዘገብ ድግግሞሽ ከአንድ ሚዲያ አልፎ ቁጥራቸው በበዛ ሚዲያዎች በዘመቻ መልክ በተመሳሳይ ጊዜ እንዲሁም የዘገባ አተያይ (Angle) የሚቀርብ ከሆነ ደግሞ የበለጠ የህዝብን አስተሳሰብ የመያዝ አቅሙ ይጨምራል።
ይሄ ስልት በአሜሪካ መራሹ የኢራቅ ጦርነት ወቅት በጉልህ ታይቷል። በዋናናት በአሜሪካ መንግስት አጀንዳ ሰጪነት የአሜሪካ ሚዲያዎች “የኢራቁ መሪ ሳዳም ሁሴን ለዓለም ህዝብ ስጋት የሆነ ጅምላ ጨራሽና ረዥም ርቀት ተጓዥ ጦር መሳሪያ አከማችቷል” የሚል አጀንዳ በቅብብሎሽና በድግግሞሽ ይዘግቡ ነበር። ለዚህ ዜናቸው ዋቢ የሚያደርጉት ደግሞ የአሜሪካ ወታደራዊ ኃላፊዎችን፣ እንደ CIA እና FBI የመሳሰሉ የደህንነትና የስለላ ተቋማትን፣ ታላላቅ የወታደራዊ ጥናትና ምርምር ባለሙያዎችን ነበር። ይሄ በኢራቅ ላይ በዘመቻ መልክ የተነዛ አጀንዳ ለወትሮው 'አገራችን ጣልቃ አትገባም፤ ልጆቻችንን ለጦርነት አንሰጥም' በሚል አቋም የፀኑትን አሜራካዊያን አስተሳሰብ ቀስ በቀስ በመሸርሸር አገሪቱ ወደ ኢራቅ ጦር በማዝመት ዓለምን ከጥፋት እንድትታደግ መደገፍ ጀመሩ።
ይሄ የአመለካከት ለውጥ የመጣው ከላይ በጠቀስነው የሚዲያዎቹ ተደጋጋሚ ዘገባ ምክንያት ነበር። ጦርነቱ ግን የተባለ መሳሪያ በኢራቅ መኖሩን ማረጋገጥ አላስቻለም። መጀመሪያም አውዳሚው ጦር መሳሪያ በኢራቅ ምድር ሳይሆን በአሜሪካ ባለስልጣናት የሴራ ዲስኩር እና በሚዲያዎቻቸው ዜናዎች ውስጥ ብቻ ነበር ህያውነት የነሳው።
ይህ ምሳሌ አገራትና መሪዎች በአጀንዳ ቀረፃ የማህበረሰብን እሳቤ እንዴት ለፈለጉት ዓላማ እንደሚያሰልፉት ሚዲያዎችን እንደ ጥሩ መሳሪያ እንደሚጠቀሙ ማሳያ ነው። በፅንሰ-ሀሳብ ቀረፃ (Agenda setting) ፍልስፍና መሰረት መሬት ላይ ያለ እውነት ቅርፁ ወይም ጭብጡ፣ ወይም አጠቃላይ እውነቱ ተለውጦ ለህዝብ የመቅረብ እድል አለው።
እውነቱ ተዛብቶ ሲቀርብ በነገሩ እውነትነት (Actual reality) እና በህዝቡ የእውነት አረዳድ (Public perception of 'reallity') መካከል ትልቅ ልዩነት ይፈጠራል። ልክ አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው መሰረታዊ እውነት እና የዓለምአቀፉ ማህበረሰብ እየተረዳው ያለው እውነት ፈፅሞ የተለያየ እየሆነ እንደመጣው ሁሉ ማለት ነው። ይህ ልዩነት የሚፈጠረው ደግሞ በሚዲያው አጀንዳ (Media reality/the media's agenda) ምክንያት ነው። መሬት ላይ ያለው ድመት የሚዲያው ስክሪን ላይ አንበሳ እንዲመስል ከተሰራ የህዝቡ መረዳት የሚዲያውን የመምሰል ወይም ከሁለቱም እውነታዎች ውጪ ብዥታ ውስጥ የመግባት እጣፈንታ አለው።
በአሁኑ ወቅት ከአሜሪካ እስከ አውሮፓ ህብረት ያሉ ባለስልጣናት፣ ተንታኞች፣ የሰብአዊ መብት ተቋማት፣ ለጋሽ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚያወጧቸው መግለጫዎችና ሪፖርቶች በሚዲያዎቻቸው እየተተነተኑ፣ ቅርፅና አውድ እየተሰራላተው ለዓለም ማህበረሰብ ፍጆታ በተዛባ መልኩ እየቀረቡ እንደሆነ እያየነው ነው።
የሚቀርቡበት የጭብጥ ቅንብብ (frame) ደግሞ የኢትዮጵያን እውነት የሚሸፍን፣ የህዝቦቿን ብሔራዊ ጥቅም የሚጎዳ በአንፃሩ ደግሞ የህወሓትን ፍላጎት እና ውንጀላ የሚያጎላ፣ ጥፋቶቹን የሚሸፍን፣ የሌለውን እንዳለው፣ ያላጣውን እንዳጣ፣ ያልተፈፀመበትን እኩይ በደል እንደ ተፈፀመበት አድርጎ የሚያሳይ ነው።
ይህ አይነቱ ህወሓትን ፃዲቅ እና ተጠቂ አድርጎ የመሳል ትርክት ከመንግስትታት እስከ ሚዲያ የተቀረፀ አጀንዳ ሆኖ ቀርቧል። ድግግሞሹ ደግሞ የዓለምአቀፉን ማህበረሰብ አረዳድ ያዛባ እየሆነ መጥቷል። እውነታው ሌላ ቢሆንም ሆን ተብሎ ተቀርፆ የሚቀባበሉት አጀንዳ ለጊዜው ከፍተኛ ጥፋት እያስከተለ ነው።
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሚዲያ አጀንዳ ቀረፃ ላይ አተኩረው የሚሰሩ ጥናቶች ሁለት አይነት የግኝት አዝማሚያዎችን እያሳዩ መሆኑን Lumen Learning የተባሉ የሚዲያ ከፍተኛ ተመራማሪ ያስረዳሉ። እንደ ሚዲያ ምሁሩ ጥናት ከሆነ በዘርፉ የሚደረጉ ጥናቶች አንደኛ ሚዲያዎች እውነትን ከማንፀባረቅ ይልቅ ወደ ማጣራት እና የእውነቱን ቅርፅ ቀይሮ ወይም ቅርፅ አስይዞ ወደ ማቅረብ አዘንብለዋል።
በሁለተኛው አተያይ ደግሞ ሚዲያዎች በጥቂት ጉዳዮች ላይ የሚያደርጉት የተለየ ትኩረት ህዝቡ የተመረጡት ጉዳዮች ከሌሎች ጉዳዮች የበለጠ ጠቃሚዎች መስለው እንዲታዩት አድርጓል።
ይህ ደግሞ የተመረጡት ጉዳዮች እውነትን የማያሳዩ የሆኑ እለት የማህበረሰብ እሳቤ ይዛባና የበለጠ የአመለካከት ዝቅጠት ወይም የእውነት መታፈን ይከሰታል። እንደ ማህበረሰብ ያለው አረዳድ የተዛባ መሆኑ የበለጠ ነገሮችን የምንረዳበት ሁኔታ አውዳሚ እንዲሆን ያደርገዋል።
ይህም በቀጥታ ሲታይ.....
“Two basic assumptions underlie most research on agenda-setting: One, that the press and the media do not reflect reality, they filter and shape it; and two, that media concentration on a few issues and subjects leads the public to perceive those issues as more important than other issues.”
እንደማለት ነው።
ከዚህ ባለፈ የመረጃዎቹ ድግግሞሽ በእራሱ ሌሎች አማራጭ ሀሳቦች ወደ ሚዲያ አውዱ መጥተው የመሰራጨት እድል በማጣታቸው ለህዝብ ተደራሽ እንዳይሆኑ እንቅፋት ይፈጥራል። የአማራጭ ሀሳቦች መታፈን ወይም ለህዝብ ተደራሽ አለመደረግ ደግሞ እውነቱን ከብዙ አማራጭ አውድ አንፃር አይተን እንዳንረዳ እድል በማሳጣት አስተሳሰባችን ወይም ለክስተቶች ያለን ግንዛቤ ሚዲያው ደጋግሞ ባቀረበልን መረጃ ላይ ብቻ እንዲመሰረት ያደርገዋል። የመረጃ ተደራሽነትም አንዱና ትልቁ ተፅዕኖ ነው...
Agenda-setting occurs through a cognitive process known as “accessibility.”
ተደራሽነት ማለት ደግሞ ሚዲያዎች ደጋግመው በዜናዎቻቸው ያቀረቡት ርዕሰ ጉዳይ ወይም ጭብጥ የበለጠ በህዝቡ ትውስታ ውስጥ የመቀመጥ እና የመገኘት እድል አለው። ይህ መረጃ በአእምሮ ትውስታችን እንዲመላለስ በሚዲያዎች በድግግሞሽ መሰራጨቱ በሂደት ወደ እውቀትነት ያድግና ስለ ክስተቱ የሚኖረን ግንዛቤ እሱ ብቻ ይሆናል።
ይህን የበለጠ ግልፅ ለማድረግ እስኪ ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ በበየነ መረብ መረጃ ፈልጉ። ጉግል እንደ ምንጭ ከሚያመጣላችሁ የመገናኛ ብዙሃን ዘገባዎችና ደረ-ገፅ መረጃዎች ውስጥ ስንቶቹ ናቸው ስለ ትግራዩ ቀውስ የሚያወሩት? አሁን ላይ ጦርነቱ በአማራ እና አፋር ክልሎች ውስጥ እየተካሄ፣ በትግራይ ምንም ጦርነት በሌለበት ሁኔታ እንኳን ሳይቀር አሁንም የዓለምአቀፉ የመረጃ አውድ የተሞላው “የትግራይ ጦርነት” በሚሉ አርዕስቶች ነው። ስንቶቹስ ናቸው ህወሓት የሰራቸውን ጥፋቶች በግልፅ የሚያሳዩት? ካልን መልሳችን ወደ ምንምነት የቀረበ ነው። ህወሓት ጥፋት እንደሰራ እንኳን ለመናገር ሌላውን ኃይል አብረው ካልወነጀሉ አይሆንላቸውም። ይህ ማለት ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ የኢትዮጵያን አሁናዊ ሁኔታ በዚህ መልኩ እንዲገነዘብ ሆንተብሎ ይህን መሰል የመረጃ ፍሰት ተሰርቶ የተዛባ ሀሳብ በቀላሁና በብዛት ተደራሽ እንዲሆን መደረጉን እንረዳለን።
ምክንያቱም ደግሞ.....
Mass media coverage in general and agenda-setting in particular have a powerful impact on what individuals think other people are thinking as well.
የሚል መገናኛ ብዙሃን ዘገባ በዋናነት እንዲሁም የአጀንዳ ቀረፃ ስልት በተለየ ሁኔታ ምን ያህል የህዝብን አመለካከት የመወሰን ተፅዕኖ እንዳለው አሁን እንደ ሀገር የተከፈተብን ሁሉን አቀፍ ጫና የሚያስረዳን ነው።
ይህን የተቀናጀ የአጀንዳ ቀረፃ እና የእውነት ብረዛ ገፈት የምናመልጠው በሁለት ነገር ነው። አንደኛ መሰል የሚዲያ ፅንሰ ሀሳብ ተፅዕኖዎችን በመገንዘብ እንደ ህዝብ ዘገባዎቻቸውን ከዘገባ ባሻገር የመረዳት፣ የመገንዘብ አቅም መፍጠርና አንድነትን በማጠናከር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የአገር ውስጥ ሚዲያዎቻችን ይህን የተገነዘበ የተግባር ስራ እንዲሰሩ፣ ዓለምአቀፉ ሚዲያ አውቆ የገፋውን ኢትዮጵያዊ እውነት ትኩረት እንዲያገኝ ግብረ መልስ ዘገባዎችን በመስራት የህዝብን እሳቤ ማጥራት፣ አማራጭ እውነቱን ለህዝብ የመረጃ ፍጆታ ማዋል፣ ቀድሞ መረጃን በማድረስ የህዝብን ብዥታ ማጥራት፣ ኢትዮጵያዊ እውነት የህዝብ አንድነት እና ህብረትን እንዲያፀና በማድረግ የአገሪቱና ህዝቦቿን ብሔራዊ ጥቅም እንዲሁም ህልውና አደጋላይ የሚጥለውን የዓለምአቀፉን የተዛባ የመረጃ ስርጭት ጉዳት መግታት ይገባል።
ጉዳዩ ቀድሞ የመረጃ ፍሰቱን የተቆጣጠረ ባለ ድል የሚሆንበት በአንፃሩ በመረጃ የተቀደመ ዋጋ የሚከፍልበት ዘመን ላይ ነንና በመረጃ እንቅደም። በመረጃ እንታጠቅ። በመረጃ እውነታችንን እናስጠብቅ። በግንባር የምናገኘውን ድል በመረጃ ፍሰቱም እንድገም!

20/01/2021

ጥር 12፣ 2013 ዓ.ም
ጆ ባይደን 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው በዋሽንግተን ዩኤስ ካፒቶል ተሰየሙ።
ከእርሳቸው ጋር ምክትል ፕሬዚዳንት ካሚላ ሀሪስ የተገኙ ሲሆን፣ የመጀመሪያዋ ሴት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።በበዓለ ሲመቱ ላይ የቀድሞዎቹ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ እና ባለቤታቸው ሚሼል ኦባማ፣ ጆርጅ ዎከር ቡሽ እና ባለቤታቸው ላውራ ቡሽ እንዲሁም ቢል እና ሂላሪ ክሊንተን ተገኝተዋል፡፡የትራምፕ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት ማይክ ፔንስም በበዓለ ሲመቱ ተገኝተዋል፡፡አዲሱ ተመራጭ ጆ ባይደን ቃለ መሀላ እስኪፈጽሙ ድረስ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ የሚደረገው ማንኛውም በረራ እንደሚቋረጥ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘግበዋል። እንዲህ ዓይነት ዜና ለመዘገብና
በኛ አገርም ቀጣይ መሪ ሲሾም የቀድሞ መሪዎች የሚገኙበት ሰላማዊ መድረክ እንዲፈጠር በተቆርቋሪነት እንሥራ።

20/01/2021

ጥር 12፣ 2013 ዓ.ም
ጆ ባይደን 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው በዋሽንግተን ዩኤስ ካፒቶል ተሰየሙ‼️

ከእርሳቸው ጋር ምክትል ፕሬዚዳንት ካሚላ ሀሪስ የተገኙ ሲሆን፣ የመጀመሪያዋ ሴት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።በበዓለ ሲመቱ ላይ የቀድሞዎቹ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ እና ባለቤታቸው ሚሼል ኦባማ፣ ጆርጅ ዎከር ቡሽ እና ባለቤታቸው ላውራ ቡሽ እንዲሁም ቢል እና ሂላሪ ክሊንተን ተገኝተዋል፡፡የትራምፕ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት ማይክ ፔንስም በበዓለ ሲመቱ ተገኝተዋል፡፡አዲሱ ተመራጭ ጆ ባይደን ቃለ መሀላ እስኪፈጽሙ ድረስ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ የሚደረገው ማንኛውም በረራ እንደሚቋረጥ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘግበዋል። እንዲህ ዓይነት ዜና ለመዘገብና
በኛ አገርም ቀጣይ መሪ ሲሾም የቀድሞ መሪዎች የሚገኙበት ሰላማዊ መድረክ እንዲፈጠር በተቆርቋሪነት እንሥራ።

28/09/2018

Getu Temesgen የሚባል ሰው የፃፈው የግጭት አዘጋገብን የተመለከተ ጽሑፍ እንድታነቡ እጋብዛለሁ::
በቅድሚያ ጌቱን አመሰግናለሁ::

"ግጭት ለጋዜጠኞች እጅግ ፈታኝና ሙያዊ ማንነታቸው በተግባር የሚፈተንበት ወቅት ነው፡፡ የመረጃ እጥረት፣ ምንጭ በተፈለገ ጊዜ አለመገኘት፣ የምንጭ ታማኝነት ጥያቄ ውሰጥ መግባት፣ የተዛቡ ወይም ለማረጋገጥ የሚያስቸግሩ መረጃዎች መናፈስ ፣

የአሉበልታ መንሰራፋትና የኤዲቶሪያል ጣልቃገብነት ችግሮች የጋዜጠኞች የሙያና የሥነምገባር ብቃት ውስንነቶች ላይ ተጨምረው ችግሮቹን ያወሳስባሉ፡፡

በመጨረሻም ሙያው ከቆመለት አላማ ውጭ ሰለባ ወይም ራሱ የግጭት መሳሪያ ይሆናል፡፡ አሁን በአገራችን እየተሰተዋለ ያለውም ይህ ነው፡፡

በሚዲያ የሚዘገብ መረጃ በተቀባዮች ዘንድ በተለያዬ ሁኔታ ተተረጉሞ ስራ ላይ ይዉላል፡፡ ለምሳሌ የግጭት ተሳታፊዎች ካለባቸው ጊዜያዊ ስጋት የተነሳ የሚያገኙትን ማንኛውም መረጃ በተረዱት መጠንና ከራሳቸው ፍላጎት አንጻር ብቻ በመተርጎም ለፈለጉት ፍጆታ ያዉሉታል፡፡

በዚህ ሂደት ውሰጥ በጥንቃቄ ያልተጠናቀረ መረጃ ያልተጠበቀ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡

በሩወንዳ እ.ኤ.አ በ1994 ለ100 ቀናት በዘለቀው ጀምላ የዘር ፍጅት አንድ ሚሊዮን ሩዋንዳዊያን ባለቁበት ወቀት ሚዲያ ትልቅ አስተዋፅኦ አንደነበረው እናስታውሳለን፡፡

እናም በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ሁሉም የአገራችን ጋዜጠኞች ብሄራዊ፣ ሃይማኖታዊ ፣ ፖለቲካዊ ወይም ማህበረሰባዊ ማንነታቸውን በመወገን ሳይሆን ሙያዊ ሥነምገባርና መርሆዎችን መሰረት አድረገው መስራት አለባቸው ብዬ አምናለሁ፡፡

ጋዜጤኛች በሚሰሩት ሥራ የተቐማቸውና የራሳቸው ሙያዊ ማንነት ይፈረጃል፡፡ በማይሰሩት ወይም መስራት በማይፈልጉት ወይም በሚተውት ክስተትም እንዲሁ፡፡

አድማጭ-ተመልካች ወይም አንባቢ ግን ሁሌም ወገን ሳይለይ ከሚዲያ ትክክለኛና ያልተዛባ ወቅታዊ መረጃ ይጠብቃል፡፡

ከዚህ በመነሳት የጋዜጠኝነት መርሆዎች አካል የሆኑ የተወሰኑ የግጭት ወቅት አዘጋገብ ሥነምግባሮችን ላካፍላችሁ ወደደኩ፡፡

1. የስራችን ውጤት ማንንም ወገን መጉዳት የለበትም

 ድጋፍ ወይም ተቃውሞ የሚያስተጋቡ የውግና ዜናዎች በአንድ ወይም በሌላ መልኩ ግጭትን ልያባብሱ ስለሚችሉ ማስወገድ

 ያልተረጋገጠ መረጃን ከመጠቀም መታቀብ፡፡ ሰዎች ስለነገሩን ብቻ መረጃውን አምኖ መቀበል ለስህተት ያጋልጠናል፡፡ በግጭት ወቅት ሰዎች የመሰላቸውን ይናገራሉ፡፡

ጋዜጠኛ መረጃውን በትክክል ሳያረጋግጥ መዘገብ የለበትም፡፡ የግለሰቦች አስተያዬት በራሱ ብቻውን ዜና አይሆንም፡፡

 የባለስልጣናት ወይም የግለሰቦች አስተያየትና የቃላት አጠቃቀም በህበረተሰቡ ውስጥ መከፋፈልና ጥላቻን አንዳይፈጥሩ የአርትዖት ሥራን በጥንቃቄ መፈጸም አለበት፡፡

በግጭት ወቅት ማንኛውም መረጃ ከሚያሳድረው አሉታዊና አወንታዊ ተጽዕኖ አንጻር ተመዝኖ መታየት አለበት፡፡

 ከማንኛውም ወገን ቢሆን በሰው ልጅ ላይ አደጋ እንዲከተል የሚያደርግ መረጃ በፍጹም መሰራጨት የለበትም፡፡

 መረጃን መደበቅ ወይም መከልከል ወይም እንዳይዘገብ ማድረግ ግጭትን ባልተጠበቀ ሁኔታ ሊያባብስ ስለሚችል ጋዜጠኞች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ለህብረተሰቡ የተረጋጋ ህይወት የሚጠቅሙና ግጭቶች በሰላም እንዲፈቱ የሚያበረታቱ ዘገባዎችን ቸል ማለት የለባቸውም፡፡

 የግጭት ሰለባዎችና ተሳታፊዎች ማንነት በሚገለጽበት ጊዜ ብሄራዊ፣ ማህበረሰባዊ፣ ሙያዊ ወይም ቤተሰባዊ ማንነታቸውን በዝርዝር ማቅረብ አደገኛ ብቻ ሳይሆን ግጭቱን የማባባስና ወደ ከፋ ደረጃ የማድረስ ኃይል አለው፡፡

በኣንድ በኩል የግጭት ሰለባዎች ወገን በማንነታቸው ተነጥለው የተጠቁ የሚያስመስል ሲሆን በሌላ በኩል አጥፊዎች ማንነታቸውን ተመክተው ጥቃት እንደፈጸሙ አድረጎ ይስላል፡፡

ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውና ተከባበረው አብረው የሚኖሩ ሰዎች መሃል ያልተገባ ስጋትና መጠራጠር ይፈጥራል፡፡

በመጨረሻም ማንነትን መሰረት ያደረገ ግጭት ሊቀሰቀስ ይችላል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ አልፎ አልፎ እየታየ ያለው ግጭት ማንነትን መሰረት አደረጎ የተፈጠረ ነው ብሎ መደምደም ያስቸግራል፡፡

ስለዚህ ሰዎች ሰው በመሆናቸው የደረሰባቸውን ወይም ያደረሱትን ከመዘገብ ዉጭ ድርጊታቸውን ከማንነታቸው ጋር ማያያዝ ተገቢ አይሆንም፡፡

ግጭት ብዙ ጊዜ ወንጀል የታከለበት ደረጊት ያስከትላል፡፡ ማንም ማንን ወክሎ ወንጀል ስለማይፈጽም ጥንቃቄ የሻል፡፡ ግጭት ጊዜያዊ ችግር ስለሆነ ያልፋል፡፡

ህዝብ ግን ለዘላለም አብሮ ኖራል፡፡ ለሚያልፍ ቀን የማያልፍ ጠባሳ መፍጠር የለብንም፡፡

2. ከመረጃ እና አሉባልታ ሰጣገባ ራስን ማራቅና ማንኛውንም መረጃ በሙያዊ ሥነምግባር ብቻ መገምገም

 ለጋዜጠኝነት ሙያ ሥነምግባር ተገዢ ሆኖ መስራት፡፡ በግጭት ወቅት በምንም አይነት መልኩ ለማንም አመለካከት አለመወገን የስፈልጋል፡፡

አሁን በስፋት አየተሰተዋለ ያለው የውግና ዘገባ ሕዝቡን ግራ የሚያጋባና ወደማይፈለግ ስጋትና አሉባልታ የሚወስድ ነው፡፡

ከዚህ የሚጠቀም ማንም አይኖርም፡፡ የጋዜጠኛ ሥራ እውነትን መሻትና መዘገብ እንጂ መወገን አይደለም፡፡

 የአንድ ወገን ስጋት ወይም ጉዳት ላይ ብቻ ከማተኮር የሁሉም ወገን ጉዳት ፣ ስጋትና ሃዘን በአግባቡ በጥንቃቄ ማስተናገድ ያስፈልጋል፡፡

የግጭት ተሳታፊዎች ተጠቂም ሆኑ አጥቂ ሁሉም የአንድ አገር ዜጎች ናቸውና፡፡

በግጭቱ ምክንያት የደረሰዉን አጠቃለይ ጉዳት ለመግለጽ ግምት ከመጠቀም የሚመለከተውን ባለሙያ መጠየቅና መብራራት

 የሚፈርጁ ወይም የሚያስጠቁ ቃላትና ቅጽል ከመጠቀም መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ወይም ገድያ፣ ንጹሃን ዜጎች ላይ የደረሰ አሰቃቂ ወንጀል፣ ጭካኔ፣ አረመኔያዊ ድርጊት፣ ጠላት …ወዘተ

ተጎጂውን ወገን ወደማይፈለግ ቁጭትና ብቀላ ሊያነሳሳ ስለሚችል ከእንደነዚህ ቃላት መታቀብና የተፈጸመውን እውነታ ብቻ ለይቶ መዘገብ ያስፈልጋል፡፡

 በግጭት አካባቢ የሚገኙ ሁሉም ወገኖች የአሉባለታ ሰለባ እንዳይሆኑ ትክክለኛ መረጃ በፍጥነትና በተደጋጋሚ እንዲያገኙ ማደረግ ያስፈልጋል፡፡

አሉባለታዎች የሚሰተጋቡት የመረጃ ክፍተት ሲኖር ነው፡፡

 ትክክለኛና ዝርዝር መረጃ ከአስተያየትና ኮመንተሪ ተለይቶ መቅረብ አለበት፡፡

ጋዜጠኞች የራሳቸውን ኮመንተሪ ወይም የሌሎችን አስተያየትና ትንታኔ በዘገባቸው ስያካትቱ በእዉኔታው ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ማስተዋል አለባቸው ፡፡

ግነት ፣ ትችት፣ ማውገዝ ፣ ድጋፍና ተቃውሞ የሚስከትል ከሆነ እወነታውን ስለሚያዛባ ቢቀር ይመረጣል፡፡

3 ከግጭት ወሬና አሉባልታ ራስን ማራቅ

 ብሄር፣ ብሄረሰብ ወይም ጎሳ ተኮር የድርጊትና የባህሪ ደምዳሜዎች (stereotypes) በግጭት ውሰጥ የገቡትን ወገኖች ክብር የማሳነስ ኃይል አለው፡፡

በተጨማሪም በዚህ ሁኔታ በሚፈረጁ ዜጎች ላይ የጥላቻና የመጠራጠር አመለካከት እንዲሰፋፋ ያረጋል፡፡ በመጨረሻም ችግሮችን ያባብሳል፡፡

በመሆኑም በግጭት ጊዜ በበጎም ይሁን በክፉ የእገሌ ብሄር ወይም ጎሳ አባላት እንዲህ ሆኑ ወይም እንዲህ አደረጉ ብሎ መዘገብ ሙዊ አይደለም፡፡ ይህ መቆም አለበት፡፡

ሁሉም ኢትዮጵያዊ ስለሆኑ በኢትዮጵያዊ ማንነታቸው መጥራትና መዘገብ ይቻላል፡፡

 ግጭትን የሚቀሰቅሱ ወይም የሚያባብሱ ማናቸውንም ፕሮፖጋንዳዎች በሚዲያ ኣለማስተናገድ፡፡

 ስሜት የሚነኩ ቀስቃሽ ቃላትና አባባሎችን እንዲሁም ምስሎች አለመጠቀም፡፡

ለምሳሌ አረመኔያዊ ድርጊት፣ ኃላቀር አባባል፣ የሰው ደም የጠማቸው፣ ፍጹም አውሬነት ፣ በጠራራ ፀሀይ ሰው መፍጅት… ወዘተ እውነታውን ከማጋነን ያለፈ ፋይዳ የለቸውም፡፡

 እርስበርስ የሚጋጩ መረጃዎች ወይም መግለጫዎች በሚያጋጥሙበት ጊዜ እስከ መጨረሻው በመሄድ ትክከለኛውን መረጃ ቆፍሮ ለህዝብ ማቅረብ የስፈልጋል፡፡

በግጭት ወቅት የሚጣረሱ መረጀዎችን እንደወረደ በማቀረብ ህዝቡን ግራ ማጋባት ተገቢ አይደለም፡፡

 ለአደጋ የተጋለጡ ወገኖችን እንደመረጃ ምንጭ በምንጠቀምበት ጊዜ ደህንነታቸው ችግር ላይ እንዳይወድቅ ጥንቃቄ ማደረግ ያስፈልጋል፡፡

 በግጭት ወቅት ሆሰፒታሎች፣ ፖሊስ እና የፀጥታ አካላት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ እና የህብረተሰብ መሪዎች ዋነኛ የመረጃ ምንጮቻችን ስለሆኑ በየጊዜው ግንኙነት በማደረግ ራስን በወቅታዊ መረጃ ማበልጸግ ያስፈልጋል፡፡

የሚያጠራጥረን መረጃ ካጋጠመም ማጣራት ከእነርሱ ይጀምራል፡፡

4 የህዝቡን ባህል ፣ ሃይማኖት ፣ እምነትና ወግ ማክበር

 በግጭት ውሰጥ ሁሉም ወገን የራሱን ነገር አጉልቶ ማዬትና የሌላውን ከራሱ ጥቅምና ማንነት አንፃር የመገምገም ባህሪ ስላለው የሚዲያ ዘገባ የሁሉንም ወገን የማንነት እሴቶች ማክበር አለበት፡፡

 ለግጭት አሰተወጽኦ የሚያደርጉ፣ መቻቻልና ገንቢ ውይይቶች አንዳይኖሩ እንቅፋት የሚሆኑ ልማዶችና ሁኔታዎች በስፋት ተፈትሸው መዘገብ አለባቸው

 ባህል ፣ ወግ፣ ሃይማኖት፣ አምነት እና ሙያ የመሳስሉ እሴቶች በምንም መልኩ በራሳቸው የግጭት መነሻ ሊሆኑ አይችሉም፡፡

5 ሁሉንም ወገን በእኩል ማስተናገድ

 ግጭት ከመከሰቱ በፊት የነበሩትን መልካምና ሰላማዊ የህዝብ ለህዘብ ግኑኝነቶች በሁሉም ወገን ዕይታ መተንተንና ጠቃሚ ገጽታውን ማቀረብ

 ግጭት ከተከሰተ በኃላ የተፈጠረው ችግር፣ የሻከረው ግንኙነት ፣ ያስከተለው ስጋት፣ ያለው ተስፋ፣ የህዝቡ የሰላም ፍላጎትና የመፍትሄ አቅጣጫ የመሳሰሉ ጉዳዮች ከሁሉም ወገን እይታና ፍላጎት አንጻር መስተናገድ አለበት

 በግጭት ያልተሳተፉና እንደገለልተኛ የሚወሰዱ ካሉ የእነርሱም ድምጽ መሰማት አለበት፡፡

 Provide diverse perspectives, which includes covering events from all possible angles, bringing in opposing views, giving voice to the discriminated and marginalized individuals and groups is an important instrument of overcoming conflict inciting moves

 በግጭት ዘገባ ጊዜ በሁሉም ወገን ዘንድ ተቀበይነት ለማግኝት መሞከር ያስፈልጋል፡፡

አንድ ወገን በዘገባችን ወዶን ሌላ ወገን የሚጠላን ከሆነ እኛም ሰለባ ሆነናል ማለት ነው፡፡"

01/09/2018

የቀጠለ ...
The lead is the first paragraph or two or any news report. In writing news, there must be a lead. As lead is the opening paragraph of the news story, it is also called “window” of a news story. It should therefore aim not only at presenting the gist of the story but also at gaining the attention of the reader.
It does not extend to the third paragraph. The lead usually gives or provides answers to the basic questions of 5 Ws and H. A good lead must:
- Be appropriate for the story.
- Make the reader want to read the rest of the story.
- Should be kept short, brief and telegraphic.
- Be based on the key features of the story.
The 5 Ws refer to WHO, WHAT, WHEN, WHERE, WHY and then the H – How. In most cases, not all the Ws are found in the lead. The who, what, when, where and why are common. The how is normally left for the body of the story. Here is an example of a lead.
Five students were shot dead, yesterday In a clash between two rival cult groups
At university of Lagos main campus, reports “The Campus Times”.
Analysis:
Who: Five students
What: Were short dead
When: Yesterday.
Where: University of Lagos main campus
Why: clash between cult groups.
The “HOW” is to be explained in the body of the story.
To test how adequate the lead is, the writer may ask and answer the following questions in which the acronym-News.
N- Newsworthiness - Does it say something news worthy?
E- Emphasis - Does it emphasis the most interesting fact?
W- The W's and H- Are the essential W's and H in the opening paragraphs
but not jammed into the first paragraph?
S- Source - Does it report the source of the information in the story?
በእያዩ ሞላ
26/12/2010 ዓ.ም
ላይክና ሸር በማድረግ እንማማር፡፡ አስተያየት ካለ እቀበላለሁ፡፡

01/09/2018

Elements of News
Headline Writing
Any single line or collection of display type that precedes a story and summarizes or introduces it can be called a headline. Such a headline has the following attributes.
Functions of the Headline
• The headline performs various functions, one of which is to index the news by stating plainly what the story contains so as to save the reader’s time in finding the aspect of the news that interest him most.
• The headline tells the news to the reader by way of conveying mandatorily the accurate information.
• Again, it conveys the relative significance of the news as expressed in terms of type display through the use of type size and weight.
• The headline beautifies the news and makes it attractive. In all ramifications, the primary function of any headline is essentially to make room for good and balance page make –up.
• Headlines to some degree are often employed to sell newspapers on the newsstand. This is true of catchy headlines.
Writing the News
Ordinarily, news writing begins from the time that a reporter sets out to gather facts. As the facts are gathered, the slants of news stories are also planned. Conventionally, news writing starts with the introduction. The introduction is technically called the Lead.
ይቀጥላል ...

25/08/2018

የዜና መሥፈርቶችና ባህርያት
የዜና መሥፈርቶች/ criteria or determinants of news
አንድ መረጃ ዜና ነዉ ሊባል የሚያስችላቸዉ ጉዳዮች የሚከተሉትን መሥፈርቶች እንደይዘታቸዉ በሙሉ ወይም የተወሰኑትን ሲያሟሉ ነዉ፡፡
1. ጠቀሜታ፣ ክብደት (Significance, impact, weight)
በህብረተሰቡ ላይ ሥጋትን የሚያጭርም ሆነ ብሥራትን የሚነግር ሆኖ የሰዎችን ትኩረት መቆጣጠር እስከሚችል ጠቀሜታ ካለዉ ዜና ይሆናል፡፡ የሰዎችን ህይወት የሚነካ ከሆነ የዚያንኑ ያህል ጠቀሜታዉ ከፍ ይላል፡፡ ዜና ሲሠራ መረጀዉ የብዙኃኑን ህይወት የሚነካ፣ ዉጤቱ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያለዉ መሆን አለበት፡፡
2. ወቅታዊነት (Timeliness)
ዜናዉ ትኩስ መሆን አለበት፡፡ አንድ ጉዳይ እንደተከሰተ ወዲያዉኑ ተዘግቦ ለህዝብ ካልተላለፈ ዜና ሊሆን አይችልም፡፡
3. ቅርበት (Proximity)
ሰዎች ለሚቀርቧቸዉና ከህይወታቸዉ ጋር በቅርበት ለተቆራኙ ክስተቶች ቅድሚያ መስጠት ይገባል፡፡ ኢትዮጲያ ዉስጥ ያለ ሚዲያ ወይም መረጃ የሚያቀብል ሰዉ አሜሪካ ከተከሰተ ጉዳይ ይልቅ ኢትዮጵያ ለተከሰተ ጉዳይ ቅድሚያ ቢሰጥ ዜናዉ የህብረተሰቡን ህይወት ስለሚነካ ቅድሚያ ይሰጠዋል፡፡ ስለሱዳን ድንበር ስምምነት ከምንዘግብ ይልቅ ስለኢትዮ ኤርትራ እርቅ ብንፅፍ ይበልጥ ለአድማጭ፣ ተመልካች ወይም አንባቢ ቅርበት ስለሚኖረዉ ቅድሚያ እንሰጣለን፡፡
4. ታዋቂነት/ ስመጥርነት( Prominence)
የታዋቂ ሰዎች ጉዳይ ለምሳሌ አንድ ታዋቂ አትሌት በጎርፍ የተፈናቀሉ ሰዎችን በገንዘብ ቢረዳ ዜና ይሠራለታል፡፡ ፕሪዝዳንት ኢሳያስ አዲስ አበባ ቢመጣ ትልቅ ዜና ይሠራል፡፡ አንድ የግሮሰሪ ባለቤት የሆነ የምፅዋ ተወላጅ አዲስ አበባ ቢመጣ ግን ዜና አይሆንም፤ በጣም ብዙ ኤርትራዊያን ዜጎችም ስለሚመጡ፡፡
5. ሰብዓዊ ፍላጎት (Human Interest)
የሰዎችን ቀልብ የሚስቡ ሆነዉ በፍቅር፣ በአስተመሪነት፣ በአስቂኝነት፣ በአዝናኝ የህይወት ገጠመኞች፣ በተፈጥሮ፣ በዱር እንስሳት አኗኗርነ የሰዉ ልጆች ህይወት ዙሪያ የሚያነጣጥሩ ያልተለመዱ ክስተቶች ወይም ገጠመኞች ዜና ይሆናሉ፡፡ ለምሳሌ እጅ ሁለት እጅ የሌለዉ ጎልማሣ እግሮቹን ተጠቅሞ ጠረጴዛና ወንበር እየሠራ ቤተሰቦቹን ቢያስተዳድር ጉዳዩ ዜና መሆን ይችላል፡፡
የዜና ባህሪያት/ News Values
እነዚህ የሚያመለክቱት ዜናዉ ጥራት ኖሮት እንዲዘገብ የሚያመለክቱ ነቸዉ፡፡
ትክክለኛነት/ Accuracy

የዜና ተዓማኒነት በጭብጦች ትክክለኛነት ላይ የተመሠረተ ነዉ፡፡ በግምት፣ በጭምጭምታ፣ በወሬና በጥርጣሬ ዜና መሥራት አደጋ አለዉ፡፡ ስሞችን፣ ቀኖችን፣ አሃዞችን፣ ወዘተ በትክክል መመዝገብ የግድ ያስፈልጋል፡፡
ሚዛናዊነት/ Balance
አንድን ዜና ከአድልዎ ለማፅዳት ሚዛናዊነትን መጠበቅ አስፈላጊ ነዉ፡፡ ስለሁለት ፓርቲዎች ወይም ቡድኖች ስንፅፍ አንዱን አሳንሰን ሌላኛዉን አጉልተን መዘገብ የለብንም፡፡
ግልፅነትና ቀጥተኝነት
ዜና አሻሚ ትርጉም እንዳይኖረዉ በግልፅና በቀላል ቋንቋ መፃፍ አለብን፡፡ አጫጭር ዓረፍተ ነገር መጠቀም ግልፅነትን ያጎለብታል፡፡ የተንዛዛ ዓረፍተ ነገር ከተጠቀምን ሰዎች ዜናዉን በትኩረት አይከታተሉትም፤ ስልቹና ግራ የተገቡ ይሆናሉ፡፡
ተዓማኒነት (Crediblity/ Loyalty
ትክክለኛነት+ ሚዛናዊነት+ ግልፅነት = ተዓማኒነት
ተዓማኒነት የትክክለኛነት፣ የሚዛናዊነትና የግልፅነት ድምር ዉጤት ነዉ፡፡
ተጨባጭነት / Objectivity
ተጨባጭነት ሲባል አንድ ድርጊት በተከናወነበት መልኩ ዜናዉ ሲቀርብ ነዉ፡፡ ስለዚህም በዜና ዉስጥ የግል አስተያየትና አቋም ሳይጨመር መቅረብ አለበት፡፡
ከላይ የዜና ምፈርቶችንና ባህሪያትና አይተናል፡፡ በቀጣይ የዜና አፃፃፍ ስልቶችንና ቅርፆችን እናያለን፡፡
በእያዩ ሞላ
19/12/2010 ዓ.ም
ላይክና ሸር በማድረግ እንማማር፡፡ አስተያየት ካለ እቀበላለሁ፡፡

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የጋዜጠኝነት መርሆች/ Principles of Journalism posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to የጋዜጠኝነት መርሆች/ Principles of Journalism:

Share