Ethiopian Institute of Textile and Fashion Technology

Call Directions Website Contact the university

Ethiopian Institute of Textile and Fashion Technology In Ethiopia, EiTEX is a premier higher education institute under Bahir Dar University for more than

In Ethiopia, EiTEX is a premier higher education institute under Bahir Dar University for more than 50 years. It is a pioneer institute in offering programs in Textile, Leather, Apparel and Fashion technology. The institute continues to strive to strengthen research, community service and technology transfer activities in order to contribute to economic development of the country as per Growth and Transformation Plan (GTP). The EiTEX is one of the limbs of the Bahir Dar University whose objectives perfectly fit the strategy of agriculture-led and export-oriented industrialization and the effort to combat the problem of textile & garment manufacturing and trade of the country. The institute aims to support and develop Ethiopian Textile, Garment, Leather and Fashion industries. Furthermore, the institute regularly organizes international conferences in the cotton, textile, apparel and leather sectors. Generally, the vision of EiTEX has been to support and enhance the capability and the competitiveness to Ethiopian Textile, Garment, Leather and Fashion industries including the small and medium enterprises.

20/10/2026
የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ተቀበለ====================================================ጥቅምት 9/2019 ዓ.ም |...
19/10/2026

የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ተቀበለ
====================================================
ጥቅምት 9/2019 ዓ.ም | BDU–EiTEX
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (EiTEX) በ2019 ዓ.ም. ትምህርታቸውን ለመከታተል ወደ ዩኒቨርሲቲው ከተመደቡት መካክል አዲስ ገቢ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን እየተቀበለ ይገኛል።
የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ታምራት ተስፋዬ ተማሪዎቹን “ወደ ተቋማችን እንኳን በሰላም መጣችሁ” በማለት በደስታ ተቀብለዋል።
በኢንስቲትዩቱ የተማሪዎች አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ ዋና ኢንስፔክተር ጣሰው አማኑ እንደገለጹት ወደ 2,000 የሚጠጉ አዲስ ገቢ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በተቋሙ ይገባሉ። የተማሪዎቹ ምዝገባ ጊዜም ጥቅምት 9 እና 10/2019 ዓ.ም. ድረስ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ናይል ኤክሰኪዩቲቭ ሊደርሺፕ አካዳሚ የአምስተኛው ዙር ሥልጠና በይፋ ተጀመረ(ባሕር ዳር፣ ጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ.ም.) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ናይል ኤክሰኪዩቲቭ ሊ...
17/10/2026

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ናይል ኤክሰኪዩቲቭ ሊደርሺፕ አካዳሚ የአምስተኛው ዙር ሥልጠና በይፋ ተጀመረ

(ባሕር ዳር፣ ጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ.ም.) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ናይል ኤክሰኪዩቲቭ ሊደርሺፕ አካዳሚ (Nile Executive Leadership Academy—NELA) የአምስተኛው ዙር (Cohort V) የአመራር ሥልጠና መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ፣ ጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (EiTEX) ቴራስ ውስጥ እየተካሄደ ይገኛል።

የሥልጠናውን መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ደሳለኝ እጅጉ በይፋ አስጀምረዋል።

የአመራር ሥልጠናው የአመራር ክህሎትን ለማጎልበት፣ ስትራቴጂካዊ አስተሳሰብን ለማዳበር፣ ውጤታማ የውሳኔ አሰጣጥን ለማጠናከርና በተቋማት ውስጥ ዘላቂ ለውጥ ማምጣት የሚችሉ ብቁ አመራሮችን ለማፍራት ያለመ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

ናይል ኤክሰኪዩቲቭ ሊደርሺፕ አካዳሚ በአመራር ልማት ላይ በማተኮር የአመራር አቅምን ለማሳደግ፣ የተቋማትን ውጤታማነት ለማሻሻልና ለሀገራዊ ልማት አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችሉ አመራሮችን ለማብቃት እየሰራ እንደሚገኝ በመክፈቻ ንግግሩ ተገልጿል።

የአምስተኛው ዙር ሥልጠና መጀመርም ዩኒቨርሲቲው በአመራር ልማት፣ በእውቀት ሽግግርና በተቋማዊ ለውጥ ላይ ለሚያደርገው ጥረት ተጨማሪ አበርክቶ መሆኑንም ተገልጿል።

ተቋሙ ለአራተኛ ጊዜ ከክፍል ትምህርት ወደ ሥራ ፈጠራ የሚያደርገውን ሽግግር ማስረጽ ላይ ያተኮረ ፕሮፖዛል አቀረበ===========================================(ባሕር ዳ...
16/10/2026

ተቋሙ ለአራተኛ ጊዜ ከክፍል ትምህርት ወደ ሥራ ፈጠራ የሚያደርገውን ሽግግር ማስረጽ ላይ ያተኮረ ፕሮፖዛል አቀረበ
===========================================
(ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ/ጥቅምት06/2019 ዓም) የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (EiTEX) ከክፍል ትምህርት ወደ ሥራ ፈጠራ ተኮር ተቋምነት ሽግግር ለማድረግ ያለውን አቅጣጫ በተመለከተ ለአራተኛ ጊዜ በቀረበው ፕሮፖዛል ላይ ውይይት አካሄደ።

የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ታምራት ተስፋዬ ”From Classroom to Enterprise: Repositioning the Ethiopian Institute of Textile and Fashion Technology as an Entrepreneurial University” በሚል ርዕስ የውይይት ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን የኢንስቲትዩቱ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣ ኦፊሰሮች እና የክፍል ኃላፊዎች በውይይቱ ላይ ተሳትፈዋል።

የውይይቱ ዋና ትኩረት ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስ ገዝነት የሚያደርገውን ሽግግር መነሻ በማድረግ ኢንስቲትዩቱ በሥራ ፈጠራ፣ በኢንዱስትሪ ትስስርና በገቢ ማስገኛ እንቅስቃሴዎች የተደገፈ የላቀ የትምህርት ተቋም ለማድረግ የሚያስችሉ አማራጮችን መመርመር ነው።

በውይይቱ የቀረበው ሀሳብ ኢንስቲትዩቱ ከባህላዊው የክፍል ትምህርት አቀራረብ በላይ በመሄድ የትምህርት፣ የምርምርና የማኅበረሰብ አገልግሎት ሥራዎቹን ከሥራ ፈጠራና ከኢንዱስትሪ ፍላጎት ጋር ማስተሳሰር እንዳለበት የሚያመለክት ነው። ይህም ተማሪዎች ከክፍል ውስጥ ከሚያገኙት የንድፈ ሐሳብ እውቀት ባሻገር ተግባራዊ ክህሎት እንዲያዳብሩ፣ የሥራ ፈጠራ ባህልን እንዲያሳድጉና ለራሳቸውም ሆነ ለሌሎች የሥራ ዕድል መፍጠር እንዲችሉ የሚያግዝ አቅጣጫ ነው።

በተጨማሪም የኢንስቲትዩቱን ሀብትና የሰው ኃይል በተሻለ ሁኔታ በመጠቀም፣ ከቴክስታይልና ፋሽን ኢንዱስትሪው ጋር ያለውን ትስስር ማጠናከር፣ የምርምር ውጤቶችን ወደ ተግባራዊ ምርትና አገልግሎት መቀየር እንዲሁም የገቢ ማስገኛ እንቅስቃሴዎችን ማስፋፋት ለተቋሙ ዘላቂነትና ተወዳዳሪነት ወሳኝ መሆናቸው በሰነዱ የተነሳውን አቅጣጫ ያመለክታል።

የኢንስቲትዩቱ ወደ ራስ ገዝነት የሚያደርገው ሽግግር በተቋማዊ አስተዳደር፣ በሀብት አጠቃቀም፣ በተጠያቂነትና በፈጠራ ሥራዎች ላይ የተሻለ ትኩረት እንዲደረግ የሚጠይቅ ሲሆን፣ ተቋሙ ለሚያጋጥሙት ተግዳሮቶች ዘላቂ መፍትሔ ለማፈላለግ የሚያስችሉ የሥራ ስልቶችን መቅረጽ የውይይቱ አንዱ ዋና ዓላማ ነው።

በመጨረሻም የትምህርት ክፍል ኃላፊዎችና ኦፊሰሮች በውይይቱ ንቁ ተሳታፊ በመሆን የኢንስቲትዩቱን የወደፊት አቅጣጫ በተመለከተ ሀሳብ አስተያየት እና ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን ተቋሙ የሥራ ፈጠራን የሚያበረታታ፣ ከኢንዱስትሪው ጋር የተሳሰረና በራሱ አቅም የሚያድግ ተቋም ለማድረግ የሚያግዙ ሀሳቦችን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን የውይይቱ አጠቃላይ አቅጣጫ ያመለክታል።

የቴክስታል ፋኩሊቲ የ2019 ዓ.ም. በጀት ዓመት የአካዳሚክ ዕቅዱን ለመምህራን አቀረበ============================================================በባሕር ዳ...
14/10/2026

የቴክስታል ፋኩሊቲ የ2019 ዓ.ም. በጀት ዓመት የአካዳሚክ ዕቅዱን ለመምህራን አቀረበ
============================================================
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (EiTEX) የቴክስታይል ፋኩሊቲ የ2019 ዓ.ም. በጀት ዓመት ዕቅድን ለፋኩሊቲው መምህራን አቅርቧል።
በውይይቱ ላይ የኢንስቲትዩቱ የአካዳሚክ ም/ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ተ/ፕሮፌሰር አዳነ ኃይሌ እና የምርምርና ማሕበረሰብ አገልግሎት ም/ሳይንትፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ትልቅ ሰው አዲስ እንዲሁም ሌሎች አመራሮችና መምህራን ተሳትፈዋል።
የፋኩሊቲው የ2019 ዓ.ም. ዕቅድ አቀራረብ በ2018 ዓ.ም. የተከናወኑ ተግባራትን እና የዕቅድ አፈጻጸምን መነሻ በማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን፣ የፋኩሊቲው ዲን አቶ ጋሻው አዘነ የ2018 ዓ.ም. የዕቅድ አፈጻጸምን እንደመነሻ ካቀረቡ በኋላ የ2019 ዓ.ም. የበጀት ዓመት ዕቅድን በማቅረብ፣ በመማርና ማስተማር፣ በምርምርና ተመራማሪዎች እንዲሁም በማኅበረሰብ አገልግሎት ዘርፎች የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ዘርዝረዋል።
በተጨማሪም የፋኩሊቲውን የትምህርትና የምርምር አቅም በማሳደግ ዓለም አቀፋዊ ተሳትፎን ለማስፋት የውጭ አገር ተማሪዎችን የመሳብ ሥራ በዕቅዱ ውስጥ አካተው አቅርበዋል።
የዕቅዱ አቀራረብ ዋና ዓላማ በቀጣዩ የበጀት ዓመት የፋኩሊቲውን የትምህርት፣ የምርምርና የማኅበረሰብ አገልግሎት ተግባራት በተቀናጀ መልኩ ለማከናወን እና የተቋሙን ተልዕኮ ለማሳካት የሚያስችል አቅጣጫ ማስቀመጥ ነው።
በመጨረሻም በውይይቱ ወቅት ከመምህራን እና ከተሳታፊዎች በዕቅድና በሥራ አፈጻጸም እና በመማር ማስተማሩ እንዲሁም በስኮላር ሽፕ ትምህርት አሰጣጥ ዙሪያ ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የፋካሊቲው ዲን አቶ ጋሻው እና ምክትል ዲን አቶ እያሱ ፈረደ እንዲሁም የኢንስቲትዩቱ የአካዳሚክ ም/ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ተ/ፕሮፌሰር አዳነ ኃይሌ እና የምርምርና ማሕበረሰብ አገልግሎት ም/ሳይንትፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ትልቅ ሰው አዲስ ለተነሱ ማብራሪያዎችና አስተያየት ጥያቄዎች ተገቢውን ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል።

REMINDER: ERASMUS+ PROGRAMME CALL FOR APPLICATIONS:Eligible students are encouraged to submit their applications for the...
13/10/2026

REMINDER: ERASMUS+ PROGRAMME CALL FOR APPLICATIONS:
Eligible students are encouraged to submit their applications for the Erasmus+ Higher Education Student Mobility Programme as soon as possible. The deadline is October 20, 2026. Don’t miss this opportunity for international academic experience!

Facebook: https://web.facebook.com/eitex.et
Website: https://bdu.edu.et/eitex/

የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (EiTEX) ወደ ስራ ፈጣሪነት የሚያሸጋግረውን ስትራቴጂያዊ ፕሮፖዛል ይፋ አደረገ::(መስከረም 29/2019 ዓ.ም | BDU-EiTEX/ ...
10/10/2026

የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (EiTEX) ወደ ስራ ፈጣሪነት የሚያሸጋግረውን ስትራቴጂያዊ ፕሮፖዛል ይፋ አደረገ::
(መስከረም 29/2019 ዓ.ም | BDU-EiTEX/ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (EiTEX) ተቋሙን ከባህላዊ የክፍል ትምህርት አሰጣጥ ወደ ስራ ፈጠራና ምርታማነት ለማሸጋገር፣ እንዲሁም የራሱን ገቢ የሚያመነጭ ተቋም ለመሆን ያለመ ትራንስፎርሜሽናል ስትራቴጂያዊ ፕሮፖዛል ይፋ አደረገ።
ፕሮፖዛሉን ያቀረቡት የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ታምራት ተስፋዬ ሲሆኑ፣ በውይይት መድረኩ የተቋሙ አመራሮችና መምህራን ተሳትፈዋል።
ፕሮፌሰር ታምራት እንደገለጹት፣ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስ-ገዝነት በሚሸጋገርበት ሂደት፣ EiTEX ያሉትን የሰው ኃይል፣ የመሠረተ ልማትና የቴክኖሎጂ አቅሞች በማስተባበር ምርታማነቱን ማሳደግና የራሱን ገቢ የሚያመነጭ ተቋም መሆን ይጠበቅበታል። ለዚህም የሰላም ሹራብ ማምረቻን፣ የናርጋ ጋርመንትንና የሰላም ቴክስታይል ፋብሪካዎችን ከትምህርትና ምርምር ሥራዎች ጎን ለጎን ምርታማ ማድረግ፣ ከኢንዱስትሪዎችና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ትስስር ማጠናከር፣ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተማሪዎችን በመሳብ የገቢ ምንጮቹን ማስፋፋት እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል።
ይህ ፕሮፖዛሉ በአምስት ዋና ዋና ምሰሶዎች ላይ ያተኩራል።
እነዚህም፦
• የስራ ፈጠራን ያካተተ የትምህርት ካሪኩለም መቅረጽ፤
• የተቋሙን ሀብቶችና መሠረተ ልማቶች ለገቢ ማመንጫ በሚያስችል መንገድ መጠቀም፤
• ከኢንዱስትሪዎች፣ ከንግድ ተቋማትና ከቀድሞ ተማሪዎች ጋር ጠንካራ ትስስር መፍጠር፤
• ለጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች የኢንኩቤሽንና የድጋፍ ሥርዓት ማቋቋም፤
• የተቋሙን ምርቶችና አገልግሎቶች በማስተዋወቅ የገበያ ትስስርን ማስፋፋት ናቸው።
በተጨማሪም የትምህርት ፕሮግራሞችን ከስራ ፈጠራ ጋር ማቀናጀት፣ የምርትና የላቦራቶሪ ክፍሎችን የገቢ ምንጭ እንዲሆኑ ማድረግ፣ የፈጠራና የሙከራ ማዕከላትን ማቋቋም፣ ከኢንዱስትሪዎች ጋር ያለውን የቴክኖሎጂና የሙያ ትብብር ማጠናከር እንደ ዋና ዋና የትግበራ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

ፕሮፖዛሉ በሦስት ዓመታት ውስጥ በአራት ደረጃዎች እንዲተገበር ታቅዷል። የመጀመሪያው ደረጃ የተቋሙን ነባራዊ ሁኔታና ዝግጁነት መገምገም፣ ሁለተኛው በሙከራ ላይ የተመሠረቱ የስራ ሞዴሎችን መገንባት፣ ሦስተኛው ውጤታማ የሆኑ አሰራሮችን ማስፋፋት፣ አራተኛው ደግሞ የተሳኩ አሰራሮችን በተቋማዊ ሥርዓት ውስጥ ማካተት ነው።
በመድረኩ በቀረበው ፕሮፖዛል ላይ የተሳታፊ መምህራን ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን፣ በፕሮፌሰር ታምራት ተስፋዬና በተባባሪ ፕሮፌሰር አዳነ ኃይሌ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቷል።
ይህ ተነሳሽነት EiTEX የትምህርት፣ የምርምር፣ የፈጠራና የምርት ሥራዎችን በማቀናጀት የተቋማዊ አቅሙን ለማጠናከርና ዘላቂ የገቢ ምንጮችን ለመፍጠር የሚያስችል አቅጣጫ እንደሚከፍት ይጠበቃል።

የፋሽን ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ያተኮረ ዉይይት አካሄደ::መስከረም 29/2019 ዓ.ም (BDU-EiTEX) – በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን...
10/10/2026

የፋሽን ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ያተኮረ ዉይይት አካሄደ::
መስከረም 29/2019 ዓ.ም (BDU-EiTEX) – በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (EiTEX) የፋሽን ትምህርት ቤት በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም፣ በምርምር ሥራዎች ማጠናከሪያ፣ በመማር-ማስተማር ጥራት ማሻሻያና ተቋማዊ ተልዕኮን በተግባር ለመወጣት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከመምህራን ጋር ውይይት አካሄደ።
በውይይቱ ላይ የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ታምራት ተስፋዬ፣ የአካዳሚክ ምክትል ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ተ/ፕሮፌሰር አዳነ ኃይሌ፣ የፋሽን ትምህርት ቤት አመራሮችና መምህራን ተሳትፈዋል።
የፋሽን ትምህርት ቤቱ ዲን አቶ ሰሎሞን እንደገለጹት፤ የውይይቱ ዋና ዓላማ በ2019 ዓ.ም የተያዙ ዕቅዶችን በተቀናጀ ሁኔታ ለማስፈጸም በመምህራን መካከል የጋራ መግባባትና አቋም ለመፍጠር እንዲሁም ውጤታማ የሥራ አፈጻጸምን ለማስመዝገብ ነው።
በውይይቱ ወቅት ከመምህራን በዕቅድና በሥራ አፈጻጸም እንዲሁም በትምህርት ሂደቱ ዙሪያ ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በትምህርት ቤቱ ዲንና ምክትል ዲን ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
በመጨረሻም የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ታምራት ተስፋዬ፣ የአካዳሚክ ምክትል ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ተ/ፕሮፌሰር አዳነ ኃይሌ እና የትምህርት ቤቱ ዲን አቶ ሰሎሞን ከፋሽን ትምህርት ቤቱ ብዙ የሚጠበቅ በመሆኑ መምህራን በትጋት እንዲሠሩና የሥራ ትብብራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።

07/10/2026

Bahir Dar University,

በስራ ቦታ ላይ የግል ጉዳትን ቅድመ መከላከል ላይ ስልጠና ተሰጠበባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በተቋማዊ ለውጥ አዘጋጅነት “በስራ ቦታ ላይ አካላዊ...
06/10/2026

በስራ ቦታ ላይ የግል ጉዳትን ቅድመ መከላከል ላይ ስልጠና ተሰጠ
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በተቋማዊ ለውጥ አዘጋጅነት “በስራ ቦታ ላይ አካላዊ ጉዳትን ቅድመ መከላከል” (Prevention of Personal Injuries at Workplace) በሚል ርዕስ ለ43 ሰራተኞች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል።
ስልጠናው ከመስከረም 23 እስከ 26 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ የተካሄደ ሲሆን፣ በስራ ቦታ ሊከሰቱ የሚችሉ የግል ጉዳቶችን አስቀድሞ መከላከል፣ የስራ ቦታ ደህንነትን ማረጋገጥ እና ሰራተኞች የጉዳት አደጋዎችን በመለየት ተገቢውን የመከላከያ እርምጃ እንዲወስዱ አቅም ለማሳደግ ያለመ ነው።
በስልጠናው ወቅት ተሳታፊዎች በስራ ላይ ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ የጉዳት ምክንያቶች፣ አደጋዎችን አስቀድሞ ስለመለየት፣ የግል ደህንነትን ስለመጠበቅ እና የስራ ቦታ አደጋዎችን ለመቀነስ ስለሚያስፈልጉ የቅድመ መከላከያ ስልቶች ግንዛቤ እንዲያገኙ ተደርጉል ሲሉ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተቋማዊ ለውጥ ቡድን መሪ አቶ በሃይሉ ስንሻው ገልጸዋል።
ስልጠናው ሰልጣኝ ተኮር (trainee-centered) የሆነ የስልጠና አቀራረብን በመከተል የተካሄደ ሲሆን ተሳታፊዎች በንቃት እንዲሳተፉ፣ ልምዳቸውን እንዲያካፍሉ እና በስራ ቦታ ያሉ ተጨባጭ የደህንነት ችግሮችን በመለየት መፍትሄ እንዲያመነጩ ያስቻለ ነው።
በአጠቃላይስልጠናውሰራተኞችየስራቦታደህንነትንእንዲያስቀድሙ፣ራሳቸውንናየስራባልደረቦቻቸውንከጉዳትእንዲጠብቁእንዲሁምየአደጋስጋትንበቅድመመከላከልየተሻለየስራባህልእንዲገነቡአስተዋፅኦእንዳለውተገልጿል።

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Institute of Textile and Fashion Technology posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Ethiopian Institute of Textile and Fashion Technology:

Shortcuts

Share